"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Thursday, 20 September 2012
የቴዲ አፍሮ የሰርግ ቀን ደረሰ
ጥቁር ሰው አልበምን በሽያጭ ላይ ከዋለ በኋላ የትዳር አጋሩን በሪሊዝ ፓርቲ አመክኝቶ ለህዝብ ይፋ ያወጣውን ድብቅ ሚስጥር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ጋብቻ እንዲቀየር በማድረግ ለሚቀጥለው ሳምንት ሃሙስ ሴብቴምበር እ ኤ አ 9/ 27/2012 በሂልተን ሆቴል የሰርጉን ስነ ስርአት እንደሚፈጽም ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ዘገባ ያመለክታል ።ከአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ስርአት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለሰርጉ ስነ ስርአት የሚያስፈልገውን እቃዎች ሁሉ በሰሜን አሜሪካ ግዢውን አጠናቆ የሄደው ቴዲ አፍሮ ባለፈው ሳምንት ቢሆንም በዚያው ሳምንት በሂልተን ሆቴል የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ለረጂም ጊዜ የተያዘ ፕሮግራም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በመንግስት ሃይሎች የመለስን መሞት በሃዘን ማሳለፍ አለባችሁ ብለው አገሪቱን አፍነው በመያዛቸው ፕሮግራሙ ሊተላለፍ እንደቻለ ተገልጾአል በዚህም ሳቢያ ለሚቀጥለው ሳምንት ሃሙስ በሚደረገው የሰርግ ስነ ስአርት ላይ አሁንም ችግር እንዳይፈጥሩ ህዝቡ ስጋቱን አሁንም ገልጾአል ።በዚህ የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ታላላቅ አርቲስቶች ፣ታላላቅ ሰዎች ባለሃብቶች እና እንዲሁም የቅርብ ወዳጆቹ እና አብሮ አደጎቹ እንደሚገኙ ተጠቁሞአል ።ከሰርጉ ስነ ስርአት በኋላ የተለያዩ ኮንሰርቶችን ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር የሚያደርገው የሙዚቃ ስራ ግን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ነው ።በአቡጊዳ ባንድ እና በቴዲ አፍሮ በኩል መካከል በተነሳ የውስጥ ችግር ወይንም አለመስማማት ጉዳዩ ታፍኖ ቢቀርም አሁንም እልባት ያገኛል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር ።ለዚህም እንደምሳሌ በስዊድን እና ሆላንድ የተሰረዘው ኮንሰርት እማኝነቱን ያሳያል ይላሉ ።ሆኖም የአቡጊዳ ባንድ ለቴዲ አፍሮ የጻፉትን የአቋም መግለጫቸውን ሊቀበለው ስላልቻለ ከአስር አመታት በላይ ያለ ውል ሲሰሩ የነበሩት ባንዶቹ አሁን ግን የቆረጠላቸው ይመስላል ። የቀጣዩን የሙዚቃ ጉዞ አስመልክቶ ሰፋ ያለ ዘገባ ከሰርጉ በኋላ በሚኖረን መረጃ ይዘን እንቀርባለን የባንዶቹንም አጠቃላይ የአቋም መግለጫ ከሚቀጥለው ሳምንት በኋላ ይዘን እንቀርባለን። ማለዳ ታይምስ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment