"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 2 June 2012

የኖርዌይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ስለወሰደው የኃይል እርምጃ በተመለከተ


 | 

የኖርዌይ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ስለወሰደው የኃይል እርምጃ በተመለከተ፤አኢጋን


ከጥቂት ቀናት በፊት ለተባበሩት መንግሥታ የስደተኞች ኮሚሽነር በዓለም ዙሪያ ግፍ እየተቀበሉ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በጻፍነው ደብዳቤ ላይ የኖርዌይ ስደተኞችን ሁኔታ በዝርዝር መጥቀሳችን የሚታወስ ነው፡፡ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን መካከል በኖርዌይ እስከ 16 ዓመታት የኖሩ የሚገኙበት ሲሆን በእነዚህ ዓመታትም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ባይሰጣቸውም ባገኙት ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ እንደስደተኛ የመንግሥትን ድጎማ እየተቀበሉ ከመኖር ይልቅ ያገኙትን ሥራ እየሠሩ፣ ግብር እየከፈሉ እንዲሁም ራሳቸውን ከማኅበረሰቡ ጋር ለማዋሃድ ቋንቋ በመማር፣ ቤት በመሥራትም ሆነ በመግዛት ቤተሰባቸውን በዓቅማቸው ለማስተዳደር ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡ ይህም ሆኖ ከኖርዌይ መንግሥት የተሰጣቸው ምላሽ ያልጠበቁት ከመሆን ባሻገር ኑሮዋቸውን እጅግ አስከፊ ደረጃ በፍጥነት እንዲደርስ ያደረገ ሆኗል፡፡
በቅርቡ ስደተኞችን አስመልክቶ የኖርዌይ መንግሥት ያደረጋቸውን ለውጦች የተቃወሙ 63 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን (ሴቶችንና ህጻናትን ጨምሮ) በኦስሎ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ጠለላ ባኙበት ወቅት የቤ/ክኑ ኃላፊዎች ከመንግሥት ጋር (ከኢሚግሬሽን ጽ/ቤት) ተነጋግረው በተስማሙት መሠረት እዚያው ኦስሎ ውስጥ ወደጊዜያዊ የስደተኛ ካምፕ ተዛውረው ነበር፡፡ ከእነዚህ ወገኖቻችን መካከል አንዲት የስድስት ወር እርጉዝ፣ ሌላ የ14 ህጻን ሴት ልጅ ያላት እናት፣ በኖርዌይ ለበርካታ ዓመታት ሲሰሩ የቆዩና በሌሎች የምዕራብ አገሮች ቤተሰቦች ያላቸው ዕድሉም ከተሰጣቸው ወደዚያው ለመሄድ የሚችሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ወደዚህ ካምፕ ተዛውረው ከኖሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ማክሰኞ ሚያዚያ 18፣ 2003 ዓም ያልተጠበቀ ሁኔታ ተከሰተ፡፡

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!”


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Friday, June 1st, 2012 | Posted by zelalem
ትንሽ ቡጨቃ፤ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!”
3
Share
ሰፈሬ ሽሮሜዳ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ግዜ በአጋንንት የተለከፉ ፀበልተኛ ወገኖች “ትለቃለህ አትለቅም” በሚለው አስገምጋሚ የአስጠማቂው ቁጣ ሁልግዜም መልሳቸው ከተረበሸ ድምፅ የሚፈልቅ “እለቃለሁ!” የሚል ሲቃ እንደነበር አይቻለሁ። ችግሩ ግን ብዙ ግዜ “እለቃለሁ” ካሉ በኋላም በነጋታው “አብሬያት አድጌ፣ አብሬው ከርሜ” ለማን ትቼው እለቃለሁ” ብለው ድጋሚ ያገረሻሉ። አሁንም አስጠማቂው “አንተ ክፉ መናጢ ትለቃለህ አትለቅም…!?” ሙግታቸውን ይጀምራሉ። መስቀል እና ፀበል ለአጋንቱ ፀር ናቸውና “እለቃለሁ እለቃለሁ…” እያለ ይለፈልፋል። ምሱን ተናግሮ ቀምሶ ጨርሶ እስኪለቅ ድረስ ግን “እለቃለሁ” ስላለ ብቻ አይታመንም!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘንድሮም “እለቃለሁ!” እያሉ ነው። በእርሳቸው ፍቅር የተለከፍን እኛ፤ “ያለ እርስዎ በሳል አመራር ችግር እና ጉስቁልና ያበስለናልና እባክዎ ይሄንን አሳብ ወደ አዕምሮዎ አያምጡት!” ብለን ብንመክርም፤ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!” እያሏቸው ይገኛሉ።
በተደጋጋሚ እንዳየነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አስለፍላፊያቸው ብዙ ነው። ከዚህ በፊት በፓርላማ ውስጥ፤ ከዛም በተለያዩ የውጪ ሃገር ጋዜጠኞች “ትለቃለህ አትለቅም!” የሚሉ አስለፍላፊዎች አጋጥመዋቸዋል። ያው የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትራችንም ደንብ ነውና፣ ስርአቱ ነውና “እለቃለሁ!” እያሉ በተደጋጋሚ ለፍልፈዋል።  ነገር ግን አለቀቁም።
እኔ የምለው ግን ክቡርነታቸው በርካታ ግዜ “ለቃለሁ” እያሉ ሲተዉት፣ “ለቃለሁ” ሲሉ ሲተዉት ሰዉ ንግግራቸውን አጓጉል ከእርኩስ መንፈስ ጋር እያዛመደባቸው እኮ ነው…!
በነገራችን ላይ ከላይ ያለውን የኪዳነምህረት ፀበል ትዝታዬን ያመጣሁት እንደው ነገር ለማሳመር ብቻ ብዬ አይደለም። በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድ የውጪ ሀገር ጋዜጠኛ “ትለቃለህ አትለቅም?” ብሎ ሲጠይቃቸው “እለቃለሁ!” ብለው በመናገራቸው (“እለቃለሁ” ብለው ሲለፈልፉ…” ልላቸው ነበር! ይቅርታ ከላይም “ለፈለፉ” የሚል ቃል ካለ ከፀበልተኞቹ ጋር ተምታተውብኝ ነውና በጅምላው ይቅርታ ጠይቄ እቀጥላለሁ)
እና ታድያ ጋዜጠኛው በጠየቃቸው ጊዜ “እለቃለሁ!” ብለው ሲመልሱ አንዱ ወዳጄ “አፈር ስሆን ‘ምስህ’ ምንድነው? በለህ ጠይቃቸው እና ያሉትን አቅርበን ቀምሰው በደንብ ይልቀቁን ሁሌ “ለቀኩ እያሉ አያስጎምጁን!” ብሎ የተናገረውን አስታውሼ ነው።
እኔ የምለው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣን መልቀቅ ከአጋንንት መልቀቅ ጋር ማመሳሰል ፍትሃዊ ንፅፅር ነው ትላላችሁ…!?

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!” tokichaw

የማያልፍ ከሆነ እኛ እንለፍ


የማያልፍ ከሆነ እኛ እንለፍ – ተድላ ጌትነት ታፈረ Www.Maledatimes.Com
SHARE THIS
       
TAGS

ለ20 ዓመታት ቀንን ቀን እየወለደው ነገን ተስፋ አድርገን ግፍና መከራን በፅናት ተሸክመን ያልፋል ብለን ግን ሳያልፍ አገር ጥለን ተሰደድን አንድ የሐይማኖት መጽሐፍ የተኮነኑ ነፍሶች አርብ ወጥተው ሰኞ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ይመለሳሉ ይህ የሚሆነው ሰንበትን ለአከበረ ሰው ነው ይላል ስለነገረ ሰንበት በተነገረ መጽሐፍ ይህ የሚያሳየው ከሲኦልም ዕረፍት ከዲያቢሎስም ምህረት ይገኛል
ማለት ነው ፡፡ ታዲያ ከዲያቢሎስ የከፋ ከሲኦልም የባሰ የሥቃይ ቦታ የት አለ ከተባለ ከዲያቢሎስ የከፋ ጳውሎስ ከሲኦል የስቃይ ቦታ የባሰ የስቃይ ሀገር ኢትዮጵያ መሆኑዋ አየጠራጥርም ሀገር በተፈጥሮ ክፉ ልትሆን አትችልም ይልቁንም የሚመሯትና የሚኖሩባት ክፉ ያደርጓታል እንጂ በኢትዮጵያ በሁለት አሀዝ ኢኮኖሚው ወድቋል /20/ ሁለት አሀዝ ካልን ወያኔ ይችን ሀገር ለመምራት የተቆጣጠራረበት ጊዜ መሆኑእደሆነ አያጠራጥርም ፡፡ ኢትዮጵያ በዘመኗ ካጋጠማት የሰው ሰራሽ ችግርም ይሁን የተፈጥሮ ከአሁን የባሰ ጊዜ በታሪክ አይታወቅም የነበሩት ችግሮች ጊዜያዊና የሚያልፉ ነበሩ አሁን ግን የነገሮች አቅጣጫና ስልት እየተቀያየሩ መከራውን ማበስ እንጂ ማቃለል ስቃዩን ማጽናት እንጂ ማላላት አልተቻለም ለምሳሌ የሀይማኖቱ መሪ እንመልከት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሀገርን ሀገር

ሰለሞን ተካልኝ መፈክር ከመሸከም ውጪ ትንፍሽ እንዳይል በሰማዕታት ስም እጠይቃለሁ፡ የአቤ ቶኪቻው ደብዳቤ ለኢህአዴግ


ሰለሞን ተካልኝ መፈክር ከመሸከም ውጪ ትንፍሽ እንዳይል በሰማዕታት ስም እጠይቃለሁ፡ የአቤ ቶኪቻው ደብዳቤ ለኢህአዴግ
SHARE THIS
       
TAGS


ሰለሞን ተካልኝ መፈክር ከመሸከም ውጪ ትንፍሽ እንዳይል በሰማዕታት ስም እጠይቃለሁ፡ የአቤ ቶኪቻው ደብዳቤ ለኢህአዴግ www.maledatimes.com

እናንት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባረካችሁ ክቡራን እና ክቡራት ሰላም እላችኋለሁ! ያው እንደምታውቁት ድርጅታችን መልካም ነገር ሲያጋጥመው የምንወዳደሰውን ያህል ችግር ባጋጠመን ግዜም ደግሞ እንዲህ በራችንን ዘግተን መገማገም እና ድርጅታችንን “ከመበስበስ” አደጋ መታደግ የዘወትር ተግባራችን እንደሆነ ይታወቃል።

ለዛሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በዝግ ብሎግ እንድናወራ አነሆ ልጀምር ነው። (በነገራችን ላይ ዝግ ብሎግ ያልኩት እንደወትሮው ብሎጌ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ስለመታገዱ ላወራ አይይደለም። (በሌላ ቅንፍ ለድርጅታችን ከጠቀመ ልሳናችንም ቢዘጋ ቅር የማይለን ቁርጠኞች መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ!) ይልቅስ በርዕሱ “ለኢህአዴግ አባላቶች ብቻ” ብዬ በማለቴ ሌሎች፤ ፅንፈኞች፣ አክራሪዎች፣ ነፍጠኞች፣ ነውጠኞች፣ ሽብርተኞች፣ ኒዬ ሊበራሎች፣ የሻቢያ ተላላኪዎች (ዉዉዉ ይሄንን ሁሉ ስም አውጥተንላቸዋል እንዴ ለካ…? ለነገሩ ከዚህም እጥፍ እጥፍ ስም አውጥተንላቸዋል። ለካስ ከኢኮኖሚ እድገቱ እኩል ተቃራኒዎቻችንን በመሞለጭም ታላቅ እምርታ አስመዝግበናልና! በእውኑ በድርጅቴ ኮራሁ! የሆነው ሆኖ፤ ባጠቃላይ እነዚህ ወዘተዎች ስለማያነቡት እና ጨዋታው የቤተሰብ ጨዋታ በመሆኑ ነው በዝግ ብሎግ ማለቴ!)))
http://www.youtube.com/watch?v=p7xtAH2aHA0&feature=youtu.be

እንደሚከተለው እጀምራለሁ…!

እኔ የምለው ባለፈው ግዜ ሰለ ጓድ ሰለሞን ተካ አንዳንድ ነገሮችን አንስቼ ተናግሬ ነበር። በርግጥ ግለሰቡ የተናገርኩትን ቢሰማም ቅሉ ሂሱን አልዋጠም። ሰሞኑን እንዳሰማሁት ደግሞ እንኳን ሂሱን እና መድሃኒቱንም በአግባቡ መዋጥ እንዳቆመ ያመላከተኝ ነገር አስተውያለሁ።

ተጠቃሹ ግለሰብ በግል ስሜቱ በመነሳሳት ፅናት በተባለ ራዲዮ ጣቢያው ላይ ድርጅታችንን ለዝቅጠት የሚዳርግ አንዳች ንግግር ተናግሯል። ሰሞኑን ጋዜጠኛ አበበ ገላው ስመ ገናናውን ጠቅላይ ሚኒስትራችን አምባገነን ብሎ በተናገረበት ንግግሩ ላይ ጓድ ሰለሞን ተካ ምላሽ ለመስጠት ሞክሮ ነበር። በእውነቱ ሙከራውን ሳላንደንቅ አናልፈም።

Thursday 31 May 2012

40 YEARS OF CONTINUED STRUGGLE



                                                                                                                       የኢትዮጵያ  ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ)                                                                                                                    
 Ethiopian  People's  Revolutionary Party (EPRP)                                                                                  

                                                                        APRIL 1972-APRIL 2012

              40  YEARS OF CONTINUED STRUGGLE                                                                                                                    

       
The EPRP was established to struggle for democracy and the sovereignty of Ethiopia.
It has stayed steadfast and true to its objectives despite the brutal repression that has
been its lot for decades.
The EPRP was established by a founding congress that lasted from April 2--April
9/1972 with the declared aim of fighting for democracy and popular people’s
government. Since that period, the EPRP has continued to struggle for democracy and
the rule of law in Ethiopia.
Outlawed by three consecutive regime (that of Emperor Haile Selassie,  of Mengistu
Haile Mariam and the present one of the TPLF led by Meles Zenawi), the EPRP has
been forced from the outset to struggle as a clandestine party. When the popular
February 1974 Revolution erupted, the EPRP was not yet strong enough to assume the
mantle of leadership but it quickly joined the upsurge and gave the popular protest
content and depth. When the military officers short circuited the Revolution and
assumed power in 1974, the EPRP successfully led the people’s peaceful struggle for
the formation of a broad based provisional popular government. The demand for this
popular rule and democracy was not to the liking of the authoritarian officers and it
was not long before the Mengistu regime launched a campaign of murder (the brutal
campaign called the Red Terror) against EPRP members all over the country. The
military regime, aided and backed by the Soviet bloc, launched the notorious Red
Terror against the party because it was defeated politically all over the country. The
violence caused the brutal deaths of no less than 250,000 people, most of them
supporters and members of the EPRP.
The EPRP waged armed struggle against the Mengistu regime from the seventies up to
its fall in 1991. It had also to withstand the military attacks of the Tigrean ethnic front                            
                                                       
                                         
(the TPLF now in power) for many years. The TPLF and its allies marched on Addis
Ababa after waging war against the EPRP in Gondar and Gojjam. Many leaders of the
EPRP have been disappeared by the TPLF, others killed in Addis Abeba and other
places and up to now the TPLF/EPRDF repression unleashed against the EPRP
continues. In all instances, be it during the period of the 1974 Revolution or the
takeover of power by the Tigrean front, the EPRP had made it clear it would struggle
peacefully and legally if democratic rights and the rule of law were respected. However,
the regimes have chosen to outlaw the EPRP and persecute it precisely because it has
vast following and is multi ethnic by composition and progressive/social democratic by
ideological persuasion. The EPRP continues to clandestinely struggle against the ruling
regime of Meles Zenawi, has broadcast to Ethiopia a radio program for more than a
decade, organized people in various ways, allied with other groups to form united
fronts (COEDF and UEDF are examples) and has now cells and structures in almost all
regions of the country.

ጨዋታ ወፖለቲካ፡- ‘አንተ’ታ እና ‘አንቱ’ታ!


ጨዋታ ወፖለቲካ፡- ‘አንተ’ታ እና ‘አንቱ’ታ!




SHARE THIS
TAGS
Share in top social networks!


ጨዋታ ወፖለቲካ፡- ‘አንተ’ታ እና ‘አንቱ’ታ!

(ሰሎሞን ተ ጂ. /ከአ.አ.) semnaworeq.blogspot.com
ይሄንንስ መቼም እነግራችኋለሁ፡፡ “ወሰድ ያደርግሃል እንዴ?” አይለኝ መሰላችሁ፡፡ መድኃኔዓለም ይውሰደውና፡፡….አርባ-አራቱ ታቦት ይውሰዱትና! ምናባቱንስና ደግሞ እሱ ብሎ ባለ ዲግሪ!….እኔማ ልክልኩን ነገርኩት፡፡ “አሁን አንተ የማስተማር ዲግሪ ምናምን አለኝ እንዴት ትላለህ?” አልኩት፡፡ ልብ-ልቡን አሳጣሁት፡፡ “እኔ በግሌ ዲግሪህን ነጥቄሃለሁ!” አልኩና ቁርጡን ነገርኩት፡፡ አሃሃሃሃ…..!!! ጭራ ሲያበቅል አየሁት፡፡ “… ስማ መልስልኝ፣ ምናምን እንዳትለኝ፡፡ ስማ! እኔ በግሌ ነው – ነጠቅኩህ – ያልኩህ፤” አልኩት፡፡ ይሄንንም መቼውንም እነግራችኋለሁ፡፡…..
“ወይ አሳምነኝ! ወይ ደግሞ እመነኝ!….ሁለቱንም ወዶ – ለሁለቱም አብዶ፣ ለሁለቱም ሰግዶ፣  አይቻልም መቀመጥ! አንዱን ምረጥ!” አልኩት፡፡ ሊሰማኝ ነው፡፡ አሻፈረኝ አለ! እንቢኝ አለ!….. እንደሱ ያለ ልብ አውልቅ ገጥሞኝም አያውቅ!…. ሰዉ ግን ምን ነክቶታል-ጃል! ባሰቀመጡት ቦታ አልገኝም አለሳ፡፡….ባለፈው ሰሞን፣ “እርሳቸው ታላቅ አፍሪካዊ መሪ ናቸው! ባለራእይ ናቸው፡፡” ምናምን እያለ ሲደሰኩርና ሲነዘንዘኝ ሰንብቶ፣ ድንገት ሰውዬው አምልጦት ይሁን አዳልጦት “መጀመሪያም የችሎታ ማነስ እንዳለባቸው እያወቅን ነው ያቆየናቸው፡፡ ገለመሌ” ሲል ጊዜ ወባ እንደያዘው ሰው ምን አንዘፈዘፈው? ድንገት በጠፍ-ጨረቃ ተነስቶ፣ “እርሱን ተወው ባክህ!” ይለኛል እንዴ? መጀመሪያውንስ፣ “አፍሪካዊ ታላቅ መሪ ናቸው! ባለራእይ ናቸው፡፡” እያለ ምን አንጫጫው! ሰውየው ሃዋርያው ዮሐንስን የሆነ መስሎት ነው ወይስ ዮሐንስ ባለረሰዕዩን? የአንዳንድ ጭፍን ቲፎዞዎች ነገር ግን ያስተዛዝባል፡፡ ማታ የቅዱሳን ማህበር አባል የደረጓቸውን ሰዎች፣ በጠዋት ተነስተው የዲያቢሎስ ካቢኔ አባል ለምን ያደርገዋቸዋል? (እኔ እምለው ግን፣ ሰዉ ምን ነክቶታል-ጃል!)……..

ብዙሃን በጥቂቶች አይን

ብዙሃን በጥቂቶች አይን




SHARE THIS
TAGS
Share in top social networks!

ሚያዝያ 30 1997 ዓ.ም የኢትዮዽያ ህዝብ ከዘመናት በሗላ በአገኘው የአንድ የነፃነት ዕድል ሰላማዊ መሆኑን፣ ፍትህ መፈለጉን፣በዲሞክራሲ ማመኑንና ያሻውን የተናገረው ለውጥ ፈላጊነቱን በከፍተኛ ደረጃ ያመላከተበት ለወያኔ ጠባብ ዘረኝነት የጠለቀ ጥላቻ እንዳለው ያሳየበት ቀን ነበረች ሚያዝያ 30 መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ እንደገመቱት ያልተከፋፈለ መሆኑን ያረጋገጠበት ከጦርነት
ይልቅ ሰላማዊ ሽግግር ዘመኑ የሚፈቀደው የፖለቲካ አካሄድ መሆኑን ህዝብ ጠንቅቆ የተረዳ መሆኑን የዘረኛዉ የመለስ ብድን ያወቀበት እንዲሁም ወያኔ እርቃኑን የቀረበት በታሪክ አንድ የነጻነት ቀን ነበር፡፡
ያሰበውና ያለመው በአንድ ቀን እንደ ጉም በኖ የጠፋበት ወዲ ዜናዊ በሳምንቱ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ካየ በሗላ የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ለማፈንና የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም አዲስ አበባን በታንክና በመድፍ ካስወረረው በሗላም ከህፃን እስከ አዋቂ ሴት፣አሮጊት ሳይል በጅምላ የጨፈጨፈው ህዝብን እየዋሸና ባዶ ተስፋ እየሰጠ መቆየት የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም በማወቁ ቀጣዩን የስልጣን ዘመን በሃይል ለማስጠበቅ በማሰብ እነ ሽብሬንና ለሌችንም ንጽሃን ዜጌች ገደለ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ወደ ደዴሳ፣ ዘዋይና ሸዋሮቢት እስር ቤቶች አጋዘ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በራስ መተማመኑ የጠፋበት አምባገነኑ 
ብድን ከምርጫ 97 በፊት በትንሹ ጭልጭል ትል የነበረችውን የዲሞክራሲ ተስፋ ጭራሽኑ አጥፍቶ በሃይል በስልጣን ላይ ለማቆየት በሚያስችለው መልኩ የጦር ሰራዊቱን በአንድ ዘር በመደራጀት ሥራ ተጠመደ፡፡ ቀደም ሲልም ከትግረኛ ቋንቋ በቀር ሌላ የማይናገሩ ከትግራይ አርሶ አደር ልጆች የተመለመሉ የአጋዚ ሰራዊት ምንም አይነት መረጃ የማይደርሰው ምንም ነገር እንዲያቅ የማይፈለግ ለመለስና ለጭፍሮቹ ፍፁም ታማኝ የሆነና የአለቆቹን ትዛዝ ለመፈፀም ሰልቶ የተቀመጠ ቅልብ ጦር ነው፡፡ የአ/አ ህዝብ የጨፈጨፈው ይህ ጦር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሌላም በኩል መደበኛ ሰራዊቱም ቢሆን በከፍተኛ የስልጣን እርከን ውስጥ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የሌላው ቢሄር ተዎላጅ ግን በተለያየ ምክንያት እየተገፋ ከስራው እየተባረረና በሰበብ በአስባቡ ወህኒ እየተወረወረ ዘመኑን በስቃይ ይገፋል፡፡ በኢኮኖሚው በኩል በይበልጥ ከምርጫ 97 በሗላ ኢትዮዽያ የነሱ ብቻ እንደሆነች በመቁጠር ዋናዋናውን ወያኔዎች ትርፍራፊውን ታማኞቻቸው በቡድንም ሆነ በነጠላ በማህበር ተደራጅተው ያገሪቱን አንጡረ ሀብት ይቀራመቱታል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ለዘመናትና በብዙ መሰዋትነት ተከብራ የኖረች አገርን ደሃ ዜጎችዋን እያፈናቀሉ በአራት ትዉልድ ለሚለካ ጊዜ ያዉም ይዞት

Wednesday 30 May 2012

LETTER TO SOUTH SUDAN GOVERNMENT


LETTER TO SOUTH SUDAN GOVERNMENT

MAY 27/2012
H.E. SALVA KIIR,
PRESIDENT,
GOVERNMENT OF SOUTH SUDAN,
JUBA,
SOUTH SUDAN.
Mr. President,
We extend our respectful greetings.
SOCEPP, a human rights organization working for an  end to the violation of
human rights in Ethiopia, has been alarmed by the recent news that refugees
from Gambella region are threatened by a deportation back to Ethiopia, from
where they fled in the first place. The regime of Meles Zenawi, condemned by
the world at large as a gross violator of rights, had in the passed committed a
massacre against the people in Gambella and is currently repressing the people in
the area who oppose the illegal land grab that is going on. Acres and acres of
fertile land in Gambella have been given to Indian, Arab and Chinese firms and
the people displaced by force. The people of Gambella have more than enough
reason to flee.
Mr. President, as a leader of movement and a people that had to endure
oppression and exile we are sure Your Excellency can sympathize with the fate of the refugees from Gambella. The refugees do not deserve deportation (many
Ethiopian refugees deported by the Beshir regime back to Meles Zenawi have
disappeared like Azanaw Demile or died in detention like Major Atanaw Wassie).
They need protection. Hence, we implore you Mr. President to act against any
attempt or measure that will send the refugees back to Ethiopia and a possible
death.
We thank you in advance
Cc: Dr. Riek Machar
Vice President
GOSS,
Juba,

South Sudan. 

ሁሴን! የተረሳ እስረኛ! (ከተስፋዬ ገ/አብ)


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Tuesday, May 29th, 2012 | Posted by zehabesha
ሁሴን! የተረሳ እስረኛ! (ከተስፋዬ ገ/አብ)
13
Share

ለመሆኑ ሁሴን ማነው?
ስለ ሁሴን ታሪክ ያወቅሁት፣ “የቃሊቲ ምስጢሮች” በሚል ርእስ ወሰንሰገድ ገብረኪዳን በቅርቡ ያሳተመውን መፅሃፍ ሳነብ ነው። ወሰንሰገድ ዝዋይ እስር ቤት እንደገባ ነበር ከሁሴን ጋር የተዋወቁት። እንዲህ አወጉ፣
“የስንት አመት ፍርደኛ ነህ?” ሲል ጠየቀኝ።
“አይ ቀላል ነው። ሌላ ክስ ግን አለብኝ” አልኩት።
“ዋናው ጤና ነው። ይኸው እኔ 14 አመት እስርቤት ኖሬያለሁ” አለኝ።
“ምን!?”
በፍፁም ላምነው አልቻልኩም። አይኔን ተጠራጠርኩ። ገና ወጣት ነው። በእኔ እይታ እድሜው ከ30 ወይም ከ35 አይበልጥም። ሰውነቱ ደልደል አለ ወጠምሻ ነው። ምናልባት እያሾፈ ወይም እኔን እያፅናና መሰለኝ።
“ግን አትመስልም”
“አዎ አልመስልም። እኔም ራሴ ካለፈ በሁዋላ መለስ ብዬ ስመለከተው ነው እንጂ፣ ይህን ያህል ጊዜ ያሳለፍኩ አይመስለኝም። ሆኖም 14 የመከራ አመታት እዚህ እስር ቤት አሳልፌያለሁ።” አለኝ አይኑን ቡዝዝ አድርጎ።
“በነፍስ ገብተህ ነው?” በተራዬ ጠየቅሁት። (በግድያ ለማለት ነበር)
“አይደለም። በሌላ ጉዳይ ነው።”
እና ሁሴን ታሪኩን ለወሰንሰገድ አጫወተው።
ሁሴን የኦነግ ተዋጊ ወታደር ነበር። በ1984 በቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ 20 አመት እስር ፈረዱበት። ሁሴን እንዲህ አለው ለወሰንሰገድ፣
“…አመክሮዬ ሲታሰብ የምፈታበት ቀን አልፎአል። እስካሁን መፈታት ነበረብኝ። ‘የፍርድ ቤት ፋይል ቁጥር ጠፍቷል’ ተብዬ ነው የቆየሁት።”
“ጉዳይ አስፈፃሚው ከኮምዩተር ላይ አያይልህም?” ስል ጠየቅሁት።
“በፍርድ ቤት የኮምፕዩተር አሰራር የተጀመረው አሁን ነው። ያኔ ኮምፕዩተር አልነበረም።”
“ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ … ጉዳይህን ፍርድ ቤት ሄዶ የሚከታተልልህ የለም?”
“የ14 አመት ልጅ ሆኜ ነው ተይዤ የታሰርኩትና የተፈረደብኝ። የእናትና የአባቴ ብቸኛ ልጅ ነኝ። ስለያቸው ራሱ አርጅተው ነበር። በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም። 14 አመታት ሙሉ እስረኞች በዘመዶቻቸው ሲጠየቁ እኔ አንድም ጠያቂ አልነበረኝም…”
ጋዜጠኛው ወሰንሰገድ ስለ ሁሴን በሁለት አረፍተነገር ይደመድማል።
“እስከዚያች ቀን ድረስ በብዙ ነገር አዝኜ ይሆናል። በሁሴን ህይወት የተሰማኝ ሃዘን ግን ይህ ነው ተብሎ ለመግለፅ አይቻልም!”
እነሆ! እኔም ተክዤያለሁ። ሁሴን በኦነግነት ተይዞ የታሰረው ሌንጮ ለታ እና ዲማ ነገዎ የኦነግ አመራር በነበሩበት ወቅት ነው። ልክ እንደ ሁሴን በአስርሺህዎች ከወያኔ ማጎሪያ ተወርውረዋል። የት እንደደረሱና ያሉበት የማይታወቅ የተረሱ እስረኞች ቁጥር ዳርቻ የለውም። ይህን እያሰብኩ የወሰንሰገድን መፅሃፍ አጥፌ ክፉኛ ተከዝኩ።

ኦጋዴን ውስጥ ተፈፅሟል ላለው ጥቃት ሂዩማን ራይትስ ዋች የኢትዮጵያ መንግሥትን በግድያና በመብቶች ረገጣ ከሰሰ


ኦጋዴን ውስጥ ተፈፅሟል ላለው ጥቃት ሂዩማን ራይትስ ዋች የኢትዮጵያ መንግሥትን በግድያና በመብቶች ረገጣ ከሰሰ
                                                                          በኦጋዴን የራቅዳና አካባቢዋ ሁከትና የመንግሥት ወገን በሆኑ ኃይሎች የጥቃት እርምጃ ላይ የሂዩማን ራይትስ ዋች መግለጫ ሰጠ፡፡
በ ሃሩን ማሩፍ / ሰሎሞን አባተ | ዋሽንግተን ዲ.ሲ.



More Sharing Services

                                                                                    ፎቶ፡ N/A
ሌስሊ ሌፍኮው - የሂዩማን ራይትስ ዋችን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር

“የኢትዮጵያ መንግሥት አካላት የሆኑ የልዩ ፖሊስ ኃይሎች ባለፈው መጋቢት ኦጋዴን ውስጥ ባካሄዱት ዘመቻ አሥር ሰዎችን እዚያው ገድለዋል” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች ትናንት ከስሷል፡፡
የልዩ ፖሊስ ኃይሉ አድርሶታል ስለተባለው ግድያና ሌሎችም የክፋት አድርጎቶችን የሚመለከተው ዝርዝር መግለጫ የወጣው የሂዩማን ራይትስ ዋች እውነት ፈታሽ ቡድን ወደ አጎራባቿ ሶማሊላንድ ባለፈው ወር ውስጥ ከተላከ በኋላ እንደነበረ ቡድኑ አስታውቋል፡፡                                                                                                                                            “እኛ ባሰባሰብነው መረጃ መሠረት መጋቢት 7 ቀን በራቅዳ ቀበሌ በአንድ የልዩ ፖሊስ ኃይል አባል የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የቀበሌው ሰዎች መሣሪያ አንስተው በወሰዱት የበቀል እርምጃ ሰባት የልዩ ፖሊስ አባላትን ገደሉ… በተከታዩ ቀን የልዩ ፖሊስ አባላት በአካባቢው ባሉ አራት የተለያዩ ቀበሌዎች ተሠማሩና ግድያዎችንና ዘረፋዎችን ጨምሮ እጅግ የከፉ የረገጣ አድራጎቶችን ፈፀሙ” - ሌስሊ ሌፍኮው፡፡
የሂዩማን ራይትስ ዋችን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል ጋሻም ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ራቅዳ ቀበሌ የተፈጠረው ለብዙ ሕይወት መጥፋትና ለብዙ ሰው መጎዳት መንስዔ የሆነው መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም ፈፅሞታል ያሉት ግድያ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
“እኛ ባሰባሰብነው መረጃ መሠረት - አሉ ሌፍኮው - መጋቢት 7 ቀን በራቅዳ ቀበሌ በአንድ የልዩ ፖሊስ ኃይል አባል የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የቀበሌው ሰዎች መሣሪያ አንስተው በወሰዱት የበቀል እርምጃ ሰባት የልዩ ፖሊስ አባላትን ገደሉ…”
ያንን አጋጣሚ ተከትሎ ስለተፈጠረው ሁኔታ ሌፍኮው ሲናገሩ “በተከታዩ ቀን የልዩ ፖሊስ አባላት በአካባቢው ባሉ አራት የተለያዩ ቀበሌዎች ተሠማሩና እጅግ የከፉ የረገጣ አድራጎቶችን ፈፀሙ” ብለዋል፡፡
እነዚህ አድራጎቶች በሥፍራው የተወሰዱ የነፃ እርምጃና የግድያ አድራጎቶችን፣ እጅግ በርካታ ቁጥር ባላቸው ቤቶችና ሱቆች ላይ ተፈፀሙ የተባሉ ዘረፋዎችን የሚያካትቱ እንደሆኑ ሌፍኮ አክለው ተናግረዋል፡፡                                                         ሂዩማን ራይትስ ዋች ስለተፈጠረው ሁኔታ የሶማሌ ክልልም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሣካለት ሌፍኮ አመልክተዋል፡፡
ሌስሊ ሌፍኮን ያነጋገረው የቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ባልደረባም ተመሣሣይ ሙከራዎችን አድርጎ እንደነበርና የሚያነጋገረው ሰው አለማግኘቱን ዘግቧል፡፡

የዕርዳታ ጥሪ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና !!

የዕርዳታ ጥሪ
በዚህ ፎቶግራፍ ላይ የምታዩት ድርቅ አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ ሲባል በደረሰበት የአይምሮ በሽታ ምክንያንት ወገናዊ የሆነ እርዳታችሁን ይሻል።
ይህ አርቲስት በጥሩ የመንግስት አሽቃባጭነትና አድር ባይነት በተለይም ያሳደገው ያበላ ያጠጣውን ህዝብ በክህደት ያደማና ያቆሰለ ሲሆን በቅርቡም ባደረገው ወይም ባወጣው የመንግስት ሙገሳ ኮተት የተነሳ መንግስት ይህ ጉዳይ እውነት ነው ወይስ ይህ ሰው ችግር አለው ሲል ባደረገለት የአይምሮ ህክምና ክትትል ..ግለሰቡ በሚገርም ምክንያት አይምሮው የተነካና ለንግግርም ቃላት አለመምረጡ ምክንያት እና ንግግርን እንደዘበት ትርጉም በማይሰጥ መልኩ መናገር መጀመሩ ከአይምሮው መነካትና መዛግ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑንና በቅርቡም ወደመጣበት አሜሪካን አገር ተመልሶ የበደለውንና በውሸት የቀጠፈውን ህዝብ ፤ በስም ማጥፋት ዘመቻ ያነሳቸውን የሞያ አጋሮች ይቅርታ ካልጠየቀ እና በሰራው ስራ በሀፍረት አንገቱን ደፍቶ መሄድ ካልጀመረ በቅርቡ በሌሎች ላይ ሊፈጠር የሚችለው ዕጣፈንታም ቀማሽ ሊሆን ስለሚችል ከዚህ አድፍጦ ከመጣበት ሞት ለመታደግ የበኩላችሁን እንድታደርጉ ጥሪያቸንን እናስተላልፋለን።የሚደግፈው ግንባር እራሱ ባለማመኑ ፤ትላንትና ማታ የመታህ ድንጋይ  ጠዋት መልሶ ብመታህ ድንጋዩ ሳይሆን ድንጋይ አንተንህ ድንጋይ፤ ብለው አሽቀጥረው ወርወሩት።
ለወገን ደራሽ ወገን ነውና !! \

Tuesday 29 May 2012

ኢትዮጵያዊው የባህል ዘፋኝ ቻላቸው አሸናፊ በተወለደ በ47 ዓመቱ አረፈ



May 29, 2012
By Bawza Staff
Share
 ተወዳጁ የባህል ሙዚቃ ድምፃዊ ቻላቸው አሸናፊ አረፈ:: በ1957 ዓ/ም በደብረታቦር የተወለደው ድምፃዊው በተለይ ከ3 አመት በፊት ባሳተመው “ገራገር” በሚለው አልበሙ በተለያዩ የአለማት ክፍል ተዘዋውሮ የመስራት እድልን አስገኝቶለት ነበር:: በጣም አሳዛኙ ነገር ደግሞ ቻላቸው በዚህ በያዝነው ወር ነበር አዲሱን የሙዚቃ አልበም ለገበያ ያበቃው:: ይህ በሆነበት ሰዐት ነው እንግዲህ ቻላቸውን በተወለደ በ47 አመቱ ሞት የቀደመው::
ነፍስህን በገነት ያኑርልን!!!

Ethiopian Singer Chalachew Ashenafi  Died at age of  47

Singer and masinqo (one-string fiddle) player Chalachew Ashenafi was born 47 years ago in Debre Tabor, close to the city of Gondar in Ethiopia where most of the famous Azmaris originate from.



Share











Tags: Chalachew Ashenafi, ETHIOPIA, music

ኢህአዴግ በደንብ ጎረመሰ…! (አቤ ቶኪቻው)


ኢህአዴግ በደንብ ጎረመሰ…! (አቤ ቶኪቻው)
SHARE THIS
       
TAGS

abetokichaw@gmail.com

በመጀመሪያም

ጋሽ ግርማን አየኋቸውኮ!

በዛን ሰሞን “ሞቱ” ተብሎ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ከተውን የነበሩት መቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ድንገት ተከስተው “እንኳን ለግንቦት ሃያ አደረሳችሁ” ብለው ፡”ሰርፕራይዝ” አድርገውናል። ትንሽ ሸንቀጥ ቢሉም እየተነፈሱ እንደሆነ በማየታችን እኛም ከመቀመጫችን ብድግ ብለን “እንኳን አብሮ አደረሰን!” ብለናቸዋል።

ኢህአዴግ አዲሳባን ከተቆጣጠረ 21 ዓመት ሞላው። ይህንንም ለማረጋገጥ ዛሬ ጠዋት አዲሳባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶላታል። ለገና እና ለመውሊድ 9 ጊዜ ብቻ እንጂተኮስ የተወሰነው መድፍ ለኢህአዴግ ልደት ሃያ አንድ ግዜ መተኮሱ መንግስት “ከሁሉ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው” ሊለን ፈልጎ እንደሆነ ግልፅ ነው።

እንግዲህ ኢህአዴግ አሁን በደንብ ጎረመሰ ማለት ነው። ይህ ወቅት ጡንቻ የሚፈረጥምበት ጢም የሚቀመቀምበት ከመሆኑም በላይ እግዜር ላልባረከው፤ ልብ የሚነፋበት ጆሮ የሚደፈንበት አስቸጋሪ ወቅት ነው። በዚህ ዕድሜ ላይ ያለ ያልተባረከ ጎረምሳ ኮረዳዎች “ሳመኝ” ሲሉት እንጂ አዋቂዎች “ስማኝ” ሲሉት ጥሪ አይቀበልም። ከላይ ከላይ መናገር እና ከኔ በላይ ላሳር ማለት ልዩ ባህሪያቱ ናቸው። (አይ ጉርምስና!) እናም ኢህሃዴግ አሁን ዋናው የአፍላ ጉርምስና ወቅቱ ላይ ይገኛል። በአራዶች ቋንቋ “ፍንዳታ” ሆነ የሚባለው ማለት ነው። ወደ ጨዋታችን ዘልቀን ከመግባታችን በፊት “ኢህአዴግዬ ጉርምስናውን በቅጡ ያድርግልህ” ብለን እንመርቀዋለን!

“ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬድዬ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል ግንቦት 20 ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት አመተ ምህረት!” የተባለ ጊዜ አብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነትን እና አባታችን ኢህአዴግን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለው ቴሌቪዥናችን በአሁኑ ግዜ ዋና የኢህአዴግ ፓስር ሆኖ ስብከቱን ሲያሰማ ውሎ ያድራል። በተለይ ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉርምስናውን ሲያከበር ኢቲቪ ውዳሴ እና ዝማሬ በማዝነብ የሚስተካከለው አልተገኘም። እኛም በተለይ ከህዝቡ ዘንድ የተደበቀውን ጥጋብ ለመየት የታደለው ኢቲቪ ይህንን ይመለከት ዘንድ የተቻለው “እንደምን ያለ አብዮታዊ ዴሞክራሲ መንፈስ ቢሰርፅበት ነው!?” ስንል አድንቀናል።

ወ/ሮ አዜብ ያለ አግባብ መሬት መውሰዳቸውን ያጋለጠው የቡራዩ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ታሰረ


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Tuesday, May 29th, 2012 | Posted by zehabesha
ወ/ሮ አዜብ ያለ አግባብ መሬት መውሰዳቸውን ያጋለጠው የቡራዩ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኛ ታሰረ
15
Share

(ፍኖተ ነጻነት) በቅርቡ በቡራዩ ከተማ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በተመራው ሙሰኞችን የማጋለጥ ስብሰባ ላይ “ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያለ አግባብ በወንድማቸው ስም መሬት ወስደዋል” ብሎ ያጋለጠው
የማዘጋጃ ቤቱ ሠራተኛ መታሰር በከተማው መነጋገሪያ መሆኑን በአካባቢው ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች ለሪፖርተራችን ገለፁ፡፡ ነዋሪዎች እንደሚሉት “መድረኩ የተዘጋጀው
በቡራዩ አካባቢ የመሬት ቅርምት ተፈጽሟል፤ በመንግስትና በህዝብ መሬት ግለሰቦች አላግባብ በልጽገዋል፤ ከፍተኛ ሙስና ተፈጽሟል ተብሎ ነበር” ይላሉ፡፡
ሆኖም ግን ይላሉ ምንጮቻችን “የመድረክ አመራሩ ተሰብስበው በአካባቢው ኃላፊዎችና ከቁጥር በማይገቡ ሙሰኞች ላይ ብቻ ጣቱን እንዲቀስር እንዲያጋልጥ ግፊት ይደረግ ነበር፡፡
ይህንን የተገነዘበው አቶ ኃይሉ ንጉሴ የተባለው የማዘጋጃ ቤቱ የፋይናንስ ሠራተኛ ተነስቶ ትኩረቱን ለምን በትንንሾቹ ብቻ ታደርጋላችሁ፡፡ ሙስናን በቁርጠኝነት የምትታገሉ ከሆነ ወደ
ላይም አትመለከቱም፡፡ በዚህ በከተማችን ወ/ሮ አዜብ መስፍን በወንድማቸው ስምመሬት ወስደዋል፡፡ ለምን አይጣራም? ለምን እሳቸውም አይጠየቁም” ብሎ ተናግሯል፡፡
በወቅቱ ስብሰባውን የሚመሩት ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ “ጥቆማው አንድና አንድ ነው፡፡ ጥቆማው በማስረጃ መረጋገጥ አለበት፡፡ ዝም ብሎ መጠቆም አይደለም፡፡” እያሉ ጥቆማውን ለማጣጣልና ለማንቋሸሽም ሞክረዋል፡፡ ይህ ሲገርመን በቅርቡ ጠቋሚውን በሙስና ትፈለጋለህ ተብሎ ታስሯል፡፡ መንግስት በተለይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሙስናን ለመዋጋት ያለውን ቁርጠኝነትና ጥያቄውስጥ የሚከት ከመሆኑም በላይ በመንግስት ላይ ያለን እምነት እየተሸረሸረ ነው፡፡” ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
አቶ ኃይሉ ንጉሴ በገፈርሳ ቡራዩ ውስጥ ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቡራዩ ማዘጋጃ ቤት የፋይናንስ ሠራተኛ ነበር ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአሁኑ ጊዜ በአገራችን
ያለአግባብ ከፍተኛ ሀብት አፍርተዋል ተብሎከሚታሙት ግለሰቦች ውስጥ አንዷ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

35 ሺህ ብር የወጣበት የመለስ ዜናዊ ግዙፍ ምስል ከአዋሬ አደባባይ ተሰረቀ


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Tuesday, May 29th, 2012 | Posted by zehabesha
35 ሺህ ብር የወጣበት የመለስ ዜናዊ ግዙፍ ምስል ከአዋሬ አደባባይ ተሰረቀ
11
Share
(ፍኖተ ነጻነት) በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡ በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስል “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግና” የሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት
ጋዜጣ ተናግሯል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ገለፁት ምስሉ ተተክሎ የቆየው ለአምስት ቀናት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የምስሉን መጥፋት ግራ አጋቢ ያደረገው የአቶ መለስ ፎቶ በላዩ ላይ የታተመበት ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን መሰረቁ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአቶ መለስን ተክለ ስብዕና የሚገነቡ ምስሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተበራክተዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ በየትኛውም የአቶ መለስ ምስል ላይ ጉዳትም ሆነ ጥፋት ደርሶ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡
አቶ ኢሳያስ ለምስሉ ከ35,000 (ሰላሣ አምስትሺህ) ብር በላይ ማውጣቱን ገልፃጿል፡፡ አቶ ኢሳያስ አክሎም 28 ካሬ የሚሆነው ይህው ምስል በመጥፋቱ እንደተደናገጠ ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡ ይኽው የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምስል ከተሠቀለበት ቦታ ተገንጥሎ የተወሰደ ሲሆን በዘመናዊ ዲጂታል የህትመት መሣሪያ በኢሣያስ ማስታወቂያ ታትሞ በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኢሳያስ ማስታወቂያ ባለቤት ወጣት ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገረው የምስሉ መጠን 7 ሜትር በ4 ሜትር መሆኑን በመግለፅና ስራውን ለእይታ ለማብቃትና አጠቃላይ የፍሬም ሥራውን
በማካተት 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ወጭ እንደተረገበት ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚኒስትሩ ምስል ግዙፍ ሆኖ ከፊት ለፊት አሁን በመገንባት ላይ ያለው የህዳሴው ግድብ በአንድ ላይ ሆኖ ከምስሉ ስር “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ
ጀግና” የሚል ፅሑፍ እንደነበረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ነዋይ ደበበ ኢትዮጵያ በመመለሱ ደስተኛ አለመሆኑን እየገለጸ ነው


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Tuesday, May 29th, 2012 | Posted by zehabesha
ነዋይ ደበበ ኢትዮጵያ በመመለሱ ደስተኛ አለመሆኑን እየገለጸ ነው
13
Share

(ዘ-ሐበሻ) አሜሪካን ሃገር ያለውን ትዳሩን እና ልጆቹን በትኖ ኢትዮጵያ ለመኖር የገባው ድምዳዊ ነዋይ ደበበ አዲስ አበባ ገና ከመግባቱና ከኤርፖርት ወጥቶ ከተማውን ሳይዘዋወርና ሳይመለከት ለራዲዮ ፋና በሰጠው ቃለምልልስ “አዲሳባ ተለውጣለች፤ የሕዝቡም የኑሮ ሁኔታ ተለውጧል” የሚል ቃለ ከሰጠ በኋላ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ሊያደርጋቸው የነበሩት የሙዚቃ ኮንሰርቶች በተመልካች እጦት የተነሳ ተስተጓጉለውበታል።
ወደ ኢትዮጵያ “እነአስቴር አወቀን፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺዎታን እና ሌሎች ባለሙያዎችን ተከትዬ ገብቼ በአሁኑ ወቅት ሙዚቃዬን የሚያቀናብርልኝ እንኳ አጥቻለሁ” በሚል ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሰይፉ ፋንታሁን የራድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ የተናገረው ነዋይ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ያን ቃለምልልስ በወያኔው ሚዲያ ራድዮ ፋና ከሰጠ በኋላ ባደረገው የጊዮን ሆቴል የሙዚቃ ዝግጅት ላይ 20 ሰው የማይሞላ ተገኝቶ በነሱም የለስላሳ ጠርሙስ መድረክ ላይ “ሃገሬን አልረሳም” እያለ እየዘፈነ ሲወጣ እንደተወረወረበት የቅርብ አመታት ትዝታ ነበር።

“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ”


“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ)
SHARE THIS
       
TAGS


“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com

“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com
በጠቅላይ ቤተክህነት የሚታተመው “ዜና ቤተክርስቲያን” የተሰኘ ጋዜጣ፤ ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ በሚል ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ጳጳሳቱ ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን ሲኖዶስ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም በወሰነው መሰረት ኮሚቴው እንደተቋቋመ ምንጮች ጠቆሙ፡፡  ጋዜጣው በርዕሰ አንቀፁ “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ ያሰፈረው  ፅሁፍ፤ የቤተክርስትያኒቱን ሕግ ያልጠበቀና የሐይማኖቱን አንድነት ለመናድ ያለመ ነው ሲሉ  ጳጳሳቱ እንደተቃወሙት ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተቋቋመውን ኮሚቴ የሰሜን ጐንደር ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ናትናኤልና ሌሎች ጳጳሳት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ ምሁራን እንደሚመሩት የጠቆሙት ምንጮች፤ ኮሚቴው የምርመራውን ውጤት በመጪው ጥቅምት ወር በሚካሄደው የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ማቅረብ ይጠበቅበታል ብለዋል፡

ጋዜጣው በ56ኛ ዓመት፣ ቁጥር 125 እትም፤ በርእሰ አንቀፁ ላይ ባወጣው ፅሁፍ፤ በ1991 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣው ሕገቤተክርስትያን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ምቾት እንጂ የቤተክርስትያኒቱን ጥቅም አልጠበቀም፤ ለጳጳሳት ነፃ ምግብና ሕክምና እየተሰጠ ለሌሎች አገልጋዮች፣ ካህናትና ሠራተኞች መከልከሉ አግባብ አይደለም ሲል  ተችቷል፡፡ጳጳሳት ለቤተክርስትያን ከተሰጠ ገንዘብ የግል ቪላ ሰርተው ያከራያሉ፣ ዘመናዊና ለነሱ የማይገቡ መኪኖችን በቤተክርስትያን ገንዘብ ይገዛሉ፣ የቤተክርስትያኒቱ ንብረት የሆኑ ቤቶች ሸጠው ወደ ግል ኪሳቸው ይከታሉ፤በማለት አላግባብ በልጽገዋል ሲል ጋዜጣው ይነቅፋል፡፡ ጳጳሳት በሞት ሲለዩ ንብረታቸውን ለቤተክርስትያን ማውረስ ሲገባቸው ለግለሰቦች ያወርሳሉ የሚለው ዘገባው፤ በጳጳሳት ምርጫና ሲመት ላይ ያለሕዝብና ካህናት ተሳትፎ በሲኖዶስ ብቻ ይሾማሉ ሲልም ይተቻል፡፡
በውጭ ሀገራት በተለይ በአሜሪካ ለረዥም አመታት በመኖር ዜግነት ያገኙ ሰዎች በጳጳስነት  መሾማቸውን የጠቆመው ጋዜጣው፤ አንድ እግራቸው አሜሪካ ሌላው ኢትዮጵያ በመሆኑ ሹመታቸው አግባብ አይደለም ብሏል፡፡

Monday 28 May 2012

‘paramilitary force’ Execute 10 people in Ethiopia


‘paramilitary force’ Execute 10 people in Ethiopia
Posted by admin on May 28, 20120 Comment
Human Rights Watch (Nairobi) – An Ethiopian government-backed paramilitary force summarily executed 10 men during a March 2012 operation in Ethiopia’s eastern Somali region. Detailed information on the killings and other abuses by the force known as the “Liyu police” only came to light after a Human Rights Watch fact-finding mission to neighboring Somaliland in April.
On March 16 a Liyu police member fatally shot a resident of Raqda village, in the Gashaamo district of Somali region, who was trying to protect a fellow villager. That day, men from Raqda retaliated by killing seven Liyu police members, prompting a reprisal operation by dozens of Liyu police in four villages on March 16 and 17. During this operation the Liyu police force summarily executed at least 10 men who were in their custody, killed at least 9 residents in ensuing gunfights, abducted at least 24 men, and looted dozens of shops and houses.
“The killing of several Liyu police members doesn’t justify the force’s brutal retaliation against the local population,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director at Human Rights Watch. “The Liyu police abuses in Somali region show the urgent need for the Ethiopian government to rein in this lawless force.”
The Ethiopian government should hold those responsible for the killings and other abuses to account and prevent future abuses by the force.

በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ – በግጭቱ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል


በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ – በግጭቱ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል

Posted by admin on May 28, 20120 Comment
ፒያሳ በተለምዶ ‹‹አትክልት ተራ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት በአከራይና ተከራይ ውል ምክንያት በሻጮችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ሳቢያ ሰዎች ታሰሩ።
ትናንት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ገደማ ላይ የቀበሌው መስተዳድሮች ፖሊሶችን ይዘው በስፍራው በመምጣት በመደባቸው ላይ ይሰሩ ከነበሩት አትክልት ሻጮች መካከል ቁጥራቸው 15 ያህል የሚገመቱትን ‹‹ቦታችሁን ለቃችሁ ውጡ›› የሚል ትእዛዝ እንዳቀረቡላቸው ታውቋል፡፡ ‹‹መንግስት ከወራቶች በፊት አውጥቶት በነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ከአከራዮች ጋር ውል አቋርጠን ነበር። ቀበሌውም ‹በእናንተ ምክንያት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለአከራዮች ምንም እንዳትከፍሉ› የሚል ሀሳብ ሰጥቶን ነበር›› የሚሉት እነዚህ ሻጮች ‹‹የቀበሌው መስተዳድር ኃላፊነት ወስዶ በሕጋዊ መንገድ ሕጋዊ ወረቀት የሚሰጠንና የሚረከበን ከሆነ እንለቃለን›› ማለታቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በወቅቱ የቀበሌው መስተዳድር ‹‹መጀመሪያ እዚህ ስትገቡ ወረቀት ማን ሰጣችሁ? ለእናንተ ወረቀት አያስፈልጋችሁም›› ካላቸው በኋላ በመሀል ፖሊሶች አንዱን አትክልት ሻጭ በጉልበት ጎትተው መደብደብ እንደጀመሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከዚያም ሰኢድ ሹመካ የተባለውን ልጅ ፖሊሶች ጎትተው ሲደበደቡት በስፍራው የነበረ ሕዝብ እንደጮኸባቸውና ከፖሊሶች ጋርም ሻጮች በዱላ ወደ መደባደብ እንዳመሩ እነኚህ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
ሰኢድም ‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ አልሄድም›› በማለቱ ፖሊሶች በጋራ ጐትተው እየደበደቡት ቀበቶውን ፈትተው ሁለት እጆቹን በካቴና በማሰር የፖሊስ መኪና ላይ እንደጫኑት ምንጮች አስረድተዋል። በዚህ ወቅትም በአካባቢ የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በጩኸት አካባቢውን መረበሻቸውን እማኞች ተናግረዋል። ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት የጀመረው ረብሻ ከቀኑ 7፡30 ገደማ ማቆሙን የሚገልፁት ምንጮች ሶስት አትክልት ሻጮች፣ የተወሰኑ ገበያተኞችና ፖሊሶች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም 15 ያህል ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አስረድተዋል።
(ምንጭ ፍትህ ጋዜጣ)

7
Share

Sunday 27 May 2012

የቴዲ አፍሮ "ጥቁር ሰው" ሙዚቃ



የቴዲ አፍሮ "ጥቁር ሰው" ሙዚቃ

                                         ዘነበ በቀለ
        ምንም እንኳ የባህል ሙዚቃ በዋናነት መለኪያው ሀገራዊ የግንዛቤ ስልት ቢሆንም አንድን ሙዚቃ
ለመገምገም በርካታ መለኪያዎችን ማስቀመጥ የሚያስፈልገው መሆኑ ግን ሀቅ ነው። በዚህም ምክንያት የቴዲን
ሙዚቃ ስንገመግም መለኪያዎቻችንን በግልፅ ማስቀመጥ ግዴታ ነው። እንዲያው በደፈናው ደስ ይለኛል፣
አይለኝም፣ ብሎ መደምደም ይቻል ይሆናል፣ ነገርግን እንደመገምገሚያ መሳሪያ ተደርጎ ሊወሰድና ወደ
ትክክለኛም ግንዛቤ ሊመራ ይችላል ብሎ መገመት ስህተት ነው። በአውሮጳውያኑ ሙዚቃ አገማገም ስልት
መሰረትነት ላይ ስንነሳ በመለኪያነት የምናስቀምጣቸው ነገሮች አሉ ከነዚህም መሃል የሚከተሉት ይገኛሉ።

1) ባህላዊ የግምገማ ዘዴ፡ ይህ አይነቱ ግምገማ በተናጠል ዜማ ይዘት ላይ ተመስርቶ የሚፈርጁት ነው።
በሞዳል ሴሰትሙ ንብረት ላይ እንጂ! በሲስተሙ ጠባዮች ላይ የሚደረግ ግምገማ አይሆንም።
2) ሼንኬሪያን የግምገማ ዘዴ፡ በኖታዎቹ ዝምድና ላይ የሚያተኩር ነው።
3) ፎርማል የሆነ የግምገማ ዘዴ፣ የሙዚቃውን ክፍሎች ለያይቶ መመልከት ነው

Family in Norway fears Ethiopia return


Family in Norway fears Ethiopia return

Posted by  on May 27, 2012by Lyndsey Smith
The Foreigner (Oslo) – Tewelde and Saba have lived in Norway for five years and have two children, Haniel (4), and Nathan (1). They have now been told that they must return to Ethiopia and have chosen not to leave voluntarily.
“We came because of problems with the authorities, so anything can happen if we go back now”, Mr Habtom Araya told NRK.

One of the huge allies organized by Ethiopians against the Deportation of the refugees from Norway

Tewelde is worried that he and his wife could be put in prison, tortured, or killed if they return, as they do not support the regime. They fear their children will be made orphans.
They currently have a lawsuit against the Norwegian state, among some 440 Ethiopians to do this. Girum Zeleke, who teaches social work at Stavanger University, is representing them.
“The situation of human rights has been deteriorating in Ethiopia. The regime exerts violence, torture and murder on its own people. This drives people to come to Norway, people who fear for their own lives,” he said.
Tewelde fears that the police could come at any time to force them to leave. He, along with the others, is waiting for a response from the Attorney General about their lawsuit.
Norway was the first country to in Europe to sign a return agreement with Ethiopia. Girum Zeleke is hoping that the lawsuit will help people to stay.
“I have great difficulty accepting that it [forced return] will happen, and we will do what we can to ensure that it does not take place.”
Deputy Minister of Justice Pål K. Lønnseth understands the children rouse peoples’ engagement, but stressed it is important to “avoid facilitating a regulatory framework in which children can become a tool to get to stay here, when the family did not meet the requirements for this intitially.”

የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ በእሳት ቃጠሎ ወደመ


አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) በኢትዮ-ሳውዲው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ እንደተገነባ የሚነገርለትና በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ ቤት ግንቦት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. በእሳት ቃጠሎ የወደመ መሆኑ ታወቀ፡፡ ቃጠሎው የደረሰው ከሁለት ወራት በላይ ሲያጋጥማት በነበረው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መዋዠቅ መሆኑንና እንዲስተካከል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ስታመለክት ብትቆይም፣ መፍትሔ የሚሰጣት በመጥፋቱ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

አርቲስት ሐመልማል አባተ
አርቲስቷ ለጋዜጣው እንደገለጸችው፣ በቤቱ መቃጠል እጅግ አስፈላጊዋ የነበሩ ንብረቶችና መተኪያ የሌላቸው ሰነዶች ወድመውባታል፡፡ ‹‹እንኳን የሰው ሕይወት አልጠፋ፤›› በማለት መናገሯንም ሪፖርተር ጨምሮ ዘግቧል፡፡
ለኮርፖሬሽኑ ከሁለት ወራት በላይ ደጋግማ ብታመለክትም ምንም መፍትሔ ማጣቷን ለጋዜጣው የገለጸችው አርቲስቷ፣ ቤቱ በራሱ ጊዜ በመጋል የቧንቧ ውኃ ሳይቀር እያፈላ ሲያስቸግራት ቆይቶ ድንገት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሊነድ መቻሉን አስታውሳ፣ ቤቱ በእሳት መያያዙ የማያስገርምና ቀድሞም ቢሆን መቃጠሉ እንደማይቀር በስጋት ይጠበቅ እንደነበር ለጋዜጣው ገልጻለች፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከደንበኞቹ የሚፈልገውን እንደሚያገኘው ሁሉ በምላሹ ደንበኞቹን ለመርዳት አለመቻሉና ለአደጋ መንስዔ የሆኑ አጋጣሚዎችን እንዲያስተካክል ጥሪ ሲደረግለት ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘናት ተናግራለች፡፡
በ500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቪላ በእሳት ሲያያዝ ጎረቤቶችና የአካባቢ ሰዎች ከእሳት አደጋ መከላከያ ድርጅት ጋር በመሆን ሊያጠፉት ሞክረዋል፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል ምክንያት የተነሳውን ቃጠሎ ከመስመር አለያይተው ለማጥፋት የሞከሩት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ሠራተኞች፣ የኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠናል ባሉበት አፍታ ከባድ እሳት መልሶ መንበልበሉ እንዳደናገጣቸው በመግለጽ ክስተቱን ታስታውሳለች፡፡ በዚህም ሳቢያ ቪላው ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ ሊሆን ችሏል ብላለች፡፡
በአርቲስቷ ቤት ላይ የደረሰውን ቃጠሎ በሚመለከት ሪፖርተር ጋዜጣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽን አነጋግሯል፤ ‹‹ቃጠሎ መድረሱን የሰማነው ቆይቶ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው በኮርፖሬሽኑ ስህተት መሆን አለመሆኑን በማጣራት ላይ ነን፡፡ አርቲስቷ ቃጠሎ በደረሰ በ24 ሰዓታት ውስጥ አመልክታ ከሆነና ችግሩ የተከሰተው በኮርፖሬሽኑ ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ካሳ ይከፈላታል፤›› ማለታቸውን ሪፖርተር ጨምሮ ዘግቧል፡፡