"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 14 August 2012

አቦይ ስብሐት “አዲስ አድማስ ጋዜጣ ውሸቱን ነው መለስ በቤታቸው የሉም” አሉ



ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ማውራት ደክሞኝ ነበር። ሳስበው ሳስበው እርሳቸው የሆኑትን ሆነው ደከመኝ ሳይሉ እኔ እንዴት ደከመኝ እላለሁ ብዬ ተፀፅቻለሁ። መቅደላዊት የተባለች ወዳጄም ከሪያድ በሰደደችልኝ አስተያየት ሀዘኑን እንረሳው ዘንድ ስለርሳቸው መጨዋወታችንን እንቀጥል እንጂ ድንኳን ሳይነሳ የምን ዝም ዝም ነው የሚል ወቀሳ ሰንዝራልኛለች። እኔም በሆዴ የምን ሀዘን ብዬ ሳበቃ  “እውነት ግን ምን ነካኝ…!” ብዬ ሂሴን ውጫለሁ!


                                 አቦይ ስብሐት “አዲስ አድማስ ጋዜጣ ውሸቱን ነው መለስ በቤታቸው የሉም” አሉ

አሁን በቅርቡ ከኔ በላይ ውስጥ አዋቂ ላሳር ያለው አዲስ አድማስ ጋዜጣ፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቤተ መንግስት እያገገሙ ነው” በሚል ርዕስ ባሰፈረው ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራት ባለስልጣናት ጋር እየተመካከሩ በቤታቸው ውስጥ የጠቅላይነት ሚናቸውን እየተወጡ ነው የሚል ሀተታ አቅርቦልን ነበር።

እርግጥ ነው በርካታ የአራዳ ልጆች የጋዜጣውን ዘገባ በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱት። አንዳንዶቹም “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤተ መንግስት እየገገሙ ነው ወይስ እያገገሙ!?” ሲሉ ጠይቀው ነበር። በአራዶች ቋንቋ “መገገም” ማለት እምቢኝ አልተውም፣ የመጣው ቢመጣ ዘወር አልልም፣ የያዝኩትን ከምለቅ ወገቤ ይላቀቅ ወዘተ. የሚል ትርጉም ቢሰጠው ብዙ አራዶች ይስማሙበታል። በዚህ የትርጉም አግባብ ታድያ አቶ መለስ በቤተ መንገስቱ እውነትም እየገገሙ ከሆነ ሞተውም ሆነ ድነው አይለቁንም ማለት ነው።

የሆነው ሆኖ ትላንት ለኢሳት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) (እናንተዬ ኢሳት እና ኢቲቪ ስማቸው እየተመሳሰለ ያለበትን ሁኔታ ልብ አላችሁልኝ!?) እና አቦይ ስብሀት ለኢሳት ሲናገሩ አዲስ አድማስ ጋዜጣ መለስ ቤተ መንግስት ውስጥ ናቸው ያለው ውሸቱን መሆኑን ተናግረዋል!  አቦይ ስብሀትን አመስግነን አዲስ አድማስን “ሼ” ብለን ስለጠቅላይ ሚኒስትራችን ጉዳይ ዳግም ለማውራት ተነሳሽነታችን እንደመጣ በይፋ እንናገራለን!

በርሰቸው ጉዳይ ሌላም ጨዋታ አለኝ

US official: United States has been in contact with several Ethiopian officials since Meles‘ disappearance


US official: United States has been in contact with several Ethiopian officials since Meles‘ disappearance
Posted by admin on August 14, 20128 Comments
A note from Awramba Times Editor: As the current Ethiopian political structure is a monolithic party-state on the shoulders of Meles, his  disappearance from the public eye for the last 53 days is sill a hot issue. Washington Times became the first paper to break the silence among US Medias on the whereabouts of Meles. A spokesman in the U.S. Bureau of African Affairs told Washington Times that the United States has been in contact with several Ethiopian officials since Meles‘ disappearance but would not speculate on what changes might occur should the prime minister not return to his duties. Please read Ioannis Gatsiounis’ analysis on the Washington Times.

Where in the world is Ethiopia’s prime minister?
By Ioannis Gatsiounis
(The Washington Times) – The question is not a geographical brain teaser but a concerned query about the well-being of Prime Minister Meles Zenawi, who has not been seen in public for two months, and about Ethiopia’s commitment to U.S. counterterrorism efforts in neighboring Somalia.

U.S. Secretary of State Hillary Clinton with Hailemariam Desalegn and Birhane Gebrekrstos, in Addis Ababa, June 14, 2011 (Photo Reuters)
Ethiopian officials say Mr. Meles, 57, is recovering from an undisclosed illness, but he has not been seen or heard from since he attended the Group of 20 summit in Mexico in mid-June.
In his absence, the government has continued to brook little dissent from the media, activists and members of opposition parties. It also has announced that Ethiopian troops will remain in Somalia to help defeat al-Shabab, the al Qaeda-linked Islamist militant group that has ruled large areas of the Horn of Africa nation.
What’s more, government insiders say Mr. Meles has been grooming his deputy, Foreign Affairs Minister Hailemariam Desalegne, to succeed him.

Monday, 13 August 2012

Mystery of ethiopia,s missing prime minister


Ethiopia’s missing prime minister has been taking part in diplomatic efforts to resolve the Sudan crisis from his sick bed, according to African Union officials.
Meles Zenawi, Ethiopia’s normally highly visible premier, has not been seen in public since June, and his government has refused to release any details of his condition.
His disappearance saw opposition groups claim that the 57-year-old had died, while there are unconfirmed reports that he has been treated for a brain tumour.
His absence became more apparent as Ethiopia hosted an important African Union summit in the capital, Addis Ababa, where Mr Meles would have expected to lead efforts to defuse the crisis in DR Congo and the simmering dispute between Sudan and newly independent South Sudan.
Despite his failure to appear at the summit – where his wife played host to African leaders – the AU say he has been in regular contact with the their chief mediator in the Sudans’ dispute, the former South African president Thabo Mbeki.
Mr Meles was understood last month to be being treated in a hospital in the Belgian capital, Brussels, but Ethiopian officials insist he has since returned to Addis Ababa. The influential information minister, Simon Berekat, a close ally of Mr Meles said he expected him to return to work “soon” and that he had taken “sick leave”.

የግፍና የሰቆቃ እስር በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ቀጥሏል


e
የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ መሆን ኦነግ መሆን አይደለም። ወያኔ ግን ንጹሐንን ኦነግና አሸባሪ በማለት ያስራል። ከላይ የምታዩአዋቸው በ እስር ቤት ከሚገኙ የኦሮሚያ ተወላጆች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
ኢህአዴግ እስር ቤቶቹን “ማረሚያ ቤቶች” እያለ ቢጠራቸውም፣ መጠሪያው እውነተኛውን የእስር ቤቱን ገጽታ ስለማይገልፀው እንደ ቀድሞ ስሙ “ወህኒ ቤት” ተብሎ ቢጠራ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ከዚህ በፊት ከነበሩት የከፉ ናቸው ለማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የግፍና የሰቆቃ እስሩ እጅግ ሰብአዊነት በጐደለው ሁኔታ በፖለቲካ አስተሳሰብና በዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ነው፡፡ ቃሊቲ ወህኒ ቤት እስር ቤት ብቻ ሳይሆን የመረጃ ማዕከልም ነው፡፡ የመላው አገሪቱ የዕለት ተዕለት መረጃ በትኩሱ በቅብብል ይደርሳል፡፡ በመላው የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ያለው ሁኔታም በየዕለቱ ይሰማል፡፡
ባለፈው ጽሁፌ ራሴን ለማስተዋወቅ እንደሞከርኩት በዚህ የዘረኞች ወህኒ ቤት 19 ዓመት ከ8 ወር ቆይቼአለሁ፡፡ እኔ ከዚህ ሳልወጣ አራትና አምስት ጊዜ ተመላልሶ የታሰረ እስረኛ አጋጥሞኛል፡፡ የሸዋሮቢት፣ የዝዋይና በቅርቡ ሥራውን የጀመረው የቂሊንጦ ከፍተኛ ወህኒ ቤት በመረጃ ደረጃ የሁለት የጐረቤታሞች ያህል መረጃ እንለዋወጣለን፡፡ በዚሁ መሠረት ዛሬ ህዝብ ስለማያውቃቸው ድብቅ እስር ቤቶችና በየድብቅ እስር ቤቶቹ ስለሚፈፀሙ ግፈኛ ድርጊቶች ላውጋችሁ፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ “በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካና የህሊና እስረኛ የለም” ይለናል፡፡ ምንም እንኳን መኖሪያ ቤታችን ቃሊቲ ቢሆንም የመንግስትን መረጃ በተሟላ ሁኔታ እንከታተላለን፡፡ ሬዲዮ ከተከለከልን ሦስት ዓመት ቢልፈንም፣ በቃሊቲ ኢቴቪ 24 ሰዓት ይሰራል፡፡ የውጭ ሚዲያዎች የሚያወሩትን ውጭ ካለው በበለጠ እንሰማለን፡፡ በተጨማሪም ጠያቂዎቻችን ሁሉንም ነገር ይነግሩናል፡፡

Sunday, 12 August 2012

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆቿን እየበላች ነውን!?


ይህ ጨዋታ ለዚህ ሳምንት ፍትህ ጋዜጣ የተላከ ነበር። ነገር ግን ፍትህ አሁንም በሀገሪቱ እንድትኖር ሰዎቻችን አልፈቀዱም። በፍርድ ቤት የታዘዘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “መጀመሪያ ሌላ ቦታ አሳትሙና በሚቀጥለው ሳምንት እኔ አትምላችኋለው” ብሎ መልስ ሰጠ ሲባል ሰማሁኝ። ይሄ በጣም አስቂኝ ነው…! ሌላ ማተሚያ ቤት እኮ የለም። አንድ ቦሌ ማተሚያ ቤት ነበረ እርሱም ደንበኛችን ስላልሆናችሁ አናትምላችሁም ብሏል። ወደየት እየተገፋን እንደሆነ እግዜር ይወቀው!

እስቲ ለማንኛውም ወጋችን ይጀምር…

ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ? ፍትህ ጋዜጣ በፍትህ ችግር ታግታ ሰነበተችና ተጠፋፋን አይደል!? ጉልቤው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ያለ ምንም ህጋዊ አግባብ የእናንተን ጋዜጣ አላትምም ብሎ ደጅ ሲያስጠናን ቆይቶ ይኸው ዛሬ “የተከበረው” ፍርድ ተቆጥቶልን ለመገናኘት በቅተናል።

ብዬ ነበር የጀመርኩት… እኔማ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማክበር የሁላችንም ግዴታ መስሎኝ ነበር። ለካስ ፍርድ ቤቱን ማክበር የአንዳንዶቻችን ብቻ ነው…! አንድ ቀን አንዳንድ ከመሆን ተላቀን አንድ እንሆን ይሆናል! ብቻ ግን አስቲ ወጋችን ይቀጥል…

ፍርድ ቤት ካልኩኝ አይቀር፤ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን “ክቡር” ፍርድ ቤቱ “ኑ እንመካከር” ብሎ ጠርቷቸው ሲያበቃ ምንም ባልተከሰሱበት እና ባልተከራከሩበት ችሎት ገትሮ እያደረጋችሁ ያላችሁትን እናውቃለን ነገረ ስራችሁ በሙሉ ጥፋት ነውና እና “ወዮላችሁ” ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው አይደለም እንዴ!?

ነገሩ እንዲህ ነው፤ የፓርቲው አመራር አባላት በትግል አጋሮቻቸው “እነ አንዷለም አራጌ    እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተፈረደው ፍርድ አግባብ አይደለም” ብለው በየ ሚዲያው ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር፤ ታድያ ፍርድ ቤት ሆዬ “ይሄማ እልም ያለ ጥፋት፤ ጭልጥ ያለ ወንጀል ነው።” ብሎ ጠርቶ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው። በነገራችን ላይ ለአንድነት ፓርቲ ፍርድ ቤቱ የላከው ደብዳቤ ላይ ተከሳሽ ማን እንደሚል ያውቃሉ…? “አቃቤ ህግ!”  ነው የሚለው። ወይ ጉድ! እናንተዬ አንዳንዴ ይሄ የኮምፒውተር ታይፕ መንፈስ ቅዱስ ያናግረዋል እንበል እንዴ!? የሆነ ሆኖ አቃቤ ህግ “ተከሳሽ” ተብሎ በተፃፈበት የመጥሪያ ወረቀት አንድነቶች ትህትና ይዟቸው ሄዱ… ከዛም ጥፋተኛ ናችሁ ተባሉ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ፍርድ ቤት ሰዎችን ጥፋተኛ ለማለት ችሎት አቁሞ ሰዎቹ ተከራክረው ዳኞች ግራ ቀኙን አይተው ነበር ጥፋተኛ የሚሉት…! ወይስ ይሄ ነገር ዘወትር ማክሰኞ ማታ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ብቻ ነው…!? ብዬ ልሳለቅ አማረኝና ግዜው የልማት እንጂ የስላቅ ነውን…!? ስል ራሴ ላይ ክልከላ አድርጌያለሁ።

እኔ የምለው ወዳጄ ልማቱ እንዴት ይዞታል!? ማለቴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በኋላም እየተቀላጠፈ ነው ወይስ እየተንቀራፈፈ ነው? አይ እርሳቸው እንደው ሜዳ ላይ በትነውን እልም አሉ እኮ! አንዳንድ የፌስ ቡክ አሽሟጣጮች “አባይን የደፈሩ መሪ ሞትንም ደፈሩት!” እያሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። እንዴት ነው ነገሩ በቃ ቁርጡ ታወቀ እንዴ!? በእርግጥ እዚህ ውጪው ሀገር የሚገኙ መገናኛ ብዙሃኖች መርዶውን ካረዱን ቆይተዋል። የሀገር ውስጥ ዘጋቢዎቻችን ግን አንዴ ገቡ፣ አንዴ ወጡ፣ አንዴ አረፉ፣ አንዴ አገገሙ እያሉ እያምታቱን ነው።

በዛ ሰሞን ፋና ኤፍ ኤም ራዲዮን “ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ነገር ቢሆኑ ማን ይተካቸዋል!?” የሚል የህግ ውይይት ማድረጉን ስሰማ ይሄ ነገር በቃ ለይቶለታል ማለት ነው…? መቼም እዚህ አገር “ደግ አይበረክትም” ብዬ ተንሰቅስቄ ነው ያለቀስኩት። አሁን በቅርቡም ለጠቅላይ ሚኒስትራችን የስጋ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው እሜቴ ሚሚ ስባቱ ራዲዮ ላይ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢያርፉ እንኳ ሀገሪቷ በአንድ ሰው መሞትና አለመሞት ላይ የሚመጣ ለውጥ የለም” የሚል እጅግ ጨካኝ የሆነ አስተያየት ሰማሁኝ! በእውኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድ ሰው የሚባሉ ናቸውን…? ለነገሩ ባለፈው ጊዜም እኚያ አቦይ ስብሀት “ፋጢመት ሞተች አልሞተች ዘሪሁን ሞተ አልሞተ መለስ ሞተ አልሞተ እኛ ምን አገባን” አይነት ነገር ሲናገሩ በሰማሁ ጊዜ በእውነቱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከእኛ በቀር አንድ እንኳ አሳቢ ሰው እንደሌላቸው ተረድቻለሁ።

ኧረ ስለ እትዬ ሚሚ ካነሳን አይቀር የምንቀደው አለን…

እማማ ሚሚ በኤፍ ኤም ራዲዮናቸው ላይ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሞቱም ግዴየለም” ከሚለው ጨካኝ ንግግር ጋር አብረው የዘመድ አንጀት ሆኖባቸው ነው መሰል “ደግሞም ሀገር ውስጥ ያለው ህዝብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤና እየፀለየላቸው ነው!” ብለው ሆድ አስብሰውኛል።  እሜቴ ሚሚ ልብ አላሉም እንጂ በውጪ ያለውም ኢትዮጵያዊ እንዴት በአንድ በአንድ እግሩ ቆሞ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚፀልይ ቢመለከቱ ይደነቁ ነበር። የምሬን ነው የምልዎት በርካታ በውጪ ሀገር የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ትልቅ ፀሎት እያደረገ ነው። እርግጥ ነው የአብዛኛው ሰው ፀሎት እርሳቸው ድነው የበደሉትን ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ለንስሀ ሞት እንዲበቁ መሆኑን ሰምቻለሁ። (እኔ እንደሆንኩ  የሰማሁትን መደበቅ አይሆንልኝም።)

ወደ እትዬ ሚሚ ስንመለስ “ክብ ጠረቤዛ” የሚል አንድ ፕሮግራም አላቸው። እርሱን ፕሮግራም አልፎ አልፎ ለማዳመጥ እድሉ ገጥሞኛል። አንድ ግዜ ቁጭ ብዬ ስሰማ አንዱ ወዳጄ ሰማኝና ምን አለኝ መሰልዎ… ይሄ ፕሮግራም “በማሽካካት እና በጫጫታ የተሞላ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ ክብ ጠረቤዛ ነው ክብ ባንኮኒ ብዬ እጠራጠራለሁ።” ብሎኛል የምር ግን እኔ ራሴ ፕሮግራሙን ሳዳምጥ በተለይ አንዳንድ ጊዜ በገደል ማሚቶ የታጀበ ሳቅ እና ሁካታውን ሳዳምጥ ይሄንን ሰፈር የት ነበር የማውቀው…? ብዬ አይኔን ጨፈን አድርጌ አስባለሁ… ትዝ ሲለኝ ለካስ ቺቺኒያ እና ካዛንቺስ ነው….! የብርጭቆው ኳኳታ የለም እንጂ በእውነት “መሸታ” ቤቶቻችንን ትውስ ያደርጋል!

በነገራችን ላይ እነ እማማ ሚሚ ሲበሳጩ የሚናገሩትን አያውቁትም እየተባሉ ይታማሉ። ባለፈው ጊዜ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ላይ ሲያደርጉ የነበረው ዘለፋ እና ስድብ የቀለጠው መንድር ድራማ ላይ እንኳ የለም።

ብዙ ግዜ ሚዲያ ላይ ያለ ሰው ለብዙሃኑ ህብረተሰብ ስሜት እና እምነት ይጠነቀቃል። ማህበረሰቡ ውስጥ የአመለካከት ችግር አለ ብሎ እንኳ ቢያምን የሚሰራውን “ስህተት” ቀስ ብሎ በተለያዩ የኪነጥበብ ዘዴዎች እና ለዛ ባላቸው አቀራረቦች ለማረቅ ይሞከራል እንጂ እንደነ እትዬ ሚሚ “የጉራንጉር ሰፈር ስድብ” እየተሳደቡ መውረግረግ እንኳንስ ሚዲያ ላይ እና ሜዳ ላይም ቢሆን ከጨዋ ልጅ የማይጠበቅ ነውር ነው።