"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Wednesday, 20 June 2012
መለስ ዜናዊ ፕሬዝዳንት ቡሽና ቶኒ ብሌር
መለስ ዜናዊ ፕሬዝዳንት ቡሽና ቶኒ ብሌር
የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ቡሽና የእንግሊዝ የቀድሞው ጠ/ሚ ቶኒ ብሌር በለንዶን
የጠ/ሚር ቢሮ ሻይ ቢጤ ይዘው ስለ የሃገራቸው የህክምና ሳይንስ እድገት እየተጨዋወቱ ነው።
ቡሽ፡ ይገርማችኋል የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ነፍስ ለመስራት ተቃርበዋል ማለት ይችላል፡፤ በቅርቡ በችካጎ ዩኒቨርሲቲ
የህክምና ማዕከል ውስጥ ሁለት እጅ የሌላት ሕጻን ተወለደች። ሳይንቲስቶቹ ባጋጣሚ ህጻኗ በተወለደችበት ቀን ከሞተች
ሌላ ሕጻን ላይ እጆችዋን ወስደው ገጥመውላት አሁን ሁለቱም እጆችዋ የተፈጥሮ እጅ ያህል ጤነኛ ናቸው። ብሎ
በመኩራራት ይናገራል።
ብሌር ፈገግ ብሎና በንቀት አስተያየት ቡሽን መልከት አድርጎ። እናንተ አሜሪካኖች ለካ ገና 18 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ
ናችሁ? እንግሊዝ ውስጥ አሁን አንተ የተደቅክበት እጅ መቀጠል የተሰራው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ሲል
በመኩራራት ከተናገረ በኋላ እኛ አሁን በጣም ረቀናል። ከአንድ ሰው ሴል ዲ ኤን ኤ በመውሰድ ያንኑ ሴል በላብራቶሪ
ካባዛን በኋላ የሰውየውን ኮፒ ወይም ክሎን መፍጠር ችለናል በማለት ቡሽና መለስ በእንግሊዝ የህክምና ጥበብ
እንደሚደነቁ ሳይጠራጠር እጅግ ተኩራርቶ በፈገግታ ይመለከታቸዋል። እውነትም ቡሽ ማመን አቅቶት እራሱን
እየነቀነቀ አድናቆቱን ገለጸ። መለስ ግን ምንም ሳይገረም እንዲህ ሲል ተራውን መናገር ጀመረ።
መለስ እናንተ ኃያላን መንግስታት ለካ በሳይንስ ረገድ ገና ብዙ ይቀራችኋል። እኛ በርሃ እያለን የሰራነውን ገና የዛሬ 100
ዓመትም የምትሰሩት አይመስለኝም። ሲል
ብሌር ደሞ ወያኔ በርሃ እያለች... ምን ሰራች ልትል ነው ? ሲል ጠየቀ።
መለስ እኛ በርሃ ሳለን ሁለት ያለ ጭንቅላት የተፈጠሩ ሰዎች አግኝተን ለአንደኛው ዱባ ገጥመንለት ስሙን አባ ዱላ
ስንለው ሌላኛውን ደግሞ ድንች ገጥመንለት አዲሱ ለገሰ ብለነዋል። ሁለቱም ዛሬ ድረስ በሙሉ ጤንነት ከኛው ጋ
ይገኛሉ በማለት ወያኔ በበርሃ የፈጸመውን የህክምና ሳይንስ ጥበብ ነግሮ አስደንቋቸዋል።
Tuesday, 19 June 2012
ትንሽ ወሬ፤ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ከሱብኝ!
ትንሽ ወሬ፤ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ ከሱብኝ!
ትላንትና ከስንት ጊዜ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርዬን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አየኋቸው። ያኔ አበበ ገላው በዋሽንግተን ዲሲ ቆሌያቸውን ከገፈፋቸው በኋላ በቴሌቪዥን መስኮት ስናያቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። (በቅንፍ፤ እንደ ድሮ ጎረቤት ብንሆን ኖሮ በቴሌቪዥን መስኮት ሲጠፉብን በሳሎናቸው መስኮት ለማየት ሙከራ እናደርግ ነበር። ዛሬ ግን ሩቅ ሆንና ናፍቆታቸው ሲያስቸግረን ሰነበተ! ብዬ ሀሳቢነቴን ለመግለፅ እወዳለሁ።)አረ እዝች ጋ ሳይረሳ ባለፈው ጊዜ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሰዎች “አበበ ገላው ዋሽንግተን ዲሲ ያልሄደው በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ስላሉ እነርሱን ፈርቶ ነው!” ብላችሁን ነበረ። ረስቼላችሁ፤ ሰውየው እኮ አንገታቸውን የደፉት በዋሽንግተን ዲሲ ነው።
ታድያ የዛን ጊዜ ያ ሁሉ የአንገት እና የቅስም ስብራት ያጋጠማቸው የጋዜጠኛ አበበ ገላው ንግግር ብቻ መስሏችሁ ከሆነ ተሸወዳችሁ።
ከውጪ የነበሩት የአካባቢው ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ጩኸትም “ምነው እግሬን በሰበረው!” አስብሏቸው ነበር። ውስጥ ደግሞ አበበ ትንታግ ሲጨመርበት…! እና ታድያ አዲስ አድማሶች ይሄ ሁሉ ነገር በዋሽንግተን ዲሲ ሲከናወን ደጋፊዎቻቸው የት ሄደው ይመስላችኋል? “በልማታዊ ስራ ተወጥረው ነበር!” ብላችሁ ሳቄን እስቲ አብዙልኝ! “ምን አይነት አዲስ አድማስ መጣ ደሞ ባካችሁ!?”
በነገራችን ላይ አሁንም እርሳቸው እርም የላቸውም የቡድን ሃያ አገራት ስብሰባ ላይ ደግሞ ሊገኙ ሲሄዱ ነው ያየኋቸው። እንደኔ እንደኔ ይሄ ቡድን ምናምን የሚባል ነገር ቢቀርባቸው ይሻላል። በርግጥ ስብሰባ ሊናፍቃቸው አንደሚችል ጠረጥራለሁ። ምን ችግር አለው ታድየ በፈለጉ ጊዜ የሚሰበስቡት በፈለጉ ጊዜ የሚበትኑት ፓርላማ አላቸው አይደል እንዴ…!? እዛው እንደሚሆኑ ቢሆኑ ይሻላቸዋል እንጂ፤ ገና ለገና የፈረንጆቹ “ቡድን” አያልቅም እና እርሳቸው “በድን” እየሆኑ የሚመጡበት ምክንያት ምንድነው!?
የሆነ ሆኖ “ታንክ ተደግፈው መፅሀፍ የሚያነቡት ጀግናው ጠቅላይ ሚኒስትራችን” በአበበ ገላው ንግግር የተነሳ ለአንድ ወር ያህል ተሸማቀው እና ተሸምቀው ሲያበቁ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለዋል።
ታድያልዎ፤ ትላንት ሳያቸው ክስት ብለዋል። ምን ሆኑ!? እንዴ ጠንከር ይበሉ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ! ቀጣዩ ጩኸት እኮ እየባሰ ነው የሚመጣው! ታድያ ጠንከር ጠንከር ማለት አይሻልም ይላሉ? ቁጣ እና ጩኸት ይህንን ያህል የሚረብሽዎት ከሆነ ግን ዘዴውን ልንገርዎት…!? እሺ አይሉኝም እንጂ ዛሬውኑ ስልጣንዎን ልቅቅ አድርገው አዲስ አገራዊ መግባባት፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ማከናወን! አቤት ያኔ ጤናዎ ላይ ራሱ ምን አይነት መሻሻል አንደሚመጣ ያዩት ነበር።
የባልካኑ የእግር ኳስ ንጉስ!(ቴዎዶር ገስላሴ)
የባልካኑ የእግር ኳስ ንጉስ!(ቴዎዶር ገስላሴ)
ከጥቂት ዓመታት በፊት ይህን ስም ማንም አያውቀውም
ከወላጆቹና አብሮ አደግ ጓደኞቹ በስተቀር ዛሬ ግን በዓለም
ላይ ያሉ የኳስ አፍቃርያን በሙሉ ማለት ይቻላል ይህን
ምትሃተኛ የቀኝ መስመር ተከላካይ ተጫዋች ዐይናቸውን
ሳያሹ የአውሮፓው ክስተት መሆኑን ያምናሉ።ይህ ልጅ ማን
ነው?የት ተወለደ?የትስ አደገ?ግለ ታሪኩን ቆንጥሬ
ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።
ቴዎዶር ገስላሴ
24/12/86 እ.ኤ.አ. በቀድሞዋ ቼኮዝላቫኪያ በአሁኗ ቼክ
ሪፐብሊክ ለትምህርት ሄዶ ፍቅር ካጣመራቸው የአገራችን
ዜጋ ከኢትዮጵያዊ አባትና ከቼካዊት እናት በትንሿ
የቼኮዝላቫኪያ ከተማ ትሬቢክ(Třebíč, Czechoslovakia)ተወለደ።
1.82cm ቁመት ያለውና የ25 ዓመቱ ወጣት ቴዎዶር
እግር ኳስን ገና የ7ዓመት ልጅ እያለ ነበር የጀመረው።
በአሁኑ ወቅት ለአገሩ ቡድን ስሎቫክ ሊበራክ ሲጫወት፣
ለወጣት ብሔራዊ ቡድኑም አገልግሏል፣በቼክ ታሪክ
ውስጥ የመጀመሪያው ጥቁር ተጫዋች ሲሆን በቀለሙ
ከባላንጣዎቹ የስፓርታ ፕራግ ደጋፊዎችና አሁን
እየተካሄደ ባለው 2012የአውሮፓ ዋንጫ ላይም ከሩሲያ
ደጋፊዎች የዘረኝነት ፀያፍ ስድቦች ደርሰውበታል።
ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቅ ግን¨እኔ ምንም አስተያየት
አልሰጥም¨በማለት ጉዳዩን ለጋዜጠኞች ዘግቶታል።
ቴዎዶር ቼክ የምትመካበት ድንቅ ተከላካይ ብቻም
ሳይሆን ፈጣንና ንቁ፣ለጎል ኳሶችን አመቻችቶ የሚሰጥ፣
በሌሎች ትልልቅ የአውሮፓ ቡድኖች የሚፈለግ የወቅቱ
ክስተት ነው።የት መጫወት እንደሚፈልግ ሲጠየቅ
¨የስፔን እግር ኳስ ይስበኛል እወደዋለሁም¨ በማለት
አጭርና ግልፅ መልስ ሰጥቷል።የዚህ ኢትዮ-ቼካዊ ወጣት
ማረፊያ የት ይሆን?
*መልካም የጫወታ ዘመን ይሆንለት ዘንድ የሁላችንም
ኢትዮጵያዊያን ምኞት ነው!¨ደም ከውሃ ይቀጥናል
ይባል የለም?¨
Like ·
የስደቱ ወላፈን በኖርዌ
የስደቱ ወላፈን በኖርዌ
(ክፍል ሁለት)
ከብ.ወ
ናታን "መጠቀምያ" ወይንስ "የስደቱ ፖለቲካ የጥቃቱ ሰለባ"?
ዘወትር በሚታተሙት የኖርዌ ጋዜጦች ላይ ሕፃኑ ስደተኛውን ናትንን ያዘለ ዜና እስከነፎቶግራፉ ብቅ ይላል።ምናልባት ማጋነን አይሁን እንጂ ከሃገሪቱ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ይልቅ በሰሞነኞቹ ጋዜጣ ላይ በመውጣት ረገድ ናታን
የመሪነቱን ደረጃ ሳይዝ ይቀራል ብላችሁ ነው። በእርግጥ በሽብርተኝነት ከተከሰሰው ከአንደርስ ብራይቪክ
ባይበልጥም።
ናታን በዚህች ዓለም በተፈጥሯዊዋ ውድ የዘር ግንድ ሃገሩ ኢትዮጵያ ሳይሆን በኖርዌ መወለዱ የሕይወት ዕጣው
ሆኖ እንጂ ፈቅዶ ያደረገው አይደለም። ናታን በፈረንጅ ሃገር መወለዱ ከእናትና አባቱ የስደት ታሪክ ጋር የተያያዘ
እንድምታ ቢኖረውም እንኳን እርሱ ራሱ - በራሱ ላይ የደነገገው ውሳኔ አይደለም። ናታን የዚህችን ዓለም ውዝግብና
ቅራኔን ያልተረዳ የሰባት ዓመት ጨቅላ ነው።
ታድያ የናታን ወላጆች - "ኖርዌን ለቃችሁ ውጡ" - ወይንም ደጎም - "ጉዳያችሁ እንደገና እስከሚታው ቆዩ" -
እየተባለ ወዲህና ወድያ ሲያወዛውዟቸው ናታንንም አብረው ያንገላቱታል። ይህ ሁኔታ የየሰዉ ዓይን የሚበላቸውን
የወላጆቹን ቅስም ያደቃል። እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነን ስንመለከተው ደግሞ ጨርሶ አንገትን አስደፊ ሆኖ እናገኘዋለን።
አበበ ባልቻ እንደ ሕወሐት?
ከተስፋዬ ገ/አብ
“ሰው ለሰው” የተባለው ድራማ በድንገት ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ትኩረቴን የሳበው ግን ስለ ተዋንያኑ ውክልና ፌስ ቡክ ላይ የተሰራጨው ወግ ነው። ይችን ቁራጭ መታጥፍ ለመክተብ መነሻ ሆኖኛል።አበበ ባልቻ ሲተውነው የቆየው ገፀባህርይ (አስናቀ አሸብር) እንደ ህወሃት ወኪል ተሰይሞአል። አስናቀ በጠባዩ ለሃገሪቱ ደንታ የለውም። ገንዘብ በጣም ይወዳል። አብሮአደጉን መስፍን ሊበቀለው ይፈልጋል። ተሳዳቢ ሲሆን፣ በጉልበቱ ይመካል። በቅጥረኞቹ በኩል ሰዎችን ያስደበድባል፣ ያስገድላል። ሃብታም ካገኘ ሊዘርፈው በማሰብ ያንዣብባል። ያም ሆኖ ግን አስናቀ መጨረሻው አላማረም። ንብረት ያከማቸበትን አዳራሽ ሲከፍተው፣ በህገወጥ መንገድ ያከማቸው ንብረት ብን ብሎ ጠፍቶአል። የነበረውን ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወዳልታወቀ ሃብታም፣ (አላሙዲ?) በማዛወሩ በድንገት ባዶውን ቀረ። እና የደም ግፊት? አንቀጥቅጦ ገደለው። የቅርብ ረዳቱ እያሳቀበት ህይወቱ አለፈች።
Subscribe to:
Posts (Atom)

