"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 5 March 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ

 የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

fisherman
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

ኡሞት ኡዶል (ፎቶ: ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)
አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ። ስለተፈጸመው ግፍ የተሞላበት ግድያና ከግድያው በኋላ ስለተከናወነው “አረመኔያዊ የእንስሳ ተግባር” ሲያስረዱ በቁጣ ነው።
በተጠቀሰው ቀን ቤተሰቦቻቸውን ቀበሌያቸው ድረስ በመሄድ በመግረፍና በማስፈራራት ወደ አብሌን ለከበባ በጠቋሚ የመጡት የመከላከያ አባላት ሰዎቹን እንደተመለከቱ ተኩስ ከፈቱ። በድንገት የተከበቡትና ዛፍ ሥር ተቀምጠው የነበሩት አንዳችም ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በጥይት የተደበደቡት ሰዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ቢያደርጉም አልሆነም። ተደራጅቶ በሶስት የወታደር ካሚዮን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ የመጣው ሰራዊት ጨፈጨፋቸው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደተናገሩት ወዲያው ህይወታቸው ካለፈው ስድስት ንጹሃን መካከል አቶ ኡሞት መሞታቸው ሲታወቅ የሰራዊቱ አባላት አውካኩ፤ በደስታ ጨፈሩ። አስከሬኑንን ጭነው ፉኙዶ ወደሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በመሄድ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ደስታቸውን አበሰሩ።
አስከሬን በመኪና በመጫን ከተማ እየዞሩ ደስታቸውን ገለጹ። በማግስቱ በጋምቤላ ከተማ ስታዲየም አስከሬኑን ህዝብ እንዲመለከተው ታዘዘ። ህዝብ ስታዲየም ተገኝቶ የአቶ ኡሞትን አስከሬን እንዲሳለም፣ ኢንቨስተሮችም ያለስጋት የመሬት ነጠቃቸውንና “ልማታቸውን እንዲቀጥሉ”፣ መሞታቸውን አይቶ ሕዝቡ እንዲያምንና ሞራሉ እንዲጎዳ የተላለፈው ውሳኔ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስተጓጎለ። ለጎልጉል መረጃውን ያስተላለፉ እንዳሉት አቶ ኡሞት አሜሪካዊ መሆናቸው ሲታወቅ ማዕከላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ። አስከሬኑን ባስቸኳይ እንዲቀብሩ መመሪያ ሰጡ። ሁሉም ነገር በመመሪያው መሰረት ተጠናቀቀ። የአቶ ኡሞት አስከሬን ባልታወቀ ቦታ ተቀበረ። አስከሬኑንን ለማየት በግዳጅ ተሰባሰበው ህዝብም ምንም ነገር ሳይመለከት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሁኔታውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢህአዴግ ሠራዊት በጎክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች በተለይም ወንዶችን እያሠሩና እያሰቃዩ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያረጋግጣል፡፡
የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት ጉዳዩን ለአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀና የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ጀምሮ እንደሚመረምረውና እስከ መጨረሻው የመንግሥት አካል እንደሚደርሱ ማረጋገጡ ታውቋል። ኢህአዴግ አቶ ኡሞትን የገደለበትን ምክንያት በማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበትም አስታውቀዋል። አቶ ኡሞት የሚጠረጠሩበት ድርጊት እንኳን ቢኖር በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ መጠየቅ እየተቻለ እንዲገደሉ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ የሚከራከሩላቸውና ጉዳያቸውን ይፋ ያደረጉት ክፍሎች ይናገራሉ።
በወቅቱ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃንና የደረሱበት ያልታወቀው ሰዎች ስም ዝርዝር ከስፍራው የደረሰን ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
  1. ጎጎ ኦቻላ
  2. ቻም ኦቻላ
  3. ዑከች አቻው
  4. አኳይ ኦሞት
  5. ኦሞት ኦባንግ
  6. አጂባ አኳይ
  7. ኦሞት ኡጁሉ ኦጎታ
  8. አንበሳው ኡጁሉ
  9. ቱወል ኦሎክ
  10. ኦችዋል ኦባንግ
  11. ኦዋር ቻም
  12. ኒሙሉ አጎሌ
  13. አብራች ኒሙሉ
  14. አኩኔ ኦሞት
  15. አግዋ ቻም
  16. ኦዋር ኒግዎ አጋክ
  17. ኦሞት ኡዶል (አሜሪካዊው)

Thursday, 28 February 2013





ትናንት እና ዛሬ




ወጨጫ ማርያም ሲነግስ በየዓመቱ ከጎረቤቶቼ ጋር እንሄዳለን፡፡ ቤተሰቦቼም የሚኖሩት እዚያው አካባቢ ስለሆነ ወጨጫ ማርያምን ካነገስን በኋላ እነሱ ዘንድ እንገባና በሚገባ ተጋብዘን እንወጣለን፡፡በየዓመቱ ስለማንቀር በደንብ ተዘጋጅተው ይጠብቁናል፡፡
ምንሄደው አምስት ሆነን ነው፡፡ የዚያ ዕለት ታዲያ ባሎቻችንን በጠዋት ወደየሥራቸው ሸኝተን መንገዱን በእግራችን እንያያዘዋለን፡፡ በጉዟችን ላይ ስለኑሯችን፣ ስለገጠመኞቻችን፣ መንገድ ላይ ስለምናየው ነገር ሁሉ እናወራለን፡፡ከንግስ መልስ ቤተሰቦቼ ቤት ስንደርስ የሚያደርጉልን አቀባበል መቼም ልዩ ነው፡፡ ሁላችንንም አገላብጠው ስመውን ሲያበቁ እንጀራው፣ ዳቦው፣ ቆሎው፣ እርጎው፣ጠላው፣ አረቄው ቀርቦ ስንበላና ስንጠጣ ውለን አመሻሽ ላይ ከዳቦውና ከቆሎው ትንሽ ትንሽ ቋጥረን መንገዱን እንያያዘዋለን፡፡ ከሞቅታው ጋር ጨዋታውን በሳቅ እያጀብን ድንግዝግዝ ሲል ወደ ቤት እንገባለን፡፡
    የአንዷ ጎረቤቴ ቤተሰቦች የሚኖሩት መናገሻ ነው፡፡ እዚያም በየዓመቱ የንግስ በዓል ሲኖር አምስታችንም ጎረቤታሞች ተያይዘን እንሄዳለን፡፡ በእኔ ቤተሰቦች ከተስተናገድነው ባላነሰ ተስተናግደን እንመለሳለን፡፡ ይሄ በየዓመቱ የሚፈፀም ክስተት ነው፡፡ከዚህ በተረፈ በየቀኑ አንዷ ጎረቤት አንዷን ሳታይ ውላ አታድርም፡፡ አንድ ቀን ካልተያየን ምን ነክቶሽ ነው ብለን እንጠያየቃለን፡፡      የታመመችም እንደሆነ ጥፍጥ ተደርጋ የተሰራች ምግብ ነገር ከቤታችን ይዘን በመሄድ፣ “እግዚሃርይማርሽ ቀላሉንያድርግልሽ” ብለን አጫውተናት ወደጎጇችን እንመለሳለን፡፡በርበሬ ወይሽሮ ያስፈጨን እንደሆነ፣“ቅመሺ ቅመሱ” ብለን ሰፍረን እንልካለን፡፡አንዷ፡ገበያ ደርሳ ስትመለ ስረከስ ያለነገር ካገኘች በርከት አድርጋ ገዝታ ትመጣና፣“ይህን ነገር ገዝቼልሻለሁ፤ ስሙኒ ወይም ሃምሣ ሣንቲም ላኪ!” ተብሎ ይላክባታል፡፡የቸገረ ዕለት፣ከመሶቡ ቁራሽ እህል የጠፋ ጊዜ፣“አንድ እንጀራ ላኪልኝ” መባባል የተለመደነው፡፡አንዷ ቤት እንግዳ የመጣም እንደሆነ፣“ከጋገርሽው ትኩስ እንጀራ ቶሎ ስደጂልኝ” እየተባባልን መረዳዳት ይዘነው የቆየነው ባህል ነው፡፡ዓመት በዓል እንዳለፈም፣“ነይ ቅራሪ  ጠጪ የሚል መልዕክት  እርስበርሳችን መቀባበል ወይም ልጅን አንድ ጠርሙስ ቅራሪ አስይዞ መላክምእንዲሁ፡፡በባሎቻችን ዘንድ የነበረው ግንኙነትም የሚያስቀና ነበር ከሥራ መልስ፣“ተማሪ ቤት እንሂድ”እየተባባሉ እየተቀላለዱ ተያይዘው ጠጅ ቤት ይሄዳሉ፡፡የአንዳችን አጥር ሲፈርስ በጋራ ሆነው ያጥራሉ፡፡ለለቅሶ ወደ ገጠር የሚሄድ ካለ ብቻውን እንዴት ተደርጎ ይባልና የአንዷ ባል አብሮት ይሄዳል፡፡ለበዓል በሬ አርደው ሲቃረጡ፣የተወሰኑት ገንዘ ብሰብሳቢ፣ግማሾቹ ገዢ፣ሌሎቹ አራጆች ሆነው ይሠራሉ፡፡ተከፋፍለው ሲለያዩ፣ ለቀጣዩ ዓመት በሰላም እንዲያደርሳቸው ተመራርቀው ይሰነባበታሉ፡፡
ዛሬ ያንን  ጊዜ አጥብቄ እንዳስታውሰው ያደረገኝ አንድ ነገር ተፈጥሯል።

፡፡ያለሁት አራስ የሆነችው ልጄ ዘንድ ነው፡፡እዚህ የመገኘቴም ሚስጥር ላርሳት ነው፡፡    ድሮ እኛን የሚያርሰን እናት ወይም እህት ሳይሆን ጎረቤት እንደ ነበር ለልጄ አወራኋት፡፡እሷን ስወልድ ያረሱኝ ሃዳስና ሙሽሪት እንደነበሩ ገለፅኩላት፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ቡላ የሚሉትን የጉራጌ ባህላዊ ምግብ የቀመስኩት ያን ጊዜ
እንደሆነና  እንዴት  እንደሚጣፍጥ  ብቻ ሳይሆን ለሰውነት ያለውን ጠቀሜታ ጭምር ተረኩላት፡፡
ሳይቸግረኝም  ስለጎረቤቶቿ  አነሳሁባት፡፡
“አይብዙምአንግባባም እሷየዚህብሄረሰብተወላጅናት፡፡” አለችኝ፡፡“ታዲያ ትሁና ምን አለበት”
“አይ አመለካከቷ ጥሩ አይደለም

እሺ ከበታችሽ ያለችውስ”
“እሷደግሞየዚያኛውብሄርተወላጅናት፡፡”
“ታዲያ ምን  ያገናኛዋል ኢትዮጵያዊ አ;ይደለች

!?”ንዴት ጉሮሮዬን እያነቀኝ ጠየኳት፡፡“አይ እማዬ በአሁኑ ጊዜ አንቺ እንደምታስቢው አይደለም፡፡ሁሉም በየብሄሩ ተከፋፍሏል፡፡መታወቂያችንን እንኳን አታይም?” አለችኝ፡፡ከልቤ አዘንኩ፡፡ልጆቼ ምን ዓይነት ጊዜ ላይ እንዳሉ እያሰብኩ ክፉኛአዘንኩኝ፡፡መቼም ልጆቼን በዚህ መልኩ በፍፁም እንዳላሳደኳቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ከጓደኞቼ መካከል ጥቂቶቹ በህይወት የሉም፡፡ቢኖሩና ይሀንን ጉድ ሲሰሙ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ማወቅ ይከብደኛል፡፡ በእኛ ጊዜ በሃዘኑም በደስታውም  አንድ ላይ ነበርን፡፡“በእኛ በትግሬዎቹ አገር እንዲህ ነው የምናደርገው፤በጉራጌ ግን እንዲህ ነው፡፡በኦሮሞ እንደዚያ ፡፡በ… እያልን እናወራለን፡፡እዚህ ላይ የእናንተ ባህል ጥሩ ነው፤እዚህ ላይ ጎጂ ነው”እየተባባልንእንነቅሳለን፡፡እንማማራለን፡፡እግዚኦ! ያዘመን ምንኛ የሚያሳሳ ዘመን ኖሯል?የሙሽሪት ክትፎ እጄን ያስቆረጥመኛል፡፡የበቀለችን ጨጨብሳ ሁሌም እናፍቀዋለሁ፡፡የሃዳስ አምባሻ፣የስፍራሽ ዶሮ ተበልተው አይጠገቡም፡፡አንዱ ካንዱ የሚማረው ሙያም ለጉድ ነበር፡፡አሁን እኔ ሁሉንም ዓይነት ምግብ ልክ እንደነሱ ልቅም አድርጌ ማዘጋጀት እችልበታለሁ፡፡ባህላቸውን ያስተማሩኝ እነሱው ናቸዋ ;በሠርግ ከጓደኞቼ ጋር እኩል ጨፍሬ፣በሃዘኑ አብሬ ተኮማትሬ ነው የኖርኩት፡፡አልቅሽ አልቅሽ አለኝ፡፡በእርግጥ ከጎረቤቶቻችን መካከል የማንግባባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ግን በዘራቸው ሳይሆን በስነምግባራቸው አሊያም በፀባያቸው ምክንያት ነው፡፡መፈቃቀር ተፈቃቀሩ ስለተባለ አይመጣም፡፡መለያየትም እንዲሁ፡፡ሰው በሚኖርበት አካባቢ እንደ አግባቡ በሰላም በፍቅር ተዋዶይ ኖራል፡፡እውነቴን ነው የምለው እስከ ዛሬ ድረስየ ሃዳስ ትግሬነት፣የስፍራሽ አማራነት፣የበቀለች ኦሮሞ መሆን፣የሙሽሪት ጉራጌነት ታውሶኝ አያውቅም፡፡ማንም እከሌ እንዲህ ነው ሳይለ ንከዘራችን በፊት ሰው መሆናችን፣ብሎም ኢትዮጵያዊነታችን አስተሳስሮን ተዋደን፣ተፋቅረን ነው ያሳለፍነው፡፡ይህንን የዛሬውን ጉድ ሳያዩ ባለፉት ጓደኞቼ ቀናሁ፡፡ብቸኝነት ተሰማኝ፡፡ልጄ በሰዎች ተከባ ባይተዋር ሆና እየኖረች ነው፡፡የህፃኑ እጣስ ምን ሊሆን ነው ሰጋሁ፡፡አባቱ ዘሩ ምን እንደሆነ ጠይቄ አላውቅም፡፡ልጄን ልጠይቃት አፌላይ አደረስኩትና፣“መልካም ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ያ ከሁሉም በላይ ነው፡፡ሌላው ትርፍ ነገር ነው፡፡” ስል አስቤ ተውኩት፡፡ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ፡፡የበቀለችን ፈገግታ፣የሃዳስን ሹሩባ፣የሥፍራሽን ንቅሳት፣የሙሽሪትን ሻሽ አስተሳሰር እንባ በጋረደው ዐይኔ ተመለከትኩ፡፡* *
ከቅዱስ መጽሐፉ ውስጥ የወጣውና በሚያምር የእጅ ጽሑፍ የተጻፈው ጥቅስ የሰዎች ዐይን

በቀላሉ የሚያርፍበት ቦታ ተሰቅሏል፡፡ “እንደ እግዚያብሔር ያለ ማንም የለም” ይላል፡፡አንድ ጎልማሳ መሳይ መጣ፡፡ወደ ጥቅሱም ሄደ፡፡ከደረት ኪሱ ቀይ ብዕር አወጣና ከጥቅሱ መሃል“ግ” የተሰኘችውን ሆሄ በቀይ አቀለማት፡፡እንዲህም ሆነ፤“እንደ እግዚያብሔር ያለ ማንም የለም” “እንደ እዚ ያብሔር  ያለ ማንም የለም” አይተንኮል  አይክፋት


 *








Wednesday, 27 February 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ለምን  100 ጊዜ  አተከፋፈሉም ተዉኝ ሞቴን ልሙትበት



ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

Sunday, 17 February 2013

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ
ጸጋዬ ገብረ መድኅን

ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡ . . .
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ . . .
... ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . .
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር . . .

የኋላ የኋላ፥ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ፥ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡
ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው . . .
የእንባ ጭለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበው፡፡
ዕጣውን ለብቻው ቆርሶ
ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ
ብቻውን ጭለማ ለብሶ
ገበናውን ሣግ ሸፍኖ
ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ
ሌሊት፥ የማታ ማታ ነው
ሕቅ እንቁን እሚነጥበው
ኤሎሄውን እሚረግፈው . . .
ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅሙ ወዙ እቶን ተፈልጦ
እንደጠፍር-ብራቅ እምብርት
እንደእሳተ ገሞራ ግት
‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው
ደም ነው፥ ፍም ነው እሚያነባው፤
ንጥረ ሕዋስ ነው ሰቆቃው
ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፥__ብቻውን ነው የሚፈታው፥
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ፥ እንደደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ፥ . . .
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፥
ተሸሽጎ ተከናንቦ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ . . .
የብቻ ብቸኝነቱ፥ የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ-ሌት፥ ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ፡፡
ጸጋዬ ገብረ መድኅን
እሳት ወይ አበባ
(፲፱፻፶፭ - አምቦ - ኮልፌ)

Friday, 15 February 2013

ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ ምሽት[እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌ እንደተመለከተው]

እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ አገራችን እንገባለን

የዳመነው ችግር;ሰማዩ  እስኪጠራ፤ ካገር ተሰደድን በተራ በተራ።አንድ ቀን ይታየኛል፡ታብሶ የኛ ዕንባ ፤እጅ ለእጅ ተያይዘን አገር ቤት ስንገባ። ይህ ዜማ በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ  በአሜሪካ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባቀረበው የሙዚቃ  ዝግጅት ላይ በአገር ፍቅርና ናፍቆት ለሚሰቃየው አገር ወዳድ  እጅ ለእጅ አያይዞ  ያላቀሰበት ዘፈን ነበር።እኛም ዛሬ በፎቶው እንደሚታየው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን  የሚያገለግለውን የእሳትን መለያ ካኔተራ በመልበስ በእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ  ምሽት ላይ በኖርዌ የምንገኝ  ስደተኞች ከአጭር ድራማ በኋላ የዘመርነው መዝሙር ነው።                                                                           ልቀጥል በዝግጅቱ ላይ የተገኘውን ህዝብ ስመለከት አንድ ነገርአሰብኩኝ፤ደግሞም ተመኘሁኝ፤ማሰብም መመኘትም መብቴ  ቢሆንም ምናልባት እኔ  እንዳሰብኩት  ይህንን ጽሁፍ የሚያንብ ሰው ሃሳቤን ይጋራል ብዬ ልገምት፤ሀሳቤ ምን መሰላችሁ፤በፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ የነበረው ዕድምተኛ በሙሉ  ለሁሉም አገራዊ ጥሪ ህብረቱ፤አንድነቱ፦ትብብሩና በጋራ መስራቱ ሁል ጊዜ እንዳሁኑ ቢሆን፤ልክ የድራማው መጨረሻ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝሙሩን በአንድነት ከልብ ከስሜት እንደዘመርን ፤በእምነታችንና በዘራችን ሊለየን ፤የንግግር፦የመጻፍና በሰላም የመኖር መብታችንን ያሳጣንን፤አገራችንን ለባዕድ እየሰጠ ገበሬውን መሬትና አገር አልባ አድርጎ በአገሩ ላይ ስደተኛ እንዲሆን የሚያደርገውን  ጨቋኝና ከፋፋይ የሆነውን የወያኔ መንግስት በጋራ ለማጥፋት፤ህብረታችን እንዲቀጥል፤የእርስ በርስ  መናቆራችንን በመተው ላገርና ለወገን የሚበጀውን ቅድሚያ  በመስጠት በህብረት ብንቀሳቀስ; ብዬ ተመኘሁ። ደግሞ ቀደም ብዬ  ተናግሬአለው  መመኘት መብቴ ነው ብዬ ።                                                                                                                                                     እስኪ ይታያችሁ እኔ  የተመኘሁት ከመጀመሪያው ቢሆን ኖሮ አይደለም 21 ዓመት አንድም ዓመት አይቆዩም ነበር።እረ  የምን አንድ ዓመት አመጣህ ያኔ ገና ሰባት እንዳሉ   በአንድ ቦምብ እምሽክ ነበር እንዳለው ይሆን ነበር።ትሉኝ ይሆናል ፤ግን ነበርን ትተን ላለፈው ክረምት  ቤት አይሰራም ለሚመጣው  ይታሰባል የሚለውን አገርኛ አባባል ተቀብልን ወደፊት በሉለት ይለይለት የሚለውን የጥላሁንን ዘፈን ለአንባቢዎቼ ስመርጥላችሁ፤ለቃሉ ታማኝ በመሆን ከእሳትና ከውሃ እሳትን በመምረጥ የእናት አገሩና የህዝቡ መጠቃት ዘወትር የሚያገበግበው እንደ  ሌሎቹ አርቲስት ነን ባዮች ምሳሌ ከርሳሙ ሰለሞን ተካልኝ እና  መሰሎቹ ለጥቅም ሳይገዛ ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠር ጀምሮ  ቃል የእምነት እዳ እንጂ የእናት አባት አይደለም በማለት ብዙ መከራና ችግር  በመቀበል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለእኛም ከኢትዮጵያ ውጭ ላለነው ምሳሌ  በመሆን እንድንሰባሰብና በደስታና በፍቅር እንድንገናኝ ላደረገው፤አንድዬና ብርቅዬ ልጃችን፤ወንድማችንና ፡አባታችን  ለሆነው የሰባዊ መብት ተሟጋች ፤አክቲቪስትና  አርቲስት ታማኝ በየን እረጅም እድሜና ጤና  ለእሱና ለመላው ቤተሰብ  እየተመኘው ጥቁር ሰው የሚለውን ዘፈን በታማኝ ስም አዳምጡልኝ በማለት ነው።                                                              በዕለቱ ስለ ነበረው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ትንሽ ነገር ልበል፤ፕሮግራሙ የሚፈለግበትን  አላማ አሟልቷል።  ማለትም የሚፈለገው ገንዘብ ማግኘት ነው አዎ  ገንዘቡ ተገኝቷል ።ቅድመ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነበር ። አብዛኛው ሰው በተለያየ ኮሚቴ  ውስጥ በመግባት ያደረገው እርብርብ  በትንሹ የሚገመት አይደለም።በአስራ አምስት ቀን  እንዳይሞት ለምግብ ብቻ  የሚሰጠውን  900 ክሮነር በመቆጠብ ከተለያዩ ቦታ ለትራንስፖርት ወጪ በማድረግ  ለማረፊያ  እንኳን ሳይጨነቁ ባላቸው ጉልበት ለኢሳት ያላቸውን ፍቅር  በተለያዩ  ስራዎች ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በካምፕ ያሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች በጣም ሊመሰገኑ ይገባል።                                                                                                                                                               የውያኔ ሰራዊት  ኢትዮጵያን  ከተቆጣጠረበት ጊዜ  አንስቶ  እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይና  እንግልት  የሚያሳይ ተመልካችን  በእንባ  ያራጨና  ወደ ኋላ  በትዝታ ወስዶ  ለካ  እንደዚህም ተደርጓል ብሎ ከልብ ያሳዘነ  በስደተኛው ተጽፎ የተዘጋጀ አጭር ተውኔት  ለዕይታ  ቀርቧል ።ተውኔቱን  የጸፉትም  ለምለም  ሀይሌ እና ያሬድ ኤሊያስ  ሲሆኑ  እንዳለ ጌታነህ ተውኔቱ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል ።በድራማው ላይ ሳላነሳ  ያማላልፋቸው እናት በመሆን  የተጫወቱት  ወይዘሮ መዓዛሽ መኮንን  እና ልጅ በመሆን የታጫወተው ያሬድ በትክክል ባህሪው  የሚፈልገውን  ካራክተር ከልብ በመጫወታቸው ሰውን በእንባ  አራጭተውታል። 
ከድራማው በኋላ ከታማኝ በየነ ጋር
                                                                                                                                                               ላልፈው  ወይም ልተወው የማልችለው ችግር ትንሽ ልበል ፤በርግጥ በትንሽ ወጪ ብዙ ብር  ማግኘት ቢሆንም አላማው ምንም አይሰራም ያልነው ሃሳብ ችግር ሲሆን አይተናል ምሳሌ  ፕሮግራምን በተመለከት፦የቅደም ተከተል ችግር ነበር።የድምጽም መሳሪያን በተመለከት፤ ዋናውና ሰው በአንክሮ ሊከታተለው የሚገባ የታማኝ ዝግጅትን በድምጽ ምክንያት ለመከታተል  ሲቸገርና ታማኝም በትክክሉባለማቅረቡ ሲበሳጭ በቅርብ ሁሉም ያየው ነው።ስራ ሲሰራ  ስተት  መፈጠሩ አይቀርም ጥሩ ትምህርት ሆኖ ያልፋል ግን ይህንን የተፈጠረውን ትንሽ ስህተት ቀድመን ስለተነጋገርን ቢያንስ ብንሰማማ ኖሮ  ችግሩ ባልመጣ ነበር ፤እንደዚ ዓይነት ብዙ ሰው የሚያሳትፍ ዝግጅት ሲኖር ቢያንስ ሙያው የሚመለከተውን ስራ ለሙያው ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ከተቻለ  ሀላፊነቱን መስጠት ካልተቻለ  ማማከር ተገቢ ነው ብዬ  አምናለው።ሃሳቡን እናንሳው እንጂ ዋናው ነገር በኖርዌ የምንገኝን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ  ጥሩ ምሽት ሆኖ አልፏል።ላሁኑ ላብቃ  ሰላም ያገናኘን ደህና  ሰንብቱልኝ።ዝግጅቱን የኢሳት ቴሌቪዥን በቅኝት ፕሮግራሙ ላይ ያቀረበውን እየጋበዝኩኝ እሰናበታለው።ጽሁፉን በተመለከተ አስተያየት መስጠት ያለኝን ደካማ ጎን ማጎልበቻ  ስለሆነ እባካችሁ ።