"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 3 October 2012

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ዩ-ቲዩብ እና ፌስ ቡክ ተዘጋ ;ኢንተርኔት መጠቀም በግቢው ውስጥ ተከልክሏል

 

October 2, 2012   ·   0 Comments
MARAKI LIBRARY
ባለፈው ሳምንት በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተከናወነውን ስብሰባ አስመልክቶ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ሃይሎች እና በዩኒቨርሲቲ መምህራን መካከል የተካሄደው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው ። “ግንቦት ሰባት እና ግንቦት ሃያ እኩል ሊታዩ ይገባል” ተባለ በሚል  ዜና መዘገባችን ይታወሳል ።ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር በመላው የአካዳሚክ ማእከል ውስጥ የሚገኙትን የኢንተርኔት ኔትወርኮች ፌስ ቡክ እና ዩ-ቲዩብ እንዳይመለከቱ መዝጋታቸውን እየሚያመለክት የዜና ምንጫችን ጠቁሟል ።
እንደ ደረሰን መረጃ መሰረት በትምህርት ተቋም ውስጥ የተከሰተው ይኸው የኢንተርኔት መታገድ ምክንያት ባለፈው በማለዳ ታይምስ ላይ ተሰርቶ የነበረውን  ዜና አስመልክቶ አስተዳደሩ ስለተናደዱ ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩ መምህራን ለማለዳ ታይምስ ጠቁመዋል ።በግቢው ውስጥ ለምተገኙ መምህራን እና ተማሪዎች የተዘጋውን ዌብሳይት ለመክፈት ይህንን ሊንክ http://pray3.com/ በመፈለጊያ ቦታው ላይ በማስቀመጥ ፈልግ ብላችሁ ፣እንዳይዘጋባችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ትብብሩን ያደርጋል ፣ለዚህም ሊንክ እንደ ገና ከተዘጋባችሁ ሌላ ተያያዥ ሊንኮችን በመቀያየር መክፈት የምትችሉ መሆኑን እንጠቁማለን ።
በተዘጋው የኢንተርኔት መጠቀምን አስመልክቶ ብዙዎችን ሰራተኞችን ተማሪዎችን እና ሌሎችንም የአስተዳደር አካላትን ያስቆጣ መሆኑን ሲጠቁሙ ፣በማደግ ላይ ያለ ተቋም ከሚባሉት ተርታ ሳይመደብ ትልቅ ተቋም ነው እየተባለ የሚወራውን ይህንን ተቋም የመረጃ ነጻነት እና የአገልግሎት እጥረት የተማሪውን የመማር አቅም የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ የወደፊት እራእያቸውን የሚያቀጭጭ ነው ሲሉ መምህራኑ አስተያየታቸውን ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል።ይህ ደግሞ የ እኛን የመምህርነት ምግባር በትክክል እንዳንሰራ የሚያግደን እና ነጻነታችንን ጭምር የሚጋፋም ነው ብለዋል ።በተለይም የተለያዩ ምርምራዊ ስራዎችን ለመስራት እና ዋቢ መጽሃፍትን ከተለያዩ ቦታዎች በአጭር ጊዜ ለመፈለግ እና እውቀትን ለተማሪዎቻችን መመገብ የሚገባንን ሁሉ ለማድረግ ያግደናል ይህ ግን የነጻነት እና የመናገር እንደዚሁም የሰውልጅ መብትን ሁሉ የሚጋፋ ነገር ነው ሲሉ ገልጸዋል።በዚሁ ሁኔታ መምህራኖች የጋራ አቋም መግለጫ ወይንም የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ በጥረት ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ለማለዳ ታይምስ ዘግበዋል።
በሌላም መልኩ በገለጹት መረጃ መሰረት አስተዳደሩ በሙስና የተጨማለቀ እና እንዲሁም ከመለስ አስተዳደር ጋር አጣብቂኝ የነበራቸው ሰዎች ዛሬም ከአማራ ክልል መንግስት ጋር እና እንዲሁም የወያኔ ኢሃዴግ አስተዳደርን የሙጥኝ ብለው የጥቅማቸው መሳሪያ ያደርጉት መምህራን እና አስተዳደሮች የጎንደር ዩኒቨርሲትይን የልዩ ጥቅም ቤታቸው አድርገው ከመሰረቱት ቆይተዋል  ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአጠቃላይ ለተለያዩ ሃገራዊ ክብረ በአሎች መሰጠት የሚገባው ክብር ቀርቶ ለግንቦት ሃያ የሚሰጡት ክብር እና ዝና ከምንም በላይ ነው በ እለቱ የሚሰጣቱት መዋእለ ነዋይ እጅግ ውድ ከመሆኑም የተነሳ የዩኒቨርስቲውን በጀት የሚያራቁት እንደሆነም አክለው መምህራኑ ገልጸዋል

No comments:

Post a Comment