"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 19 December 2013

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ

አያሌው-ጎበዜእርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ     ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን
                                                                                                                  የሚያስታውሱት ነው   ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ እንዲህ ነው እንጂ ተላላኪ ብሎ ትምህርት ሚኒሰቴር ሲያደርገው ለእርስዎ ግን ቅንጣት ታህል አለመስጠቱ ሱዳኖች እንኴን እንዲታዘቡት አድርጔል፡፡
እርስዎም ደመቀ ምክትል ጠ/ሚኒስቴር ሲሆን ቅናት ቢጤ አድርዎቦት ከሳምንታት በፊት 40 ካ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የሀገሮትን መሬት ለሱዳን ማስረከብዎን ሰምቼ ድሮስ የጎበዤ ልጅ ከማን ያንሳል ብዬ ኮራሁ፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን መሬታችን ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ የእርስዎ የቅርብ ዘመዶች ቤታቸው የተሸጠው መሬት ላይ በመገኘቱ ሱዳን ለዘላለም ትኑር አባይ የሱዳን ነው እያሉ መዘመራቸውን ሱዳን የሚገኝ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል፡፡
እናማ ይሄውልዎ ተሰናባች አያሌው የእርስዎ ክልል ግዞት የሆነው የአማራ ህዝብ ብዙ እየሰማ እና እየተሰማው ሲኖር አንድም ቀን ተናግርዎት አያውቅም ለምን መሰለዎት ምን አልባት ነጋዴው ክልሉን ለሱዳን ሸጠው ከመለስ ዜናዊ አገዛዝ ነፃ ያወጡናል ብሎ ስላሰበ ይሆናል፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ ለእርስዎ ያላቸውን ፍቅር የተረዳሁት ጉራፈርዳ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጉራፈርዳ በቃን አያሌው ጎበዜ ናፈቀን ብለው ቢለመኑ እምቢኝ ብለው እርስዎ ክልል ሲመጡ ነው፡፡
እናም በመጨረሻም እንኩ ምስጋናዬን ተቀበሉ
1.   ሰፊውን መሬታችንን ሽጠው ጠጋ ጠጋ ብለን በመኖር ማህበራዊ ህይወታችን እንዲጠናከር በማድረግዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
2.   እንደ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ሳይሞቱ በመልቀቅዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
3.   በ1998 በኮምቦልቻ፣ በ1999 በደሴ፣ በ2000፣ በ2003 የጎንደር እና የጎጃም ህዝብን በወያኔ ወታደሮች በጥይት አስገድለው ከዘንድሮው የኑሮ ውድነት እንዲያመልጡ ስላደረጉ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
አክባሪዎ ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.

Saturday, 12 October 2013

“አውጣኝ ያለም ወጣ አብላኝ ያለም በላ፣ምስኪኑ ጥንቸል ግን ተኝቶ ተበላ”

 
(ቴዲ - ዘአትላንታ)
ዕውቀት ጥራዝ ነጠቅ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ከጥራዝ ነጠቅ ሰው ጋር መከራከርም አይቻልም፣ ለሱ እሱ ልክ ነው፣ ምክንያት አምጥቶ፣ ብልት አውጥቶ አይከራከርም - የሚያውቀው ትችት ብቻ ነው። ጥራዝ ነጠቅነት ከስሜታዊነት ጋርም ይያያዛል። እንዲህ አይነት ሰዎች ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታ አሉ - ይኖራሉም።

ሰሞኑን ከዚሁ ዓይነት ጥራዝ ነጠቅነት የመጣው ሃሳብ “ለኢትዮጵያ ለምን ይጸለያል - ናይጄሪያም እኮ አምላክ አለው” የሚል ነው። እንዲህ ዓይነት አስተሳስብ ጥራዝ ነጠቅነት ይባላል - አንዲት ነገር ፣ በአንዲት ጎን እና በአንድ መነጽር ብቻ አይቶ የሚሰጥ ጭፍን ድምዳሜ ነው።
...
ስለኢትዮጵያ ማሸነፍ መጸለይ ፣ ከናይጄሪያ መጸለይ አለመጸለይ ጋር ምን ያገናኘዋል? አንድ ሰው ሎተሪ ቆርጦ አንደኛው ዕጣ እንዲደርሰኝ እርዳኝ ብሎ ቢጸልይ ፣ አይይ .. ብዙ ሰው ቆርጧልና ለሌላው አይድረስ ለኔ ብቻ ይድረስ ማለት ስለሆነ አትጸልይ ሊባል ነው? አንድ ሥራ ቦታ የተወዳደረ ሰው "እግዜር ይህን ሥራ እንዳገኝ ርዳኝ" ብሎ ቢጸልይ .. አይይ ብዙ ሰው ተወዳድሯልና ለኔ ብቻ ብለህ አትጸልይ! .. ሊባል ነው? ሁሉም የሚጸልየው እኮ ለራሱ ነው።

እኛ እንደኢትዮጵያዊ፣ ለኢትዮጵያ እንጸልያለን፣ ናይጄሪያኖችም ለራሳቸው ይጸልዩ .. እግዜር ደግሞ የፈቀደውን ይስማ። አንድ ታሪክ ጣል ላድርግ … አንድ አንበሳ ተራበና .. እባክህ አብላኝ አብላኝ እያለ ወደ ፈጣሪው ጸለየ ….. ጸሎቱን እንደጨረሰ ቀና ሲል አንዲት ሚዳቆ አየ። “አይ ፈጣሪ! ጸሎት እንዲህ ፈጥነህ የምትሰማ ተመስገን .. አለና ሊያዛት ሲሮጥ .. እሷም በበኩሏ ወደ ፈጣሪዋ “አውጣኝ፣ አውጣኝ፣ አድነኝ” እያለች በመጸለይ መሮጥ ጀመረች። እግዜር ማንን ይስማ? (ናይጄሪያም ይጸልያል፣ ኢትዮጵያም ትጸልያለች .. እግዜር ማንን ይስማ? ስለዚህ አንጸልይ ለሚሉት ነው ..) .. ታሪኩ ይቀጥላል .
…. አንበሳው ሲከተል፣ ሚዳቆም ስትሮጥ ቆዩ። መጨረሻ ላይ ሚዳቆ አመለጠች፣ አንበሳም ደክሞት እንደተራበ አረፍ ለማለት ሲሞክር ሳይጸልይ ተኝቶ የሚያንኮራፋ ጥንቸል አገኘ። “ተመስገን - ሚዳቆ ብትነሳኝ ጥንቸል ሰጠኸኝ” በማለት ምሳ አደረገው።
ያን ጊዜ እንዲህ ተባለና ተገጠመ
“አውጣኝ ያለም ወጣ አብላኝ ያለም በላ፣
ምስኪኑ ጥንቸል ግን ተኝቶ ተበላ”

እናም ጸሎት ምን ይሰራል፣ ተኙ የሚሉ ጥራዝ ነጠቆች “የ7 ቢሊዮን ሰው ጸሎት በአንድ ሰከንድ መስማት የሚችልን እግዜር ፣ ግራ አታጋቡት ሊሉ ይሞክራሉ። የሱን ጥበብ ማን ያውቃል? ናይጄሪያና ኢትይጵያ ቢሸናነፉ እንኳን ሌሎች አገሮች በተለያየ ምክንያት “ዲስኳሊፋይ” ተደርገው ሁለቱም ሊያልፉ ይችላሉ እኮ! .. የኛ ድርሻ መጸለይ ነው፣ ጸሎታችንን መስማት አለመስማት የእግዜር ነው። ከጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ይሰውረን!!

Thursday, 3 October 2013

A MIRACLE IN SYRIA


In December 2004 a Saudi Arabian man, a Moslem, appeared before several news agencies to relate the following incredible event he experienced and which changed his life (this story appeared on TV, the Internet, radio, and was circulated in newspapers, magazines, and pamphlets throughout Saudi Arbia, Syria, Palestine, and evidently in all neighboring countries.Some years ago, this man married a Moslem woman who was very rich, but sterile. As the years passed, and despite all their efforts and significant medical expenses with many doctors, they remained childless. The man's parents suggested to him that he marry a second woman, while upholding his initial marriage (as the local laws permits up to four concurrent marriages).

Saturday, 28 September 2013

የሞት “ድግስ”



መስከረም 4 ቀን 1996ዓ.ም ለኢትኦጵ ጋዜጠኛ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። “ በነገው እለት ከቀኑ 6ሰአት መስቀል አደባባይ በሚገኘው የትግራይ ልማት ዋና ቢሮ 4ኛፎቅ እንድትገኝ” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ነበር የደረሰው። ከዛ በፊት ለስድስት ወር የአየር መንገድ የደህንነት ሃላፊ ሃይሌ ጋዜጠኛውን ሲያስጨንቀው፣ የተለያዩ የማግባቢያ ወይም መደለያ ሃሳቦችን ሲያቀርብለት ቆይቷል።                                                                                                        መስከረም 2 ቀን ደግሞ በቀበሌ 06/07 መ/ር ቢሮ እንዲገኝ የሚገልፅ መጥሪያ ቢደርሰውም በአጋጣሚ ጋዜጠኛው ስላልተመቸው አልሄደም። በማግስቱ የቀበሌውን ሊ/መ አቶ ቢሻው አበጋዝን ያገኘውና     « ትላንት ፈልጋችሁኝ ነበር፤ ለምን ነበር?» ሲል ይጠይቀዋል፤ ቢሻውም « እኛ አይደለንም የፈለግንህ፤ ከደህንነት ቢሮ የመጡ ሰዎች ናቸው የፈለጉህ፤ ባለመምጣትህ ተናደው ነው የሄዱት፤ ለምን እንደፈለጉህ አልነገሩንም፤» በማለት መለሰ። …ከዛ በኋላ ነው - የመስከረም 4 ጥሪ የደረሰው፤ በማግስቱ በተባለው ቢሮ ተገኘ። ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ የማህበሩ ዳይሬክተር « ከሚፈልጉህ የበላይ አካላት ጋር አገናኝሃለሁ» በማለት ለጋዜጠኛው ተናግሮ በሚያሽከረክራት ኒሳን መኪና ተያይዘው ቦሌ በሚገኘው የደህንነት ቢሮ አመሩ።..               ከአንድ ግዙፍና አስፈሪ ገፅታ ካለው ሰው ጋር ጋዜጠኛውን አገኛኝቶት ወጥቶ ሄደ። ..« እሺ ኢየሩሳሌም አርአያ..» አለ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ፤ አስከተለና፥ « ወ/ስላሴ እባላለሁ፤ ....ከእኛ ባልደረባ ጋር ስትገኛኝ ነበር፤ መንግስት ብዙ አማራጮችን አቅርቦልህ..አንተ ግን አሻፈረኝ ብለሃል። ለመሆኑ የምታወጣቸው መረጃዎች ተፅፈው ነው የሚሰጡህ?...ለምንድነው መረጃ የሚሰጡህን የሕወሐት ሰዎች የማትነግረን?..የምናስራቸው፣ የምንጠይቃቸው መስሎህ ነው?...» ሲል ሹሙ ሲናገር፣ ጋዜጠኛው ግን የቀረቡትን መደራደሪያዎች እንደማይቀበል ተናገረ። ለሁለት ሰአት ተኩል ከደህንነት ሃላፊው ጋር ውዝግብ የተቀላቀለበት ቃላት ተለዋወጡ። በተለይ የደህንነት ሹሙ « ..የትግራይ ተወላጅ ያውም ቤተሰብህ አድዋ ሆነው..እንዴት ፀረ-ሕወሐት ትሆናለህ?..ከጠላቶቻችን አንዱ ከሆነው ኢትኦጵ ጋዜጣ ጋር እንዴት ትሰራለህ?..» እያለ ከመናገሩ በተጨማሪ « እንዳንተ የተለማመጥነውና የታገስነው የለም። ብንገድልህስ?..» ሲል በንቀት ሲጠይቅ፣ ጋዜጠኛውም « ምንም ጥያቄና መልስ አያስፈልገውም፤ አሁኑኑ ሽጉጥህን መዘህ ልታደርገው ትችላለህ። እኔ ብእር እንጂ የያዝኩት - ከጀርባዬ ያሰለፍኩት ሰራዊትና መሳሪያ የለም። ..ደግሞም ለስልጣን ያበቋችሁን 36ሺህ ታጋዮች ላይ ምን እንደፈፀማችሁ ስለማውቅ..» አላስጨረሰውም፤ ..« እሱ አይመለከትህም፤ ከማን ጋር ምን እያወራህ እንዳለህ እወቅ!?..ከዚህ በኋላ እንድታስብበት የ15 ቀን ጊዜ ብቻ ሰጥተንሃል። በነዚህ ቀናት አቋምህን አስተካክለህ፣ የተባልከውን ካልፈፀምክ ግን…እንገድልሃለን!! ማንም አያድንህም!! ጨርሻለሁ።» በማለት አምባረቀበትና አሰናበተው። ..ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ረቡዕ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 ሰአት ገደማ በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ ወ/ስላሴ ያሰማራቸው ሰባት የፌደራል ፖሊስ አባላት “አቦ ድልድይ” አቅራቢያ ጋዜጠኛውን ጥብቀው በያዙት ዱላ የቻሉትን ያክል ቀጥቅጠውና ከፍተኛ ጉዳት አድርሰው ወደ ድልድዩ ወረወሩት። ሶስት ጥርሱ ተሰበረ፣ ጭንቅላቱ 5 ቦታ ተፈነካከተ፤ ሁለቱ እጆቹ፣ ግራ እግሩ፣ ወገቡ፣..አጠቃላይ አካሉ ተጎዳ። ...እነ ወ/ስላሴ ከድርጊቱ በኋላ ለጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና 5 ጊዜ ስልክ ደውለው « የኢየሩሳሌምን ሬሳ ሂድና ከምኒሊክ ሆስፒታል ውሰድ..» ሲሉ ተሳለቁ።…ከጨካኞች፣ ገዳዮችና አምባገነኖች ..የሚጠብቅ ፈጣሪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባትን የጋዜጠኛውን ነፍስ በኪነ-ጥበቡ ታደጋት። እነሆ ከአስር አመት በኋላ የቀድሞ የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል እስር ቤት ሲወረወር፥ በእርሱ “ሞት የተደገሰላት” የጋዜጠኛው ነፍስ በህይወት ቆይታ ለማየት በቃች። ሁሉም የዘራውን ሊያጭድ ግድ ነው!! …ይህ ታሪክ የእኔ ነው። (በምስሉ የሚታየው ለስድስት ወር ያልጋ ቁራኛ የዳረገኝ የግድያ ሙከራ ከተፈፀመብኝ በኋላ፣ )


Monday, 19 August 2013

BEWKET SEYUM sele EYOB MEKONENE



                                                                      ከጥቂት አመታት በፊት ባንድ የበጎ አድራጎት ትርኢት ላይ ለመሳተፍ፣ከዘፋኞች ጋር ወደ ደሴ ተጉዠ ነበር፡፡የተሣፈርንበት አውቶብስ ጉንጫቸውን በጫት አሎሎ በወጠሩ ዘፋኖች ተሞልቷል፡፡ ዘፋኞቹ ሲሻቸው ይተራረባሉ፣ ሲሻቸው ይጮሃሉ፣ይጨፍራሉ፡፡የአውቶብሳችን ሽማግሌ ሹፌር ሳይቀር፣ አልፎ አልፎ መሪውን እየለቀቀ በማጨብጨብ በ‹‹ቅወጣ›› ከዘፋኞች እንዳማያንስ በማሳየት ላይ ነበር፡፡በጫቱም፣ በጭፈራውም የሌለበት ድምጻዊ ኢዮብ መኮንን ብቻ እንደሆነ ተመለከትሁ፡፡ በርጋታ ተቀምጦ፣ ባውቶብሱ መስኮት አሻግሮ፣ የሚሮጡ የግራር ዛፎችን ይመለከታል፡፡ልዩነቱ ግልጽ ነበር፡፡
ድሮ ድሮ፣ኢዮብ መኮንን አቤሴሎም የሚዘናፈል ረጅም ጸጉር ያለው ጎልማሳ ነበር፡፡ድንገት ጸጉሩን ተሸለተ፡ከጸጉሩ ጋር የጥንት ባህርይውን አራገፈ፡፡ጭምት መንፈሳዊና በመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር የነደደ ምእመን ሆነ፡፡
በተገናኘን ቁጥር፣ኢዮብ ስለ ስለ እምነት እንድንወያይ ይፈልጋል፡፡ብዙ ጊዜ እምነት የሚያጠብቅ ሰው አንዳች ችግር ይኖርበታል ብየ አስብ ነበር፡፡ኢዮብ ግን እጅግ መልካም ሊባል በሚችል ሕይወቱ ይሄንን አመለካከቴን ውድቅ አድርጎብኛል፡፡
የዛሬ ሳምንት ገደማ ኢዮብ ዘፈን በመሥራት ላይ ነበር፡፡እና ላንድ ዜማው ግጥም እንደሠራለት ጋበዘኝ፡፡ከዚህ በፊት የሞርኳቸው የዘፈን ግጥሞች ስለከሸፉብኝ ግብዣውን ለመቀበል አመነታሁ፡፡ግን ደሞ ወድያው፣ በኢዮብ ድምጽ ግጥሜን ተዘፍኖልኝ ለማየት ጓጉዋሁ፡፡ውሀ ልማት አካባቢ፣ ሌክስፕላዛ ሕንጻ ሥር መኪናው ውስጥ ቁጭ ብለን ዜማዎችን ማድመጥ ጀመርን፡፡ዘፈኑ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች አብዛኞቹ ወደ መዝሙር ያዘነብላሉ፡፡ ኢዮብ ዘፈኑን ለፈንጠዝያ ሳይሆን ለስነምግባር ግንባታ ሊጠቀምበት ፈልጓል፡፡አንድ በጣም ልብ የሚበላ የሶ...ማሌ ዘፈን አስደመጠኝ፡፡
‹‹ሶማሊኛ ትችላለህ እንዴ?>>
‹‹አዎ፣ትግርኛም አውቃለሁ!››
‹‹የት ተማርከው?>>
‹‹አስመራ፣የወታደር ልጅ መሆኔን አትርሳ››
ከዘፈን ውጭ ምን ታደርጋለህ?
‹‹ኦን ላይን፣ ጊታር እየተማርሁ ነው፡፡ቆይ ላሳይህ››…ላፕቶፑን ለኮሰና ጥቂት አስጎበኘኝ፡፡ከዛ ከመኪናው ስወርድ የመኪናው እጀታ ስለማይሠራ ወርዶ ከውጭ ከፈተልኝ፡፡ኢዮብ ብዙ ብሮችን መቆጠር የሚችል ልጅ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ይሁን እንጂ እንኳን መኪናውን የመኪናውን እጀታ ማስቀየር አልፈለገም፡፡ምናልባት፣ዓመት በአልን ጠብቆ ልብስ የሚቀይር ብዙ ሰው ባለበት አገር ውስጥ፣ መኪና መቀያየሩን እንደ ኃጢአት ቆጥሮት ይሆናል፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ ልኡል የተባለ ዘፋኛ ጓደኛየ የኢዮብን በድንገት መውደቅ ሲነግረኝ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ሄድኩ፡፡ዘፋኞችና አዘጋጆች መጠበቂያው ክፍል ላይ ተደርድረው ይተክዛሉ፡፡ዘሪቱ፣ዳግማዊ አሊ፣እቁባይ በርሄ፣አጃቸውን አገጫቸው ላይ ጭነው፣ተቀምጠዋል፡፡የኢዮብ ባለቤት ወድያ ወዲህ እየተንቆራጠጠች ታነባለች፡፡
ዛሬ ደግሞ ይሄው ሞቱን ሰማሁ፡፡ለካ፣ወደ ደሴ የሚሄደውም አውቶብስም ሆነ፣ሌክስ ፕላዛ ሕንጻ ስር፣ የቆመው ቪታራ መኪናው መዳረሻቸው አንድ ነው፡፡መቃብር!!
ኢዮብ!!! በጠፈሩ ውስጥ፣ ያለ ግብ ከሚዞሩ ኮረቶች፣ያለ ምክንያት ከሚበሩ ኮከቦች በቀር ምንም የለም ብየ እንደማምን ታውቃለህ፡፡ይሁን እንጂ ለዛሬ እንኳ፣ የኔ እምነት ከሽፎ ያንተ እምነት እውነት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡በምድር ለገጠመህ መራራ እጣ ሰማያዊ ካሳ(ጉማ) እንድታገኝ እመኛለ