"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 11 October 2012

ወ/ሮ አዜብ ፈርሃታቸውን ገለጡ ከህዝብ በላይ ነኝ በማለት እራሳቸውን ሲያቆለጳጵሱ ተሰምተዋል


አዜብ መስፍን ፈርተዋል!!
“የተሰጠኝ ቤት ለደኅንነቴ አያመችም፣ ለፕሮቶኮሌን አይመጥንም”


መለስ የሚያቆላምጧቸው ወ/ሮ አዜብ ለመቀማጠልና ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤተመንግሥቱን “አልለቅም” ማለታቸውን የጎልጉል ምንጮች አረጋገጡ። የአዲስ አበባ መረጃ አቀባዮቻችን እንደሚሉት ከሆነ የቀድሞዋ “ቀዳማዊት እመቤት” ሶስት ቪላዎች እንዲያማርጡ ቢለመኑም አሻፈረኝ በማለት ባነሱት የደኅንነት ጥያቄ ገፍተውበታል።
ከህወሓት መከፈል በኋላ አቶ መለስ ህወሓትን በመዳፋቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ገንነው የወጡት ወ/ሮ አዜብ የተባረሩት፣ የተባረሩት ደጋፊዎችና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ኢህአዴግ ውስጥ ጥርስ የነከሱባቸው ይበረክታሉ። የሥልጣን እርከን በመጣስ ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በተጨማሪ ለሚያካሂዱት የንግድ ስራ ሲሉ መመሪያ በመስጠት፣ የማይፈልጉትንና አልታዘዝ የሚሉዋቸውን ባለሥልጣናት በማስገደድ፣ በተለይም ተወላጅ ሳይሆኑ በህወሓት አመራሮች ላይ ሲያሳዩ የነበረው የበላይነት ዛሬ አደጋ እንዳመጣባቸው የዜናው ምንጮች ይናገራሉ።

የመለስን በጠና መታመምና ይፋ ያልተገለጸ ሞት ተከትሎ፣ ከዚያም “የውድ ባለቤታቸው” ህልፈት ይፋ በሆነ ማግስት፣ ብዙ የተወራባቸው ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸውን “ሲሰናበቱ” የባለቤታቸውን የፖለቲካ አቅጣጫ “ውርስ” የማይበረዝ ከሆነ እንደሚገፉበት የተጠቆሙበትን ቃል አቶ ሃይለማርያም በቀጥታ ቃል በቃል መድገማቸው ወ/ሮ አዜብን “አሁንም የሚደፍር የለም” የሚል አስተያየት እንዲሰነዘር አድርጎ ነበር።

በወቅቱ አንደ አንድ ጉሊት ቸርቻሪ፣ ችግር እንደ ገረፋት ቅጠል ሻጭ እናት “ልጆቼን በማሳደግ እፈተናለሁ” በማለት ሲናገሩ መሳለቂያ የሆኑት ወ/ሮ አዜብ ኢህአዴግ ውስጥ እየጋመ ያለው የውስጥ ለውስጥ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫ “ደመራው” ወደ የትኛው ወገን እንዳዘነበለ ባልታወቀበት ሁኔታ ተወጥረው ተይዘዋል።


ለጠ/ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቅርበት ያላቸው ክፍሎች እንደሚሉት ወ/ሮ አዜብ የኃይል ሚዛኑን በበላይነት ከያዙት ክፍሎች ጋር ቢመደቡም በእርሳቸው ጎትጓችነት፣ በባለሃብቶች ጠቋሚነት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር ከኦህዴድ ግምገማ ተርፈው ለወዳጃቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መላካቸው ታውቋል።

በአቶ ሙክታር ፊርማ ቤተ መንግስት ለቀው እንዲወጡ አንድ ሳምንት የተሰጣቸው ወ/ሮ አዜብ፤ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ለተሰናባች ጠ/ሚኒስትር ባስገነቡት የሚኒሊክ ቤተ መንግስት ውስጥ በሚገኝ ቪላ ለመኖር ያቀረቡት ጥያቄ ወደ ጎን ተብሏል። የጎልጉል ዘጋቢ ባገኘው መረጃ መሰረት ወ/ሮ አዜብ ለጊዜው አድራሻው በግልጽ ያልታወቀ ትልቅ ግቢ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሌላ ምንጭ ደግሞ ወ/ሮ አዜብ የሚከራከሩት በታችኛው ቤተ መንግስት (ኢዮቤልዩ) ከፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጎን ተጎራብተው ለመኖር እንደሆነ ጠቁመዋል። ሁሉም መረጃዎች እንደሚያስረዱት ወ/ሮ አዜብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አለማግኘቱን ነው።

የቀረቡላቸውን ሶስት ቪላዎች “ለደህንነቴ አይመቹም፤ ለፕሮቶኮሌ አይመጥኑም፤ ሰው ይበዛባቸዋል” በሚል ምክንያት ባለመቀበል ወ/ሮ አዜብ ቤተ መንግስቱን የሙጥኝ በማለታቸው ምክንያት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማለዳ ብስራተ ገብርኤል ከሚገኘው ቤታቸው ሲወጡ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ተመልሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ በተፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ነዋሪዎች መጨናነቃቸውን ሰንደቅ ጽፏል። እርሳቸው ባይፈልጉትም ለደህንነታቸው ሲባል በሚደረገው ጥብቅ ጥበቃ የአካባቢው ሰዎች እንደ ልብ መውጣት መግባት ተስኗቸዋል። ጋዜጣው ወ/ሮ አዜብ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ማስነበቡ በአቶ በረከትና በወ/ሮዋ መካከል የተፈጠረ ችግር ሊኖር እንደሚችል አመላካች እንደሚሆን፣ አሊያም አቶ በረከት ተቀናቃኞቻቸውን ለማግባባት ወ/ሮ አዜብን የመክዳት እርምጃቸውን ለማሳየት የተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ተሰንዝሯል።

ወ/ሮ አዜብ በሚኒስትሮች ደረጃ የሚሰጥ ቤት ቀርቦላቸው እንዲያማርጡ መጠየቃቸውን የጠቆሙት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች አቶ ሃይለማርያምን “ልፍስፍስ” ይሏቸዋል። አያይዘውም ክብራቸውን ማስጠበቅና ስልጣናቸውን ባግባቡ መገልገል አለመቻላቸው ወደፊት ሊጎዳቸው እንደሚችል በመጠቆም በተለይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጠንካራ የተሐድሶ ዕርምጃ እንዲወስዱ የሚቀርቡላቸውን መጠነሰፊ ጥያቄዎች የማስፈጸማቸውን ጉዳይ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር “ካንደበቷ ትንታግ ይወጣል” በሚል አድናቆትን የሚቸሯቸው ወ/ሮ አዜብ ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄ የተለያየ አስተያየት ቢያስከትልም እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ማረፊያቸው እንደሚታወቅ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል። አያይዘውም ከሜጋ ማተሚያ ድርጅት ስልጣናቸው ሲነሱ አኩርፈው አረብ አገር ሄደው በአንድ ታዋቂ ባለሃብት ሽምግልና ተመልሰው ሃላፊነታቸውን ተረክበው የነበሩት ወ/ሮ አዜብ ጉሸማው ከበዛባቸው በዚሁ በቀድሞው ሽማግሌያቸው አማካይነት ሃብት ተቆርሶላቸው ህወሓትን “ደህና ሰንብት” ሊሉት እንደሚችሉም ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ወ/ሮ አዜብ በትውልድ ቀዬያቸው ነዋሪዎችና አባቶች ክፉኛ የሚወነጀሉና የተወለዱበትን የአማራ ክልል የከዱ እንደሆኑ በመግለጽ የሚቃወሟቸው ጥቂት አይደሉም። የተወለዱበትና እትብታቸው የተቀበረበት ምድር ተቆርሶ ሲወሰድ ዝምታንየመረጡ የዘመኑ “ዮዲት ጉዲት” የሚሉዋቸውም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በሁሉም ጎን የተወጠሩትና “ስኳር” ይወዳሉ የሚባሉት ወ/ሮ አዜብ ያላቸው አማራጭ አቶ መለስ ከተወዳጇቸው የእስያ አገሮች ወይም ቀደም ሲል ወዳኮረፉበት አረብ አገር የመዛወራቸው ጉዳይ ሚዛን የደፋ ሆኗል። ወዳጆቻቸው ለ“ለባለ ራዕዩ መሪ” ሲሉ አምባሳደር አድርገው ከሾሙዋቸው የሁሉም ትንቢት ፉርሽ ይሆናል። ሁሉም እንደሚስማሙበት ግን ወ/ሮ አዜብ አገር ቤት አይመቻቸውም። እርሳቸውም አውቀውታል – ከቤተ መንግስት ውጪ!!


No comments:

Post a Comment