"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday, 16 June 2012

ኪነትና ነፃነት


 (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

በደርግ ዘመን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የኪነት ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፤ እንጉርጉሮ በምትል ትንሽ የግጥም ጥራዝ ሳይሆን አይቀርም ለስብሰባው ተጋብዤ ነበር፤ በዚህ ስብሰባ ላይ አቶ አያልነህ ሙላትና ዶር. ኃይሉ አርአያም አስተናጋጆች እንደነበሩ አስታውሳለሁ፤ የመክፈቻው ንግግር ሥርዓት እንዳበቃ መድረኩ ለአስተያየት ሲከፈት የመጀመሪያው ጠያቂ እኔ ነበርሁ፤
‹‹በመድረኩ ላይ የተባለው ሁሉ በትክክል ገብቶኝ እንደሆነ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ፤ ስለዚህም አንድ ጥያቄ ላቅርብ፤›› ብዬ- ‹‹ኪነት ማለት አዝማሪነት ማለት ነው ወይ?››-- ብዬ ተቀመጥሁ፤ በሦስቱም የስብሰባ ቀኖች ‹‹ኪነት አዝማሪነት ነው ወይ?›› የሚለው ጥያቄ እየተነሣ ቆየ፤ አዝማሪነት ስትል ምን ማለትህ ነው ብለው የጠየቁ ነበሩ፤ በቀለለ አማርኛ ልገልጽ አልችልም በማለት እስከ ሦስተኛው ቀን ቆየሁ።
አንድ ሎሌ እየተውዘገዘገ ርእዮተ ዓለምንና አብዮትን የሕይወት ካባ አስመስሎ ‹‹ከርእዮተ ዓለሙ ውጭ ምን አለ!›› እያለ አለማወቁን አሳወቀ፤ ኪነት አዝማሪነት ነው፤ አዝማሪነት ኪነት ነው ማለቱ ነበር፤ ሌሎችም ኪነትንና አዝማሪነትን ለማጋባት የቃጣቸው ሎሌዎች ነበሩ፤ አንዳንዶች ግራ ገብቶአቸው ለቡና ስንወጣ የጠየቁኝ እንደታምራት ሞላ ያሉ የኪነት ሰዎች ነበሩ፤ በእውነቱ እዚያ ውስጥ ከነበሩት ውስጥ ማንኛውም ቢሆን በልቡናው ኪነትንና አዝማሪነትን መለየት ያቃተው የነበረ አልመሰለኝም።
በሦስተኛው ቀን ተነሣሁና በአንዲት ልጅ ፍቅር ተወጥሬ አንድ ግጥም ብጽፍ ርእዮተ ዓለሙ ወይም አብዮቱ በእኔና በልጅቱ መሀከል በምን ቀዳዳ ይገባል? ሕይወት አይቆምም፤ ይቀጥላል፤ ርእዮተ ዓለም ግን በርእዮተ ዓለም ይለወጣል፤ ለአብዮትም አብዮት አለው በማለት ሎሌዎቹን አስደንግጬ ድርሻዬን ተወጣሁ!

ኪነት ነፃነት ነው፤ ኪነት የፈጣሪነት ጥበብ ነው፤ ኪነት ውበት ነው፤ ኪነት ደስታና ሳቅ ነው፤ ኪነት ሐዘንና ለቅሶ ነው፤ ነፃነት፣ የፈጣሪነት ጥበብና ውበት የኪነት መለያ ባሕርዮች ይመስሉኛል፤ ኪነት በሰው ልጅ ውስጥ የፈጣሪው እስትንፋስ መኖሩን የሚገልጽና ፈጣሪነትን ከፈጣሪው የሚጋራበት ስጦታም ችሎታም ነው፤ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የአንድ አገር ዓይንና ጆሮ፣ አእምሮና ኅሊና ናቸው፤ የአንድ አገር ሕዝብ የሥልጣኔ ደረጃ በእንደዚህ ያሉ ሰዎች ብዛትና በድንበር-ዘለል ተጽእኖአቸው ይለካል፤ ለምሳሌ ፈረንሳይ የኪነት ሰዎችን ከየትም የመሳብ ችሎታዋ ወደር የሌለው ነው፤ እንዲሁም አሜሪካ በሙሉ ባይባልም ኒው ዮርክ የኪነት ሰዎችን የሚስብ ከተማ ነው።

በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከመቃብር ውስጥ በጥሩ መልኩ በጉዱ ካሣ ያመለከቱት ይመስለኛል፤ ክፉ መልኩ ግን አስቀያሚ ነው፤ ዘፈኖች የሚታሰሩበት አገር ነው፤ የኪነት ሰዎች የሚታሰሩበት አገር ነው፤ መጻሕፍትን ማቃጠልም እናውቅበታለን፤ አሁን ደግሞ ከየመሥሪያ ቤቶች ቤተ መጻሕፍት እያወጡ መጻሕፍትን መሸጥ ፈሊጥ ሆኖአል፤ በአጠቃላይ የፈጠራ ሰዎችን ከነፈጠራቸው ማፈን የሚወራረሱት ልማድ ሆኖአል፤ ከተለመደውና ከተፈቀደው ወጣ ያለ ነገር ወይ ለእስር ወይ ለስደት ይዳርጋል፤ በእውነቱ ከሆነ ኪነት የሚሰደድ አይመስለኝም፤ የኪነት ሕይወቱም ሆነ ሞቱ በነፃነት ነው፤ የተሰደደ ኪነት የሬሳ ጭፈራ ነው።

በብዙ አገሮች ኪነትን የሚደግፉ ሀብታሞች አሉ፤ በኢትዮጵያም አቶ መሀመድ አላሙዲ የዘፋኞች አለኝታ መሆኑ ይነገራል፤ አንድ ሰው መኖሩ የጠቅላላውን ጨለማ አይገፈውም። ግራም ነፈሰ ቀኝ ራሱን ነፃ ያላወጣ ኪነት ከአዝማሪነት ይቆጠራል፤ አዝማሪነት ከመዝፈን ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም፤ ውዳሴንም ሆነ ገድልን ለወፍራም እንጀራ የሚጽፍ አዝማሪ ነው፤ በሌሎችም ሙያዎች ያው ነው። አዝማሪነት የፈጣሪነት ጥበብንና ውበትን ሊይዝ ይችል ይሆናል፤ ነፃነት ግን ለአዝማሪነት የባሕርዩ አይደለም፤ ጥቅምን አይቶ የሚነሣ አዝማሪነትና ያለምንም ምኞት አፍአዊ ሁኔታዎች በሚቀሰቅሱት ሀሳብና ስሜት በጥልቀት ነፍሱ ሲነካ ነፍሱን ቧጥጦ የሚወጣው ኪነት አንድ ሊሆኑ አይችሉም። በአንድ ዓይነት ኪነት ላይ ያለውን የባህል አጥር እየጣሱ ስሜታቸውን በመጠኑም ቢሆን የሚገልጹ ሰዎች ነበሩ፤ አዝማሪዎች፣ አልቃሾችና እረኞች፤ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ የኪነት አገር ለመሆን አልታደለችም፤ ነፃነት ሲመጣ ኪነት ይነግሣል፤ ችጋርም ይጠፋል።

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ በፖሊሶች ተደብድቦ መሞቱ ተገለጸ

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ላለፉት አምስት ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ይሠራ የነበረው አቶ ሀሚድ ወዳጆ የተባለ ግለሰብ፣ ሰኔ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት ላይ ቄራ አካባቢ በፖሊሶች በደረሰበት ከባድ ደብደባ ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ አቶ ሀሚድ በፖሊሶች ተደብድቦ ሕይወቱ ሊያልፍ የቻለው ከጓዳኞቹ ጋር ሲዝናኑ አምሽተው የ2012 የአውሮፓ ዋንጫ ተፋላሚ የነበሩትን የጀርመንና የፖርቹጋል ጨዋታን በሚመለከት የተወሰኑት ‹‹ወደ ቤት እንግባ›› ሲሉ የተወሰኑት ደግሞ ‹‹ጨዋታውን እንመልከት›› በማለት ሲነጋገሩ ‹‹ለምን ትረብሻላችሁ?›› በማለት ፖሊሶቹ ባነሱት ጥያቄ አለመግባባት ላይ በመድረሳቸው፣ በደረሰበት ድብደባ መሆኑን ከጓደኞቹ የተረዱት ቤተሰቦቹ ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ አብሮት የነበረው ጓደኛው እንደገለጸው፣ ቄራ አካባቢ ሲዝናኑ ቆይተው  መስቀልኛ ጫፍ ላይ ሲደርሱ ‹‹ኳስ እንይ ወይስ ወደቤት እንግባ?›› እየተባባሉ ሲነጋገሩ፣ አራት ዱላ የያዙና ሁለት ክላንሽኮቭ መሣሪያ የያዙ ስድስት ፖሊሶች ተጠግተዋቸው ‹‹ምን ያስጮሀችኋል? ለምን ትረብሻላችሁ?›› ብለው ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው ተናግሯል፡፡

Friday, 15 June 2012

ማመልከቻ፤ “ኢህአዴግ” ከሚለው ውስጥ ዴ እንድትወጣ ስለመጠየቅ




እኔ የምለው ኢህአዴግ ድሮ “ብሶት የወለደው” ነበር የሚባለው። አሁን ደግሞ የሚሰራውን ልብ ብለው ያዩ አንዳንድ ግለሰቦች “ጭንቀት የወለደው እያሉ”  ሲጠሩት እየሰማሁ ነው። ስጠረጥር የሆኑ እጣ ፈንታ ነጋሪ፤ “መጨረሻህ እየደረሰ ነውና ከባድ ጥንቃቄ አድርግ” ብለው አስጨንቀውታል መሰለኝ!  በየቦታው የሚወሰዱ ከእርግጫ የሚስተካከሉ እርምጃዎችን ልብ ብትሉ  የምርም ጭንቀት የወለዳቸው ናቸው!   (እኔን ጭንቅ ይበለኝ!  ወይስ አይበለኝ…?)

እናም ሀገሬው “ጭንቀት የወለደው የኢህአዴግ ሰራዊት በሃያ አንድ አመቱም በርካታ ነገሮችን እየተቆጣጠረ እና እየቆጣጠረ ይገኛል” እያለ እየቦጨቀው ይገኛል።

በየጊዜው የሚወጡት አዎጆች እና ህጎች በሙሉ “አይቻልም” የሚሉ ናቸው። ማንኛውም ታጋይ እና የታጋይን ገድል በየ ግንቦት ሃያው የሰማ ሰው እንደሚያስታውሰው ህውሐት ያኔ ጫካ እያለችም የማትከለክለው ነገር አልነበራትም። እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ተፈጥሯዊ የሆነውን የወንድና ሴት ግንኙነት ራሱ በጥብቅ ከልክላ ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ “ታጋዮቹ የፈለጉት ነገር ሁሉ ሲፈቀድላቸው እኛ ህዝቦቹ በተራችን ሁሉንም ነገር እየተከለከልን ነው።”  የሚል ሰው ተበራክቷል። እስከ አሁን በይፋ ያልተከለከለው የፍቅር ግንኙነት ብቻ ነው። እርሱም ቢሆን፤ “ተገናኝተን ሻይ ቡና እንኳ ለማለት የሚያስችል አቅም በማጣታችን እንደተከለከለ ቁጠረው!” ያሉኝ ወዳጆች አሉ።

የምር ግን ወዳጄ ዘንድሮ ያልታገደ ነገር ምንድነው? በየነጋው የምንሰማው ሁሉ እንትን ተከለከለ፣ እንትን ታገደ፣ እንትን ተዘጋ፣ የሚል ብቻ ሆኗል። ከዚህ በፊት ኢቲቪ እንደነገረን፤ “የአሁኑ መንግስት ልማታዊ መንግስት ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትሩም ልማት እንጂ ለዚህ  ህዝብ ዴሞክራሲ ምንም አያደርግለትም በሚለው ዜማቸው ሲናገሩ እንደሰማነው “ዴሞክራሲ እና ልማት ምንም ግንኙነት የላቸውም።” ብለውናል። አንዳንድ ካድሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሲተረጉሙ ዴሞክራሲ “እንደውም የእድገት ፀር ነው።” ብለው እየተናገሩ ነው።

ታድያ እንደዚህ ከሆነ በአውራው ፓርቲ ስያሜ ኢህአዴግ ውስጥ “ዴ” ምን ልታደርግ ተሰነቀረች? ሰዉ እኮ ፊልም ሲታገድ፣ ስካይፕ ሲታገድ፣ ዌብ ሳይቶች ሲዘጉ፣ ራዲዮ ጣቢያዎች ሲጠረቀሙ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሲታወኩ “እንዴ!” እያለ የሚደነቀው እኮ በስማችን ውስጥ “ዴ” በመኖሯ ሳቢያ ነው።

“ዴ” ማለት ዴሞክራሲ ማለት ነው። እንግዲያስ ከልካዩ መንግስታችን ሁሉን ነገር እየከለከለ አረ የ ”ዴ” ስራ ምንድነው? በሚል ለተቺዎች አጋልጦ ከሚሰጠን አንድ ጊዜ ስያሜውን ቢያስተካክለው ግልግል ይሆናል የሚል አስተያየት አለኝ። ስለዚህም እንደሚከተለው አመለክታለሁ።

እኔ አመልካቹ ግለሰብ በሀገሪቱ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ገደብ የለሽ ክልከላ በሙሉ ልቤ የምደግፍ ስሆን፤ በዴሞክራሲ እና “በልማት መካከል ምንም ግንኙነት የለም” የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሬን ንግግር ወደ መዝሙር ቀይሬ ጠዋት ማታ የማንጎራጉር መሆኔንም ለማሳወቅ እወዳለሁ።

መንግስታችን ሁሉንም ነገር መከልከሉ ለእኛው አስቦ እንዳንበላሽ ሰግቶ እንደሆነም አምናለሁ።   ዴሞክራሲ የሚባለው ነገርም አጉል ቅብጠት መሆኑ ገብቶኛል። በመሆኑም በገዢው ፓርቲ ስያሜ “ኢህአዴግ” ውስጥ ያለችውን “ዴ” እንድትወጣልን በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ።

Thursday, 14 June 2012

The Ethiopian government has clamped down on Internet-based voice-calling service, making their use a criminal offence. By Craig Wilson.


The Ethiopian government has clamped down on Internet-based voice-calling service, making their use a criminal offence. By Craig Wilson.

Ethiopia’s state-owned Internet service provider, the Ethiopian Telecommunication Corporation (Ethio-Telcom), has begun performing deep-packet inspection of all Internet traffic in the country. The country’s government recently ushered in new legislation that criminalises the use of services such as Skype, Google Talk and other forms of Internet phone calling.


The new law, which came into effect on 24 May, makes use of Internet voice services punishable by hefty fines and up to 15 years in prison.


The official line from the government is that the move is intended to protect national security and protect the national, state-owned telecoms carrier from losing revenue to Skype and similar services; this, despite the fact that Ethiopia’s fixed-line penetration rate is the second worst in Africa (after Sierra Leone) at an estimated 1% of its 85m strong population.

Ethiopia has instituted numerous restrictions on its digital community in recent years. The government has previously closed down Internet cafes offering voice-over-Internet protocol services and, in December 2006, made it obligatory for Internet cafes to keep records of the names and addresses of their customers in an effort to clamp down on bloggers and other users critical of the regime.

The new law prohibits all VoIP traffic along with audio and video data traffic via social media. The Africa Review reports that the law also gives the government the right to inspect any imports of voice communication equipment and accessories.

The OpenNet Initiative, which tracks Internet filtering and surveillance, says in a report on Ethiopia that the country already blocks all blogs hosted at blogspot.com and at nazret.com, a site that aggregates Ethiopian news and has space for blogs and forums.

The new legislation is no doubt also motivated by the events of the Arab Spring that saw mass protests organised via social media. With many bloggers critical of Ethiopia’s current government, censorship by the state looks likely to increase

Skype users in Ethiopia could face 15 years of jail time



Skype users in Ethiopia could face 15 years of jail time
Posted by admin on June 14, 20120 Comment
By Aljazeera – a new law in Ethiopia has criminalized the use of VOIP (Voice Over Internet Protocol) services such as Skype. Users could face up to 15 years of jail time. The law was passed May 24th, but the story wasn’t picked up by international media until recently. 
http://stream.aljazeera.com/story/ethiopia-skype-me-maybe-0022243