"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 29 May 2012

35 ሺህ ብር የወጣበት የመለስ ዜናዊ ግዙፍ ምስል ከአዋሬ አደባባይ ተሰረቀ


About Us
Jobs (minnesota)
Short Stories
Poem
Video
Free Media
American Law
Contact Us

Tuesday, May 29th, 2012 | Posted by zehabesha
35 ሺህ ብር የወጣበት የመለስ ዜናዊ ግዙፍ ምስል ከአዋሬ አደባባይ ተሰረቀ
11
Share
(ፍኖተ ነጻነት) በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች መሰረቁ ተገለፀ፡፡ በኢሳያስ ማስታወቂያ ታትሞ የተተከለው የአቶ መለስ ምስል “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደደፈረ ጀግና” የሚል መፈክር የያዘ እንደነበር የድርጅቱ ባለንብረት አቶ ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት
ጋዜጣ ተናግሯል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ገለፁት ምስሉ ተተክሎ የቆየው ለአምስት ቀናት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የምስሉን መጥፋት ግራ አጋቢ ያደረገው የአቶ መለስ ፎቶ በላዩ ላይ የታተመበት ከመሆኑ በተጨማሪ በቀን መሰረቁ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአቶ መለስን ተክለ ስብዕና የሚገነቡ ምስሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተበራክተዋል የሚሉት ነዋሪዎቹ በየትኛውም የአቶ መለስ ምስል ላይ ጉዳትም ሆነ ጥፋት ደርሶ እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡
አቶ ኢሳያስ ለምስሉ ከ35,000 (ሰላሣ አምስትሺህ) ብር በላይ ማውጣቱን ገልፃጿል፡፡ አቶ ኢሳያስ አክሎም 28 ካሬ የሚሆነው ይህው ምስል በመጥፋቱ እንደተደናገጠ ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡ ይኽው የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምስል ከተሠቀለበት ቦታ ተገንጥሎ የተወሰደ ሲሆን በዘመናዊ ዲጂታል የህትመት መሣሪያ በኢሣያስ ማስታወቂያ ታትሞ በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኢሳያስ ማስታወቂያ ባለቤት ወጣት ኢሳያስ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገረው የምስሉ መጠን 7 ሜትር በ4 ሜትር መሆኑን በመግለፅና ስራውን ለእይታ ለማብቃትና አጠቃላይ የፍሬም ሥራውን
በማካተት 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ወጭ እንደተረገበት ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚኒስትሩ ምስል ግዙፍ ሆኖ ከፊት ለፊት አሁን በመገንባት ላይ ያለው የህዳሴው ግድብ በአንድ ላይ ሆኖ ከምስሉ ስር “በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ
ጀግና” የሚል ፅሑፍ እንደነበረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment