"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday, 4 August 2012

ወያኔ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባዳ ሆነውብን ይዘልቃሉ



ዋለልኝ መኮንን
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር ከሞቱ/ከታመሙ ጀምሮ የህወሃትና ወይም ኢህአዴግ( ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጭበርበር የወጣ ስም መሆኑን እንዳትዘነጉ) ምን ያህል ከአንድ ጎጥ የተውጣጣ የበሰበሰና የተበላሸ የፓርቲና የግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ ግልዕ አድርጎልናል:: በጣም አስገራሚው ደግሞ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውን እርፍ አሉት::
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መሞት፣ የሬሳ ሳጥኑ ምን አይነት ነው ፣ መታመም፣ ምን እንዳመማቸው “ካሁን በሁዋላ የሚያሳትም የሚፅፍ የሚያወራ በአሸባሪነት ሊከሰስ እንደሚችል” የሚል ያዘለ መልዖክት አስተላልፈዋል::የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውናል እዚህ ጋር በረከት ስምዖን አንድ እውነት አለው ይህም የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ህዝብ የጠቅላይ ሚንስቴሩን ስልጣን አላገኙም::
ሌላው የመለስ ዜናዊ መሞት/መታመም የት እንዳለ የሚያውቁት ወያኔዎች ብቻ ናቸው ሊያውም ጥቂት አድዋዎች:: ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች አይደለም የመለስን መሞት/መታመም ይቅርና ትላልቅ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የሚሰሙት ልክ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመጀመሪያ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ባሉ የህዝብና የግል ሚዲያዎች ሲሆን ከዛም በሁዋላ በወያኔ የሚዲያ ማሰራጫዎች እንደማስተባበያ ሆኖ ሲቀርብ ነው:: በዚሁ ሳልናገር የማላልፈው ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስቴር መሞት ፣ መታመም እና የወያኔን እርቃኑን መቅረት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ህዝቡ የሚያደርገውን የዲሞክራሲ የፍትህና የኩልነት ትግል እንዲቀላቀሉ እመክራቸዋለው::
ሀወሃት/ኢህአዴግ/ ወያኔ ምንም ድርጅታዊ አሰራር መዋቅር መንፈስ የሌለው የጥቂት በሰፈር የተቡዋደኑ ፣ ለአራት አስርት አመት ያህል አመለካከታቸው መቀየር ያቃታቸው ፣ ጥቂት የሰባዊነት ስሜት በውስጣቸው የሌለ ማፊያ ግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ በቀላሉ አስረድተዉናል:: አሁን ልክ እንደጠንቁዋያቸው የሚያዩትና የሚሰግዱለት መሪያቸው መሞት/መታመም በሰፊው ከተነገረ በሁዋላ እንኩዋን የታየባቸው ባህሪ ይሉኝታ የሌላቸው ፣ የሃገር መፍረስ የህዝብ መራብ መቸገር ሳይሆን የወያኔ/የአድዋ አምባገነናዊ ሰልጣን የሚያሳስባቸው የቀን ጅቦች ናቸው:: ወያኔ በህግ መተዳደር የማይፈልግ ፣ የበታችነት መንፈስ ያናወዛቸው ፣ የስግብግብነት ስሜት ደማቸው ውስጥ የሚሮጥባቸው ፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ፣ በጠብመንጃ እንጂ በዕውነቶች ዙሪያ መደራደር የማይችሉ ስለመሆናቸው ያለፈው ስራቸው አስገንዝቦናል::
ዲሞክራሲያዊ ስርአት ስም ኢትዮጵያውያንንና የአለምን ህዝብ ያጭበረበሩበት የወያኔን ስልጣንና ጥቅም ብቻ የሚያስከብረው ፧ በአለም ላይ የምርጦች ምርጥ ብለው የሚፎክሩበት ፧ በወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ማሻሻል የሚሞከረው ህገ መንግስታቸው በሁሉም መልኩ ቀዳዳ የበዛበት ነው:: ጠቅላይ ሚንስቴሩን ዘላለማዊ አድርጎ አስቀምጦዋቸዋል :: እነዚህን ቀዳዳዎች ወያኔ እስካሁን ለማሻሻል ለመድፈን አልፈለገም እንደውም ለማጭበርበርና ለማምታታት በሰፊው ሲጠቀምባቸው ተስተውሎዋል ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቶቼ ተጥሰዋል ህገ መንግስቱ ይከበር ብሎ ሲጠይቅ ወያኔ ደግሞ ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ ብሎ ይከሳል :: ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ህገመንግስቱ ላይ “መያኔ ብቻ ህገ መንግስቱን መጣስ ይችላል” ተብሎ የተፃፈ ይመስል በየቀኑ መጣስ ብቻ አይደለም እየቀደደው ኖሮዋል ::
የኢትዮጵያን ህዝብ የዋህነት ፣ ታጋሽነት ፣ ጨዋነትና ታዛዝነት ልክ እንደ ፈሪነት፣ ሞኝነትና መሃይምነት ቆጥረውት በጠራራ ዐሃይ በሬ ወለደ ውሸት እየዋሹ ምንም እውነተኛ መረጃ እንዳያገኝ እያፈኑ በጠብመንጃና ኢትዮጵያውያንን እንደፈለጉ እስርቤት በሚያጉሩበት በአራዊት ህጋቸው እያስፈራሩ የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለማረጋገጥ አቅማቸው የቻለውን ሁሉ እያደረጉ ነው:: አሁን ጠቅላይ ሚንስትራቸው ሞቶም/ታሞም ሁሉም የወያኔ አባላቶች ፧ ደጋፊዎች ፧ በዘር የተዛመዱዋቸውና በስርዐቱ አላግባብ የከበሩ እያሰቡና እየሰሩ ያሉት እንዴት ወያኔ የበላይ ሆኖ እንደሚቀጥል እንጂ እንዴት አገራዊ መግባባት እንደሚፈጠር ፣ የህግ የበላይነት እንደሚሰፍንና ፣ አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ቀውስ በምን መልኩ መውጣት እንዳለባት አይደለም::
ወያኔዎች ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የሚይዘው የሚጨብጠውን ያጣውን የወያኔን የማፊያ ስርአት እናስወግድ::

ምናባዊ ቃለ-ምልልስ ከማስታወቂያ ሚኒስትሩ ከአቶ በረከት ጋር (ደረጀ ሃ/ወልድ)

 | 

ከደረጀ ሃብተወልድ
ጥያቄ፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? የት ነው ያሉትስ?
መልስ፦ እነዚህ ወገኖች የትራንስፎርሜሽኑን እቅድ ይፋ ስናደርግ ፦”ፖለቲካዊ ውጥረቱን ለማርገብ የተቀየሰና ሊሳካ የማይችል እቅድ ነው እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ የነበሩ ናቸው”
ጥያቄ፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉ? ወይስ የሉም? መቼስ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ?
መልስ፦”…ከዚያም የህዳሴውን ግድብ ስንጀምርም፤ በተመሣሳይ መንገድ ፦“መንግስት ይህን ታላቅ ግድብ እሠራለሁ ብሎ የተነሳው፤ በሰሜን ምስራቅ አፍሪቃ የተነሳው ዓይነት አብዮት እንዳይነሳበ
ት የህዝብን አቅጣጫ ለማስለወጥ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ማራገብ ጀመሩ…”
ጥያቄ፦ “ክቡር ጠ/ ሚኒስት
ሩ ደክመዋል፤ከዚያም አልፎ አርፈዋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡኮ ነው።
መልስ፦ “እህ … እነዚህ ወገኖች አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጤንነት በተመለከተ አሉባልታ እየነዙ ያሉት፤ ልማታችንን በማደናቀፍ የሚናፍቁትን የዓረብ አብዮት ለማስነሳት ካላቸው ከንቱ ምኞት በመነሳት ነው፤ይህ ግን እንደማይሳካላቸው ያውቁታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት 20 ዓመታት ያጣጣማቸውን የልማት ድሎች በተጨባጭ ተገንዝቧቸዋል። ከእንግዲህ ወደ ሁዋላ አይመለስም”
ጥያቄ፦”ክቡር ሚኒስትር፤ እስካሁን ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት ላቀረብኩት ጥያቄ የሰጡኝ ቀጥተኛ ምላሽ የለም”
መልስ፦”እህ. እ….ክቡር ጠ/ሚ/ሩ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።.. ከእንግዲህ በእርሳቸው ጤንነት ዙሪያ የሆነ ነገር በተባለ ቁጥር ፤መንግስት ለእያንዳንዷ ነገር መልስ የሚሰጥበት ሁኔታ አይኖርም”(ይህች ምላሽ ቃል በቃል ከኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር ከአቶ አሊ አብዶ የተወሰደች ትመስላለች) እናም… ሀኪም ያዘዘላቸውን እረፍት ጨርሰው ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ ብለን እናስባለን።
ጥያቄ፦ እረፍቱ እስከ መቼ ነው?አቦይ ስብሀት በአስር ቀናት ውስጥ ይመሳሉ ቢሉንም ፤ያተረፍነው ነገር፦
<ትመጣለች ብዬ- ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት ዓይኔ- ሟሟ እንደ በረዶ> የሚለውን ዘፈን ማንጎራጎር ብቻ ነው። እርስዎ በትክክል ይንገሩን? እስከ መቼ እረፍታቸውን ጨርሰው -መቼ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ?

የጥሩነሽ በወርቅ “ማድመቅ” እና የ “አመለወርቅ” በሀሽሽ “ማሸማቀቅ!”

 | 

የጥሩነሽ በወርቅ “ማድመቅ” እና የ “አመለወርቅ” በሀሽሽ “ማሸማቀቅ!”

Share

አቤ ቶኪቻው
ከቀናት በፊት አንድ አሳፋሪ ዜና ሰምተን ነበር። “ኢትዮጵያዊቷ ዲፕሎማት ሃሽሽ ሲያዘዋውሩ ተገኝተው በቁጥጥር ስር ዋሉ” የሚል አስደንጋጭ ዜና። ዜናው የተሰማው ከወደ እንግሊዝ ነበር። ዴፕሎማቷ ሴትዮዋ ለስሙ ስማቸው አመለወርቅ ነበር። ነገር ግን ስማቸውን መላዕክ አላወጣላቸውም እና “ድንቄም እቴ አመለወርቅ!” የሚያሰኝ ፀያፍ ስራ ሲሰሩ ተይዘው። እኛንም በአለም ፊት አሸማቀውናል!
የሰላሳ ስድስት አመቷ ወይዘሮ አመለወርቅ ይዘው የተገኙት 56 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተሰኘ ሀሽሽ ነው። እስቲ እንደው አፈር ስሆን፤ ወንጀሉ ይቅር፣ እኛን ማሸማቀቅም የለመዱት ይሁንላቸው… ነገር ግን ይህንን ሁሉ ሲሸከሙ የጡንቻ መሸማቀቅ ይይዘኛል ብሎ ማሰብ ትንሽ አይገባም…!?
ይህንን ዜና የሰማሁ ጊዜ መንግስታችን እንደዚህ አይነት ዲፕሎማቶችን በውስጡ አቅፎ ደግፎ ይዞ ሌሎች ምስኪን ወገኖች ላይ “መልካም ገፅታዬን አጠፋችሁ፣ የሀገር ደህንነት ስጋት ሆናችሁ፣ ወዘተ ወዘታችሁ” እያለ እስር ግልምጫ እና ጡጫ ማድረሱ “የሚጠምዱትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የማይባል ግፍ ሆኖ ነው ያገኘሁት።
ለማንኛውም ከቀናት በፊት ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ በእንግሊዝ የሚገኙ ሚዲያዎች የመንግሰት ዲፕሎማቷ የሰሩትን አሳፋሪ ስራ በዘገባቸው ይዘው ወጥተው አንገታችንን አስደፍተውን፣ ሽምቅቅ ብለን፤ ኪሏችን ሁሉ ቀንሶ ነበር የሰነበትነው።

Amelework Wondemagegne tried to claim diplomatic immunity when she was caught with 56 kg of cannabis (© AFP)
ትላንት ደግሞ በተቃራኒው ጥሩነሽ ዲባባ ከባልንጀሮቿ ጋር በመሆን ቀና ብለን እንድንራመድ አድርጋናለች። ባንዲራችንን ከፍ አድርጋ እኛም ከፍ ብለን እንድንታይ በተዓምረኛ እግሮቿ ተአምር አሳይታናለች።
ኬኒያዊቷ ተፎካካሪዋ ከጨዋታው በፊት ለሀገሯ ዜጎች አንድ መልዕክት አስተላልፋ ነበር። “ከአሁኑ ወርቅ እንዳገኘን ርግጠኛ ሁኑ እናም ፅዋቹን አንሱ” ብላ ነበር አሉ። በንግግሯ ልበ ሙሉነት የተደሰቱት ኬኒያውያንም ቀድመው በደስታ ሞቅ ብሏቸው ነበር ሩጫውን ሲጠባበቁ የነበሩት።
በአንፃሩ ደግሞ ጥሩዬ፤ “ውጤቱን ከወዲሁ መገመት አልችልም ሜዳ ላይ ይለያል… ደሞም እግዜር ያውቃል” በሚል ትህትና ነበር የጀመረችው። ስትጨርስ ግን ለኬኒያውያኖቹ ትህትና አላሳየችም “እለፉ” አላላቻቸውም ጥላቸው እብስ አለች እንጂ… አሁን እዚህ አልነበረች እንዴ…!? ብለው አጠገባቸው ቢመለከቷት እርሷ ዙሩን ጨርሳ ባንዲራዋን ለብሳለች!
“እኛስ ኮራን በናንተ…!” ቴሌቪዥናችን ከፈተልን እኛም አብረን ዘመርን!
እኔ የምለው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች ላይ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ስም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመፃፍ እጁ እምቢ ያለው ለምንድነው…!? “ክቡር ፕሬዘዳንታችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋችኋል” ብሎ ሲነግረን የጠቅላይ ሚኒስትራችንን የደስታ መግለጫ ለማየት የቋመጥን በርካታ የእርሳቸውን መልካም የምንመኝ ግለሰቦች ነበርን…! ኢቲቪ ግን ምነው እንዲህ ጠምዶ ያዛቸው…!? ችግር አለ እንዴ!?
ለማንኛውም ወዳጄ የመንግስት ባለስልጣኖቻችን “በአጠፋሪስ” ንግድ ያሸማቀቁን ከተማ ላይ አትሌቶቻችን ደግሞ በወርቅ አድምቀው ታሪካችንን ድጋሚ አድሰውልናል። እንኳን ደስ አለን! በቀጣይም ወርቁን ያብዛልን! አሜን!

Friday, 3 August 2012

የርዮት አለሙ 14 ዓመት ወደ 5 ዓመት ዝቅ ተደረገ!

 



በተከሰሰችበት የ “አሸብረሽናል” ክስ 14 አመት እና ብዙ ሺህ ብር ቅጣት ተበይኖባት የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ፤ የሚያስፈርድብኝ አንዳችም ማስረጃ አልቀረበብኝም እናም  “አቤት ክቡር ፍርድ ቤት” ብላ ይግባኝ ጠይቃ እንደነበር ይታወቃል። የማይታወቅም ከሆነ ይኸው አሁን ተናግሬያለሁ።
የርዕዮት ይግባኝ በቀጠሮ ሲንከባለል ቆይቶ በዛሬው እለት “ውሳኔ” አግኝቷል።
በውሳኔው ርዕዮት፣ ቤተሰቦቿ እና ጠበቀዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ ምንጮቼ ነግረውኛል። እንደ ምንጮቼ ከሆነ የርዕዮት ቤተሰቦች እና ጠበቃዋ “የይግባኙ ውሳኔ አቃቤ ህግ ምንም ማስረጃ ባለቀረበበት ሁኔታ የተወሰነ በመሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔ ነው ለማለት አያስደፍርም።” ብለዋል በመሆኑም ውሳኔውን ርዕዮት እና ጠበቃዋ በመካከር ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊወስዱት እንደሚችሉ ምንጮቼ ሹክ ብለውኛል።
በዛሬው ዕለት የርዕዮትን ፍርድ ከአስራ አራት አመት ወደ አምስት አመት ዝቅ እንዲል የወሰኑት ዳኛ ርዕዮትን፤ “አንቺም ብትሆኚ በጋዜጠኝነት ስትሰሪ ደህና ደህና ነገር መፃፍ ይገባሽ ነበር!” ሲሉ “መክረዋታል” ይህንን የታዘቡ አንዳንድ አሽሙረኞችም “ደህና ደህና ነገር አለመፃፍ አምስት አመት ያሳስራል ማለት ነው!” ሲሉ ማሸሞራቸውን ሰምቻለሁ!

Thursday, 2 August 2012

ትንሽ ወሬ፤ “መለስን ጥራ ሲሉት በረከት መጣ!



በመጀመሪያ ርዕሱን ቁልብጭ ለማድረግ ብዬ የተከበሩትን ሰዎች አንተ በማለቴ ይቅርታ ጠይቃለሁ። (በቅንፋችንም ካለፉት ጊዜያት ልምድ በመነሳት ባለስልጣኖቻችንን እኔ የተከበሩ ብዬ ስጠራ አንዳንድ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች የተቀበሩ ብለው እንደሚያነቡ ተደርሶበታል። ነገር ግን ይህ አግባብ አለመሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ። ምክንያቱም ቀብር ገና ነውና…! የተቀበሩ አይባልም እላለሁ!)
ትለንት ቀን ላይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዜና እወጃ “የአቶ መለስ ጤና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ” የሚል ዜና ሰምተን፤ አለቅጥ ተደስተን፣ ልባቸን በሀሴት ሰክራ ዋለች። አንዳንዶችም “አላዛርን ከሞት ያስነሳ ታምሩ የማያልቅ ጌታ እንደምን ያለ ፅድቅ ቢሰሩ እንዲህ አስነሳቸው…!”  እያሉ ለአምላካቸው ምስጋና አቀረቡ! ዝርዝር ዜናውን ለመስማት ጋዜጠኛይቱ “ምሽት ላይ እንገናኝ” ብላ ቀጠረችን።
ምሽት ለካስ እንዲህ ቀርፋፋ ነው…!? ምሽቱን መጠበቅ የአለም ፍፃሜን ከመጠበቅ እኩል ረዘመብን።
በሀሳባችን መለስ እንደወትሮው ከዙፋናቸው ጉብ ብለው “ስለ ተጨነቃችሁልኝ አመሰግናለሁ… ትንሽ ጉንፋን ብጤ ይዞኝ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያን ሰላም ማየት ያማይሹ የውጪ ሃይሎች የሻቢያ ተላላኪዎች እና የሀገር ውስጥ ነጭ ለባሾች ብዙ ነገር ሲያስወሩ እንደነበር ሰምቻለሁ እኔ ግን ይኸው አለሁ።” ሲሉን እየታየን ፈነደቅን።