"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 29 May 2012

“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ”


“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ)
SHARE THIS
       
TAGS


“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com

“የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” (ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ) www.maledatimes.com
በጠቅላይ ቤተክህነት የሚታተመው “ዜና ቤተክርስቲያን” የተሰኘ ጋዜጣ፤ ጳጳሳት ያልተገባ ጥቅም ያገኛሉ በሚል ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ጳጳሳቱ ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሲሆን ሲኖዶስ ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም በወሰነው መሰረት ኮሚቴው እንደተቋቋመ ምንጮች ጠቆሙ፡፡  ጋዜጣው በርዕሰ አንቀፁ “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተክርስቲያን ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ ያሰፈረው  ፅሁፍ፤ የቤተክርስትያኒቱን ሕግ ያልጠበቀና የሐይማኖቱን አንድነት ለመናድ ያለመ ነው ሲሉ  ጳጳሳቱ እንደተቃወሙት ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ጉዳዩን እንዲያጣራ የተቋቋመውን ኮሚቴ የሰሜን ጐንደር ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ናትናኤልና ሌሎች ጳጳሳት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ ምሁራን እንደሚመሩት የጠቆሙት ምንጮች፤ ኮሚቴው የምርመራውን ውጤት በመጪው ጥቅምት ወር በሚካሄደው የሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ማቅረብ ይጠበቅበታል ብለዋል፡

ጋዜጣው በ56ኛ ዓመት፣ ቁጥር 125 እትም፤ በርእሰ አንቀፁ ላይ ባወጣው ፅሁፍ፤ በ1991 ዓ.ም ተሻሽሎ የወጣው ሕገቤተክርስትያን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ምቾት እንጂ የቤተክርስትያኒቱን ጥቅም አልጠበቀም፤ ለጳጳሳት ነፃ ምግብና ሕክምና እየተሰጠ ለሌሎች አገልጋዮች፣ ካህናትና ሠራተኞች መከልከሉ አግባብ አይደለም ሲል  ተችቷል፡፡ጳጳሳት ለቤተክርስትያን ከተሰጠ ገንዘብ የግል ቪላ ሰርተው ያከራያሉ፣ ዘመናዊና ለነሱ የማይገቡ መኪኖችን በቤተክርስትያን ገንዘብ ይገዛሉ፣ የቤተክርስትያኒቱ ንብረት የሆኑ ቤቶች ሸጠው ወደ ግል ኪሳቸው ይከታሉ፤በማለት አላግባብ በልጽገዋል ሲል ጋዜጣው ይነቅፋል፡፡ ጳጳሳት በሞት ሲለዩ ንብረታቸውን ለቤተክርስትያን ማውረስ ሲገባቸው ለግለሰቦች ያወርሳሉ የሚለው ዘገባው፤ በጳጳሳት ምርጫና ሲመት ላይ ያለሕዝብና ካህናት ተሳትፎ በሲኖዶስ ብቻ ይሾማሉ ሲልም ይተቻል፡፡
በውጭ ሀገራት በተለይ በአሜሪካ ለረዥም አመታት በመኖር ዜግነት ያገኙ ሰዎች በጳጳስነት  መሾማቸውን የጠቆመው ጋዜጣው፤ አንድ እግራቸው አሜሪካ ሌላው ኢትዮጵያ በመሆኑ ሹመታቸው አግባብ አይደለም ብሏል፡፡
ፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 4፣ ንዑስ አንቀጽ 39ኝን በመጥቀስም ጳጳሳት ለአበአበው (ፓትርያርክ) አለመታዘዛቸው አግባብ አይደለም ይላል – በዘገባው፡፡
የ1991ዱ ሕገቤተክርስትያን እንዲሻሻል የጠቆመው ጋዜጣው፤ ይህንና በመቃወም ድምጽ የሚያሰሙ ጳጳሳትን በተመለከተ ባሰፈረው ፅሁፍ፤ “…በነፃ ፕሬሶች ውዝግብ በመፍጠር የራሳቸውንና የቤተክርስትያኒቱን ገበና ያጋልጣሉ፡፡ የቤተክርስትያን ተከታይ የሆነው ወጣት ትውልድም ተቀናጅቶና አንጃ ለይቶ በሆነ ባልሆነው በነፃው ፕሬስ መወዛገብ የጀመረው ከነዚሁ አባቶች ተምሮ ነው፡፡
ይህም ሲባል ፓትርያሪኩ ከሕግ በላይ የፈለገውን ያድርግ ማለት አይደለም፡፡” በማለት ተችቷል፡፡
የጋዜጣው ፅሁፍ አስነዋሪ ነው ያሉት ጳጳሳቱ፤ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብፁአን ጳጳሳት አይወክልም፤ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ሆነው ቤተክርስትያኒቱን ለመሰነጣጠቅ የሚጣጣሩ የባዕድ ተወካዮች በጉያዋ መኖራቸው ያሳዝናል” ብለዋል፡፡

Share this:


Facebook
inSh

No comments:

Post a Comment