“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ)
SHARE THIS
TAGS
“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com
“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com
በጠቅላይ ቤተክህነት የሚታተመው “ዜና ቤተክርስቲያን” የተሰኘ ጋዜጣ፤ ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ በሚል ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ጳጳሳቱ ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን ሲኖዶስ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም በወሰነው መሰረት ኮሚቴው እንደተቋቋመ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ጋዜጣው በርዕሰ አንቀፁ “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ ያሰፈረው ፅሁፍ፤ የቤተክርስትያኒቱን ሕግ ያልጠበቀና የሐይማኖቱን አንድነት ለመናድ ያለመ ነው ሲሉ ጳጳሳቱ እንደተቃወሙት ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተቋቋመውን ኮሚቴ የሰሜን ጐንደር ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ናትናኤልና ሌሎች ጳጳሳት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ ምሁራን እንደሚመሩት የጠቆሙት ምንጮች፤ ኮሚቴው የምርመራውን ውጤት በመጪው ጥቅምት ወር በሚካሄደው የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ማቅረብ ይጠበቅበታል ብለዋል፡

በውጭ ሀገራት በተለይ በአሜሪካ ለረዥም አመታት በመኖር ዜግነት ያገኙ ሰዎች በጳጳስነት መሾማቸውን የጠቆመው ጋዜጣው፤ አንድ እግራቸው አሜሪካ ሌላው ኢትዮጵያ በመሆኑ ሹመታቸው አግባብ አይደለም ብሏል፡፡
ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 4፣ ንዑስ አንቀጽ 39ኝን በመጥቀስም ጳጳሳት ለአበአበው (ፓትርያርክ) አለመታዘዛቸው አግባብ አይደለም ይላል – በዘገባው፡፡
የ1991ዱ ሕገቤተክርስትያን እንዲሻሻል የጠቆመው ጋዜጣው፤ ይህንና በመቃወም ድምጽ የሚያሰሙ ጳጳሳትን በተመለከተ ባሰፈረው ፅሁፍ፤ “…በነፃ ፕሬሶች ውዝግብ በመፍጠር የራሳቸውንና የቤተክርስትያኒቱን ገበና ያጋልጣሉ፡፡ የቤተክርስትያን ተከታይ የሆነው ወጣት ትውልድም ተቀናጅቶና አንጃ ለይቶ በሆነ ባልሆነው በነፃው ፕሬስ መወዛገብ የጀመረው ከነዚሁ አባቶች ተምሮ ነው፡፡
ይህም ሲባል ፓትርያሪኩ ከሕግ በላይ የፈለገውን ያድርግ ማለት አይደለም፡፡” በማለት ተችቷል፡፡
የጋዜጣው ፅሁፍ አስነዋሪ ነው ያሉት ጳጳሳቱ፤ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብፁአን ጳጳሳት አይወክልም፤ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ሆነው ቤተክርስትያኒቱን ለመሰነጣጠቅ የሚጣጣሩ የባዕድ ተወካዮች በጉያዋ መኖራቸው ያሳዝናል” ብለዋል፡፡
Share this:
inSh
No comments:
Post a Comment