"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 25 February 2014

ከበዕውቀቱ መጣጥፎች ውስጥ ሁለቱን ጀባ ልበላችሁ\\

ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…

አጤ ካሌብ የተባለ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባንድ ወቅት በቅድመ-እስልምና የመን የሚኖሩ ክርስቲያኖች ባንድ ያይሁድ ገዥ መዳፍ ስር መማቀቃቸው አስቆጥቶት ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ተበቅሎላቸዋል። የዛሬውን አያድርገውና ፣ እንኳን ለቤት ለጎረቤት ጥቃት የሚቆረቆር ንጉሥ ማፍራት ችለን ነበር፤ አንኳን ለቤት ለጎረቤት እርዳታ የሚበቃ ጉልበት ማካበት ችለን ነበር ። ዛሬ ግን ጊዜ ከካሌብነት ወደ ከልብነት ደረጃ አውርዶናል። (“ከልብ” በግዕዝ ውሻ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዘይቤ አንድ ሰው ያለ ካሳ ያለ ጉማ ደሙ ፈሶ ሲቀር ደመ ከልብ ሆነ ይባላል)።
አቅመ-ቢስ ሕዝቦች በጉልቤ ሕዝቦች መዳፍ ስር ገብተው መከራ ማየታቸው በታሪክ ብርቅ አይደለም። እኔን የሚገርመኝ በፋንታችን መከራ ማየታችን አይደለም ፤ እኔን የሚገርመኝ ከዚህ ሁሉ መከራ በሁዋላ ከመከራ የሚታደገን የኑሮ መላ አለማፍለቃችን ነው። ከመከራ መደራረብ በሁዋላ ያፈለቅነው የስልጣኔ ፍሬ የሙሾ ግጥም ብቻ መሆኑ ያስደንቃል።
አይሁድ በሁለተኛው ያለም ጦርነት ግፍ ከደረሰባችው በሁዋላ አንሰራርትው በርትተዋል፤ እንደ ኒቼ “ጨርሶ የማያጠፋኝ ሁሉ ያበረታኛል” ብለዋል። ዛሬ በነዳጅ መስክ ላይ የበቀሉ አረሞችን (አረቦችን) ያርበደብዳሉ ። ጀርመኖች በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማክተሚያ ላይ በጠላቶቻቸው ከስክስ ጫማ ደቀዋል። ግን በአጭር ጊዜ አንሰራርትው ሃይላችውን እንደ ንስር አድሰዋል፤ እኛስ ይሄን ማድረግ ያቅተናል? አያቅተንም። ያገራችን አስተዳዳሪዎች ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ፣ የሃይማኖት መሪዎች ፣ ሀያል መንግስቶች ከመከራ ዶፍ የማይታደጉን ነዳላ ጃንጥላ መሆናችውን አይተናል። የራሳችን አዳኞች ራሳችን መሆናችንን አንርሳ ፤ ጎበዝ የዳይኖሰርን ፈለግ ከመከተላችን በፊት ትንሽ መላ እንምታ::

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው” ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!

musevini


የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ  ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
uganda 1ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡
ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡
ናይጄሪያም ከአንድ ወር በፊት ተመሳሳይ ሕግ ያወጣች ሲሆን የዑጋንዳው ሕግ በረቂቅነት ከወጣ የዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ምዕራባውያን ከፍተኛ ተጽዕኖ በማድረግ ሕጉ ተግባራዊ እንዳይሆን፤ ከሆነም በአብዛኛው የህጉ ክፍል እንዲሸራረፍ በርካታ ሙከራዎችን፣ ማስፈራሪያዎችንና ውስወሳዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡no homosexual
በአሜሪካ የፕሬዚዳንት ኦባማ አፈቀላጤ የህጉን መጽደቅ “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ዑጋንዳ ባስቸኳይ ሕጉን እንድትሰርዝ የጠየቁ ሲሆን አሜሪካ ከዑጋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምታጤነውም ተናግረዋል፡፡ አውሮጳውያንም በበኩላቸው የሕጉን መጽደቅ የኮነኑ ሲሆን የተወሰኑ የአውሮጳ አገራት ለዑጋንዳ የሚሰጡትን ዕርዳታ እንደሚያቋርጡ ዝተዋል፡፡ ሌሎች አገራት ግን እንዲህ ዓይነቱ የዕርዳታ ማቋረጥ ውሳኔ ዑጋንዳውያንን የሚጎዳ በመሆኑ እርምጃው መወሰድ የለበትም ይላሉ፡፡
የዑጋንዳ ሕግ አውጪዎች ያረቀቁትን ሕግ በፈረሙበት ጊዜ ሙሴቪኒ እንዳሉት ምዕራባውያን በዑጋንዳ ጉዳይ በግልጽ ጣልቃ እየገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ “አፍሪካውያን በሌሎች ላይ የራሳችንን አመለካከት አንጭንም” ያሉት ሙሴቪኒ ምዕራባውያን እስካሁን ያደረጉት ጣልቃገብነት ትክክለኛ እንዳልነበረ እና ይህም ደግሞ “ማኅበራዊ ኢምፔሪያዝም” ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡ ግትርና ግዴለሽ ምዕራባዊ ድርጅቶች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፋፋት እየጣሩ መሆናቸውንና ለዚህም ሰዶማዊነት ተግባር የኡጋንዳን ህጻናት እየደለሉ ወደ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሚያስገቧቸው ከሰዋል፡፡ በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሰዶማውያን ደሃ ዑጋንዳውያንን ዒላማቸው በማድረግ በገንዘብ በመደለል ለግብረሰዶማዊነት እንደሚጋብዟቸውና ቀጥሎም ለግብረሰዶማዊ አዳሪነት እንደሚዳርጓቸው ሙሴቪኒ ተናግረዋል፡፡
የዑጋንዳን ውሳኔ አስመልክቶ የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሙያ የሆኑ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት “ኢህአዴግም ከየምዕራቡ ለሚለቃቅመው ዕርዳታ ብሎ የአገርን ባህልና ማኅበራዊ እሴት ከሚያጠፋ ይልቅ ተመሳሳይ ተግባር ሊወስድ ይገባዋል፤ የተቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት በጸረ አሸባሪ ህግ ስቃዩን ከሚያሳይ የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በማውጣት ይህንን በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ወረርሽኝ መላ ሊለው ይገባል” ብለዋል፡፡

Thursday, 6 February 2014

በአዲስ አበባ የ“ዳይመንድ ድራማ” ተጧጡፏል!


ኔትዎርክ ያቆማል የተባለው የ“ማሾ ዳይመንድ” 4ሚ. ብር ተሸጧል
የዳይመንዱን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡት “የውጭ ኤክስፐርቶች” ናቸው
ባለሃብቶች የሚጭበረበሩት በሚያውቋቸውና  በቅርብ ባልንጀሮቻቸው ነው
በአዲስ አበባ የሚኖሩት አቶ አየለ ጣፋ እና አቶ ጎሽሜ ሁንያንተ የልብ ጓደኛሞች ሲሆኑ ሁለቱም በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው፡፡ አቶ ጎሽሜ ለበርካታ አመታት በጣሊያን ኖረው ነው ወደ አገራቸው የተመለሱት፡፡ አቶ አየለ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ከውጭ እያስመጡ የሚሸጡ ሲሆን ልጆቻቸውም በስራቸው ያግዟቸዋል፡፡
ከጥቂት አመታት በፊት አቶ አየለ ሰሚት አካባቢ መኖሪያ ቤት ሲገዙ፣ የልብ ጓደኛቸው አቶ ጐሽሜ አለኝታነታቸውን የገለፁት የ300ሺ ብር ስጦታ በማበርከት ነበር፡፡ ትንሽ ቆይተው ታዲያ ውለታ ጠየቁ - አቶ ጐሽሜ፡፡ በእርግጥ ውለታው ከባድ አልነበረም፡፡ ዘቢደር የተባለች ዘመዳቸው አቶ አየለ ቤት፣ በቤት ሠራተኛነት እንድትቀጠር ነው የፈለጉት፡፡
አቶ አየለም፤ “አንተ ብለህ ነው?” በማለት ዘቢደርን ለሌሎች ሠራተኞቻቸው ከሚከፍሉት ደሞዝ በእጥፍ ቀጠሩላቸው፡፡ 300ሺ ብር በስጦታ ላበረከተ ለጋስ ጓደኛ ይህቺ ምን አላት! አቶ አየለ አንድ ሴራ እየተጐነጐነላቸው መሆኑን ግን አላውቁም፡፡
የአቶ ጐሽሜ ዘመድ ናት የተባለችው ዘቢደር፣በእንክብካቤ አንድም ነገር ሳይጐድልባት አቶ አየለ ቤት ለአንድ ዓመት ቆየች፡፡ ዋና ተልዕኮዋ የሚጀምረውም ከዚህ በኋላ ነው፡፡ አጐቴ የምትላቸው አቶ አጐናፍር (ዋና ስማቸው መኮንን ሃብታሙ) ከገጠር “ሊጠይቋት” ይመጣሉ፡፡ አመጣጣቸው ግን ለሌላ ነበር፡፡ 

Thursday, 19 December 2013

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ

አያሌው-ጎበዜእርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ     ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን
                                                                                                                  የሚያስታውሱት ነው   ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ እንዲህ ነው እንጂ ተላላኪ ብሎ ትምህርት ሚኒሰቴር ሲያደርገው ለእርስዎ ግን ቅንጣት ታህል አለመስጠቱ ሱዳኖች እንኴን እንዲታዘቡት አድርጔል፡፡
እርስዎም ደመቀ ምክትል ጠ/ሚኒስቴር ሲሆን ቅናት ቢጤ አድርዎቦት ከሳምንታት በፊት 40 ካ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የሀገሮትን መሬት ለሱዳን ማስረከብዎን ሰምቼ ድሮስ የጎበዤ ልጅ ከማን ያንሳል ብዬ ኮራሁ፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን መሬታችን ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ የእርስዎ የቅርብ ዘመዶች ቤታቸው የተሸጠው መሬት ላይ በመገኘቱ ሱዳን ለዘላለም ትኑር አባይ የሱዳን ነው እያሉ መዘመራቸውን ሱዳን የሚገኝ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል፡፡
እናማ ይሄውልዎ ተሰናባች አያሌው የእርስዎ ክልል ግዞት የሆነው የአማራ ህዝብ ብዙ እየሰማ እና እየተሰማው ሲኖር አንድም ቀን ተናግርዎት አያውቅም ለምን መሰለዎት ምን አልባት ነጋዴው ክልሉን ለሱዳን ሸጠው ከመለስ ዜናዊ አገዛዝ ነፃ ያወጡናል ብሎ ስላሰበ ይሆናል፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ ለእርስዎ ያላቸውን ፍቅር የተረዳሁት ጉራፈርዳ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጉራፈርዳ በቃን አያሌው ጎበዜ ናፈቀን ብለው ቢለመኑ እምቢኝ ብለው እርስዎ ክልል ሲመጡ ነው፡፡
እናም በመጨረሻም እንኩ ምስጋናዬን ተቀበሉ
1.   ሰፊውን መሬታችንን ሽጠው ጠጋ ጠጋ ብለን በመኖር ማህበራዊ ህይወታችን እንዲጠናከር በማድረግዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
2.   እንደ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ሳይሞቱ በመልቀቅዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
3.   በ1998 በኮምቦልቻ፣ በ1999 በደሴ፣ በ2000፣ በ2003 የጎንደር እና የጎጃም ህዝብን በወያኔ ወታደሮች በጥይት አስገድለው ከዘንድሮው የኑሮ ውድነት እንዲያመልጡ ስላደረጉ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
አክባሪዎ ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.

Saturday, 12 October 2013

“አውጣኝ ያለም ወጣ አብላኝ ያለም በላ፣ምስኪኑ ጥንቸል ግን ተኝቶ ተበላ”

 
(ቴዲ - ዘአትላንታ)
ዕውቀት ጥራዝ ነጠቅ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ከጥራዝ ነጠቅ ሰው ጋር መከራከርም አይቻልም፣ ለሱ እሱ ልክ ነው፣ ምክንያት አምጥቶ፣ ብልት አውጥቶ አይከራከርም - የሚያውቀው ትችት ብቻ ነው። ጥራዝ ነጠቅነት ከስሜታዊነት ጋርም ይያያዛል። እንዲህ አይነት ሰዎች ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ቦታ አሉ - ይኖራሉም።

ሰሞኑን ከዚሁ ዓይነት ጥራዝ ነጠቅነት የመጣው ሃሳብ “ለኢትዮጵያ ለምን ይጸለያል - ናይጄሪያም እኮ አምላክ አለው” የሚል ነው። እንዲህ ዓይነት አስተሳስብ ጥራዝ ነጠቅነት ይባላል - አንዲት ነገር ፣ በአንዲት ጎን እና በአንድ መነጽር ብቻ አይቶ የሚሰጥ ጭፍን ድምዳሜ ነው።
...
ስለኢትዮጵያ ማሸነፍ መጸለይ ፣ ከናይጄሪያ መጸለይ አለመጸለይ ጋር ምን ያገናኘዋል? አንድ ሰው ሎተሪ ቆርጦ አንደኛው ዕጣ እንዲደርሰኝ እርዳኝ ብሎ ቢጸልይ ፣ አይይ .. ብዙ ሰው ቆርጧልና ለሌላው አይድረስ ለኔ ብቻ ይድረስ ማለት ስለሆነ አትጸልይ ሊባል ነው? አንድ ሥራ ቦታ የተወዳደረ ሰው "እግዜር ይህን ሥራ እንዳገኝ ርዳኝ" ብሎ ቢጸልይ .. አይይ ብዙ ሰው ተወዳድሯልና ለኔ ብቻ ብለህ አትጸልይ! .. ሊባል ነው? ሁሉም የሚጸልየው እኮ ለራሱ ነው።

እኛ እንደኢትዮጵያዊ፣ ለኢትዮጵያ እንጸልያለን፣ ናይጄሪያኖችም ለራሳቸው ይጸልዩ .. እግዜር ደግሞ የፈቀደውን ይስማ። አንድ ታሪክ ጣል ላድርግ … አንድ አንበሳ ተራበና .. እባክህ አብላኝ አብላኝ እያለ ወደ ፈጣሪው ጸለየ ….. ጸሎቱን እንደጨረሰ ቀና ሲል አንዲት ሚዳቆ አየ። “አይ ፈጣሪ! ጸሎት እንዲህ ፈጥነህ የምትሰማ ተመስገን .. አለና ሊያዛት ሲሮጥ .. እሷም በበኩሏ ወደ ፈጣሪዋ “አውጣኝ፣ አውጣኝ፣ አድነኝ” እያለች በመጸለይ መሮጥ ጀመረች። እግዜር ማንን ይስማ? (ናይጄሪያም ይጸልያል፣ ኢትዮጵያም ትጸልያለች .. እግዜር ማንን ይስማ? ስለዚህ አንጸልይ ለሚሉት ነው ..) .. ታሪኩ ይቀጥላል .
…. አንበሳው ሲከተል፣ ሚዳቆም ስትሮጥ ቆዩ። መጨረሻ ላይ ሚዳቆ አመለጠች፣ አንበሳም ደክሞት እንደተራበ አረፍ ለማለት ሲሞክር ሳይጸልይ ተኝቶ የሚያንኮራፋ ጥንቸል አገኘ። “ተመስገን - ሚዳቆ ብትነሳኝ ጥንቸል ሰጠኸኝ” በማለት ምሳ አደረገው።
ያን ጊዜ እንዲህ ተባለና ተገጠመ
“አውጣኝ ያለም ወጣ አብላኝ ያለም በላ፣
ምስኪኑ ጥንቸል ግን ተኝቶ ተበላ”

እናም ጸሎት ምን ይሰራል፣ ተኙ የሚሉ ጥራዝ ነጠቆች “የ7 ቢሊዮን ሰው ጸሎት በአንድ ሰከንድ መስማት የሚችልን እግዜር ፣ ግራ አታጋቡት ሊሉ ይሞክራሉ። የሱን ጥበብ ማን ያውቃል? ናይጄሪያና ኢትይጵያ ቢሸናነፉ እንኳን ሌሎች አገሮች በተለያየ ምክንያት “ዲስኳሊፋይ” ተደርገው ሁለቱም ሊያልፉ ይችላሉ እኮ! .. የኛ ድርሻ መጸለይ ነው፣ ጸሎታችንን መስማት አለመስማት የእግዜር ነው። ከጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ይሰውረን!!