"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 12 December 2012

በቃ! ትቸዋለሁ (ወረፋ ይጠብቅ)


Alternative title (ወረፋ ይጠብቅ)

የሰሞኑ ዘፈኔ እና ትዝብቴ



በ Naod ቤተሥላሴ



የአሸብር በላይ ‹‹እኔ ነኝ ያለ›› የሚለውን ዘፈን የሰማሁት በቅርቡ ነው፡፡ የቆየ ዘፈን ይሁን አይሁን እንጃ፤ ለእኔ ግን አዲስ ነው፡፡ ባሕላዊ ዘፈን ይሏል ይሄ ነው፡፡ የወንዶቹን እስክስታ አይቼ አልጠገብኩትም፤ የሴቶቹን ኦሪጂናሊቲ አድንቄዋለሁ፤ ፉከራው ደስ ይላል፤ ከሁሉ በላይ ግን የዘፈኑ ታሪክ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ሀገር መርቆ የሰጠውን ቆንጆ ሚስት የሚከላከል ጀግና አባወራን ጀግንነት የሚተርክ ዘፈን ነው፡፡

እንደ አጭር ልብወለድ የሚነበብ ታሪክ ያለው ዘፈን ወዳጅ ነኝ፡፡ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ስሜት የሰጠኝ ተራኪ ዘፈን ‹‹ቅዳሜ ገበያ›› የሚለው የቤተልሔም ዘፈን ነበር፡፡ ገበያ ልትገበይ ወጥታ፤ ፍቅር ሸምታ የተመለሰችው፡፡ ከልጆቼ ጋር ክብ አየሰራን፤ ስንት ዙር እንደጨፈርን አትጠይቁኝ፡፡

ከሰሞኑ የዘፈን ምርጫየ ባሻገር ግን የባሕል ዘፈን ሳይ የምታዘበው ነገር አለ፡፡

የሰሞኑ ምርጥ ዘፈኔ


በጎ ትዝብት
1ኛ-ነጭ የባሕል ልብስ ባለባቸው ሌሎች ዘፈኖች ላይ የማየው የሴቶች ባሕላዊ ቀሚስ፤ የደረሰበት የፋሽን እና የዲዛይን ጥበብ ደረጃ ያስደስተኛል፡፡ በዚህ በኩል ወንዶች ተበድለናል፡፡ፋሽን ልብስ ሰፊዎች፤ በተለይ የሕንድ የሚመስለውን ቀሚሳችንን ቢያስወግዱልን ጥሩ ነበር፡፡እኔ እንድወድላቸው ከፈለጉ፡፡

2ኛ- ከነጩ ልብስ በላይ ደግሞ የሚስገርመኝ ለየብሔረሰቡ የተሰጡት ዘመነዊ ልብሶች ናቸው፡፡ የጎጃም አረንጓዴ ቁምጣ እና ባለ መስመር ካናቴራ፤ የጉራጌ ደመቁ ቀሚስ እና ሻሽ፤ ወዘተ…እኒህም የተሸሻሉ የባሕል ልብሶች መሆናቸው መሰለኝ፡፡ የዚህም ደጋፊ ነኝ፤ ብዙ እውነት አለውና፡፡

Monday 10 December 2012

ቀደዳ በግሩም ተ/ሃይማኖት

 
‎den ‎11 ‎december ‎2012, ‏‎02:09:58 | staff reporter
እንተዋወቅ በተከታታይ የምንገናኝ ይመስለኛል:: አይ!…ካላችሁ ከዚሁ እንሰነባበት፡፡ የእናንተን ስም ቀስ እያላችሁ ታስተዋውቁኛላችሁ:: የእኔው ከላይ ስፍሯል:: /ማሽ አላህ አትሉም?/ቆንጆ ነው አትሉም? ለመሆኑ እንዴት ናችሁ? የስደት ኑሮ ቅብብሎሹ እንዴት ይዧችኋል? እንዴ!…ምነው ተገረማችሁ? ልክ ነኝ እኮ ኑሮ ቅብብሎሽ አይደል እንዴ? አቦ! አስቡታ ሰኞ ወደ ማክሰኞ..ሲጠልዘን..ማክሰኞ ተቀብሎ አባብሎ ወደ ረቡዕ ሲወረውረን መስከረም ወደ ጥቅምት ሲጠልዘን ጥቅምት ለህዳር..ህዳር ለታሀሳስ እያለ ቅብብሎሹ በርትቶ እዚህ ደርሰን የለ? አሁንም ቅብብሎሹ አንዱ ወደ አንዱ መለጋቱ እንደቀጠለ ነው..
ይሄ ታዲያ ቀደዳ ሳይሆን እውነታ ነው:: ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰ እንደሞተ የረሳ አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የጥላሁን ገሰሰ ልጅ አንደኛ አመቱን ሲያከብር ከትላንት ወዲያ አዲስ አበባ ነበርኩ ብሎኝ እርፍ….ከላይ ቤትም መላክ ተጀመረ እንዴ ብዬ ዝምታዬ ውስጥ መዋኘት ጀመርኩ፡፡ የቀደዳ ነገር ሲነሳ ትዝ አለኝ እና ነው:: በአራዲኛ ስጥ እንግዲህ..ረገጣ፣ ቀደዳ..የመሳሰሉት ስያሜ አለው አይደል? በየመንኛ/አረቢኛ; ጡርጡር ይስማማው ይሆን? የአሁን ዕለቱ በቀደም ደግሞ አንዱ “ቆለለው”አለኝ ራሱን ካበው ሊል ፈልጎ::መቼም በየእለቱ የሚፈበረኩ ቃላቶች ግርም ይሉኛል::
አንዱ ደግሞ ‹‹ዘሪሁን ስምጥጡ አለ?››አለኝ፡፡ እኔን ከዘሪሁን መኖር አለመኖር የበለጠ ያሳሰበኝ ‹‹ስምጥጡ›› የሚለው ቃልን የተሸለመበት ምክንያት ነው፡፡ ‹‹ምን ለማለት ነው ስምጥጡ ያለችሁት አልኩ፡፡
‹‹እንዴ!? ቀላል ይሰመጥጥልሀል እንዴ?›› ጉድ በል የቀዳጆች ማህበር ሊቀመንበር፡፡ ጉድና የኪስ ቦርሳ ከወደ ኋላ ነው አለ ኦቦሀማ፡፡

ምሁራንና ‘አክቲቪስቶቻችን’ ሆይ ትግላችን ከመለስ ዜናዊ ወይስ ከሥርዓቱ?

 

አንዳንድ በትኩሱ ስሜታዊነትን እንዳዘሉ የሚሰነዘሩ ሀሳቦችን ትንሽ ፋታ መስጠትና ማስተዋል የታከለበት የታረመና የተስተክካለ ሀሳብን መጠበቅ መልካም ምግባር ነው። የጠቅላይ አስለቃሻችን ነብስ ሙታኑን ከተቀላቀሉ በሁዋላ በአሳርና በመከራ ያልታሰበው ሰው ሁሉም ወደሚያስበው ስልጣን ላይ መምጣቱን ተከትሎ የሚሰነዘሩት ሀሳቦች ግን አሁን ድረስ ስክነት አሳይተዋል ብዬ ላስብ አልቻልኩም። ስህተቱ የኔ ከሆነ እዳው ገብስ ነው። የኔ አይነት ሀሳብ ያላቸው ሰዎች ብዙ ከሆኑ ግን መመለስ ያለበት ጥያቄ አለ ማለት ነው።

አቶ ኃይለማርያምን በተመለከተ ከፈጣሪ ጋራ ቀጥታ የግንኙነት መስመር አላቸው ከሚሉን አንስቶ ስለመልካም ባህሪያቸውና የአስተዳደር ችሎታቸው የሚነግሩንን ሰዎች የተለያዩ መድረኮች አስተናግደዋል። ፍትህን እውነትንና ነጻነትን በምድር፣ ሰማያዊ አምላክን ደግሞ ለነብሱ የያዘ ሰው ራሱ ተኩሶ ባይገድል እንኳን በአባሪነትና በተባባሪነት ወንጀል ስሙ ሊነሳ የግድ ነውና እንደምን ሆኖ መልካሙ ሁሉ እንደተቸራቸው ማሰብ ይከብዳል። በአንድ ስርዐት ውስጥ ያገለገለ ሁሉ የግድ ወንጀለኛ ነው ለማለት ፈጽሞ አይደለም። ነገር ግን የፖለቲካ ስልጣን ይዞ ቁንጮ ሆኖ የተቀመጠና በግድ ያልተመደበ ሰው እሺ ወይም እምቢ የማለት መብት አለውና የማይጠየቅበት ምክንያት የለም። እራሴን ለማዳን ሌሎቹን ማደን ግዴታዬ ነበር የሚል ካለ የፍትህ አካል የሚዳኘው ጉዳይ ይሆናል።

In Defense of Religious Freedom in Ethiopia


by Alemayehu G. Mariam
The Precarious State of Religious Freedom in Ethiopia
In a weekly column entitled “Unity in Divinity” this past June, I expressed grave concern over official encroachments onIn Defense of Religious Freedom in Ethiopia religious freedom in Ethiopia. I lamented the fact that religious freedom was becoming a new focal target of official human rights violations. But I was also encouraged by the steadfast resistance of some principled Christian and Muslim religious leaders to official interference in religious affairs. I noted that “For the past two decades, Ethiopia has been the scene of crimes against humanity and crimes against nature. Now Ethiopian religious leaders say Ethiopia is the scene of crimes against divinity. Christian and Muslim leaders and followers today are standing together and locking arms to defend religious freedom and each other’s rights to freely exercise their consciences.”
Officials of the ruling regime in Ethiopia see the issue of religious freedom as a problem of “religious extremism”. The late Meles Zenawi alleged that some Christians at the Timket celebrations (baptism of Jesus, epiphany) earlier this year had carried signs and slogans expressing their desire to have a “Christian government in Ethiopia”. He also leveled similar accusations against some Ethiopian Muslims protesting official interference in their religious affairs for being “Salafis” linked to Al Qaeda. Meles claimed that “for the first time, an Al Qaeda cell has been found in Ethiopia. Most of them in Bale and Arsi. All of the members of this cell are Salafis. This is not to say all Salafis in Ethiopia are Al Qaeda members. Most of them are not. But these Salafis have been observed distorting the real teachings [of Islam].”
A Statement issued by the U.S. Commission on International Religious Freedom (USCIRF) last