"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 10 September 2012

በአቶ መለስ ሞት ተጋርዶ የነበረው የኃይልዬ ታደሰ አዲሱ አልበም አድማጭ እያገኘ ነው


በአቶ መለስ ሞት ተጋርዶ የነበረው የኃይልዬ ታደሰ አዲሱ አልበም አድማጭ እያገኘ ነው


inShare
Share
(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በተነገረበት እለት አዲስ የሙዚቃ አልበሙን አውጥቶ የነበረው ድምጻዊው ኃይልዬ ታደሰ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ የትኛውም ሙዚቃ ቤት ሙዚቃ እንዳይከፍት፣ የናይት ክለቦችም ሙዚቃ ከፈታችሁ ተበለው በመታሸጋቸው፣ እንዲሁም የመንግስት ራድዮና ቴሌቭዥኖች የሃዘን ዋሽንት ሙዚቃና ክላሲካል ዘፈኖችን በማስደመጣቸው አልበሙን ገዝቶ የሚያደምጥ ጠፍቶ ነበር። አልበሙም ከሽያጭ በሃዘኑ ምክንያት ተጋርዶ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ አድማጭ ጆሮ መግባት መጀመሩን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከኢትዮጵያ ዘግበዋል።
ቴዲ አፍሮን ጨምሮ ታላላቅ የሃገራችን ገጣሚያን እና የዜማ ባለሙያዎች የተካፈሉበት የሃይልዬ አዲሱ አልበም የአዲሱን ዓመት በማስመልከት በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እንዳገኘለትም ዘጋቢዎቻችን ጨምረው ገልጸዋል። በተለያዩ ቦታዎችም አልበሙ እየተደመጠለት ይገኛል። ከአዲሱ አልበም ውስጥ አንዱን ዘፈን እንጋብዛችሁ።
ይህ የኃይልዬ አልበም 3ኛው ነው።
 s


No comments:

Post a Comment