October 21, 2012 · 0 Comments
በግጥሙ እና በዜማዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው የጥቁር ሰው ባለአባት ቴዲ አፍሮ በትላንትናው እለት በጊዮን ሆቴል ባደረገው የሙዚቃ ዝግጅት የተሳካ እንደነበር ምንጮቻችኝ ጠቁመዋል ።በተለይም የማለዳ ታይምስ የአዲስ አበባ አንባብያን በፌስ ቡክ መልእክት ማስተላለፊያ ላይ እንዳሰፈሩት ከሆነ የቴዲ ዘፈን ካለው አቋም አንዳችም ፈቀቅ ሊል እንዳልቻለ እና አሁንም የውስጡን ፍላጎት መተንፈስ የሚችልበት አዲስ ምእራፍ እንዳሳየ “አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ “እያለ ማቀንቀኑ እና እስካሁን ድረስ ምንም ለውጥ በሃገሪቱ ላይ እንደሌለ የሚያስየውን ስንኙን እንደቋጠረ እና ዜማውንም እንደተቀኘ ገልጠዋል ።ይህንን ዜማ ህብረተሰቡ አብሮ ተቀብሎ እያዜመ አብሮ እንደጨረሰውም የገለጡት እነዚሁ ወገኖች የጃ ያስተሰርያል የሚለውን ዘፈን እንዳለቀ ድጋሚ እንዲዘፈን ቢጠየቅም መድገም እንደማይፈልግ እና መግለጽ የሚፈልገው አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ እንደሌለው ሁሉም አንድ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ መሆኑን የሚያመለክት ሃሳብ ገልጾ “አዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ” በማለት በድጋሚ የዜማውን እና የግጥሙን ስንኝ መዞ ከህዝቡ ጋር አብሮ እንደ ዘፈነው ተገልጦአል ።በዚህ ደስታ የጦዘው የሙዚቃ አፍቃሪው በከፍተኛ ደስታ ሰክረው እንደነበር እና እስከመጨረሻው ድረስ ዜማቸውን ሲያንቆረቁሩት እንደነበር እና በተለይም የጨዋታው ፕሮግራም ካለቀ በኋላም አንዳንድ ሰዎች ከጊዮን ግቢ ውጭም አዲስ ንጉስ እንጂ እያሉእየዘመሩ መንገዳቸውን ሲጓዙ ተሰምተዋል ይላል የማለዳ ታይምስ ምንጫችን ከአዲስ አበባ ።
በዚህ ባሳለፍነው ወር መጨረሻ ላይ የሰርግ ስነስራቱን በደማቅ ሁኔታ ያደረገው ቴዲ አፍሮ ከጋብቻው በኋላ የተጫወተው ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት የመጀመሪያው ቢሆንም ጥቁር ሰው አልበምን ካወጣ ጊዜ ጀምሮ በአራተኛነት ደረጃ ሊካተት የሚችል እንደሆነ ተገልጦአል በሌላም በኩል ባሳለፍነው ወራት በቴዲ አፍሮ እና በባንዱ መካከል ስለተፈጠረው አጠቃላይ ውዝግብ አስመልክቶ ዜናዎችን አጠር አድርገን መዘገባችን የሚታወስ እንደሆነ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ሆኖም ከባንዱ አካል አንዱ የሆነው አበራ አለሙ ከዛሬ ጀመሮ የባንዱ አካል አይደለሁም ብሎ ይህንን ጊዮን ላይ የተደረገውን ኮንሰርት ሳይሰራ ወደሚኖርበት ስቴት መመለሱን ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ሪፖርቱ ደርሶአል ።የተፈጠረው የውስጥ ችግር ቴዲ ሊፈታው ባለመቻሉ እና ቅድሚያ የራሱን ጥቅም ብቻ ለማስከበር ስለሮጠ እኛም የራሳችንን ጥቅም ማስከበር ይገባናል ለ10 አመታት ያለምንም ኮንትራት ወንድማማች በተሞላበት እና የሙዚቃ ፍቅር ባለበት ስንሰራ ቆይተናል ከአሁን በኋላ ግን መስራት ካለበኝ ሊከፈለኝ የሚገባውን ክፍያ በስምምነት አድርገን ከዚያም የጠየኩት ክፍያ ሲፈጸም ብቻ ካልሆነ ምንም ነገር ላልሰራ ወሰኛለሁ የባንዱም አካል አይደለሁም ከአሁን በኋላ የባንዱ አካል ተብዬም ልጠራ አልፈቅድም ሲል ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ገልጾአል።በአትላንታ በሚደረገው ለኖቬምበር 21 ኮንሰርት ልትሳተፍ ትችላለህ ወይ ተብሎ ለተጠየቀውም አበራ ሲመልስ ክፍያው ተጠናቆ ከተከፈለኝ ልሰራ እችላለሁ ቀድሞ እንደምንሰራው የግሩብ ስራ ክፍያ ሳይሆን እኔ በግሌ ሊከፈለኝ ይገባል የምለውን ብቻ ክፍያው ሲጠናቀቅ ከመስራት ወደኋላ አልልም በማለጥ ገልጾአል ።በሌላም በኩል ስለ እነ ሩፋዔል ወልደማርያም፣ቴዲ አሃዱ እና ዔርሚያስ ከበደ ፣ከባንዱ አባልነት ለምን እራሳቸውን አላገለሉም በማለት የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ የጠየቀው ሲሆን የእነሱን ሙሉ መረጃ እና ማረጋገጫ የለኝም ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ለልምምድ ተብሎ ከሁለት ወራት በላይ አብረን ቆይተን ከዚያም ስምምነቱ ሊመጣ ስላልቻለ እኔ ሰርጉን ውዬ መመለስ እንዳለብኝ ወሰንኩ የ እነሱን ጉዳይ ግን እራሳቸው ናቸው የሚያውቁት አጠቃላይ ግን የሚወሰነው ከሄዱበት አገር ሲመለሱ ሁሉም ነገር ይለያል ብዬ አምናለሁ ስለዚህ ከእኔ እና ቴዲ ጋር ያለው ጉዳይ ግን አብቅቷል ጉዳዩም በራሳችን የዝግ ችሎት ጨርሰናል ሲል ገልጾአል ለሙሉ የዜና መረጃ ጥንቅር ማለዳ ታይምስ
No comments:
Post a Comment