"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 13 September 2012

ድምጻዊት አቦነሽ አድነው ዘፈን አቁማ ዘማሪ መሆኗን አስታወቀች




(ዘ-ሐበሻ) “ባላገሩ” በተሰኘው አልበሟ የምናውቃት ድምጻዊት አቦነሽ አድነው ሙዚቃ ማቆሟን እና ወደ መንፈሳዊ ዘማሪነት መግባቷን ይፋ አደረገች። ድምጻዊቷ ካሁን በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና መሠረት እግዚአብሄርን አመሰግነዋለውም ብላለች።
“ይህንን ውሳኔ ለመወሰን 5 ዓመታት ያህል ፈጅቶብኛል” ያለችው ድምጻዊቷ “ማታ ማታ ዘፍኜ እቤቴ ስገባ ደስተኛ አልነበርኩም፤ የ እግዚአብሄርን ቃል ሁልጊዜ አስብ ነበር” ብላለች። ድምጻዊቷ በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ቆማ እንደገለጸችው ደግሞ “ማታ ማታ ስዘፍን አድሬ ጠዋት ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ባልደርስም ቢያንስ ቃሉን ሰምቼ እሄድ ነበር።” ካለች በኋላ “በአዲሱ ዓመት አሮጌው ማንነቴን ቀይሮ እዚህ እንድገኝ እግዚአብሔር ስላደረገኝ አመሰግነዋለሁ” በማለት “አበረታኝ ጌታዬ የሚለውን መዝሙር ዘምራለች።
የቀድሞዋን ድምጻዊት አቦነሽ አድነውን ምስክርነት የሚያሳየውን ቪድዮ ይመልከቱ፦
በነገራችን ላይ አቦነሽ አድነው ጁላይ መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያን ሄሪቴጅ 2ኛ ዓመት በዓል ላይ በዋሽንግተን ዲሲ በትልቅ መድረክ የዘፈነችው የመጨረሻዋ የሙዚቃዋ መጨረሻ መድረክ ሊባል ይችላል።


No comments:

Post a Comment