"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 15 August 2012

(ሰበር ዜና) በኩክ የለሽ ማርያም ቤ/ክ አካባቢ በደረሰ ፍንዳታ ምእመናን ሞቱ


Share
(ዘ-ሐበሻ) ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አሁን ከኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ደብረብርሃን ከተማ አካባቢ በተለምዶ ኩክ የለሽ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቤ/ክ አካባቢ ምንነቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ለሱባዔ የገቡ ምዕመናን ሞቱ፤ በርከት ያሉ ሰዎችም እንደቆሰሉ የምንጮቻችን ዘገባ አመለከተ። ምንጮቻችን በኩክ የለሽ ማርያም አካባቢ የፈነዳውን ማን እንዳጠመደው እንዳልታወቀ ገልጸው፤ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም እስካሁን እየተጣራ መሆኑም፤ የቆሰሉትም በርካታ እንደሆነ እንጂ ቁጥሩ ለጊዜው እንደማይታወቅ ገልጸዋል።
የ16 የኪነምህረትን ጾም በማስመልከት በኩክ የለሽ ማርያም ቤ/ክ በርከት ያሉ ምዕምናን ከተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ ሱባዔ የሚገቡ ሲሆን ይህ አደጋ መከሰቱ እጅጉን እንዳነጋገረ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች መንግስት ራሱ አፈንድቶ ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር ለማያያዝ ያደረገው ሴራ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው።
መረጃውን አጠናቅረን ጠለቅ ያለ ዘገባ ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።  

ዋልድባ ጉድ እያፈላች ነው፤ አቡነ ጳውሎስም ሆስፒታል ገቡ




Share

(ዘ-ሐበሻ) ዋልድባ ገዳምን የተዳፈሩ ሁሉ እግዚአብሄር እየቀጣቸው እንደሆነ በርከት ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ያምናሉ። የተከበረውን ገዳም የስኳር ማሳ ለማድረግ የወያኔ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፤ እነ አቡነ ጳውሎስም ገዳሙ አይነካም፤ ልማት ነው እያሉ ሲከራከሩ ነበር። ያን ጊዜም የሚከተለው ግጥም በዘ-ሐበሻ ላይ ቀርቦ ነበር።
እያንገራገረ ህዝቡ እያባባ
አበው እያዘኑ ወጣት እያነባ
እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ
ዜናው በዓለም ዓቀፍ እየተስተጋባ
ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ
ከፍ ከፍ ብሎ ለዚያውም ዋልድባ
ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ
በአቋሙ ጠንክሮ በአቋሙ ጸንቶ
አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ
ጣፋጭ የነበረው ሊመር ነው ከቶ
ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ
ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ
ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ
ምን ይውጥሽ ይሆን ከእንግዲህ መርካቶ
አባቶ ች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ
በአባቶች አጽም ላይ ሸንኮራን ሲተክሉ
ከተቀበረበት እየፈነቀሉ
በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ
በውሳኔ ጸንቶ
ኸረ እግዚኦ በሉ!
ይሄስ ጥሩ አይደለም
ከአቅም በላይ ሆኖ ህዝቡ ቢበደለም
አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግድ የለም
ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ
በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ
ጸሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ
ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ
በዋልድባ 4 የፌደራል ፖሊሶች በጅብ የመበላታቸው ዜና ከዚህ ቀደም ተዘግቧል። ገዳሙን ለመጠበቅ ከሄዱት መካከልም የሚታመሙ ብዙ ናቸው። የአቶ መለስ ዜናዊ ሕመምም እንዲሁ ከዚሁ ዋልድባ ገዳም ጋር ተያያዞ የገዳሙ አባቶች ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡›› እየተባሉ ሲዋከቡ ነበር። ዛሬ ደጀሰላም ድረ ገጽ እንደዘገበው ደግሞ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸውን ዘግቧል። ይህን ተከትሎ የዋልድባ አባቶች ጸሎት እየተሰማ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በየቦታው በርክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አስተሳሰባችንን በማናወጥ ወንጀል” ሊጠየቁ ይገባል ተባለ!


ይህንን ቃል ለመጀመሪያ ግዜ የሰማሁት ሰፈሬ እንጦጦ ኪዳነምህረት ፀበል ነው። ተጠማቂዎች በአጋንንት እና በሌሎች ርኩስ መናፍስት አይምሯቸው ይናወጥ እና በአስጠማቂዎች ፍዳቸውን ያያሉ። “ያናወጥከውን አዕምሮዋን መልስ…! ልቀቅ…! ውጣ!” ይባላል። ከዛም ወዶ ሳይሆን በግዱ ይለቃል። ያናወጠውን አዕምሮም ይመልሳታል።
ዛሬ ደግሞ ጋዜጣ በማሳተም የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ከፍ አደርጋለሁ ብሎ መከራውን ሲያይ የነበረው ወዳጃችን ተመስገን ደሳለኝ “የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በማናወጥ” ወንጀል ተከሷል።
ይሄንን ነገር እርኩስ መናፍስት ብቻ የሚያደርጉት ሲመስለን የነበርሁ።ን እኛ፤ በነገሩ ግራ ተጋብተን እንዴት አድርጎ አስተሳሰባችንን እንዳናወጠ  አቃቤ ህግ የሚያቀርበውን ማስረጃ ለመስማት ተቻኩለናል። የተሜን የክስ ሂደት አስመልክቶ እየተከታተልኩ የአቅሜን ያህል “አንጀት ላይ ጠብ የሚል” መረጃ ለማቀበል እሞክራለ
አሁን ግን ነገሩን ያነሳሁት “የህብረተሰቡን አሰተሳሰብ ማናወጥ” የሚለው ክስ እኛ ለእርኩስ መናፍስት እንጂ ለምድራዊው ሰው የሚቀርብ ስላልመሰለን ትተነው እንጂ በአሁኑ ግዜ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስተሳሰባችንን ያናወጠ ማን አለ!? ብለው የሚጠይቁ አንዳንድ ወዳጆችን በመስማቴ ነው።

እስከመቼ ከባለድል አትሌቶች ጀርባ ተደብቀው ያጭበረብራሉ?


August 14, 2012


አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ሀላፊዎችና የፕሬስ አታሼ ከባለድል አትሌቶች ጀርባ ተደብቀው እስከመቼ ያጭበረብራሉ?
“ፊሽ – የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፕሬስ አታሼን አነጋግርና አትሌቶችን ለቃለ መጠይቅ የምናገኝበትን መንገድ እስቲ አመቻች” የሚለው ጥያቄ የመጣው የ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የኦሎምፒክ ዜና አገልግሎት (Olympic News Service) ውስጥ በምሰራበት ወቅት የአትሌቲክስ ቡድን ስፖርት ባለሞያ ከሆነው ባልደረባዬ ነበር። የዜና አገልግሎቱ ስራውን ሲጀምር ወደለንደን የሚመጡት የኦሎምፒክ ቡድኖች ህዝብ ግንኙነት ወይም ፕሬስ አታሼ ሀላፊዎች የብሪታኒያ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ቁጥር መረጃ ከሀላፊዎቹ ስም አጠገብ የሰፈረበት የመገናኛ ብዙሀን መመሪያ አነስተኛ መጽሀፍ ተሰጥቶን ነበር። ታዲያ ባልደረቦቼ የእኔን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪነት እና ቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረኝ የሬድዮ ጋዜጠኝነት ሞያን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድንን በተመለከተ መረጃዎችን የማሰባሰብ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጡኝ። ባልደረቦቼ ያላወቁት ነገር ቢኖር ከኢትዮጵያ የመንግስት ድርጅቶች መረጃ ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ነዳጅ ማውጣት የሚቀል መሆኑን ነው።
የመጀመሪያው ስራዬ የነበረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፕሬስ አታሼ ማን እንደሆነ መፈለግ ነበር። ከጥቂት አሰሳዎች በኋላ ገበያው ታከለ የሚል ስም የተሰጠን የመገናኛ ብዙሀን የግንኙነት መረጃ መመሪያ ላይ ተጽፎ አየሁ። ገበያው ታከለ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የገንዘብ ያዥ እንደነበሩ ስለማውቅ ‘እውነት ከሰውዬው ጋር ትክክለኛ የሚዲያ ስራ መስራት ይቻላለን?’ የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገደደኝ። ሌላኛው የአእምሮዬ ክፍል ደግሞ ‘ምንአልባት ነገሮች ተለውጠውና ተሻሽለው ይሆናል’ የሚል ሀሳብ አነሳና በሁለት ሀሳብ ተወጥሬ ለማንኛውም ሰውዬውን ላግኛቸውና የግንኙነት መስመራችንን ላመቻች በሚል ስልክ ለመደወል ስዘጋጅ ከገበያው ታከለ ስም አጠገብ የስልክ ቁጥር እንደሌለ ተገነዘብኩ። ቀጣዩ አማራጭ የነበረው ከሀገርቤት የሚመጡ ጋዜጠኞችን በመገናኘት የአቶ ገበያው ታከለን አድራሻ ለማግኘት መሞከር ቢሆንም የቀድሞ ባልደረቦቼም ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው ለማወቅ ሰከንዶች አልወሰደበኝም። በሮች ሁሉ ዝግ የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከኦሎምፒክ ስታዲዬሙ አጠገብ የሚገኘው የአትሌቶች መለማመጃ ቦታ ላይ ያገኘሁት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቡድን አባል ስለቡድኑ አንዳንድ ዝግጅቶች እንዲነግረኝ ስጠይቀው “ለቃለምልልስ ከላይ ትእዛዝ ማግኘት አለብኝ” የሚል መልስ ከመስጠቱ በተጨማሪ “የፕሬስ አታሼውን ስልክ ቁጥር ነገ አመጣልሀለሁ” ብሎኝ ከተለያየን በኋላ እንደተደበቀኝ የለንደን ኦሎምፒክ ተጠናቀቀ።
በኦሎምፒኩ የፕሬስ አታሼው ቀዳሚ ስራ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር ግንኙነቶችን በመፍጥር ለሚመለከተው አንባቢ፣ ተመልካችና አድማጭ ስለሚፈልጋቸው ሰዎች መረጃዎችን እንዲያገኝ ማስቻል ቢሆንም ገበያው ታከለ ግን አይደለም የኢትዮጵያ አትሌቶችን ሊያገናኝ እራሱም ሳይገናኝ ቀርቷል።

Tuesday, 14 August 2012

ቻልኩበት የተሰኘው የኩኩ ሰብስቤ አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ይለቀቃ


ቻልኩበት የተሰኘው የኩኩ ሰብስቤ አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ይለቀቃ

በለስላሳ ወይንም ትዝታ እየተባለ በሚታወቀው የሙዚቃ ስልት እና በአዘፋፈኖቿ ቅላጼዎቿ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላት የድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ “ቻልኩበት ” የተሰኘው አልበም በሚቀጥለው ሁለት ሳምንታት ለህዝብ በይፋ ይለቀቃል ።በአዲካ አከፋፋይነት የሚለቀቀው ይኽው የሙዚቃ አልበም በአቢይ አረቃ እንደተቀናበረ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ። በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሰው የቅርብ መረጃ እንደሚያመለክተው ከብዙ ልፋት እና ጥረት በሁዋላ አልበሟን ለመልቀቅ ከፍጻሜ እንደደረሰች ተገልጾአል ። በኢትዮጵያ ውስጥ እና በአውሮጳ እና እንዲሁም በሌሎች አገራት በሚከሰተው የሰው ልጅ ስራ ፈጠራ መብትን ገፈፋ ወይንም የኮፒ ራይት ጥሰትን አስመልክቶ ብዙሃኑ ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን ለህዝብ ከማቅረብ ይልቅ ለማፈን ተገደው የነበረ አስታውሰው ፣ከማፈን ምንም ለውጥ እንደሌለ በመረዳት ስራዎቻቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ገልጸዋል በዚህ ስድስት ወራት ተከታታይ ከሶስት ያላነሱ የሙዚቃ ስራዎች መለቀቃቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁን ሰአት በመላው አለም የሚከናወነውን የሰዎችን የፈጠራ ስራ የሚያስከብር ማህበር በሰሜን አሜሪካ በቺካጎ አካባቢ ፈቃድ ማግኘቱን እና ስራውን በሰፊው በቅርቡ በመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ እንደሆነ ከድርጅቱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይኸው ድርጅት ከአሜሪካ የኮፒራይስ ኦርጋናይዜሽን ጋር ጥምረትን ፈጥሮ በከፍተኛ ደረጃ የሚሰራ ሲሆን ይበልጥ የኢትዮጵያን ኮፒ ራትይ ስራዎችን በሰሜን አሜሪካ ያለማንም ፈቃድ አባዝቶ መሸጥ በስፋት የሚከናወን ሲሆን በተለያዩ የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ሱቆች ውስጥ እንደሚሸጡ    አጣርቶ መረጃዎቹን የያዘ መሆኑ አክሎ ገልጦአል ። ፈቃዱን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮም ከአሜሪካን ፌደራል ኢንቨስቲጌሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ጥናቶቹን እያደረጉ ክሶችን ማዘጋጀትም እንደጀመሩ ተገልጾአል፣ ።በሌላም በኩል በሰሜን አሜሪካ ለሚከናወነው የፈጠራ ስራዎችን መብት የማስከበር ስራን ለመተባበር እያንዳንዱ ደራሲ ፣ሃያዚ ፣ሙዚቀኛም ፣ሆነ የባለቤትነት መብትን ማስከበር የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ በአፍሪካን አርት ኤንድ ፓተንት ራይት በተሰኘው ድርጅት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ድርጅቱ ጥሪውን ለማለዳ ታይምስ ያስተላለፈ ሲሆን ፤ንበረቶቻቸው የተዘረፉባቸውን ሰዎች በሙሉ በድርጅቱ ጠበቆች አማካይነት ወዲያውኑ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል ይገልጻል ።     በቅርቡም በኮሚዲያን ፍልፍሉ ላይ ተፈጽሞብኛል ብሎ በቪድዮ ማስረጃ በዘሃበሻ ጋዜጣ አዘጋጅ ሄኖክ አለማየሁ በኩል የተለቀቀውን የምስል ቅንብር እና የጥያቄና መልስ  በመመልከት ይህንን የመብት ጥሰት ለማስቆም ኮሜዲያኑን ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን በሚቀጥለው አምስት ቀናት ውስጥ በቺካጎ ውስጥ ለሚያደርገው የመድረክ ዝግጅት ፕሮግራም ላይ ፍልፍሉን ለማነጋገር መዘጋጀቱን እና እንደ አንድ አባልነት እንዲመዘግበው ጥሪ ሊያቀርብለት እንደሚችልም ገልጾአል። በሌላም በኩል የፍልፍሉን የስራ መብት ጥሰት ያደረገውን ግለሰብ አጣርቶ ያወቀው ሲሆን በአትላንታ ከተማ እንደሚኖር እና ከኢትዮጵያ ጀምሮ እስከ አሜሪካ  በዲጄነት እንደሚሰራ ጭምር አክሎ ገልጾአል ሆኖም ግን ስለ ግለሰቡ ማንነት ከፍልፍሉ ውሳኔ በሁዋላ ወደ ፍርድ ቤት በሚያመራበት ወቅት ሊገልጽ እንደሚችል አክሎአል ።  ይህንን ጉዳይ ከፍልፍሉ ከተቀበኩ ክሱን እስከመጨረሻው ድረስ እገፋዋለሁ ያለው ይኸው ድርጅት የመብት ጥሰትን ለማስቆም አንደኛ አላማችን ስራችንን በተግባር መስራት ነው ብሎአል ። የዚህ ድርጅትን የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ቁጥርንም አያይዞ እንዲገለጽለት አመክሮ ጠቁሞአል.8467233  ኢልኖይ ሲሆን ለምዝገባው በቅርቡ በማለዳ ታይምስ እና እንዲሁም በኮንስትራክሽን ላይ ባለው ዌብሳይት ላይ እንደሚለቅ ተገልጾአል   ።