"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 5 September 2012

በሕግ አምላክ! ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትሪያሪክ አይሾምም



መግቢያ:

አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን ፓትሪያሪክ የሆኑት አባ ጳውሎስ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨገ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ድንገተኛና አነጋጋሪ ሞት ተከትሎ መንበሩ በማን ይተካ? ለሚለው ጥያቄ ባለፈው ሳምንት “ፓትሪያሪክ መርቃሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ!” ስል ለንባብ ማብቃቴ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ስርዓትና ቀኖና በጠበቀ መልኩ በምትካቸው ከነባር ሊቃነ ጳጳሳት መካከል መርጣ መሾምና ሹመቱንም ማጽደቅ አዲስ ነገር አይደለም። ሆነም ግን የቤተ-ክርስቲያኒቱ መሪዎች የውጭ ተጽእኖዎችና እክሎች በሚገባ መቋቋም ተስኖአቸው ከከፈቱት ክፍተት የተነሳ ላለፉት ፪፰ ዓመታት ለሰሚ በሚያሳፍር መልኩ እርስ በርስ ሲተረማመሱና መሪው ወደ ወሰደው የሚሄደው ሕዝብም ሲታመስ እዚህ መድረሳቸው የሚታወስ ሆኖ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የቤተ- ክርስቲያን መሪዎች በሚወስዷቸው እርምጃዎችና በሚያስተላልፍዋቸው ውሳኔዎች ቀደም ሲሉ የተፈጠሩ ችግሮች በመቅረፍ ረገድም ሆነ በአንጻሩ ጉዳዩን በማወሳሰብ ቁልፍ ሚና መጫወታቸው የማይቀር ነው።
ይኸውም: ራሱ የቅዱሳን ማህበር በሚል የቁልምጫ አጠራር የሚጠራ ፊዘኛ ድርጅት ፈለግ በመከተል ፓትሪያሪክ በህይወት ሳለ (ፓትሪያሪክ ሳይሞት) አዲስ ፓትሪያሪክ ለመሾም የደፈሩ: የተቀመጡ ወይንም የመረጡና የሾሙ እንደሆነ ሰላም የሚባለውን ነገር ላለማየት ብቻ ሳይሆን ቋንቋው በራሱ ላለመስማት ከመቁረጣቸው በላይ ያለ ኃጢአታቸው ሲወቀሱ: ስማቸው ሲነሳና ሲረገሙ የኖሩትን አባ ጳውሎስ ከዚህ ሁሉ ተጠያቂነትም ሆነ ሃላፊነትም ከመውሰድ ነጻ መሆናቸው ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ያለፈውን ስህተት ላለመድገም ስርዓተ ቤተ- ክርስቲያን ከማፋለስ አንጸር ድርጊቱ ሕገ ወጥ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ/ሌላ ፓትሪያሪክ መሾም በራሱ ሊያስከትለው የሚችለውን ጠንቆችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም እንዲቀጥል በማድረግ የቀድሞ ፓትሪያሪክ ወደ መንበራቸው የሚመለሱበት መንገድ የፈጠረ እንደሆነ ለዓመታት የዘለቀውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን ችግር መፈታቱ ነው።

የጽሑፉ ዓላማ:

በጽሑፉ ርእስ በግልጽ እንደ ሰፈረ “ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ አዲስ ፓትሪያሪክ አይሾምም!” ከሚለው ባሻገር ተቆርቋሪነቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ለማውደምና ለማፈራረስ እስካልሆነ ድረስ የተጀመረውን እርቀ ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከማድረግ ይልቅ አባቶች ያላሰቡትን እያሳሰበ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመሩና ያልተፈለገ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱም እሳት እያነደ የሚገኘውን እሳባቂ ማህበር “ማህበረ ቅዱሳን” ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ አዲስ ፓትሪያሪክ ተሹሞ ማየት ለምን እንደቋመጠ:ይህን ህልሙ እውን ሆኖ ያይ ዘንድም ምንና ለምን ይህ እያደረገ እንዳለ: የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን እንደ ድሃ ቀብር እያጣደፈ ሳይውሉ ሳያድሩ ፓትሪያሪክ ይሾሙ ዘንድ የአህዛብ ማኅበር “ማኅበረ ቅዱሳን” ለምን እየተጣደፈ እንደሚገኝ:ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ አዲስ ፓትሪያሪክ በመሾም ስነ ስርዓትም “ማኅበረ ቅዱሳን” ተጠቃሚ የሚሆነው እንዴት ነው?የሚሉቱንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄቆች ለመመለስ ተጻፈ።
ሐተታ:

መንፈሳዊ ቤትም ሆነ መንፈሳዊ አሰራር በተመለከተ/በማንሳት በተወያየንባቸው በርካታ ጊዜያት “በባሌ በቦሌ” ተብሎ ፈሊጥ እንደሌለ ብቻ ሳይሆን መንገዱ አንድና አንድ ይኸውም የጽድቅና የእውነት መንገድ ለመሆኑ ሳናነሳ ያለፍንበት ጊዜም ሆነ ቅጽበት የለም። ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ራሱን የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ ግብረ እኩይ ማህበር ትናንት “እንደማይሆን ተገንዝቦ” የአዞ እንባ እያነባ የአስታራቂነት ካባ ተላብሶ “በእኔ ይሁንባችሁ፣ እኔ ላስታቃችሁ! በሞቴ!” እያለ ሲያላዝንና ሲያሾፍ እንዳልነበረ ዛሬ ደግሞ ሸሽቶ ማምለጥ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱንና ቁርጡን ሲያውቅ ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማህበሩ በሚያስተዳድራቸውና በሚዘውራቸው የወሬ ፋብሪካዎቹ እንዲሁም የሐሰትና የቅጥፈት ልሳኖቹ በመጠቀም “ባርባንን ፍታልን ኢየሱስን ስቀልልን!” እንደማለት የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች የሚያደርጉትን ከማድረጋቸው በፊት ቆም ብለው ሁለቴ የሚያስቡበት ፋታና ዕድል በማሳጣት ማህበሩ በጨለማ የቀርጸውና የነደፈውን ስውር አጀንዳ በመደገፍ ድምጻቸውን ያሰሙና ይሰጡ ዘንድ ከዚህ ቀደም የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች በማስመልከት ለንባብ ባበቃው ጽሑፍና የማህበሩም እምነት መሰረት ነውር ያለባቸውን በነውራቸው በማስፈራራት: ጥቅመኞችን በጥቅም በመደለልና ቅኖቹንም ደግሞ መንታ በሆነው የዘንዶ ምላሱ በማታለል ነገሮች በጥድፍያ ያከናውኑለት ዘንድ ከመቼውም በበለጠ ጊዜ ራሱን ከሌሊት እንቅልፍ ከቀንም ዕረፍት ከልክሎ ይገኛል።
እዚህ ላይ አጽንዖት ሰጥቼ ለማውሳት የምፈልገው ነጥብ ቢኖር በመዋቹ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ፈንታ መንበሩን በማን ይተካ?ለሚለው ጥያቄ በማስመልከት ጉዳዩን ከማድበስበስ አልፎው ማህበሩ በሕጋዊ ድረ ገጽ በኩል “ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስና ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምን ይላል?” ሲል ግንቦት11- 2003 ዓ.ም ባወጣው ጽሑፍ የሚያውቅብኝ የለም በማለት ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን እስታኮ በከፍተኛ የማጭበርበር ድርጊት ተዘፍቆና ተሰማርቶ ነው የምናገኘው። ለዚህም መልሱ አጭርነው። አዎ! “ማህበረ ቅዱሳን” ይህን የቤተ ክርስቲያን ስርዓት የሚያምንና የሚቀበል ከሆነ: የተቋቋመበትም ዓላማ ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ጠብቆ ለማስጠበቅ ከሆነ ይኸው ስርዓተ ቤተ- ክርስቲያን በጠራራ ጸሐይ ሲጣስ (ወደዛ እየተኬደ ስላለ ነው)ስርዓተ ቤተ- ክርስቲያን ይከበር! “ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ አዲስ/ሌላ ፓትሪያሪክ አይሾምም!” በማለት ተቃውሞውን ሊያሰማ በተገባ ነበር። ዳሩ ግን የማህበሩ ዓላማ በግርግር የሚገኝ ትርፍ በመለቃቀም ራስህን ማሳበጥና ጎልተህ መውጣት ነውና ይኸው ጋጠ ወጥነትን በማራገብ ስራ ተጠምዶ መሬት እየመሸበት ይገኛል።
ታድያ ቤተ- ክርስቲያኒቱ አሁን ለምትገኝበት ውጣ ውረድ የፓትሪያሪክ ጳውሎስ ፓትሪያሪክነት ፓትሪያሪክ በህይወት ሳለ በፓትሪያሪክነት መሾማቸው ተከትሎ የተፈጠረ ነው ሲል በሥጋ ባረፉት ፓትሪያሪክ ስላቁንና ወቀሳውን ያልተወ ማህበር በተራው በስህተት ላይ ስህተት በጥፋት ላይ ጥፋት ለመፈጸም እንቅልፍ ሲያጣ እያየንና እይሰማን እኔና እርስዎ ካላስቆምነው ማን ያስቁመው? ማንስ ኸይ ይበለው? ማንስ ይቃወመው?
ሌላው ነጥብ “ማህበረ ቅዱሳን” ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ አዲስ ፓትሪያሪክ ተሹሞ ማየት ለምን ቋመጠ? የሚለውን ጥያቄ ነው። እንግዲህ “ማኅበረ ቅዱሳን” ማለት ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲል ያገሬ ሰው የቤተ- ክርስቲያን መሪዎች-
➢አለመግባባት፣
➢አለመስማማት፣
➢አለመቀባበል፣
➢አንድአለመሆን፣
➢አለመደማመጥ፣
➢መለያየት፣
➢መከፋፈል፣
➢ከዚህም አልፎ እርስ በርስ መናቆርና መባላት፣
➢መተረማመስ፣

➢ጎራም ለይቶ መፋጀት ማለት “ለማኅበረ ቅዱሳን” አሁን ባለበት ከዚህም በባሰና በከፋ መልኩ ተደራጅቶ ቤተ ክርስቲያንና የቤተ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ለማውደም፣ ለመዝነፍ፣ ለማራቁትና በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን የጦር አውድማ በማድረግ በግርግሩ ማሃል ያለ አንዳች ከልካይና ጠያቂ በሕግ የውንብድና ስራ መስራቱም ሆነ ህልውናውን ማቆየት የሚያስችለው በቀላሉ የማይገኝ ፍቱን የዕድሜ ማራዘምያ መድሃኒት ነው።
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አንድ መሆን ማለት “ማኅበረ ቅዱሳን” ብሎ አታላይ፣ ስራ ፈት ጎበዝ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ዕድል ፈንታ/ህልውና አይኖረውም። ይህን ሐቅ ደግሞ “የማኅበረ ቅዱሳን” የስራ አመራርና አባላቶቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለሆነም በአሁን ሰዓት “የማኅበረ ቅዱሳን” ጸሎትና ትጋት በአንድም በሌላም አመካኝቶ የጫረውን እሳት የሚያያዝበትና እየተንበጎበጎም የሚነድበት ምክንያት ይፈልጋል እንጂ “ተዉ ያለፈውን ይብቃ! በስህተት ላይ ስህተት ቀርቶ ሰላም አውርዱ፣ ይቅር ተባባሉ፣ የሚሻለውም ዕቅርን ማውረድ ነውና ተስማሙ!” ብሎ ግሳጼ አይውለውም። ታድያ የራሱን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ሲል የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ገደል ይግባ ባይ ማኅበር “ታላላቆችን” እንደ ዛር ፈረስ እየጋለበ ከፊቱ የሚቆመውም ሁሉ ወግቶ ለመጣልና ውርውሮም ለማጋደም ጦሩን ስሎ መነሳቱ የቅዱሳን ስራ እየሰራ መሆኑ ነው? በዚህ አጋጣሚ “ማኅበረ ቅዱሳን” ሲባል እንደ ስሙ መንፈሳዊ ማኅበር ለሚመስላችሁ ወገኖች በሙሉ፡ ድርጅቱ ምንም በመጠሪያው መንፈሳዊ ስም የያዘ ቢሆንም ማኅበሩ መንፈሳዊ ማኅበር ሳይሆን መጽሐፍ ዲያብሎስን የብርሃን መልዓክ መምሰል ይችልበታል እንዲል ይህ ግብረ እኩይ ማኅበርም በቤተ ክርስቲያን ጉያ ስር ተወሽቆ መንፈሳዊ ካባ ለብሶና ተከናንቦ አገር አጥፊ ትውልድ ገዳይ ሰውር አጀንዳ ያለው አታላይ ድርጅት ለመሆኑ ለመግለጽ እወዳለሁ።
ለመሆኑ “ማኅበረ ቅዱሳን” የመዋቹ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ፕትርክና ይቀበላል አይቀበልም? አቡነ መርቆሪዮስስ ቢሆኑ “በማኅበረ ቅዱሳን” ዘንድ ማን ናቸው? “የሀገር ቤቱ” የሲኖዶስ አባላት በመዋቹ ፓትሪያሪክ ፈንታ በአስቸካይ ፓትሪያሪክ ሾመው ያጸድቁ ዘንድስ “ማኅበረ ቅዱሳን” እንዲህ የተጣደፈው ይህን ለማስፈጸምም ቀደም ሲል በምዝበራና በማጭበርበር ያካበተውን ከፍተኛ ሀብትና ገንዘብ እንደ አመድ እየበተነ የሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አራተኛ ፓትሪያሪክ በማለት ስማቸው በመዝገብ ያሰፈረችው ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ሞተዋል ብሎ ስለሚያምን ይሆን? ለመሆኑ ይህ ጋጠወጥ የአህዛብ ስብስብ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ላይ ተቀምጠው ልዩነቶቻቸውን በማጥበብና ችግሮቻቸውንም በመቅረፍ ቢስማሙ: ወደ  አንድነት ቢመጡና ስምምነት ላይ ቢደርሱ “ማኅበረ ቅዱሳን“ እንዲህ በቁሙ የሚያስቃዠው፣ ሊደፋው ያለና የሚያስቀዝነው እውነት “ማኅበረ ቅዱሳን“ የቅዱሳን ህብረት ስለሆነ ነውብለው ያምኑ ይሆን? ኦ እግዚእ …!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

No comments:

Post a Comment