den 11 december 2012,
02:09:58 | staff reporter
እንተዋወቅ በተከታታይ የምንገናኝ ይመስለኛል:: አይ!…ካላችሁ ከዚሁ
እንሰነባበት፡፡ የእናንተን ስም ቀስ እያላችሁ ታስተዋውቁኛላችሁ:: የእኔው ከላይ ስፍሯል:: /ማሽ አላህ አትሉም?/ቆንጆ ነው
አትሉም? ለመሆኑ እንዴት ናችሁ? የስደት ኑሮ ቅብብሎሹ እንዴት ይዧችኋል? እንዴ!…ምነው ተገረማችሁ? ልክ ነኝ እኮ ኑሮ
ቅብብሎሽ አይደል እንዴ? አቦ! አስቡታ ሰኞ ወደ ማክሰኞ..ሲጠልዘን..ማክሰኞ ተቀብሎ አባብሎ ወደ ረቡዕ ሲወረውረን መስከረም
ወደ ጥቅምት ሲጠልዘን ጥቅምት ለህዳር..ህዳር ለታሀሳስ እያለ ቅብብሎሹ በርትቶ እዚህ ደርሰን የለ? አሁንም ቅብብሎሹ አንዱ ወደ
አንዱ መለጋቱ እንደቀጠለ ነው..
ይሄ ታዲያ ቀደዳ ሳይሆን እውነታ ነው:: ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰ እንደሞተ የረሳ አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የጥላሁን ገሰሰ
ልጅ አንደኛ አመቱን ሲያከብር ከትላንት ወዲያ አዲስ አበባ ነበርኩ ብሎኝ እርፍ….ከላይ ቤትም መላክ ተጀመረ እንዴ ብዬ ዝምታዬ
ውስጥ መዋኘት ጀመርኩ፡፡ የቀደዳ ነገር ሲነሳ ትዝ አለኝ እና ነው:: በአራዲኛ ስጥ እንግዲህ..ረገጣ፣ ቀደዳ..የመሳሰሉት ስያሜ
አለው አይደል? በየመንኛ/አረቢኛ; ጡርጡር ይስማማው ይሆን? የአሁን ዕለቱ በቀደም ደግሞ አንዱ “ቆለለው”አለኝ ራሱን ካበው ሊል
ፈልጎ::መቼም በየእለቱ የሚፈበረኩ ቃላቶች ግርም ይሉኛል::
አንዱ ደግሞ ‹‹ዘሪሁን ስምጥጡ አለ?››አለኝ፡፡ እኔን ከዘሪሁን መኖር አለመኖር የበለጠ ያሳሰበኝ ‹‹ስምጥጡ›› የሚለው ቃልን የተሸለመበት ምክንያት ነው፡፡ ‹‹ምን ለማለት ነው ስምጥጡ ያለችሁት አልኩ፡፡
‹‹እንዴ!? ቀላል ይሰመጥጥልሀል እንዴ?›› ጉድ በል የቀዳጆች ማህበር ሊቀመንበር፡፡ ጉድና የኪስ ቦርሳ ከወደ ኋላ ነው አለ ኦቦሀማ፡፡
አምና አንድ ወዳጄ ጆሮዬን ግምኛ ሲቃለድበት ‹‹የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው.. የሚለው ተረት ቀረ::..እንዲያውም ከየመጽሀፉ ላይ እንዲሰረዝ በጠ/ሚኒስትሩ ታዘዘ፡፡›› ያለኝ ወዳጄ..ቡትረፋውን ጀመረኝ:: ምነው ጠፋህ የሚለውን እንደዘበት የወረወርኩንትን ጥያቄ አስከትሎ ኢትዮጵያ ከርሞ ከመጣ ገና ሁለት ቀኑ እንደሆነ አስረግጦ ማለልኝ:: እንዳምነው መሆኑ ነው:: እንዴት ነው የማምነው? የጆሮዮን ኦዞን ያሳሳው የሱ ቡትረፋ አይደለም እንዴ? ልክ እንደ ኢቲቪ አንድ እንኳን እውነት አይቀላቅልም፡፡ ያ-ማነው ዜና የሚያነበው እሱን ቁጭ.. ‹‹..ጠ/ሚኒስትሩ ሲናገሩ ሰማህ አባይ ከተገደበ በኋላ ውሀ ከቆጣሪ ውጭ በነጻ ይሆናል አሉ::..›› አለኝ፡፡ ያላሉትን ብሎ ሊክባቸው፡፡ ነፍሳቸውን ይማር..እንኳን በነጻ ሊሰጡ…ሙት ወቃሽ አያርገኝ እና በቦንድ በግድ ስንቱን አስለቀሱት፡፡ አረ እንዲያውም እንባ ጠባቂ ኮሚሽን ሁሉ የተቋቋመቀው እንባውን አጠራቅሞ ለአባይ መጋቢ ወንዝ እንዲያዘጋጅ ነው ይባል ነበር፡፡ እነዚህም ሌላ ቀዳጅ ናቸው፡፡
ለዚህም ነው ቦንድ በግድ ሲባል ሁሉ ብርድ ብርድ ያለው፡፡ እንዲያውም አንድ ሰውዬ እዚህ የመን ውስጥ ኤምባሲ በሄደ ቁጥር ቦንድ..ሎተሪ፣ ኢቃማና ቀራማ…እያሉ እንደ ፈረንጅ ላም ሲያልቡት መረረው፡፡ ታዲያ አይሞት ‹‹የአባይ ቦንድ ግዢ..›› ሲሉት ‹‹አሁን የለኝም የእኔን ፋንታ ክፍት ይተዉት ሳገኝ፣ ስሄድ እሰራዋለሁ ብሎ እርፍ፡፡ ታዲያ የስታይል ለውጥ አድረገው …አረ!….
ውሀ በነጻ….በስመአብ…እንኳን በቁም በህልምም አይሉም፡፡..እንዲያውም አጉል እክባቸዋለሁ ብሎ የተቀደደውን ቢስሙ ሞቱ እንጂ ስቀላት ሁላ ሊርዱበት ይችላሉ…ሆሆሆሆይይይይይይ ውሀ በነጻ…ከዚህ በኋላ እንዲህ ለሚያወራበት ሁሉ ግብር ክፈል እንደሚባል አላወቀም:፡ ወዳጄ ሙት የረባ ፈስ ከፈሳህ፣ ግርማ ሞገስ ካለው የማርሽ ባንድ አንቀሳቅሰሀል ተብለህ ታክስ ትጠየቃለህ፡፡ ለሰላምታ እንኳን ቫት ክፈሉ እንደሚባል ነው በመጪው ጊዜ እንኳን ውሀ በነጻ ሊባል..ቱ!!!!ቱ!!..ለማየት ያብቃን ዝናብ መጥቶ ጣራ ላይ ባረፈው መጠን ሂሳብ መጠየቁ አይቀርም:: ከምላሴ ጸጉር….(ቆይ! ሰዎች ከምላሴ ጸጉር የሚሉት ምላሳቸው አናታቸው ነው እንዴ? የእኔ ነገር
ከርዕስ ወጥቼ ቀደዳዬን ካደመኩ በኋላ ወደ መስመሬ ልመለስ፡፡) ግን..ግን..ስሙኝማ የቀደዳ ነገር ሲነሳ ትዝ አለኝ::በአራዲኛ ስጥ እንግዲህ..ረገጣ..የመሳሰሉት ስያሜ አለው፡፡ ስያሜውን አስቡት ግን አጥኑት አላልኩም፡፡ ፈተና የለም፡፡
እንደእኔ አይናፋር ከሆኑ ይሉኝታ የምትባለው ቫይረስ ከተጣባዎት ቀደዳ ለሚቀዱ ሰዎች አመቺ ኖት፡፡ አፈር ስሆን ይሉኝታ አብሮ አድግዎ ካልሆነ ኤጭ!.. በቃ በሉልኝ፡፡ እንዲያው ለነገሩ አንድ ቀን 22000 ክፍዬ ቁርስ በላሁ ብሎት ዝምብ ብለው የቀዳጆች ማህበር አባል ሊያደርጉኝ ነው፡፡ ከፊትዎ ይለጥፈኝ ለአንድ ቁርስ 22000 ሲህ ከፍያለሁ፡፡ ልብ ማት ያለቦት ግን እውነታነቱን ነው፡፡ ሶማሊያ ውስጥ ነው ታዲያ 22000 የሶማሊያ ሽልንግ…ታዲያ ውሽት ነው ይላሉ? ቀድሞ ማጣራትም ወዳጅ እንዳያቱ ያግዞታል፡፡
ዋና ቀደዳ 1 እናሎት ስረ-መሰረቱን አብጠርጥረው የሚያውቁት፣ የቁራሌው ጆንያ የመሰለች ቦርጩን ወጥሯል፡፡ ሊቀደድሎት ነው፡፡ ቤቱ ሲገባ ዘይት ያልጎበኘው፣ ከውሀ የቀጠነ፣ ከነሽንኩርት ስላም ያልተባባለ፣ ለጭልፋ የሚያስቸግር ሽሮውን ጥንግርግር ባለ ደነዝ እንጀራ ሙድ በሌለው ሁኔታ ጎርሶ በውሀ የሚያወራርድ መሆኑን ያውቁታል:: ቂም የመሰለች በሽሮ ወጥ ያላሰለሰ ጥረት የተገኘች ቦርጩን እያሻሸ ‹‹እኔ ሸሮ ነገር አልወድ››አይስማማኝም..በቀደም እለት የታመመ ሰው ለመጠየቅ ሰው ቤት ሄጄ ሽሮ ወጥ አቀረቡልኝ:: እምቢ ብዬ አላሳፍራቸውም ዝቅ ያለ ኑሮ ስለሚኖሩ ንቆን ነው ይላሉ ብዬ በላሁ:: በኋላ ፉድ ፖይዝን ለጉድ በቃ!..ፌንት ስረቼ፣ ሀያት ሆስፒታል ስንትና ስንት ብር ጨርሼ..ከዘራቸው ሀያት ሆስፒታል የሚታከም ቀርቶ በሩ ላይ የቀመ የለም-እንኳን ሊታከሙበት:: አህ!..ገንዘብ..ገንዘብ ካልሸተትክ ሀያት በር ላይስ ማን ያስቆምሃል?” ደሞ የመድሀኒት…”ቀደዳውን ቀጥሏል:: እርሶ ጆሮዎትን በበቃኝ ዘግተዋል:: ጭንቅላትዎ ስለእሱ ደሳሳ ጎጆና የየእለት ቋሚ ተሰላፊ ቀለቡ ሽሮ እያሰቡ ነው:; ልብ በሉ እስኪ በእናታችሁ ሽሮ በልቶ ፉድ ፖይዝን ሲይዘው ይታያችሁ፡፡…እንደዛማ ቢሆን ኖሮ ምድረ ሀበሻ አንጀታችን በፉድ ፖይዝን ተበጣጥሶ ሽንት ቤት የቀብር ስነ-ስራዓቱ እንደዘበት በተጸዳዳን ቁጥር በተፈጸመ ነበር::
አብሶ እኔ ከህጻንነቴ ጀምሮ ሽሮ ነው ኮትኩቶ ያሳደገኝ:; እንደሱ አባባል አንጀቴ በፉድ ፖይዝን ተበጣጥሶ ባዶዬን ነው ያደኩት ማለት ነው:: እውነት እንነጋገር ካልን የሽሮዋን ነገር ሳስባት ሽሮ የቅርብ ዘመዴ..አረ ለሁላችን የወንድም ያህል አይደል እንዴ ቀረቤታው? አብሮ አደግ ነን:: ሽሮ ተብዬ ሁሉ በየሁሉም ቤት የመሶብ አምባሳደር አይደል?በቃ!!..የምን መደባበቅ ነው?አብሮ አደግ ነን..ነን ከጡጦ ቀጥሎ ሽሮ::ሽሮ ለዘላለም ይኑር!!!ከኮሌስትሮል ነጻ..ሽሮ:: ለቫራይቲ..ሽሮ:: ማን እንደ ሽሮ …
በቀጣይ ሌላ የቀደዳ ወግ እንገናኝ

No comments:
Post a Comment