"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 22 November 2012

ሰማቱ የኔሰው ገብሬ ለፍትህ እና ለነፃነት ሲል እራሱን አቃጥሎ የሞተበትን አንድኛ ዓመት በኦስሎ ታሰቦ ዋለ። በእንዳለ ጌታነህ ኖርዌ


መቼም አንረሳችሁም



የክረምቱ ቅዝቃዜ መጣሁ
መጣሁ እያለ  ያስፈራራል።ቀኑ ደግሞ በጣም አጭር በመሆኑ ጭለማው  ረጅሙን ጊዜ እየወሰደ የድብርቱን ሰዓት አራዝሞታል።[በተለይ ስራ  ለሌለን ሳንወድ በግድ በካምፕ ውስጥ ለተጎለትን] ግማሹ ከራሱ ጋር ያወራል  ሌላው አጠገብ ከሚገኝ ጉዋደኛው ጋር በረባ ባረባው ይጨቃጨቃል ፤ይጣላል፤ ደግም ምን አዲስ ነገር አለ  በሚለው ዘመን አመጣሽ ጥያቄ ሃሳብ ይሰበስባል ደግም ላልሰሙት ያሰራጫል። ግማሹ ኮምፒውተር ላይ ተቀምጦ  የሆነ ያልሆነውን  ይከፍታል ይዘጋል ።ገሚሱ ደግም ሰብሰብ ብሎ ቡናውን እያፈላ እናንተ ሰማችሁ የተባለውን ዛሬ እኮ ፓርላም የሚያወሩት ስለ  ስደታኛ ነው እኮ  አሉ፤ሌላዋ ትቀጥላለች የሆነ ካፕ ውስጥ ፖሊሶች ገብተው ፈተሸው ሰው ይዘው ሄዱ፤እረረረረ  እንዳው ምን ተሻለን ?ደግም ይቀጥላል........ ። እንግዲህ የየዕለቱ ውሎዋችን ይህንን ሲመስል አልፎ አልፎ  ግን ከሰው  ጋር የሚቀላቅለን አንዳንድ አገራዊ ጉዳዮች ሲኖሩ ያቅማችንን ለመሳተፍ ወደ ከተማ ብቅ እንላለን።ስለዚ በዛሬው ዕለት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት   አዘጋጅነት በኦስሎ  ለወጣቱ ስለፍትህ ስለ ነፃነት ስለ ሰብአዊ መበት መከበር ሲል ውድ ህይወቱን ቤዛ ላደረገልን መምህር የኔሰው ገብሬ እና በግፍ የታሰሩና የተገደሉ የነፃነት ታጋዮችን ለማሰብ እና ለማስታወስ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት  ይደረጋል ። በዚሁ ስነ  ስርዓት  ላይ ለመገኘት እና  ያቅሜን አስተዋፅኦለማድረግ ከተባለው ሰዓት ቀደም ብዬ  ነው በቦታው ላይ የታደምኩት።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች ቀደም ብለው በመገኘት ለዝግጅቱ ግባት የሚሆኑትን ቁሳቁሶች ለታዳሚው በማደል የድምጽ ባለሙያው[sound man] ቀስስስስ ብሎ  ሆድን እያባባ ማንነታችንን የሚያስታውስ፤ የደሀውን ገበሬ አባታችንን  ልፋት፤ በጀርባዋ ቅጠል ተሸክም ያሳደገችንን እናታችንን ድካም፤ምንም ነገር ሳንፈይድለት እርስ በእርስ ባለመስማማት አንድነትና ፍቅር አተን አለንልህ ሳንለው ቀርተን በግፍና በመከራ የሚሰቃየውን ህዝብ በዓይን ህሊናችን እያሳየን በሀሳብ ባህር ያሳፈረ በዋሽንት ብቻ የሚንቆረቆረው ሀገርኛ የባህል ሙዚቃ ይዞን ጭልጥ ሲል፤ የፕሮግራሙ  መሪ ከሃሳባችን ወይም ከተሳፈርንበት ተውስታ ላይ ውረዱ በማለት የእለቱ ፕሮግራም መጀመር አበሰረን ። ከድርጅቱ ሊቀ መንበር ጀምሮ  የተለያዩ  ታዋቂ ሰዎች ንግግር አድርገዋል ። በተለይ ዶ/ር ሙሉ ዓለም ባደረጉት ንግግር በውጭ ሀገር የምንኖር ኢትዮጵያውን  ከምንጊዜውም በበለጠ ህብረትና ወገናዊ ፍቅርን በመካከላችን በመመስረት በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት እረገጣ ሰለቸኝ ደከመን ሳንል ለህዝባችን ነፃ መውጣት መታገል አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።                                                                                                          

በዝግጅቱ ላይ ታዋቂውና አንጋፋው አርቲስት ዳምጠው አየለ በቀረርቶ ቀስቃሽ የሆነውን ጥዑም ዜማውን ሲያቀርብ እንዲሁም እኔም የሙያ ባልደረባው  እንዳለ  ጌታነህ በክራር  ፋኖ ፋኖ የታባለውን ዘፈን በማቅረብ ለየኔሰው ገብሬ እና በግፍ እስር ቤት ያሉትንና የተሰው የነጻነት  ታጋዮችን  ያለንን ክብር ገልጸናል።  በተጨማሪ አቶ ማተቤ  እና  አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ  ግጥሞችን ያቀረቡ ሲሆን በማይክ እጥረት ያሰቡት ቅንብር  ትንሽ  ቢስተጓጎልም በወይዘሮ ገነት የቀረበው ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዛብሄር ትዘረጋለች የሚለው  በውጭ አገር ሰው የተጻፈ ግጥም በእንግሊዘኛ አቅርበዋል።የዕለቱ ሰማዕታትን የመዘከሩ  ፕሮግራም በጥሩ ቅንብር ታዳሚው በብርዱ ሳይማረርና በፕሮግርሙ ሳይሰለች ባማረ ሁኔታ ተደምድሟል።እንኤም የዕለቱን ዘገባ እዚህ ላይ በመጨረስ  ካሜራ ማኑ እስክንድር በዕለቱ የቀረጸውን  ቪዲዮ  በመጋበዝ ነው

No comments:

Post a Comment