"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Friday, 28 September 2012
ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው
ጣቱ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን የማይወድ እና የማያደንቅ ወጣት አዛውንት የለም ሆኖም ይህንን የሰርጉን ቀን አስመልክቶ ወዳጅ ዘመዶቹ ታላቅ የደስታ ቀናቸው ነበር ።በዛሬው እለት የተፈጸመው ይህ ሰርጉ ደማቅ ከመሆኑም በላይ ታሪክ የተሰራበት እለት መሆኑን ታዳሚዎቹ ገልጸዋል ።ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉበት ይህ የሰርግ በአል የእርሱን ኩራትም ሆነው በሰርጉ እለት አሳይተውታል። ቴዲ አፍሮ ለውዱ ባለቤቱ እሱ ከመድረክ ላይ ሆኖ ሙሽሪት ከሚዜዎቿ ጋር ከመድረክ ስር እየጨፈረች ጸባየ ሰናይ የሚለውን ዘፈኑን አቀንቅኖላታል ።ከዚያም በላይ አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ የሚለውን ዘፈን ሲዘፍን ተሰምቷል በዚህም ዘፈን ላይ መድረክ ላይ በመውጣት የጋራ ዳንሳቸውን አሳይተዋል ።በመጨረሻም የሰርግ ዘፈን ሲዘፈን በታዳሚው ፊትለፊት እየተሳሳሙ የፍቅር ጉያቸውን በሞቀ ትንፋሻቸው አሙቀውታል ሌሎችም የሙዚቃ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከሰአት ማጠር የተነሳ ሃይልዬ ታደሰ እና ታምራት ደስታ ብቻ ሳይዘፍኑ ፕሮግራሙ ተጠናቆአል ።ይህ የቴዲ አለም ዛሬ ታላቅ ቀን ነበር ያሉት ታዳሚዎቹ ቴዲ ለዚህች አገር እና ለሙዚቃ ወዳጆቹ ብዙ መሰዋእትነትን ከፍሎአል አሁንም በዚህ ክብረ በአሉ ላይ ወዳጆቹ መንገዶችን ሞልተው ሞተር ሳይክል አሸከርካሪዎች በተለያዩ ሾዎች እያሳዩ ፍቅራቸውን ለግሰውታል አድናቆታቸውንም ቸረውታል ።ከዚያ በተለየ መልኩ ሻንበል እና ሰአሊ ለማ ጉያ አስደናቂ የሆነ ስጦታ ለቴዲ አፍሮ ቴዲ ስጦታ ያወረሱት ሲሆን ከስእሎቻቸው መሃል ለዚህ ለሰርጉ ቀን ተብሎ የተሳለ የአጼ ቴዎድሮስን ስእል ከአንበሳ ጋር ያለበትን ታላቅ ስጦታ ሲያበረክቱለት የህዝቡ ስሜት ታላቅ ነበር ብለዋል ።በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሱት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በዚህ ስጦታ ላይ ተዲ ሳቅ እና ለቅሶ ሲታይበት ሰአሊውን አቅፎ ለረጂም ሰአት ስሟቸዋል። ኢዮብ መኮንን (ብረባም ባልረባም ትወጂኛለሽን) ሲያቀነቅን ጎሳዬ ተስፋዬ ከራሱ ዘፈኖች እና ከቴዲ ዘፈን ዘፍኖአል ሸዋንዳኝ የቀረብኝ የለም ሲል አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ ብሏል ታደለ ገመቹ ኦሮምኛ ሲያዘም ግርማ ካሳ ፣ተሾመ ወልዴ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፣ዳግማዊ አሊ ፣ሳምሶን ጃፋር ፣ፋሲል ውሂብ፣አሸናፊ አሊ ፣አቡጊዳ ባንድ ፣ኤክስፕረስ ባንድ፣ ክብረት ዘኪዎስ ፣ታምራት ሃይሉ (ቁም ነገር መጽሄት) :ታምራት ደስታ
እና ሃይልዬ ታደሰ የመድረኩ አጋፋሪዎች ነበሩ ።ከላይ እንደጠቀስነው በፕሮግራሙ መጣበብ ምክንያት ሃይልዬ እና ታምራት ብቻ ሳይዘፍኑ የሰርጉ ሁኔታ ተጠናቆአል።ሁሉም አርቲስቶች በጣም ተደናቂ የሆኑትን እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ዘፈኖቻቸውን አቅርበዋል።
በዚህ የክቡር ቀን ለአካል ጉዳተኞች የአንድ መቶ ሺህ ብር በብሄራዊ ቴአትር ጋር ማስረከቡን ይበልጥ ኩራት ለህዝቡ ሆኖታል ፣የአካል ጉዳተኞችም ደስታቸውን እና የሰርጉን ድምቀት ሆነውት አልፈዋል ።
ማለዳ ታይምስ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment