በሰሞኑ የኢትዮጵያን አመራሮች እና በህወሃት የቀድሞው አመራር አካል አቶ ስብሃት ነጋ ከፍተኛ ውጥረት ሲኖር ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጉዳይ ላይ መዘገባችን ይታወሳል ።በዛሬው እለት ከኢዮጵያ በደረሰን ዜና መሰረት የመገናኛ ብዙሃን ሚንስትር መስሪያ ቤት አመራር አካላት አንዱ ከሆኑት አንዱ አቶ በረከት ስምኦን የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይን) ለማገድ በቅተዋል ። ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅን አስመልክቶ እገዳው እንደተጣለባቸው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከስፍራው ገልጾአል ።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የመገናኛን አፈና ከጊዜ ወደዜ እየተባባሰ መምጣቱን አስመልክቶ ይህ በባለስልጣኖቻቸው የሚደረገው አፈና እና እገዳ በበለጠ በግልጽ አፈናውን የሚያሳይ መሆኑን ማእከላችን ይገልጻል ። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከስልጣናቸው ላይ ከተለዩ ጊዜ ጀምሮ የህወሃት አባሎች መላ ቅጡ የጠፋቸው ከመሆኑ በላይ እርስ በእርሳቸው ከመባላታቸውም አልፈው የስልጣን ሽኩቻቸውን በገሃድ አውጥተውታል ። በትላንትናው እለት የኢትዮጵያን ሪቪው ድህረ ገጽ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቦታ መተካታቸውን የዘገበ ሲሆን የአሜሪካ ባለስልጣናቶች በጠቃላይ ሚንስትሩ ቦታ ጣልቃ ገብተው ስልጣኑን እንዳስረከቧቸው መገለጹን ይታወሳል
በአሁን ሰአት የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያኖች ስለ ሃገራቸው ወቅታዊ ጉዳይ ወቀሳ ያቀረቡ ከመሆኑም በላይ አስቸኳይ የሆነ መግለጫ ከመንግስትም ሆነ ከመላው አለም አቀፍ ተቋማት መቀረብ እንዳለበት አሳውቀዋል ። በተለይም ባሳለፍነው ሳምንት የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩን ጨምሮ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ስብሰባቸው ዋነኛ አጀንዳ የሆነው በእነ አቦይ ስበሃት ነጋ ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረውን የህወሃት ድርጅትን አፍርሶ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርጉት ትልቅ ትግል መሆኑን ከተገለጸ በሁዋላ የህዝቡ እና የተቀዋሚ ፓርቲዎች ጠንካሬአቸውን አሳይተው ሃገራቸውን ከአስከፊ ስቃይ መታደግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል ።


