"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 20 December 2012

ሰር ዜና:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች አድማ መቱ! ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ!!




ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ!!ለ 29ኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ በዝግጅት ላይ ያለዉ ብሔራዊ ቡድናችን ተጨዋቾች እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ላይ ባላቸዉ ቅራኔ በ09/04/2005 ዓ.ም ለሁለት አመት ብሔራዊ ቡድኑን ስፖንሰር ያደረገዉ ሔንከን ቢራ ባዘጋጀዉን የፎቶ የመነሳት ፕሮግራም ላይ ፎቶ አንነሳም በማለት የተጀመረዉ ተቃዉሞ በዛሬዉ አለት ደግሞ (10/04/2005 ዓ.ም) የዕለቱን ልምምድ (training) ባለመስራት ተቃዉሟቸዉን እንደቀጠሉ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ጨዋቾቹ የሚያነሱት ዋነኛዉ ጥያቄ…..የፌዴሬሽኑ አመራር አባላት ከ 31 አመታት በኃላ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋችን ያደረጉልን ምንም ነገር የለም (በአጭር ንግግር ቃል የተገባልን የሽልማት ገንዘብ አልተከፈለንም ማለታቸው ነው) ቢያንስ ባረፍንበት ሆቴል እንኳን መተዉ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያነጋግሩን አልቻሉም የሚል ሲሆን፤ በተፈጠረዉ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የፌዴሬሽኑ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በፅህፈት ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል፡፡ ችግሩ በፍጥነት ተፈትቶ ወደ ስራ እንዲገቡ ብልሐት የተሞላበት ዉሳኔ እንጠብቃለን።፡፡በአስቸኳይም ወደ ልምምዳቸው እንዲመለሱ የሁሉም ስፖርት ቤተሰብ ምኞት ነው። የወዝግቡን ሂደት እየተከታተልን በትኩሱ ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፍሪካ በሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት ከሚታወቀው የደቡብ አፍሪካው MTN ኩባንያ ጋር የስድስት ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ስምምነት ለማድረግ እየተነጋገረ ሲሆን በቅርቡም ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሳምንት በፊት ከታላቁ የቢራ አምራች ድርጅት ከሆነዉ ሔንከን ቢራ ጋር የሁለት አመት የስፖንሰር ስምምነት በ24 ሚሊዮን ብር ($ 1.3 million) ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ዕለት የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ ከስምምነቱ የሚገኘው ገንዘብ ለተጨዋቾቹ አስፈላጊው ሁሉ እንዲሟላላቸው ከማድርግ ባለፈ ከክለቦች ጋር ምንም ትስስር አይኖረውም ማለታቸዉ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፍሪካ በሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት ከሚታወቀው የደቡብ አፍሪካው MTN ኩባንያ ጋር የስድስት ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ስምምነት ለማድረግ እየተነጋገረ ሲሆን በቅርቡም ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሳምንት በፊት ከታላቁ የቢራ አምራች ድርጅት ከሆነዉ ሔንከን ቢራ ጋር የሁለት አመት የስፖንሰር ስምምነት በ24 ሚሊዮን ብር ($ 1.3 million) ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ዕለት የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ ከስምምነቱ የሚገኘው ገንዘብ ለተጨዋቾቹ አስፈላጊው ሁሉ እንዲሟላላቸው ከማድርግ ባለፈ ከክለቦች ጋር ምንም ትስስር አይኖረውም ማለታቸዉ ይታወሳል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፍሪካ በሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢነት ከሚታወቀው የደቡብ አፍሪካው MTN ኩባንያ ጋር የስድስት ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ስምምነት ለማድረግ እየተነጋገረ ሲሆን በቅርቡም ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሳምንት በፊት ከታላቁ የቢራ አምራች ድርጅት ከሆነዉ ሔንከን ቢራ ጋር የሁለት አመት የስፖንሰር ስምምነት በ24 ሚሊዮን ብር ($ 1.3 million) ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ዕለት የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ ከስምምነቱ የሚገኘው ገንዘብ ለተጨዋቾቹ አስፈላጊው ሁሉ እንዲሟላላቸው ከማድርግ ባለፈ ከክለቦች ጋር ምንም ትስስር አይኖረውም ማለታቸዉ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment