"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 7 November 2012

ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር የጎደለው የወያኔ ሰላይ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ላወጣው ጽሁፍ ምላሽ ቢሆን




ወያኔ በሰራው በውሸት የታሰሩ ማለት እነዚ ናቸው 
ከእንዳለ ጌታነህ  ኖርዌ  ኦስሎ 07 11 2012                                                                                                          ባንድ ወቅት ባንድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ይመስለኛል ኧንድ ታዋቂ ዘፋኝ ከአንድ ጋዜጠኛ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት እና በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚተላለፍ የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ አንድ ጥያቄ ያቀርብለታል። ጥያቄው አርቲስቱ በጊዜው ጥሩ ዝና  ላይ የነበረበት ወቅት  ነው። ባንድ ኮንሰርት[የሙዚቃ  ዝገጅት]ላይ በዙ ተመልካች ተገኝቶ ነበር።አንዳንድ አድናቂ ነን ባዮች ፈርምልን እያሉ ትንሽ ግርግር ይፈጥራሉ ይባስ ብለው እንስት እህቶች ጡታችን ላይ ፈርምልን  በማለት አስቸግረው ነበር እሱም ጡት ላይ ፈረመ  ተብሎ ተወራ ። ጋዜጠኛው ፊት ለፊት ይህንን ጥያቄ  ይጠይቀዋል ።በእውነት እንደሰማነው የሚፈረምበት ጠፍቶ ጡት ላይ ፈረምክ?  ይታያችሁ ፕሮግራሙ በቀጥታ ይተላለፋል ፧ዘፋኙ ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው?በእውነት ይህ ጥያቄ  እዚህ የሚጠየቅ አይደለም።  በዙ ትላልቅ ስራዎችን  የሰሩ አንቱ የተባሉ ሰዎች  ባሉበት ጥያቄው መነሳቱ አሳፋሪ ነው ።ግን የተባለውን ነገር ቃሉን አልደግመውም  ላለማድረጌ  ኢትዮጵያዊ ሆኜ መፈጠሬ ይበቃል።ኢትዮጵያዊ ማለት ፈሪያ እግዛብሄር ያለው፤ታላላቆቹን የሚያከብር  በይሉኝታ እራሱን የሚጎዳ ወዘተ.....ህዝብ ነው፤እኔ ደግሞ ከዚህ ህዝብ መገኘቴ ባህሌን ወግ ማዕረጌን እና ክብሬን  እንድጠብቅ አስተምሮኛል አለና በጥሩ ኢትዮጵያዊ በሆነ ስነ ምግባር መለሰለት ።አዎ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደዚ ነን አንድ ሰው ሲያዛጋ እንኳን አፉን እሰው ፊት አይከፍትም ዘወር ወይም በእጁ ከለል  አድርጎ ነው። አሁን ግን ምን አይነት ጊዜ ላይ እንደደረስን እንጃ ?ዝም ብለው እንደፈለጉ አፋቸውን የሚከፍቱ ክፍት አፎች በዝተዋል፤[ለቃሉ አጠቃቀም ይቅርታ አማራጭ አጥቼ ነው]ውሻ በበላበት ይጮሀል፤እንዲሉ የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ ቀርተው  ወያኔ የሚወረውርላቸው ፍርፋሪ እንዳይቋረጥ ሲሉ ዝም ብለው ባገኙበት የሚረግጡ እንደ እብድ ውሻ ያገኙትን ሁሉ የሚለክፉ አድር ባዮች  በዝተዋል።መድሀኒታቸውን ቶሎ መስጠት ዋናው መፍትሄ ነው። ምን ለማለት እንደፈለኩኝ ወይም ዋናው ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ አንድ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ ዳዊት ነኝ በማለት  አልሰለጥን ያለው ዲያስፖራ ብሎ  ሪፖርተር በተባለው ጋዜጣ ላይ ያወጣውን ጽሁፍ ተመልክቼ ትንሽ ለማለት ነው።አበው ሲተርቱ ማንነትህን እንድነግርህ ከፈለክ ጓዋደኛህን ነገረኝ ይላሉ፤ ለኔ በአሁኑ ሰዓት ለአቶ ዳዊት ተበየው ጓዋደኛው አማረ አረጋዊ ነው ። እንዴት? አትሉም፡  አላችሁ?ያወጣው ጽሁፍ ብዙ በውሸት ያለበት ሆኖ ሳለ እንኳዋን ባደገችው አገር በኖርዌ ይቅርና  ባላደጉት አገር የማይደረግ ውሸት ህዝብ በሚያነበው  ሚዲያ  ላይ ማውጣት  አንድም የልብ ጉዋደኛ ወይም የትግል አጋር ነው።                                                                                                                                            አቶ ዳዊት ካሉት ላይ ልግለጽ                                                                                                                           ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የግል ባንኮች መካከል ስሙ ከሚጠቀስ አንድ ታዋቂ ባንክ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በቂ የሚባል ደመወዝ እየተከፈለውና መኪና ተመድቦለት፣ እንዲሁም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች እያገኘ መልካም የሚባል ኑሮ የሚኖር ሰው፣ በሥራ  ምክንያትወደኖርዌይአቅንቶ እዚያውስለመቅረቱዳዊትአውግቶናል፡፡                                                                                                                                      የሰው ልጅ ኑሮን ኖረ ተብሎ  የሚገመተው  መኪና ጥሩ ቤት  ጥሩ ደሞዝ  ስለሚከፈለው  ነው እንዴ?ይህ ከተሟላለት ፈላጎቱ አበቃ  ማለት ነው?እሱ ጥሩ ቤት እየተኛ ጎዳና ላይ ለሚተኛው ወንድሙ ማን ይጩህለት፤እሱ ጥሩ ደሞዝ ሲከፈለው ሌላው  ወንድሙ ግን ከጎኑ በአስተዳደር በደል ሲደርስበት፤ በዘር ምክንያት ከስራ ሲባረር፤ቤተሰቡ ለችግርና  ለመከራ ሲዳረግ ፤እኔ  ምን አገባኝ በሎ አርፎ  መቀመጥ አለበት እንዴ ? በርግጥ ህሊና ለሌላቸው እንደ ጋሪ ፈረስ ፊት ለፊት የራሳቸውን ኑሮ  ብቻ ለሚያዩ  ወያኔና ሆድ አደሮች ልፋታቸው  ድካማቸው በአብዛኛው ምስኪን ህዝብ ላይ ተደላቆ መኖር ስለሆነ ተልክስክሰው ሰውን በሀሰት እየወነጀሉ፡ማሳሰር፤ማስገረፍ፤ማስገደል እና ካገር እንዲሰደዱ ፦አድርገው በሀገሪቱ ላይ ህዝቡ እርስ በራሱ እንዳይተማመን እንዲፈራራ  በዘር እንዲከፋፈል ከዛም.......ስለሆነ የነሱ መለኪያ ገንዘብ፦ ቤትና ጥር ሰራ ነው።ሰለዚ አቶ ዳዊት የወያኔ ፍርፋሪ ለቃሚናቸው።                                                                                                                                                   ጋዜጣው እራሱ የአቶ ዳዊትን ንግግር እንዴት እንደተመለከተው አስተውሉ ።የሚገርም ጨዋታ ቀጥሏል።ጨዋታ የሚለው ቃል ይሰመረበት።ጨዋታ ማለት  ቀለደ፧አፌዘ፧አሳቀ፦አሾፈ ማለት ሲሆን  ዳዊት የሚናገረው የዲያስፖራ ውሎ  እንደ ጋዜጠኛው አገላለጽ  በቀልድ ላይ የተመሰረት ውሸትማለቱ ነው።  ይኸኛው አገላለጽ ደሞ የሚገርም ነው። ሙሉ በሙሉ የወያኔ ባለስልጣኖች ኖርዌ መጥተው  ስልጣን ይዘው ከሆነ ነው እንጂ መቼም አሁን ባለው መንግስት ሊደረግ ቀርት የማይታሰብ አባባል፤               ከእነሱ ዓላማ በተፃራሪ ወይም መሀል ሰፋሪ የሆኑትን በመሉ በሐሰት በመወንጀል ያስገርፋሉ፣ ያሳስራሉ፣ እንዲባረሩ ያደርጋሉ ይላል፡፡ ግርፋት እና  እስር በኖርዌ አገር፤ይገርማል እንጂ ምን ይባላል።ፍርድ ቤቱ በውሸት ምስክር ይፈረዳል ሰዎችም በውሸት  ይመሰክራሉ።አንድ ምሳሌ;ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል፤ወያኔ የፈለገውን አሸባሪ በማለት ተለጣፊ ስም በመስጠት ያስራል፧በውሸት ያስመሰክራል፤ለይስሙላ  ባቆመው ፍርድ ቤት ሲጠሩት ለአፍ የሚከብድ 20 15 ዓመት  እድሜ ልክ  በመበየን ስንቱን በጭለማ ቤት እንዳሰቃየውና ስንቱ እየተሰቃየ እንዳለ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት  ወህኒ ቤቶች ይመስክሩ።እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ  አቶ ዳዊት ተብዬው ግን የተላከበትን የስለላ ስራውን  ባግባቡ ባለመወጣቱ ከግምገማ ለማምለጥ የዘባረቀው ውሸት  ነው።ውሸቱ አላለቀም    ልቀጥል፤                                                                                                                                                                                                                                                                                                                  በየቀኑ ስለ ኢትዮጵያ መንግሥት የራሳቸውን አዳዲስ መረጃዎች ይፈጥራሉ ፣ ለአገሪቱ መንግሥት ያቀብላሉ፣ በአካባቢው    ለሚኖሩይነግራሉ ያስነግራሉይላል።  ሌላየሚጋጭጽሁፍ ደምልጨምር                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                        ብዙ ጊዜ የሚያወሩት ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጸሙ ስለሚባሉ ግፎችና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ነው፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ የሚያቀብሉዋቸው ታማኝ ምንጮች እንዳሉዋቸው ነው።ከላይ የራሳቸውን መረጃ ይፈጥራሉ ይላል፧እንደገና ደገሞ  መረጃ የሚያቀብሉዋቸው ታማኝ ምንጮች እንዳሉዋቸው ነው፤ይላል ይህ ሰው በእውነት ጤነኛ  ነው ወይስ አለቆቹን ያሳመነ መሰሎት ዝም ብሎ እየተተረተረ ነው ?እንግዲ እዚ ላይ ነው ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ የተሳነውን ዳዊትን የምናገኘው። በተከፈተ አፍ ባዶ ጭንቅላት ይታያል፤በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ፧ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባባትም ።እዩት ምሳሌያዊ አባባላችን እንኳን  ምን ያህል እንደሚያስተምሩ።ላጠቃል   ለመልስ ያህል ያለኝን ወርውሬአለው አቶ ዳዊት ያንን ጽሁፍ የጻፈው ካለቸው ወያኔያዊ ፍቅር ተነስተው  ነው እንጂ ከእውነታው አይደለም ግን ለአቶ ዳዊት የ3 000 ሺ ብር ደሞዝ እያገኙ የ30 ሚሊዮን ብር ህንጻ   የገነቡትና  የቤት ኪራዩን በውጭ አገር ባንክ የሚያስቅምጡት አጠገባቸው እያሉላቸው ?በአሸባሪ ስም ስንቱን እስርቤት ያጎሩት ወያኔዎች አጠገባቸው ተቀምጠው ?ምን አይነት ዕድገት ምን አይነት ሹምት አስጎምጅቷቸው እንደዚ መቀደዳቸው በእውነት  እግዚያብሄርም አይወደውም፧በሆድዎ ማሰብን ትተው  ወደ ህሊናዎ ይምለሱ።ጭንቅላትዎ የተሰራው አንገትዎ  ላይ እንዲቀመጥ ሳይሆን እንዲያስቡበት ነው።                                                                                                                                                      የወያኔ መጥፊያው ህብረትና  አንድነት ነው። ስለዚ አንድ እንሁን እንተባበር እንፋቀር ፤ እናቸንፋለን                                     እንዳለ  ጌታነህ ከኖርዌ

No comments:

Post a Comment