Movement For Artists' Rights
"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Thursday, 24 January 2013
ብሔራዊ ቡድኑን የስነልቦና ቀውስ ውስጥ ለመክተት ሕወሓት እየሰራ ነው!!
የትግራይ ልማት ማህበርና ኢትዮጵያ ኢምባሲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በስነልቦና እየጉዱት ነው
የደደቢት 5 ተጫዋቾች የአቶ መለስን ቲሸርት ከማሊያ ስር እንለብሳለን ሲሉ 18ቱ ተጫዋቾች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አታጣሉን እያሉ ነው
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስታዲየሙ ውስጥ የአቶ መለስን ቲሸርት የለበሰ ተጫዋች ካየን ተቃውሟችንን እናሰማለን ብለዋል
“ኢቲቪ ኳሱን ሰርቆ ማስተላለፉ አሳፍሮናል”
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የትግራይ ልማት ማህበር እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ በጋራ የአቶ መለስ ዜናዊን ቲሸርት በማሰራት የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በቡኪና ፋሶውና በናይጄሪያው ጨዋታ ለብሰው እንዲጫወቱ በማስገደድ ላይ እንደሆኑና በአሁኑ ወቅት ቲሸርቱን እንለብሳለን፤ አንለብስም በሚሉ መካከል ብሔራዊ ቡድኑ እንደተከፈለ የደቡብ አፍሪካ የዘ-ሐበሻ የዜና ዘጋቢዎች አጋለጡ።
የትግራይ ልማት ማህበር በደቡብ አፍሪካና የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአቶ መለስ ቲሸርትን አሰርተው ተጨዋቾቹ ለብሰው በመግባት በተለይ ጎል ሲያገቡ ቲሸርቱን ገልጠው እንዲያሳዩ ቢጠይቁም 18ቱ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች እንዳልተስማሙና ለትግራዩ ደደቢት ክለብ የሚጫወቱት ተጫዋቾች ግን ቲሸርቱን እንለብሳለን በሚል ለሁለት መከፈላቸውን ያጋለጡት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በተለይ ይህ ሚስጢር ከወጣ በኋላ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ማስከተሉን ዘግበዋል።
“የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ውስጥ የውሃ ላስቲኮችን እና ሌሎችንም ነገሮች በዛምቢያው ጨዋታ ላይ በመወርወራቸው” ፌዴሬሽኑ 10 ሺህ ዶላር የተቀጣ ሲሆን በቡርኪናፋሶውም ሆነ በናይጄሪያው ጨዋታ ላይ አንድም ተጫዋች የአቶ መለስን ቲሸርት ለብሶ ቢገባ ደጋፊው እርምጃ እንደሚውስድ ከወዲሁ ማስጠንቀቁን ያስታወሱት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች “እኛ የኢትዮጵያ ሕዝብን እናከብራለን፤ የአቶ መለስን ቲሸርት አንለብስም ያሉትን ተጫዋቾች እናደንቃለን፤ የደደቢቶቹ ተጫዋቾች ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያደፋ ተግባር በዚህ ጨዋታ ላይ ከፈጸሙ እርምጃው የከፋ ይሆናል” በሚል ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተነጋገረበት እንደሆነም አስምረውበታል።
“ይህ ኢትዮጵያ የምትከበርበት ዕለት እንጂ አቶ መለስ የሚታወሱበት ዕለት አይደለም” በሚል ቁጣቸውን እየገለጹ የሚገኙት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፊፋ ተጨማሪ ቅጣት በብሔራዊ ቡድኑ ላይ ያድርግ እንጂ አንዳችም ተጫዋች የአቶ መለስን ቲሸርት ከውስጥ ለብሶ ማየት አንፈልግም እያሉ ነው። የኢምባሲው ሰራተኞችም ኢትዮጵያ እየተደዋወሉ አስር ጊዜ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በቀጣይ ጨዋታ ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ፤ በቲሸርት መልበስ ዙሪያ ማስጨነቃቸውን እንዲያቆሙ ሕዝቡ እየጠየቀ ነው።
ብሔራዊ ቡድኑ ያረፈበት ናታን ስትሪት አካባቢ የሰፈሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ለተጫዋቾቹ ስልክ በመደወል “ቲሸርት ልበሱ ቢባሉ እንዳይቀበሉ” በመናገር ላይ ሲሆኑ ተጫዋቾቹም በትግራይ ልማት ማህበርና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰዎች በሚደርስባቸው ጫና ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እንዳሉ ለመረዳት መቻሉን ዘጋቢዎቻችን አስታውሰው፤ ምናልባትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ በዚህ ውድድር በዛምቢያ ጨዋታ ላይ ያሳየውን ድንቅ ብቃት በሌሎች ጨዋታዎች ላይ ላያሳይ ከቻለ ተጠያቂዎቹ እነዚሁ የስር ዓቱ ደጋፊዎች የሆኑ 2 ተቋማት ተጠያቂ ይሆናሉ በሚል ደጋፊው ከፍተኛ አቋም መያዙን እነዚሁ ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል።ይህ በ እንዲህ እንዳለም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን ሰርቆ ማስተላለፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንገታችንን አስደፍቶናል” በሚል ስሜታቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸው
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment