"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 2 May 2013

የአቡነ ጵጥሮስ ሃውልት መነሳት በበውቀቱ ስዩም አገላለጽ

ማለዳ መነሣት አልወድም፡፡ዛሬ ግን አቡነ ጴጥሮስ ከመታሰቢያቸው ዙፋን ሲወርዱ ለመታዘብ በማለዳው ካልጋየ ጨክኘ ወረድሁ፡፡ለአቡነ ጴጥሮስ ፍቅር ስል የማለዳ እንቅልፌን ብሰዋ አይቆጨኝም፡፡በቅርቡ በሚከፈተው ጦማሬ ላይ ስለ ጀግናው ጴጥሮስ በሰፊው የመጻፍ ሐሳብ አለኝ፡፡
በቦታው ስደርስ፣የጴጥሮስ ሀውልት በጣውላ ተገንዞ ቆሟል፡፡ድብርት ተጫጫነኝ፡፡ምናልባት አያቶቼ አቡኑ ሲረሸኑ በተመለከቱበት ሰአት የተሰማቸው ስሜት እንዲህ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የራስ ቁር የደፉ የቀን ሠራተኞች በአቡኑ ትክሻ ላይ እንደ ወፍ ሰፍረዋል፡፡ ወደ መርካቶ በሚሄዱ ተሳፋሪዎች የተሞሉ ሚኒባሶች አደባባዩን ታክከው ሽው ይላሉ፡፡ ተሳፋሪዎቹ፣ በመስታውት አሻ......ግረው የሚመለከቱት ትእይንት ብዙ የመሰጣቸው አይመሰልም፡፡በፋሲካ አስፈሪ የዶሮ ዋጋ ለተጠመደ አእምሮ ታሪክ ምኑ ነው??
ከተመልካቹ በላይ የፖሊሱ ቁጥር የሚበልጥ መሰለኝ፡፡አንድ ፒካፕ መኪና ስትበር መጣችና ቁና ሙሉ ፌደራል ፖሊስ አራገፈች፡፡ሰብሰብ ብለን በቆምንበት አንዱ ፖሊስ ጠጋ አለና‹‹ እናንተን አይመለከታችሁም ከዚህ ሂዱ›› አለ፡፡ካጠገቤ የቆመ ጎበዝ ‹‹ማየት መብታችን ነው›› ብሎ መልሶ ጮከበት፡፡አሀ! የጴጥሮስ መንፈስ አልከሰመም ማለት ነው፡፡ፖሊሱ ምንም ሳይመልስ ከሬድዮ መገናኛው ጋር እየተመካከረ ካካባቢው ራቀ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጋዜጠኛ ጓደኞቼ ካሜራቸውን ታጥቀው ደረሱና ተቀላቀሉኝ፡፡ ሀውልቱን ማስቀረት ስላልቻሉ ምስሉን ቀርጸው ለማስቀረት ተሯሯጡ፡፡
ድንገት ቀና ብየ ሳይ ከሀውልቱ ፊትለፊት ጅማ በር የሚባል ፣ጣልያን የሠራው አሮጌ ሕንጻ ይታየኛል፡፡ባቡሩ የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ ደቅድቆ ሲያልፍ፣ጣልያን ሠራሹን ግንብ ንክች አያደርገውም፡፡ጉደኛ ባቡር!!!
በጣውላ የተገነዘውን የአቡኑን ሀውልት ለመሸከም አንድ አዳፋ ረጅም ተጎታች መኪና ብቅ አለ፡፡ዳይኖሰር የመሰለ ክሬን ሀውልቱን ነቅሎ ሲያንጠለጥለው፣ሀውልቱ የነበረበት ቦታ ጥርስ የወለቀበት አፍ መሠለ፡፡ቀሪውን የማየት ፍላጎት ስላልነበረኝ ከጓደኛየ ጋር ወደ ፒያሳ አቀናሁ፡፡ብዙ ነገር እዬተለወጠ መሆኑን አየሁ፡፡የጥንቱ መሀሙድ መዚቃ ቤት ወደ ቡቲክ መቀየሩን አስተዋልሁ፡፡የጥንቱ አያሌው ሙዚቃ ቤት ፍራፍሬ መሸጫ ሱቅ ሆኗል፡፡ከጥቂት ወራት በፊት ብርቱካኔ የሚለው ሙዚቃ ይንቆረቆርበት የነበረው ቦታ ፣አሁን ብርቱካን በኪሎ ይሸጥበታል፡፡
አዲስአበባ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያለጥርጥር፣ባቡር ይኖራታል፡፡ቀለበት መንገዶች ይኖሯታል፡፡አሪፍ ህንጻዎች ይኖሯታል፡፡ነገር ግን፣ ትናንት የሚባለው ነገር አይኖራትም፡፡ A city without past ላዲስ አበባ የተገባ ቅጽል ነው፡፡
ወደ ሰፈሬ የሚሄድ ታክሲ ስፈናጠጥ፣ የሚከተሉት የጸጋየ ገብረመድህን ግጥሞች ሽው አሉብኝ፡፡
….መጭው ደመና ጥቁረቱ፣
ጮቁ ፣ማጡ፣የክረምቱ፣አቤት ዝቅጠቱ ማስፈራቱ
የኛስ ትውልድ አከተመ፣አገራችንን አምክነን
የነገስ ዘር ምን ይበለን፣ስንተወው ሲኦል አውርሰን

የእነ አንዱዓለም አራጌ ይግባኝና የዛሬው የፍርድ ቤት ብይን

ኢትዮጵያ

 

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤ በእነ አንዱዓለም አራጌ መዝገብና በሌሎች መዝገቦች ፤ በአሸባሪነት ተከሠው ይግባኝ የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአመራር አባላትና የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጉዳይ መርምሮ፣ ከአንደኛው በስተቀር የሁሉንም የእሥራት ብይን እንዲጸና አድርጓል።
የክንፈ ሚካኤል በየነ እሥራት ፤ ከ 25 ዓመት ወደ 16 ዓመት ዝቅ እንዲል ወስኗል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተወነጀሉት እና ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ እስር ላይ ያሉትን፤ አምደኛ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዉ አንዱአለም አራጌ፤ ያቀረቡትን ይግባኝ ዉድቅ አደረገ።
«ብይኑ አሁንም ትክክል ነዉ፤ ምንም አይነት ቅነሳ አይኖርም ሲሉ» የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ደጀኔ መላኩ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዲፕሎማቶች በዘመድ እና በጓደኛ በተሞላዉ ብይን ላይ ከዉሳኔዉ በኋላ « እዉነት አንድ ቀን ይወጣል» ሲል በስሜት መናገሩ ተገልጾአል።
Anwalt Abebe Guta im Prozess Journalist Eskinder Nega und Oppositionellen
Andualem Arage 020513.
Foto: Yohannes G/Egziabher DW Korrespondent 2013 ጠበቃ አበበ ጉታ
እስክንድር ነጋ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዉቅ የምንፈልገዉ እዉነት እራሱ በግዜዉ ይወጣል፤ የግዜ ጉዳይ ብቻ ነዉ» ብሎአል። አንዱአም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ተቃዋሚ ቡድን ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለዉ እስክንድር የ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አንዱዓለም ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር እጎ እ 2012 ዓ,ም ዓለም አቀፉ የደራስያን ድርጅት ፔን በዓለምአቀፍ ደረጃ በሥራቸው ምክንያት ለታሠሩ ወይም አደጋ ላይ ለወደቁ ደራስያንና ጋዜጠኞች የሚበረከተዉን የመፃፍ ነፃነት ሽልማት ማግኘቱ ይታወቃል። ዝርዝሩን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ወኪላችን ተከታትሎታል።
ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
ተክሌ የኋላ

Saturday, 20 April 2013

Police stopped meeting in Tasta bydelshus ሰበር ዜና፣ በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ውርደት ተከናንባ ተመልሳለች]

አማርኛውን ሪፖርት እና ኖርዌ ስታቫንገር ያለ ጋዜጣ ያወጣውን  ወደ እንግሊዘኛ በመቀያር እንድታዩት አያይዠዋለው።
ከአባይ በፊት የህዝብ ስቃይ ፤እስር ፤ስደት፧ መፈናቀል ፡ይቁም

አምባሳደሯ በሁለት ወያኔዎች ታጅባ ስለ ፓስፖርትና፣ ስለ አባይ ግድብ ቦንድ መናገር ከመጀመሯ የኖርዌይ ኢትዮጵያውያን “የለም የለም ኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ስለታሰሩ፣ በዘራቸው ምክንያት በሀገራቸው እየተፈናቀሉ ስላሉት ወገኖቻችን በቅድሚያ ጥያቄ አለን” በማለት አምባሳደሯን ሰንገው ይይዟታል።
ኢትዮጵያውያን ከኖርዌ ስብሰባ ያባረሯት የወያኔ አምባሳደር "መብራት በየነ አባይ"።

ስብሰባው የወያኔዋ ተወካይ ባሰበችው መንገድ መሄድ አልቻለም። ተረበሸ። ግርግሩ በርትቶ በመጨረሻም አምባሳደሯ እና አጃቢዎቿ በፖሊሶች ታጅበው በመጡበት እግራቸው ተመልሰዋል።

 
.The police came out with three cars and six policemen and stopped a meeting of Tasta bydelshus where the atmosphere was becoming so very irritably among the more than 300 attendees.
OFF: toril RisholmPublished: April 20, 2013 7:51 p.m. Updated: April 20, 2013 8:13 p.m.

The 300 attendees were Ethiopian asylum seekers or people with Ethiopian background. The police feared that it would get completely out of control when people in the audience went to the hard verbal confrontation against two representatives from the Ethiopian Embassy in Stockholm who had called for and chaired the meeting.The police gave the first message that all protesters to leave the meeting while the two embassy people and their potential supporters can be seated. This denied the attendees protesters, and several feared it would come to an open confrontation between police and people in the audience. Then, specific efforts manager Øyvind Sveinsvoll of Rogaland police to stop the meeting and clear the room.It was a wise decision, said several of those present protesters. They did not want the two embassy people should be left as "victors" while they were evicted.- Our goal was to stop the meeting.

Wednesday, 17 April 2013

“ማሪያም ነኝ” ባዩዋ ተፈረደባት


በአሸናፊ ደምሴ
የፌዴራሉ አቃቤ ህግ የማይገባትን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች በመንቀሳቀስ ሰዎችን በማታለል “እኔ ማርያም ነኝ፤ እንደኢየሱስም በጅራፍ ተገርፌያለሁ፤ ከሞትም ተነስቻለሁ፤የወለድኳቸውንም ልጆች ያገኘሁት በመንፈስ ነው”
ስትልና የዓለም ፍፃሜ ደርሷል በሚል የሰዎችን የግል ሀብት ለራሷ ስታደርግ ደርሼባታለሁ ሲል ክስ የመሰርተባት የ34 ዓመቷ ትዕግስት ብርሃኑ ወ/ጊዮርጊስ፤ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርባ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ በ2 ዓመት
ከ4 ወራት ፅኑ እስራትና በአንድ ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ባሳለፍነው ሳምንት ወሰነ።
እንደአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ከሆነ ግለሰቧ በአራት የተለያዩ ክሶች የተወነጀለች ሲሆን፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
“ለሰው ህይወት ማለፍ ሳቢያ ነች” ሲል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ያልተሟላ ነው ሲል ውድቅ ሲያደርገው በተቀሩት
ሶስት ክሶች ግን ጥፋተኛ ነች ብሎ እንድትከላከል ብይን ሰጥቶ ነበር።
ተከሳሿ ጥፋተኛ የተባለችበት አንደኛ ክስ በየካቲትና በመጋቢት ወራት ውስጥ 1999 ዓ.ም የማይገባትን ጥቅም

ለማግኘት አስባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 21 ልዩ ቦታው ኪዳነምህረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ300 በላይ ሰዎችን በመሰብሰብ “እኔ ማርያም ነኝ፤ እንደኢየሱስም በጅራፍ ተገርፌ፤ ከሞትም ተነስቼያለሁ” የሚል የሀሰት ወሬ በመንዛትና የዓለም ፍፃሜ ደርሷል ንብረት አያስፈልግም በሚል ያላችሁን ንብረት አምጡ ስትል ከተለያዩ የግል ተበዳዮች ጥሬ ገንዘብና ወርቅ የተቀበለች ሲሆን፤ በአጠቃላይም 40ሺ ብር ለግል ጥቅሟ አውላለች ሲል በክስ መዝገቡ ያስረዳል።
እንደአቃቤ ህግ ቀጣይ ክስ ደግሞ ተከሳሿ በሰኔ 1 ቀን 1999 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 16 ልዩ ቦታው ላምበረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 50 የሚደርሱ ሰዎችን በመያዝ ወደደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በመጓዝ ወንጭ ገዳም ተብሎ ወደሚጠራው መንፈሳዊ ቦታ በመውሰድ በፆምና ፀሎት ሰበብ አብረዋት የነበሩት ሰዎች ለአምስት ቀናት ምግብ እንዳይበሉ በማድረግ እንዲዳከሙና ለከፋ ጉዳት እንዲዳረጉ አድርጋለች ሲል በክሱ ያትታል።
በሌላም በኩል ግለሰቧ በጥር 24 ቀን 2003 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ ቦታው ተክለሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ ወደ 20 የሚጠጉ ህፃናት ልጆችና ሴት ተከታዮቿን በመያዝ፣ “እኔ ማርያም ነኝ፤ ልጆቼን የወለድኳቸውም በመንፈስ ነው እንጂ ከወንድ ጋር ተኝቼ አይደለም” በማለትና ተከታዮቿም እርሷ ማርያም ነች።
ሞታም ተነስታለች እንዲሁም 40 ቀን ያለምግብ ትፆማለች በማለት ሀሰተኛ ወሬዎችን እንዲነዙ በማድረግ ስታስተምር እንደነበር ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ ደርሶኛል ያለው ዐቃቤ ሕግ፤ በዚህም ምክንያት በቤተ-ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ምዕመናን “ ሀሰት ነገር አትናገሪ” ሲሉ በመቃወማቸው ወደሁከት ውስጥ እንዲገቡ ያደረገች በመሆኑ በፈፀመችው የሀሰት ወሬዎችን በማውራትና ህዝብን በማነሳሳት ወንጀል ተከሳለች ይላል።
ጉዳዩን ሲመረምረው የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ወንጀል ችሎትም የዐቃቤ ሕግን ክስ ተከሳሿ ማስተባበል ባለመቻሏ ጥፋተኛ ሆና አግኝቻታለሁ ሲል፤ መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በ2 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስራትና በ1000 ብር እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል።¾
ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ