"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday, 25 December 2012

ምነው ኖርዌ ምነው ኦስሎ[ወለላዬ ከስዊድን]



ሀገራችን በግፍ ችንካር ተከንችራ፤.............. በሞት ሽረት ተውጥራ፤

የመከራ የጭንቅ ማቅ፤............. ተከናንባ ስትማቅቅ፤

ከግፈኞች መዲፍ ወጥተን፤............ ባንቺ ጉያ ተወሽቀን፤

ግዜ ባማጥን ቀን በገፋን፤............... ምነው! ምነው! ምነው! ኖርዌይ ምነው! ኦስሎ?

ችግራችን ታየሽ ቀሎ። ...........ምን አጥፍተን ጨከንሽብን .......ምነው ፊትሽ ጠቆረብን፤

ምነው ጣልሽን ከእቅፍሽ፤ ..........ምን አረግን ምን በደልንሽ?

ደራሽ ሆነሽ ለተጎዳ፤ ..........አግኝተሽን ባንችው ጓዳ፤

ምነው ውጪ ወረወርሽን፤ ..............በምን ጥፋት ተቀየምሽን?

ምነው! ምነው! ምነው ኖርዌ ምነው! ኦስሎ? ........ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

ምነው ኦስሎ ምነው ኖርዌ፤ .............ሀገራችን የዘር ደዌ፤

ይዟት ታማ ስትማቅቅ፤ ............በችግሯ ስትጨነቅ፤

የሰው ክብር ሰብዓዊነት፤ .........ዱሞክራሲ እኩልነት፤ ......ጭራሽ አጥታ ቆማ እራቁት፤

ሕግ ጠፍቶ ፍርድ ሲጎድል፤ .........ባንቺ ጉያ ብንጠለል፤

ጉዳጉዱን በጠረግን፤ ...........ስርቻውን ባጣጠብን፤

ምን አጥፍተን ምን በደልን፤ ..........ፀዲል ፊትሽ ጠቆረብን።

ጉያሽ ኖረን ሇብዙ ዓመት፤ .........ሳንጨብጥ ትንሽ ቅሪት፤

ካንቺው ወስደን፤ ......ላንቺው ሰጥተን፤ .......አጎብሰን አንገት ደፍተን፤ ......ግብር ከፍለን ሕግ አክብረን፤

አጎንብሰን አንገት ደፍተን፤ ...........በኖርንብሽ በመዋተት፤

ምነው! ኖርዌ ምነው? ኦስሎ፤ .........ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

ደጅሽ ተርፎ ተትረፍርፎ፤ ...........እጅግ በዝቶ ሀብትሽ ገዝፎ፤

ሆነሽ ሳለ ሀብታም ምድር፤ ............ምነው? ጣልሽን እኛን ላአሳር?

ሲቸግረው ሰው ሲከፋ፤ ................በሀገሩ ሲያጣ ተስፋ፤

ሁለም ቢሆን ይሰደዳል፤ .............ዛሬም አለ ፊትም ደርሷል።

ሆኖም ወጥቶ ለሚጠለል፤ ........የታላቁ መጽሐፍ ቃል፤ ........ድጋፍህን ስጠው እንዱል


እያወቅሽው እያስተማርሽ፤ ..........በዓለም ዙሪያ እየሰበክሽ፤ ..........ሰብዓዊ ሀገር ጥሩ እያለሽ፤

ምነው በእኛ እንዲህ ጨከንሽ? .............ምነው! ምነው! ምነው! ኖርዌ ምነው! ኦስሎ፤

ችግራችን ታየሽ ቀሎ?

No comments:

Post a Comment