ይህን ተከትሎ የአቶ መለስ ህመም እጅግ አደገኛነቱን ያሳያል የሚሉት ታዛቢዎች እንዳሉ ሆኖ ዛሬ
አዲስ አበባ እንደገቡ ሲወራ የነበረው አቶ መለስ አሁንም በውጭ ሃገር ህክምና ላይ እንዳሉና በቅርብ ጊዜ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ የዘገበው ሪፖርተር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሥዩም መስፍን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚታከሙበት ቦታ ሄደው ከጐበኟቸው ባለስልጣናት መካከል ይጠቀሳሉ ብሏል። ይህን የሰሙ አስተያየት ሰጪዎች አቶ መለስ መንግስት እንደሚለው እረፍት ብቻ የሚያስፈልገው በሽታ ከያዛቸውና በሽታውም ቀላል ከሆነ እነዚህ ባለስልጣናት እንዴት ረዥም አገር አቋርጠው ጥየቃ ሊሄዱ ቻሉ? ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ መለስን ሚስታቸው በፓርላማ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ እንኳ ከአጠገባቸው ያልተለዩት አቶ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ መሆናቸውንም ሪፖርተር ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ፓርላማውን አቶ መለስ ንግግር አድርገው እንደሚዘጉት መግለጫ የሰጠ ቢሆንም፤ አቶ መለስን የሚታከሙበት ቦታ ጠይቀው የተመለሱት አባዱላ ገመዳ አማካኝነት ፓርላማው ካለ መለስ “ቡራኬና ስድብ” ሳይዘጋ ቀርቷል።
በሌላ በኩል ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ለመጎብኘት ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ በደህንነት ሚ/ሩ ጌታቸው አሰፋ መከልከሉን ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ላይ የተዘገበው የሟቹ ክንፈ ገ/መድህን የጀመሪያ ልጅ “መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ፤ መለስ ዜናዊን እፋረደዋለሁ”ብሎ በአደባባይ ከተናገረ በኋላ መለስን እንዳይበቀል፤ ሽማግሌ ሆነው ሲያግባቡት የነበሩት እነዚሁ መለስን የታመመበት ሃገር የጠየቁት ባለስልጣናት እንደነበሩ ይታወሳል።
ዜናውን ላላነበባችሁት እዚህ ጋር ተጭነው እዩት።
No comments:
Post a Comment