"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 15 February 2013

ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ ምሽት[እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌ እንደተመለከተው]

እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ አገራችን እንገባለን

የዳመነው ችግር;ሰማዩ  እስኪጠራ፤ ካገር ተሰደድን በተራ በተራ።አንድ ቀን ይታየኛል፡ታብሶ የኛ ዕንባ ፤እጅ ለእጅ ተያይዘን አገር ቤት ስንገባ። ይህ ዜማ በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ  በአሜሪካ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባቀረበው የሙዚቃ  ዝግጅት ላይ በአገር ፍቅርና ናፍቆት ለሚሰቃየው አገር ወዳድ  እጅ ለእጅ አያይዞ  ያላቀሰበት ዘፈን ነበር።እኛም ዛሬ በፎቶው እንደሚታየው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን  የሚያገለግለውን የእሳትን መለያ ካኔተራ በመልበስ በእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ  ምሽት ላይ በኖርዌ የምንገኝ  ስደተኞች ከአጭር ድራማ በኋላ የዘመርነው መዝሙር ነው።                                                                           ልቀጥል በዝግጅቱ ላይ የተገኘውን ህዝብ ስመለከት አንድ ነገርአሰብኩኝ፤ደግሞም ተመኘሁኝ፤ማሰብም መመኘትም መብቴ  ቢሆንም ምናልባት እኔ  እንዳሰብኩት  ይህንን ጽሁፍ የሚያንብ ሰው ሃሳቤን ይጋራል ብዬ ልገምት፤ሀሳቤ ምን መሰላችሁ፤በፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ የነበረው ዕድምተኛ በሙሉ  ለሁሉም አገራዊ ጥሪ ህብረቱ፤አንድነቱ፦ትብብሩና በጋራ መስራቱ ሁል ጊዜ እንዳሁኑ ቢሆን፤ልክ የድራማው መጨረሻ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝሙሩን በአንድነት ከልብ ከስሜት እንደዘመርን ፤በእምነታችንና በዘራችን ሊለየን ፤የንግግር፦የመጻፍና በሰላም የመኖር መብታችንን ያሳጣንን፤አገራችንን ለባዕድ እየሰጠ ገበሬውን መሬትና አገር አልባ አድርጎ በአገሩ ላይ ስደተኛ እንዲሆን የሚያደርገውን  ጨቋኝና ከፋፋይ የሆነውን የወያኔ መንግስት በጋራ ለማጥፋት፤ህብረታችን እንዲቀጥል፤የእርስ በርስ  መናቆራችንን በመተው ላገርና ለወገን የሚበጀውን ቅድሚያ  በመስጠት በህብረት ብንቀሳቀስ; ብዬ ተመኘሁ። ደግሞ ቀደም ብዬ  ተናግሬአለው  መመኘት መብቴ ነው ብዬ ።                                                                                                                                                     እስኪ ይታያችሁ እኔ  የተመኘሁት ከመጀመሪያው ቢሆን ኖሮ አይደለም 21 ዓመት አንድም ዓመት አይቆዩም ነበር።እረ  የምን አንድ ዓመት አመጣህ ያኔ ገና ሰባት እንዳሉ   በአንድ ቦምብ እምሽክ ነበር እንዳለው ይሆን ነበር።ትሉኝ ይሆናል ፤ግን ነበርን ትተን ላለፈው ክረምት  ቤት አይሰራም ለሚመጣው  ይታሰባል የሚለውን አገርኛ አባባል ተቀብልን ወደፊት በሉለት ይለይለት የሚለውን የጥላሁንን ዘፈን ለአንባቢዎቼ ስመርጥላችሁ፤ለቃሉ ታማኝ በመሆን ከእሳትና ከውሃ እሳትን በመምረጥ የእናት አገሩና የህዝቡ መጠቃት ዘወትር የሚያገበግበው እንደ  ሌሎቹ አርቲስት ነን ባዮች ምሳሌ ከርሳሙ ሰለሞን ተካልኝ እና  መሰሎቹ ለጥቅም ሳይገዛ ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠር ጀምሮ  ቃል የእምነት እዳ እንጂ የእናት አባት አይደለም በማለት ብዙ መከራና ችግር  በመቀበል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለእኛም ከኢትዮጵያ ውጭ ላለነው ምሳሌ  በመሆን እንድንሰባሰብና በደስታና በፍቅር እንድንገናኝ ላደረገው፤አንድዬና ብርቅዬ ልጃችን፤ወንድማችንና ፡አባታችን  ለሆነው የሰባዊ መብት ተሟጋች ፤አክቲቪስትና  አርቲስት ታማኝ በየን እረጅም እድሜና ጤና  ለእሱና ለመላው ቤተሰብ  እየተመኘው ጥቁር ሰው የሚለውን ዘፈን በታማኝ ስም አዳምጡልኝ በማለት ነው።                                                              በዕለቱ ስለ ነበረው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ትንሽ ነገር ልበል፤ፕሮግራሙ የሚፈለግበትን  አላማ አሟልቷል።  ማለትም የሚፈለገው ገንዘብ ማግኘት ነው አዎ  ገንዘቡ ተገኝቷል ።ቅድመ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነበር ። አብዛኛው ሰው በተለያየ ኮሚቴ  ውስጥ በመግባት ያደረገው እርብርብ  በትንሹ የሚገመት አይደለም።በአስራ አምስት ቀን  እንዳይሞት ለምግብ ብቻ  የሚሰጠውን  900 ክሮነር በመቆጠብ ከተለያዩ ቦታ ለትራንስፖርት ወጪ በማድረግ  ለማረፊያ  እንኳን ሳይጨነቁ ባላቸው ጉልበት ለኢሳት ያላቸውን ፍቅር  በተለያዩ  ስራዎች ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በካምፕ ያሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች በጣም ሊመሰገኑ ይገባል።                                                                                                                                                               የውያኔ ሰራዊት  ኢትዮጵያን  ከተቆጣጠረበት ጊዜ  አንስቶ  እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይና  እንግልት  የሚያሳይ ተመልካችን  በእንባ  ያራጨና  ወደ ኋላ  በትዝታ ወስዶ  ለካ  እንደዚህም ተደርጓል ብሎ ከልብ ያሳዘነ  በስደተኛው ተጽፎ የተዘጋጀ አጭር ተውኔት  ለዕይታ  ቀርቧል ።ተውኔቱን  የጸፉትም  ለምለም  ሀይሌ እና ያሬድ ኤሊያስ  ሲሆኑ  እንዳለ ጌታነህ ተውኔቱ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል ።በድራማው ላይ ሳላነሳ  ያማላልፋቸው እናት በመሆን  የተጫወቱት  ወይዘሮ መዓዛሽ መኮንን  እና ልጅ በመሆን የታጫወተው ያሬድ በትክክል ባህሪው  የሚፈልገውን  ካራክተር ከልብ በመጫወታቸው ሰውን በእንባ  አራጭተውታል። 
ከድራማው በኋላ ከታማኝ በየነ ጋር
                                                                                                                                                               ላልፈው  ወይም ልተወው የማልችለው ችግር ትንሽ ልበል ፤በርግጥ በትንሽ ወጪ ብዙ ብር  ማግኘት ቢሆንም አላማው ምንም አይሰራም ያልነው ሃሳብ ችግር ሲሆን አይተናል ምሳሌ  ፕሮግራምን በተመለከት፦የቅደም ተከተል ችግር ነበር።የድምጽም መሳሪያን በተመለከት፤ ዋናውና ሰው በአንክሮ ሊከታተለው የሚገባ የታማኝ ዝግጅትን በድምጽ ምክንያት ለመከታተል  ሲቸገርና ታማኝም በትክክሉባለማቅረቡ ሲበሳጭ በቅርብ ሁሉም ያየው ነው።ስራ ሲሰራ  ስተት  መፈጠሩ አይቀርም ጥሩ ትምህርት ሆኖ ያልፋል ግን ይህንን የተፈጠረውን ትንሽ ስህተት ቀድመን ስለተነጋገርን ቢያንስ ብንሰማማ ኖሮ  ችግሩ ባልመጣ ነበር ፤እንደዚ ዓይነት ብዙ ሰው የሚያሳትፍ ዝግጅት ሲኖር ቢያንስ ሙያው የሚመለከተውን ስራ ለሙያው ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ከተቻለ  ሀላፊነቱን መስጠት ካልተቻለ  ማማከር ተገቢ ነው ብዬ  አምናለው።ሃሳቡን እናንሳው እንጂ ዋናው ነገር በኖርዌ የምንገኝን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ  ጥሩ ምሽት ሆኖ አልፏል።ላሁኑ ላብቃ  ሰላም ያገናኘን ደህና  ሰንብቱልኝ።ዝግጅቱን የኢሳት ቴሌቪዥን በቅኝት ፕሮግራሙ ላይ ያቀረበውን እየጋበዝኩኝ እሰናበታለው።ጽሁፉን በተመለከተ አስተያየት መስጠት ያለኝን ደካማ ጎን ማጎልበቻ  ስለሆነ እባካችሁ ። 

No comments:

Post a Comment