"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 28 May 2012

በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ – በግጭቱ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል


በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ – በግጭቱ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል

Posted by admin on May 28, 20120 Comment
ፒያሳ በተለምዶ ‹‹አትክልት ተራ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት በአከራይና ተከራይ ውል ምክንያት በሻጮችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ሳቢያ ሰዎች ታሰሩ።
ትናንት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ገደማ ላይ የቀበሌው መስተዳድሮች ፖሊሶችን ይዘው በስፍራው በመምጣት በመደባቸው ላይ ይሰሩ ከነበሩት አትክልት ሻጮች መካከል ቁጥራቸው 15 ያህል የሚገመቱትን ‹‹ቦታችሁን ለቃችሁ ውጡ›› የሚል ትእዛዝ እንዳቀረቡላቸው ታውቋል፡፡ ‹‹መንግስት ከወራቶች በፊት አውጥቶት በነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ከአከራዮች ጋር ውል አቋርጠን ነበር። ቀበሌውም ‹በእናንተ ምክንያት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለአከራዮች ምንም እንዳትከፍሉ› የሚል ሀሳብ ሰጥቶን ነበር›› የሚሉት እነዚህ ሻጮች ‹‹የቀበሌው መስተዳድር ኃላፊነት ወስዶ በሕጋዊ መንገድ ሕጋዊ ወረቀት የሚሰጠንና የሚረከበን ከሆነ እንለቃለን›› ማለታቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በወቅቱ የቀበሌው መስተዳድር ‹‹መጀመሪያ እዚህ ስትገቡ ወረቀት ማን ሰጣችሁ? ለእናንተ ወረቀት አያስፈልጋችሁም›› ካላቸው በኋላ በመሀል ፖሊሶች አንዱን አትክልት ሻጭ በጉልበት ጎትተው መደብደብ እንደጀመሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከዚያም ሰኢድ ሹመካ የተባለውን ልጅ ፖሊሶች ጎትተው ሲደበደቡት በስፍራው የነበረ ሕዝብ እንደጮኸባቸውና ከፖሊሶች ጋርም ሻጮች በዱላ ወደ መደባደብ እንዳመሩ እነኚህ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
ሰኢድም ‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ አልሄድም›› በማለቱ ፖሊሶች በጋራ ጐትተው እየደበደቡት ቀበቶውን ፈትተው ሁለት እጆቹን በካቴና በማሰር የፖሊስ መኪና ላይ እንደጫኑት ምንጮች አስረድተዋል። በዚህ ወቅትም በአካባቢ የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በጩኸት አካባቢውን መረበሻቸውን እማኞች ተናግረዋል። ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት የጀመረው ረብሻ ከቀኑ 7፡30 ገደማ ማቆሙን የሚገልፁት ምንጮች ሶስት አትክልት ሻጮች፣ የተወሰኑ ገበያተኞችና ፖሊሶች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም 15 ያህል ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አስረድተዋል።
(ምንጭ ፍትህ ጋዜጣ)

7
Share

No comments:

Post a Comment