ጸጋዬ ገብረ መድህን (1928-1998) ባዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀኃሥ ትምህርት ቤት ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952 እንደ ውጡ በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ ፍራንሴዝ ተከታትለዋል። ከ1954 እስከ 1964 የቤሄራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት አገለግለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።
ሆኖም በ1960ዎቹ ደርግ አብዛኛውን የቴአትር ስራዎቻቸውን ሲያግድ እሳቸውንም ለማሰር በቅቷል።
ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ በርካታ ግጥሞችን፥ የቴአትር ሰራዎችን የተለያዩ መጣጥፎችንና ዘፈኖችን አበርክታዋል። ጸጋዬ በ1990 ለጉበት በሽታ ሕክምና በመሻት ወደ ማንሃታን በሄዱበት አርፈዋል። በአዲስ አበባ በስላሴ ቤተክርቲያን ተቀብረዋል። ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን::
እንደ፡ አዉሮፓ፡ አቆጣጠር፡ በ 2002 ዓ.ም. የብላቴን ሎሬት ጸጋዬ፡ ገብረ መድህን፡ ግጥም፡ ("Proud to be African") በአዲስ፡ በተመሰረተዉ፡ የአፍሪካ፡ አንድነት፡ መህበር፡ በሕዝብ፥ መዝሙርነት፡ ተመርጧል።
... ...ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን ቀዌሳ እነሆ በሞት ከተለየን ድፍን አስር አመታት ተቆጠሩ። ቦዳ
(አምቦ) የተጀመረ ሕይወት ማንሀተን (ኒው ዮርክ) ተቋጨ። ግብአተ መሬቱም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
(አዲስ አበባ) ተፈጸመ። ይቺ ፅሁፍ አራተኛ ሙት አመቱን (February 25, 2006) በማሰብ የግጥም ስራዎቹን
በግርድፉም ቢሆን በማውሳት እነሆ የፀጋዬ ዝክር ትላለችፀጋዬ ከማረፉ አራት አመታት ቀደም ብሎም በዶ/ር ኄራን ሠረቀብርሃን**** አስተባባሪነት በዋሽንግተን ዲሲ የፀጋዬ
ግጥሞች በሲዲ ተቀርፀው ተመርቀዋል።
1የእረፍት ዋዜማ
የስንብት ዝግጅት ይሆን። ትንቢት አስቀድሞ ለነገር እንዲሉ።
ፀጋዬ ከማረፉ አስራ አምስት ቀን አስቀድሞ የ«አንድምታ» ባልደረባ አናግሮት ነበር። እስኪ ሁለቱን የሎሬት
ፀጋዬን ጥኡም ወጎች ላስቀድም።
በአፄ ምኒልክ ዘመን እንግሊዞች ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ዝሆን ያድኑ ነበርና አንዴ አደናቸውን ተከትለው ሲገስግሱ
ከኢትዮጵያ ኬላ ደርሰው ኖሮ ድንበር አላሳልፍ ካሉ የኬላ ጠባቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ይደረግና ከአዳኞቹ
አንዱ በዚሁ ምክንያት ይሞታል። እንግሊዞችም አቤቱታ ያሰሙና ነገሩ አባ መላ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ)
ዘንድ ይደርሳል። እንግሊዞቹ ያለአግባብ ሰው እንደተገደለባቸው አመልክተው የደም ካሳ እንዲሆናቸው
ከኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ነበር የጠየቁት። አባ መላ ነገሩን ያጠኑና ችግር እንደሌለው
ለእንግሊዞቹ ይገልጻሉ። ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት ግን ይኸ ህግ እናንተ ሃገርም እንደሚሰራበት ማየት ስለምንሻ
በሰነድ መልክ ረቂቁ ካለ እስቲ እንየው። እውነት የእንግሊዝ ሰው የዌልስን ሰው ቢገድል እንግሊዝ ከመሬቷ
ለዌልስ የምትሰጥ ከሆነ እኛም እንሰጣለን። እሱም የሚሆነው ለተገደለብን የኬላ ጠባቂ ካሳ የሚሆን ከቱርካና
ሃይቅ አካባቢ መሬት ከተረከብን ይሆናል ብለው መለሷቸው።
ፀጋዬን ጥኡም ወጎች ላስቀድም።
በአፄ ምኒልክ ዘመን እንግሊዞች ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ዝሆን ያድኑ ነበርና አንዴ አደናቸውን ተከትለው ሲገስግሱ
ከኢትዮጵያ ኬላ ደርሰው ኖሮ ድንበር አላሳልፍ ካሉ የኬላ ጠባቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ይደረግና ከአዳኞቹ
አንዱ በዚሁ ምክንያት ይሞታል። እንግሊዞችም አቤቱታ ያሰሙና ነገሩ አባ መላ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ)
ዘንድ ይደርሳል። እንግሊዞቹ ያለአግባብ ሰው እንደተገደለባቸው አመልክተው የደም ካሳ እንዲሆናቸው
ከኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ነበር የጠየቁት። አባ መላ ነገሩን ያጠኑና ችግር እንደሌለው
ለእንግሊዞቹ ይገልጻሉ። ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት ግን ይኸ ህግ እናንተ ሃገርም እንደሚሰራበት ማየት ስለምንሻ
በሰነድ መልክ ረቂቁ ካለ እስቲ እንየው። እውነት የእንግሊዝ ሰው የዌልስን ሰው ቢገድል እንግሊዝ ከመሬቷ
ለዌልስ የምትሰጥ ከሆነ እኛም እንሰጣለን። እሱም የሚሆነው ለተገደለብን የኬላ ጠባቂ ካሳ የሚሆን ከቱርካና
ሃይቅ አካባቢ መሬት ከተረከብን ይሆናል ብለው መለሷቸው።
ሌላው ደግሞ ሎሬት ፀጋዬ ከ«ሕይወት ቢራቢሮ» ግጥሙ መታተም ጋራ ተያይዞ ለአንድምታ ባልደረባ ያወጋው
ነው። መጀመሪያ የግጥሟን ቅንጫቢ ነቢይ መኮንን ከተረከው እነሆ!
*ዶ/ር ኄራን ሠረቀ ብርሃን ከታሪክ ባለሙያነቷ በተጨማሪ ለስነ-ጥበብ ባላት ፍቅር፤ ከስነ ጥበብ ባለሙያዎች
ጋር ባላትም ልባዊና ቤተሰባዊ ትስስር በስፋት ትታወቃለች። ብዙዎች እንደሚመሰክሩላትም “እገዛዋን”
የሚለው ቃል ያንሳል፤ በጎ ፈቃድዋን፣ ጊዜዋን፣ ገንዘቧን፣ እውቀቷን እና ያላትን ቤተሰባዊ ትስስር ተጠቅማ
ሰሎሞን ደሬሳን፤ ገብረ ክርስቶስ ደስታን እና ፀጋዬ ገ/መድሕንን ከ1970ዎቹ ወደኛ ዘመን የስነጥበብ
ቤተሰብነት አሸጋግራልናለች። በአንባቢያን ስም በስነጥበብ አፍቃሪያን ስም ለኄራን እጅ እነሳለሁ። 2
«...ምን አይተሻል ከቄጤማ፣ ምን አይተሻል ከለምለሙ
ቀን አብረሽ አብበሽ ውለሽ፣ ሲመሽ አብረሽ መስለምለሙ?...
አስተምሪኝ ቢራ ቢሮ፣ ሰው ለመባል አለኝታዬ
ቀድሞ የት ነው መነሻዬ
ሲመሽ የት ነው መድረሻዬ...
ሲተረትማ ሲወጋ፣ ከየብልጭታው ውጋጋን
የሰው አራዊት የአእዋፍ፣ ውስብስብ ነገደ-ጉንዳን
ሲነሳ ሲሮጥ ሲደፋ፣ ሲያጋድል ሲያዛባ ሚዛን
በማይመጠን ታላቅ ኃይል፣ በተፈጥሮ ግዙፍ ሥልጣን
ሊፍተለተል ይወለዳል፣ ሳይነቃ ይወድማል ይባላል
ልደቱ ዕድሜና ሞቱ፣ አለማቋረጥ ይጓዛል፤
ይኸ ይሆን አልፋ - ኦሜጋ? ይኸ ይሆን አስቀድሞ ቃል?»
ፀጋዬ እንዲህ አለ።«እሷ ግጥም በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግስቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ ቢራውን እስቲ
አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው» ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል። ትንሽ ትከዝ ብሎም
«መንግስቱ ምን የመሰለ ደማም ቋንቋ የነበረው ሰው ነበር። አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ»።
አፈሩ ይቅለለውና ሎሬት ፀጋዬ የኛን ትውልድ <<ጫት አመንዣኪ>> ትውልድ ነበር የሚለው። እንዲህ እንደነሱ
ዘመን ባይጎሉም ውድድሩም ቢጠናባቸውም አሁንም እኮ አንቱ የተባሉ ወጣት ደራሲያን መንግስቱዎች ወጣት
ገጣሚያን ፀጋዬዎች አሉን። ጊዜው ሲደርስ እንዘክራቸዋለን።
አምቦ አካባቢ ልዩ ስሟ ቦዳ ከኦሮሞና ከአማራ ወገኖቹ የተወለደው ፀጋዬ ገና በልጅነቱ ነበር ሶስቱ ቋንቋዎች
አማርኛ እንግሊዘኛና ኦሮሞኛ የተገሩለት። በኦሮምኛ መፃፍ ብቻ ሳይሆን መግጠምም፤ እንዲሁም በፈረንሳይኛ
ይግባባ እንደነበር የግእዝ ትምህርትም እንደነበረው የሕይወት ታሪኩ ያወሳል።
2
በትምሕርት እየጎለመሰ
ሲሄድም ደራሲነቱን ገጣሚነቱን እንዲያ ሲልም ፀሃፊ-ተውኔትነቱን በዋነኛነት በጎልማሳነት ዘመኑ ደግሞ
ማህበረሰባዊ ሃያሲነት እና የአፍሪካ የሰው ዘር እና የቅብጥ ቋንቋ እና ባህል ጠቢብነትን አክሎበት እስከ እለተ
ህልፈቱ ዘልቋል። በትዳር ሕይወቱም ከወ/ሮ ላቀች ቢተው ጋር ተጋብተው በስድስት ልጆችና የልጅ ልጆች
ተባርኳል። በኩላሊት በሽታ መለከፉ እና አለመዳኑን እንዲያም ሲል በጉብዝናው ወራት ያላሰበውን ስደት
በሕክምና ሳቢያ የአብራኩ ክፋይ ልጆቹ ወዳሉበት አሜሪካ አቅንቶ ቢያሰለስለውም፣ እንደተመኘው ሀገሩ ጦቢያ
በዓይኑ ላይ እንደዋለለች ህመሙ ጠንቶበት በዚያው በስደት ሀገሩ አሸልቧል። የማሳረጊያ ግጥሙም ይህንን
ተስፋ ቢስነትን አመላካች ይሆን።
የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም
እሳትእሳት እሳት « አንድአንድ አንድ ነገርነገር ነገር !»፦፦፦
ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን ከመሞቱ በፊት የጦቢያን ምድር መርገጥ እንደተመኘ ነው አይምሬ ሞት
የቀደመው። በአንድ ወዳጁ አይን እንየው ፀጋዬን ።ጋሽ ፀጋዬን አሜሪካ ሄጄ ደውዬ አጣሁት። ሊታከም ሄዷል
አሉኝ-ለዳያሌሲሱ። ሳላገኘው በመቅረቴ ትልቅ ፀፀት ይሰማኛል። በስልክ እንኳ አግኝቼ አናግሬው ቢሆን፤
ቢያንስ የመጨረሻው ድምፁ ውስጤ ይቀር ነበር። ምናልባት የኔንም ድምፅ ይዞት ይሄድ ነበር። ትንሽ ስንቅ
ቢሆነው። ከጥቂት ወራት በፊት በአንድ የጋራ ወዳጃችን በኩል «እባክህ አንድ ነገር ፍጠርና ጥሩኝ - ላገሬ አፈር
አብቁኝ» የሚል መልእክት ሲልክብኝ በዕንባዬ ነው የሰማሁት። በየከርሞ ሰው ቴያትሩ በገጠሬው በአብዬ ዘርፉ
ልሣን፤
...ተረት ሆኜ መቅረቴ ነው፣
ለፍሬ ዕድሜዬ ሳትበቃ
ምኞቴ እንደጉም መጥቃ
ተስፋዬ እንደጉድፍ ወድቃ
የወንድሜን ልጆች ጭምር፣
ለርስታቸው ሳላበቃ!...
ያለኝ ይመስለኛል። ስሜቱን የላከልኝ ያህል ውስጤን ጨረሰኝ። ይኸው ዛሬ እጥፍ ሀዘን የሆነ ነገር ሆነ። አንድ
ነገር ፈጥረን ሳንጠራው፣ አስከሬኑን ልንቀበል ነው። ፀፀት ነው!
ቃልቃልቃል ቃልቃልቃል ቃልቃልቃል ቃልቃልቃል ሃያልሃያል ሃያል
የሕግ ትምህርቱን በአሜሪካ የትያትር ትምሕርቱን በአውሮፓ የተከታተለው ፀጋዬ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ
የሚታወቀው በገጣሚነቱ እና ፀሃፊ-ተውኔትነቱ ሲሆን ዘመን ሲቀያየር ባወጣቸው እንደ እናት አለም ጠኑ፣ ሀሁ፣
በስድስት ወር፣ እና መልክተ ወዛደር ( ከግጥም እሳት ወይ አበባን) በ1960ዎቹ ቴዎድሮስ 1970ዎቹ ሀሁ ወይስ
ፐፑ እንዲሁም ጴጥሮስ ያቺን ሰአት በ1980 ዎቹ ለህዝብ በማድረሱ ስመ ገናና ሆኗል። እነዚህን እና ሌሎች
ከሰላሳ የማያንሱ ትያትሮች መድረሱ ብቻ ሳይሆን በማዘጋጀትም ጭምር ተሳታፊ ነበር። በነዚህ ትያትሮችም
አንቱ የሚባሉ የሃገራችን ምርጥ ተዋንያን ተሳትፈውበታል።
በትያትሮቹም ሆነ በግጥሞቹ በሳልነት በቃላት አጠቃቀሙ ረቂቅነት እጹብነት የሚታወቀው ፀጋዬ ሃያሲያን ተው
ቢሉትም በጅ ሳይል የኖረ ነው። በዚህም የተነሳ ይመስላል ተውኔቶቹ ፈታኞች ስለሆኑ ጎምቱ ጎምቱ ተዋንያንን
በዋናነት ሲያሳትፍ የነበረው።
ከነዚህም ጎምቱዎች ወጋየሁ ንጋቱ የእናት አለም ጠኑን ጅሉ ሞሮን ሆኖ ሲጫወት የገጠመውን እንዲህ ሲል
በምናቡ ይተርከዋል።«ገራፊው ገብረየስ ጅራፉን እንደ መብረቅ እያስጮኸ የጀግናውን የበላይ ዘለቀን ጀርባ
በጅራፍ ይተለትላል። እናት አለም ጠኑ ከነኩታራዎቿ ብቅ ስትል ታየች፤ ልጋጋሙ ነዳዩ ባዩ ዱሽ እጁን ታቅፎ
መድረኩን የሃዘን ድባብ አጠላበት፤ ተክልዬ አፈሊቁ አቅራራ፤ ሌሎች ገፀ ባህርያት ብቅ ጥልቅ እያሉ ተደራሲያንን4
በስሜት አማለሉ።» ሲቀጥልም የቃለ ተውኔቱ አገላለፅ ራሱ ፈታኝ ነው ይለዋል።
4
ወደ ሎሬት ፀጋዬ ዝርዝር
ግጥሞች ከመታደማችን በፊት ወጋየሁ ወዳነሳው ጉዳይ ወደ ፀጋዬ የቃላት ሃይል እንዝለቅ። ፀጋዬ
የሚጠቀምባቸው ቃላት ታሪክን ተመርኩዞ ከሁለቱ ቋንቋዎች እንዳስፈላጊነቱ ከነባህሉ እያጣቀሰ እየነቀሰ ነው።
ከአብዛኛዎቹ የሃገራችን ደራሲያን በተለየ ሁኔታ ፀጋዬ የቃላትን ሀያልነት የተገነዘበ ይመስለኛል።የጸጋዬ ቃላት
ሚስጥር፤ ሰምና ወርቅ ባይሆኑም ተደራቢ ትርጉም አዘል ናቸው። ባጭሩ የፀጋዬን ግጥሞች ቅኔዎች ናቸው
ማለቱ ይቀላል።
ቃል ከፍ ሲልም በሰማያዊው «በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም
እግዚአብሔር ነበረ።...ቃልም ስጋ ሆነ»።
5
ቃል ዝቅ ሲልም በአለማዊው ሰው ዓይንም (በአምሃ አስፋው)
እንዲህ ስንኝ ተሰኝቶለታል።
«ቃልቃል» ቃልቃል
ማን ያውቃል፣
ይለወጥ ይሆናል ቃል፣
ወደሚጨበጥ አካል።
አስማተኞች ሲደግሙ፣
መተታቸውን ሲያሰሙ፣
እቃ ሲፈጥሩ ከምንም፣
ቃላቸውን ወደ ነገር፣
ምኞታቸውን ወደገዝፍ፣
መለወጣቸው ይሆን?
ማን ያውቃል፣
እንደነበር አስቀድሞ፤
ቃል።
6
በራሱ በፀጋዬ አፍ ግጥምና ቃልን እንዲህ ያስባቸዋል።«ገጣሚው ውስጣዊና ህያዊ ባህርዩን መርጦ፤ አንቅቶ፤
ውበት አክሎ፤ በአስተዋይ ህሊናችን ውስጥ ቁስሉን የመፈወሱን ጥረት ያደርጋል...ቃል ኃይል ነውና። ቃል ውበት
ነውና።ቃል እውነት ነውና። ቃል ሕይወት ነውና።ይቀጥላል.........
No comments:
Post a Comment