"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 10 August 2012

በደሴ “አረብገንዳ” መስጊድ ፖሊስ ጥቃት ሰነዘረ




(አቤ ቶኪቻው) 
ላለፉት ስምንት ወራት የቀጠለው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያሰሙት ተቃውሞ በዛሬው ዕለትም በተለይም በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ እና በደሴ አረብገንዳ መስጊድ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ፖሊስ በደሴ የተገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ወሬዎች ደርሰውኛል።
የረመዳን ፆም እንደገባ “ድምፃችን ይሰማ” በሚል ተቃውሞውን ሲያስተባብሩ የነበሩት የኮሚቴ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቢውሉም ህብረተሰቡ በራሱ አስተባባሪነት “ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ” የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አንግቦ ተቃውሞውን ቀጥሏል።

ባለፈው ሳምንት ተቃውሞቸውን በይፋ የጀመሩት የደሴ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ወገኖችም ተቃውሟቸውን በተጠናከረ መልኩ ዛሬም የቀጠሉበት ቢሆንም ልዩ የፖሊስ ሀይል “ከመስጊድ እንዳይወጡ ከልክሎ” የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱን ሰምቻለሁ። በተተኮሱ አስለቃሽ ጭሶች ሴቶች እና በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች ራሳቸውን ስተው በመስጊድ ውስጥ እርዳታ ሲደረግላቸው እንደነበር ከስፍራው የሰማሁት ወሬ ያስረዳል። (ያረዳል ብንለው ይሻላል)
ባለፈው ጊዜ፤ “ህብረተሰቡ ተረባርቦ ይሄንን ተቃውሞ የማያስቆም ከሆነ የከፋ ነገር ይመጣል!” ሲሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በሞቅታ ይሁን በብስጭት ሲናገሩ ሰምቻቸዋለሁ።
እኔ የምለው ግን የራሳችን ሀገር ፖሊስ “ወዮላችሁ!” እያለ የሚያስፈራራን ከሆነ ጠባቂያችን ማነው!? ብሎ መጠየቅ ይቻላል!?



Ethiopian police crack down on Muslim press


Nairobi, August 9, 2012-Ethiopian authorities must release a journalist who has been detained for almost three weeks, and allow three Muslim news outlets to resume publishing immediately, the Committee to Protect Journalists said today. Local journalists believe the Muslim press in Ethiopia is being targeted for its coverage of protests by the Muslim community.



In recent months, Ethiopian Muslims have begun staging protests on Fridays to oppose government policies they say are interfering with their religious affairs, according to news reports . These protests are a highly sensitive issue for the government, which fears a hardline Islamist influence within the predominantly Christian country, news reports said. Local journalists believe the recent harassment of Muslim journalists and newspapers are part of an attempt by Ethiopian authorities to quell coverage of the ongoing protestsin the capital.

Wednesday, 8 August 2012

“እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ሆነ ፆማቸው… ከአምላክ ለመድረስ ቀጠሮ እንዳላቸው” ማን ያውቃል




የአሁኑ አመጣጤ ክርስቲያን ወዳጆቼን አንኳን ለፆመ ፍልሰታ አደረሳችሁ ለማለት እና ሙስሊም ወዳጆቼን ደግሞ የተጀመረው “ዱዓ” ይቀጥልልን ብሎ ለማበከር ቢሆንም “በልጅ አመካኝቶ ይበላል እንኩቶ” እንዲል እንኮቶ ያማረው አባት… እግረ መንገዴን  ከመጣሁ አይቀር ኮስተር ብዬ የማነሳው አንድ ጉዳይ አለኝ።

ትላንት አንድ መረጃ ለጥፌ ነበር። መረጃው “በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በህቡዕ የሚንቀሳቀስ” አንድ ንቅናቄ ያወጣው መግለጫ ነበር። ይህ መግለጫ “የሰራዊቱ አባላት ከዚህ በኋላ ህዝብ ላይ አንተኩስም እስከ መቼ ለአምባገነን መሪዎች አግዘን፤ እኛ መሳሪያ ታጥቀን ቀበቶ እና መቀነት ብቻ የታጠቀውን ህዝብ እንደበድባለን!? ይሄ ነገር ነውር መሆኑን አየን ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነት ነገር ላለመፈፀም ዝግጅታችንን አጠናቀናል”  የሚል ነበር።

ታድያ በዚህ ወሬ የተነሳ በርካታ አስተያየቶችን ተቀብያለሁ። “እሰይ የኔ ወሬ አቀባይ በርታልኝ” ብለው ያበረታቱኝ እንዳሉ ሆነው አንዳንድ ወዳጆች ደግሞ “አንተ ከሀገር ወጥተህ እኛን ልታስጨርስ ነው!” የሚል ወቀሳ ሰንዝረዋል። ይህ ወቀሳ ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ፉርሽ መሆኑን እንደሚከተለው አስረዳለሁ!

ሀ    የንቅናቄው መግለጫ የሚለው የመንግስት ግልበጣ ላድርግ አይደለም፣ ጫካ ገብቼ ጦርነት ልክፈትም አላለም። ከዚህ በኋላ መንግስት ተኩስ ባለኝ ቁጥር ግን ህዝቤ ላይ አልተኩስም ነው ያለው።  በኛ የጨዋታ ስልት ሲቀርብ ደግሞ “ክላሽ እኮ ካውያ አይደለም… ሰውን ያበላሻል እንጂ ልብስን አያሳምርም!”  ስለዚህ ከእንግዲህ ፖሊስም ሆነ ሌላው የጦር ሃይል ከህዝቡ ወገን ነው እንጂ የህዝቡ ወጊ አይደለም ነው ያለው። ታድያ ይሄ እንዴት ሆኖ ነው ህዝብ ማስጨረስ የሚሆነው??? (ጥያቄ ምልክት ጨምሩልኝ!)

ፌደራል ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ “የጁነዲን ሳዶን ባለቤት ያሰርኩት በሽብርተኝነት ጥርጥሬ ነው” አለ



የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሁለት ሣምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሽብር ተግባር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገ ሲል ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።
የፌዴራል ፖሊስ የውጪና ሕዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወ/ሮ ሃቢባ የተያዙት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ ከፍ/ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ መሠረት ነው። ፖሊስ ያለማስረጃና ያለበቂ ጥርጣሬ ከመሬት ተነስቶ አንድን ግለሰብ ሊይዝ የሚችልበት ሕጋዊ መሠረትም እንደሌለ አስረድተዋል።
ተጠርጣሪዋ ከተያዙ በኋላ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ ተፈቅዶ በምርመራ ላይ መሆናቸውን ኮማንደር አበበ አስታውሰዋል።
ሚኒስትር ጁነዲን የምርመራ ሂደቱ ሳያልቅ ባለቤታቸው ንፁህ መሆናቸውን መናገራቸው ተገቢ አለመሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል። ‘‘የአንድ ሰው ነፃ መሆን የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ ነው። ፖሊስና የዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ባልተሰማበት ሁኔታ ባለቤቴ ንፁህ ናት ብሎ መናገር ተገቢ አይደለም’’ ብለዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ይኸው ጋዜጣ በዛሬው እትሙ በሕዝበ-ሙስሊሙ እና በመጅሊሱ መካከል ላለፉት ሰባት ወራት የተፈጠረውን አለመግባባት በሽምግልና ለመፍታት እየተሞከረ ነው፤ ሽምግልና ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ያሉት በራስ ተነሳሽነት የተሰባሰቡ ስምንት አባላት ያሉት ገለልተኛ ግለሰቦች ናቸው ሲል ዘገበ።
አለመግባባቱን በሽምግልና ለመፍታት ጥረቱን የጀመሩት የእምነቱ ተከታይ የሆኑ የሀገር ሽማግሌዎችና የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው። ይህንኑ ሙከራቸውን በተመለከተ በመንግስት በኩል ያለው ምላሽ እስካሁን አለመታወቁን ሽምግልናውን ጀምረናል ካሉት መካከል አንዱ ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለጹለት ዘግቧል።
የሽምግልናው መጀመር በተመለከተ በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት መፍጠሩን ምንጮቻችን አመልክተዋል ያለው ሰንደቅ ሽምግልናውን የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ ቀላል የማይባሉ የእምነቱ ተከታዮች ጅምሩን በጥርጣሬ አይን እያዩት ነው። ሽምግልናውን ከጀመሩት የኮሚቴ አባላት አንዱ የሽምግልናው መጀመር መደገፍም ሆነ መቃወም መብት መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ‘‘እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን’’ ማለት ግን አክራሪነት ነው ብለዋል።
‘‘አንደኛውም ሆነ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሰላም ስምምነት ነው የተፈታው’’ ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሽምግልናው ኮሚቴ አባል ችግሩ በእርቅና በሽምግልና ይፈታ ማለት የሃይማኖታችንና የሀገራችን ባህል ነው ብለዋል።
የሽምግልና እንቅስቃሴው ከተጀመረ በኋላ አንዳንድ ታዋቂ ሰዎችም በጉዳዩ ውስጥ ለመግባት ፍላጐት እያሳዩ መሆኑም ታውቋል። ሽምግልናው የታሰሩትን አባላት ከማስፈታት ባለፈ ችግሩን ከስሩ መርምሮ የመፍታት ዓላማ እንዳለው ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስትን ከመደገፍና ከመቃወም በዘለለ እንደ ሀገር መኖር ስላለብን መንግስት የሽምግልናውን ሂደት በሆደ ሰፊነት ይመለከተዋል የሚል ተስፋ አለን ብለዋል።
ሕዝቡ ሙስሊሙ በተመለከተ የቁርአንን ሕግና የነብዩን ትምህርት ላይ የቀረቡ ደንብና ስርዓቶችን እያገናዘበ እንዲጓዝ እንፈልጋለን ያሉት የሽምግልናው አስተባባሪዎች፤ ሕዝበ-ሙስሊሙ የቁርአንን ሕግ፣ የእስልምና ታሪክ በወጉ በማወቅና በሰከነ መንፈስ እንዲጓዝ ጠይቀዋል። ‘‘ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም’’ የሚሉት አስተባባሪዎቹ የሃይማኖት ጉዳይ በወጉ መያዝ እንዳለበት አሳስበዋል። የሽምግልናው ሂደት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ሲል ማንነታቸውን በግልፅ እንደሚያሳውቁም አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በመንግስት በኩል ስለ ሽምግልናው ያለው ምላሽ ለጊዜው አልታወቀም። አንደ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የመንግስት ባለስልጣን መንግስት ከወንጀለኞች ጋር አይደራደርም ማለታቸው የሽምግልናውን ሂደት አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋትን ከወዲሁ ፈጥሯል።
ባለፉት ሰባት ወራት በእስልምና ም/ቤት መጅሊስ አመራር ምርጫ፣ ምርጫው የትና በማን ይከናወን፣ በአወሊያ ት/ቤት አስተዳደር፣ በአሕባሽ አስተምህሮ ጉዳይ በሕዝበ-ሙስሊሙ እና በመጅሊሱ እንዲሁም በመንግስት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ይታወሳል። አለመግባባቱንም ተከትሎ በታላቁ በአንዋር መስጊድና በአወሊያ ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች መጎዳታቸውና መታሰራቸው ይታወቃል።

i

አምባሳደር ስዩም መስፍን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ተክተው እየሰሩ መሆኑ ተጠቆመ



የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ከ45 ቀናት በላይ በመደበኛ ስራቸው ላይ ባለመሆናቸው በኢህአዴግ አመራሮች መካከል በስልጣን ሽኩቻ እንደተፈጠረና አቶ ስዩም መስፍን የአቶ መለስን ቦታ ተክተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
የፍኖተ ነፃነት ታማኝ ምንጮች እንደገለፁት የቻይና ዲፕሎማቶች ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድርድር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ስዩም መስፍን ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ጋር በመምጣት ቤተመንግስት ሆነው የመሪነቱን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን ይህንን ለማጣራት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ጋር ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ስልካቸው ባለመነሳቱ ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠይቀናቸው “አምባሳደር ስዩም መስፍን በአሁን ወቅት በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ናቸው፡፡ መደበኛ ሥራቸውም ይሄ ነው፤ ከዛ ውጭ እንደማንኛውም አምባሳደር ለስራ ጉዳይ ሀገር ቤት ይመጣሉ” በማለት ተጨማሪ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጤና አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እየተገለፀ ቢሆንም በቅርቡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጠ/ሚኒስትሩን መታመምና በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው በሐኪሞቻቸው እንደተነገራቸው ከማሳወቅ ውጭ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በግልፅ ማን እየመራ እንዳለ ከመግለፅ በመቆጠቡ ይታወሳል፡፡