Monday, 19 November 2012

የታክሲ ውስጥ ጥቅሶች

‹‹ ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል ››

·    የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ·  ሠውን ማመን ተፈራርሞ ነው·  ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
·   በቴሌቶን ሂሳብ መክፈል ክልክል ነው
·   ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
·   ለፀባይኛ ተሳፋሪ የፀባይ ዋንጫ እንሸላማለን
·   ለስራ ነው የወጣነው
·   በመጀመሪያ የጋለ ደምህን ተቆጣጠርና ሀሳብህን ግለፅ
·    ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
·   ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
·  ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር
·   ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል
·   ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን
·   ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር
·  ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ
·  ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ
·  ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ     አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::
·  ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን
·  ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ
·  መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!
·  ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል
·  በጭነት መኪና መታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ
·  የክፍለ ከተማ ሠዎች ካላችሁ ሒሳብ በቅድሚያ
·  ኑሮአችሁ ሳይሞላ "ታክሲው አልሞላም?! " ትላላችሁ!·  ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን
መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡
·  ለዓለም ሙቀት መጨመር መንስዔው ጭቅጭቅ ነው
·  ይህ ታፔላ የሚሉት ከመጣ ፤ ምሳችን በቆሎ ራታችን ቂጣ
·  ታክሲው ሳይቆም መውረድ ይቻላል፡፡
·   እንዴት ጭት አትቃሙ ይባላል፣ ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነው

·  የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ
·  ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
·  የቤትህን አመል እዛው!!!
·  የሠው ትርፍ የለውም . . . ተጠጋጉ!
·  በታክሲ. . . . .  ህግ አላውቅም
·  ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም
·  ለታላቅ መልስ አይሰጥም
·  ነገን ለመኖር መጀመሪያ ዛሬን ኑር..በመቃም
·  ‹‹ደሀ›› ከፍ ብሎ የሚታየው ባስ ላይ እና እራሱን ሲሰቅል ብቻ ነው፡፡
·  እባክዎን የአባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ ይበሉልን
·  ለካፌና ለላዳ ብዙ ይከፍላሉ፤ እኛ ጋ ሲሳፈሩ ለምን ይጨቃጨቃሉ

በመጨረሻ
ተሳፋሪ፡- የሰጠከኝ ልክ አይደለም፤ሒሳብ አትችልም" ? አልተማርክም? ደደብ . . . .
ወያላ፡- ጋሼ  ድንጋይ ለመጫን እስከ ሁለተኛ ክፍል መማር በቂ ነው
አበቃሁ፡፡

No comments:

Post a Comment