Sunday, June 3rd, 2012 | Posted by zehabesha
በርከት ያሉ ምዕመናን በዋልድባ ጉዳይ በሚደረገው ሰልፍ ለመካፈል ወደ ዲሲ እየተመሙ ነው
13
Share

ትናንት ቅዳሜ ጁን 2 ቀን 2012 ከሚኒሶታ የተነሱት ምዕመናንን ጨምሮ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተንቀሳቀሱ ምእመናን በዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ እዚያ የሚኖረው ምእመናን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዘጋቢዎች ከስፍራው ተናግረዋል።
ከሚኒሶታ የተንቀሳቀሰው ቡድን 8 የ እንግሊዘኛ እና 8 የአማርኛ መፈክሮችን ይዞ እንደሄደ የታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም በሎስ አንጀለስ ነገ ጠዋት በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ወደ 40 የሚጠጉ መፈክሮች እንደተዘጋጁ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስና በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የሚያዙት 18 የእንግሊዘኛ መፈክሮች የሚከተሉት ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያዘውን 18 የ እንግሊዘኛ መፈክሮች PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ከሚኒሶታ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሄዱ ም እመናን የያዟቸው 16 የአማርኛና የ እንግሊዘኛ መፈክሮችን PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ነገ ጁን 4/2012 በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገውን ሰልፍ ለመዘገብ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ሪፖርተርም ዋሽንግተን ዲሲ ገብታለች። ዘገባዎችን እንዳደረሰችን ለድረ ገጻችንን አባቢዎች እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።
No comments:
Post a Comment