"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 31 August 2012

“ቴዲ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳብ የለውም” – ዘካርያስ ጌታቸው (የቴዲ ማናጀር)


(ፍኖተ ነጻነት) ታዋቂው አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሟቹን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት አስመልክቶ ነጠላ ዜማ አዘጋጅቷል መባሉን የድምፃዊው ማናጀርና የአዲካ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ማናጀር ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት የመለየታቸውን ዜና መንግስት ይፋ ካደረገ በኋላ ላለፉት ሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን መታወጁን ተከትሎ ታዋቂው አርቲስት
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የአቶ መለስ ዜናዊን ሀዘን ምክንያት በማድረግ ነጠላ ዜማ ለቋል የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ሰንብተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ድምፃዊው በብሄራዊ ቤተመንግስት በመገኘት ሀዘኑን ለመግለጽ በሞከረበት ወቅት በስፍራው የተገኘው ህዝብ ጩኽት በማሰማቱ ወደ ውስጥ ሳይዘልቅ እንደተመለሰ ተናግሯል፡፡ ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የአዲካ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ማኔጀር ሠርካለም ታፈሰ ግን ቴዲ አፍሮ ለአቶ መለስ ምንም አይነት ነጠላ ዜማ አለመስራቱን ተናግረው “ከሁለት ዓመት በፊት የሰራውን ሙዚቃ በአቶ መለስ እና በቴዲ ፎቶዎች በማጀብ የተቀናበረ ምስል በዩቲውብ ተለቆ አይቻለሁ” ካሉ በኋላ ቅንብሩ ከቴዲ እውቅና ውጪ እንደተሰራ ለፍኖተ ነፃነት አረጋግጠዋል፡፡
የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆኑት አቶ ዘካርያስ ጌታቸውም ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀው “ቴዲ ምንም አይነት ሙዚቃ አልሰራም፤ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳቡም የለውም” ብለዋል፡፡ ብሔራዊ ቤተመንግስት አጋጠመው የተባለውም ተቃውሞ መሠረት ቢስ መሆኑን አብራርተው “አርብ ዕለት ቤተመንግስት ሳንገባ የተመለስነው በተቃውሞ ምክንያት ሳይሆን ለጀነራሎች የተዘጋጀ ልዩ የሀዘን ስነ ሥርዓት በመኖሩ ነው። ” ካሉ በኋላ በስፍራው የነበረው ህዝብ የአድናቆት ድምጽ ማሰማቱን ብቻ እንደሚያውቁ አስረድተዋል፡፡ ቴዲ ከዛ በኋላ ሄዶ ለቅሶ መድረሱንም ማናጀሩ ተናግረዋል። ታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በ1997 ዓ.ም ያስተሰርያል በሚል ርዕስ ባወጣው አልበሙ ምክንያት ከመንግስት ጋር እሰጣገባው ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በአወዛጋቢ ክስ ከሁለት አመት በላይ በቃሊቲ በእስር ማሳለፉም አይዘነጋም፡፡ 

ከኢቲቪ ምስሎች በስተጀርባ – የሚዲያ ትንተና – በያሬድ ጥበቡ


ዳያሰፖራ ውስጥ በምንኖረው ኢትዮጵያውያን መሃል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕይወትና ሞት እንዳከራከረን ኖሮአል ። ሰሞኑን ደግሞ የሽኝት ስርአታቸው ሌላው ድራማ ነው ። ዛሬ 10ኛ ቀኑን የያዝው ይህ ድራማ ራሱን ለፖለቲካ ትንታኔ በሚያውስ መልኩ እየተተወነ ይገኛል ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ቦሌ አየር ማርፊያ ሲደርስ፣ የኢቲቪ ካሜራ ትኩረት አቶ በረከት ላይ ስለነበረ፣ “የመለስ መንግስት ወራሸ ሰለሆኑ መሆን አለበት” የሚል ትርጉም ነበር የሰጠኝ ።
የወያኔ አመራር አባላትን ለማየት ብሞክር ከስዩም መስፍን በቀር አንዳቸውም አይታዩም ። “እየዶለቱ ቢሆን ነው ቦሌ ያልተገኙት” ብዬ ከራሴ ጋር ተሟገትኩ ። የሃዘኑ ትርኢት ቀጠለ፣ ሆኖም የነዚህ የወያኔ ቱባ ባለስልጣኖች ክስመት እተጋነነ ሄደ ። ወዴት ገብተው ይሆን ብለን ስንጨነቅ፣ ዕድሜ ለአውራምባ ታይምስ፣ የመለስ ወንድም ቤት ሐዘን መቀመጣቸውንና፣ አቦይ ስብሃት “መለሰ ብቻውን አይደለም የሞተው፣ ወያኔን ቀብሮ እንጂ ነው!” እያሉ ማንባታቸውንና በጠባብ ብሄርተኝነትና በሙስና እየተከሰሱ ከድርጅቱ የተባረሩትንና የተሰናበቱትን ሁሉ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ሰማን ። ከዚህ ዜና ብስረት በሁዋላ ደግሞ የሚከተሉተን የሚዲያ ትዝብቶች ለማድረግ ቻልን ።
በሚቀርቡት የመለስ ገድሎች ሁሉ፣ ተሓህት፣ ህወሓት፣ ወያኔ የሚባሉ ድርጅቶች ውስጥ የታገሉና የመሩ መሆናቸውን በሚያስረሳ መልኩ፣ መለስ ከኢህአዴግና ኢትዮጵያ ጋር ብቻ ተዳብለው እንዲታዩ ተደረገ ። ከጎንደርና ወሎ ገበሬዎች ጋር ሲወያዩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ይበልጥ አመዘኑ ። ስለ ስውዬው ማንነትም ሰብዕናቸውን የሚመሰክሩት እነ ስብሃትና አባይ መሆናቸው ቀርቶ እነ ሬድዋንና ኩማ ሆኑ ። የወያኔ መሪዎች ወይ አኩርፈው አንተባበርም ብለዋል፣ ወይም ኢቲቪ መንደር ድርሽ እንዳይሉ ታግደዋል ። መለስ የብሄረሰቦችን እስር ዘለው ለኢትዮጵያ ሴቶችና ወጣቶች ህይወታቸውን የሰጡ ታጋይ ሆነው ቀረቡ ። በዚህ ሁሉ መሃል የወያኔ አንጋፋዎች ምስል ተዳፍኗል ።
እሮብ በማለዳ በ12 ሰአት ዜና ላይ ቀዳሚዎቹ ሶስት ዜናዎች፣ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ቢሾፍቱ በሚገኙ የአየር ሐይል አባላት፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ለጠቅላይ ሚኒሰትሩ ራዕይ ቀጣይነትና ለህገ መንግስቱ ያላቸውን ታማኝነት መግለጻቸውን የሚያበሰር ነበር ። ጥያቄው ለምን ይህ አስፈለገ የሚል ነው ። ለህገመንግስቱ ያላቸውን ታማኝነት ይዞ ምን ለማድረግ? አሰላለፉ ግልፅ ይመስላል ። የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ራዕይ እናስፈጽማለን ብለው በአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ዙሪያ በበረከት አስተባባሪነት ሚዲያውን ይዘው በቆሙትና፣ ኒቆዲሞስ መኖሪያ ቤት ዙሪያ በተኮለኮሉት የወያኔ ጎምቱዎች ። ይህንኑ ጥርጣሬ የሚያጠናክሩ ትርኢቶችም በዛሬው ዕለትም ቀጥለዋል ።
ሐሙስ ምሽት የአዲስ አበባ ሴቶች የጧፍ ማብራት ትዕይንት በመስቀል አደባባይ ነበር ። መድረኩ ላይ ግዙፍ ከሆነው የመለስ ፎቶግራፍ ስር፣ በህይወታችው ሳሉ ያልተደመጡትና ስንናፍቀው የኖርነው “በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ…” የሚል ጥቅስ ይታያል ። ሴቶች ሲያነቡ፣ ሲገጥሙ ከቆዩ በሗላ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታው ብቅ ብለው፣ የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ራዕይ ከመተግበረና አንድነታቸንን ከመጠበቅ የሚቀናቀኑንን እናወግዛለን ይሁን እናወድማለን የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አደረጉ ። ለመንግስት የውጪ ተቃዋሚዎች ያልተሰነዘረ መሆኑን በሚያሳበቅ መልኩ ነው ያን ያሉት ። ለምን? በመስቀል አደባባዩ ሰልፍ ማሳረጊያ ላይ አስተባባሪው “የፌዴራል ፖሊስ የሙዚቃ ባንድ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርን ማርሸ አሰምቶ ሰልፉ ይጠናቀቃል” ቢሉም፣ አስቀድሞና መዝሙሩን ተከትሎ የቀረበው ግን ኢህዴን ውስጥ ሳለን ህላዌ ዮሴፍ ያቀነባበረው፡
ስንቶች ተኮላሽተው ከአረንቛ ዘቀጡ
ሰንቶች ተደናብረው ከጎዳና ወጡ፤
ጥቂቶች ቆራጦች ያልተንበረከክነው
ነግ እልፍ እንሆናለን ታሪክ ምስክር ነው
የሚለው መዝሙር ነበር። ለምን?
የመዝሙር ነገር ካነሳን አይቀር፣ ህወሓት ስለ መስዋእትነት ብዙ የዘመረ ድርጅት መሆኑን እናውቃለን ። እኔ ራሴ እንኳ የምዘምረው “ጀጋኑ ብጾት” አንዱ ነው ። ሆኖም በትግራይ ቲቪ ፕሮግራሞች እንኳ እነዚያ መዝሙሮች አይደመጡም ። የአማርኛ ዋሸንትም በእኩል ደምቆ ይቀርባል ።
ምናልባት ይህ ሁሉ በወያኔ መሪዎች ትብብር፣ የመለስን የመጨረሻ ስንብት እድሜ ልኩን ሲዋጋ የኖረውን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ተቀበሎ እንዲሄድ የሚደረግ፣ ይዞት ከቆየው ስልጣን ጋር የሚመጣጠን የፖለቲካ ሽግግር ሊሆን ይችላል ። ይህ ቢሆን እሰዬው ነው ። ትልቅነት ነው ። ምናልባትም የህወሓት አመራር አባል የሆኑት አቶ አባይ ፀሃዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በኢቲቪ መታየታቸው ተፋጠው የቆዩት ቡደኖች መሃል ዕርቀ ሰላም መውረዱን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል ። ወይም ቀድሞ ወያኔ ውስጥ በነበረው ክፍፍል እንዳደረጉት ሁሉ፣ ተሸናፊውን ወገን የማሽተት ክህሎት ያላቸው ሰው ሰልፍ ማስተካከላቸውም ሊሆን ይችላል ። ሆኖም ከኒቆዲሞስ ግቢ ድንኳን የሚሰማው ልቅሶ ግን ያንን አይጠቁመንም ። እንዲያውም ፍርሃትህ ምንድን ነው ብትሉኝ፣ እነ በረከት “ሁሉን ነገር በቁጥጥር ስር አድርገናል ሽግግሩ ከቀብር በሗላ ቀስ ብሎ ይደርሳል” ብለው በፈጠሩት የሚዲያ የበላይነት ሲዝናኑ፣ “ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረስናቸው” የሚል አምባገነን እንዳይቀድማቸው ነው ።
 

“መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ፤ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ” – የክንፈ ገ/መድህን ልጅ በረከት።…አዜብ መስፍንን ለማጽናናት በቤተመንግስት ይገኛል እውነት ለአባቱ ገዳይ ያለቅስ ይሆን ?


ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ለመጎብኘት ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ በደህንነት ሚ/ሩ ጌታቸው አሰፋ የተከለከለው የሟቹ ክንፈ ገ/መድህን የጀመሪያ ልጅ “መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ፤ መለስ ዜናዊን እፋረደዋለሁ”ብሎ በአደባባይ መናገሩ በርካታ ሲኒየር የሕወሓት አባላትን ማሳፈሩን ሆርን ታይምስ የተባለው መጽሄት ዘገበ።
አቶ መለስ ዜናዊ ከቀድሞው የደህንነት ሚ/ሩ ክንፈ ገ/መድህን የአሁኑ ባለቤቱን አዜብ መስፍንን በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደወሰደ የዘገበው መጽሄቱ በረከት ክንፈ ያን ጊዜ የ2 ዓመት ሕጻን ልጅ ነበር ብሏል። በረከት ክንፈ ወላጅ አባቱ አቶ ክንፈ ገ/መድህንን በ8 ጥይት መትተው የገዱሉት ሻለቃ ጸሐዬ የመለስ ቀኝ እጅ ናቸው በማለት ለ6 ዓመታት በ እስር ላይ በቆዩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ሊጎበኛቸው ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነበርና የሻለቃ ጸሐዬ ባልታሰበ ለሊት ድንገት መገደል ምስጢሩን ለመደበቅ የተደረገ ሙከራ ነው በማለት ጥያቄ ማንሳቱን ሆርን ታይምስ መጽሄት አጋልጧል።
በተለይ ከአባቱ መገደል በኋላ የደባል ሱስ ባለቤት ሊሆን ችሏል የተባለው የአቶ ክንፈ ገ/መድህን ልጅ ወላጅ እናቱ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት ውጭ ሁልጊዜ እንደሚያገኙት መጽሔቱ ገልጾ በእንጀራ አባቱ አቶ መለስ ላይ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ፍራቻ ልጁ ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ ተከልክሏል ብሏል።
በቅርቡ በኖርዌይ ኦስሎና በሲንጋፖር ለጭንቅላት ቲሞር ሕክምና ሄደ የነበሩት አቶ መለስ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር እርሳቸው ሳይሆኑ ባለቤታቸው አዜብ መስፍን ናቸው ማለት ይቻላል የሚለው መጽሔቱ ከርሱ በተጨማሪም የሕወሓት አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋም ወደ ቤተመንግስት እንዳይገቡ በወ/ሮ አዜብ ተከልክለዋል። የሟቹ የክንፈ ገ/መድህን ልጅ አንድ እርምጃ እንዳይወስድ በአዜብ የተመረጡት ባለስልጣናት ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ጌታቸው አሰፋ፣ በረከት ስምዖንና አባ ዱላ ገመዳ መሆናቸውም ተዘግቧል።

bereket with azeb
የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያሳትማት መዲና ጋዜጣ ላይ “ከክንፈ ገ/መድህን ግድያ በስተጀርባ የአቶ መለስ እጅ አለበት” በሚል ከአንድ የሕወሓት ሴት ታጋይ የተገኘ ምስጢራዊ ዜናን በማውጣቱ አቶ መለስ የሚያዙት ፍትህ ሚ/ር በአዘጋጁ ላይ ክስ በመመስረት ምንጭህን አምጣ በሚል ለእስር ተዳርጎ እንደነበርና፤“ምንጬን አልናገርም” ያለው ሔኖክ ለ24 ሰዓታት በማዕከላዊ እስር ቤት ጨለማ ክፍል ታስሮ በ10 ሺህ ብር ዋስትና መለቀቁ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። በረከት ይህንን ቃል የተናገረው ባለፈው አመት ቢሆን በአሁን ሰአት ወላጅ እናቱ አዘብ መስፍን በሞት የተለያትን ባለቤቷን ለማጽናናት በረከት በቤተ መንግስት የሚገኝ ሲሆን ያለፈውን የአባቱን ግድያ ወደ ጎን በመተው ይቅር ለእግዚአብሄር በማለት ፍቅርን ለማስተማር እናቱን እያጽናናት እንደሆነ ምንጮቻችን ልከውልናል ።በተለይም ባባቱ ግድያ መቆጨቱን የሚናገረው በረከት ከወላጅ እናቱ አዜብ ጋር ምንም ግንኙነት ለማድረግ እንደማይፈልግ ወስኖ እንደነበር ቢታወስም አሁንግ ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ ሞት የመቀራረቢያ መንገድ ብርሃን ሳይፈነጥቅለት እንዳላለፈ ይገልጻሉ ።ከተከለከለበት ቤተመንግስትም ለመግባት መቻሉን እና እናቱንም በጥልቅ ሃዘን ምሬት በመሆን እያጽናናት ነው ።…እውነት ለአባቱ ገዳይ ያለቅስ ይሆን >፧?

Thursday, 30 August 2012

Meles Zenawi's Legacy[የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም]

[የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም ] ይላል ያገሬ ሰው ነገር ሆዱ  ሲገባው።እንዳውም ዘፋኞቹ ያኔ በግዳጅ ሳይሆን ለሙያ ፍቅር በሚሰራበት ጊዜ  ከተዘፈኑት ውስጥ  ለምሳሌ ያህል                                                                                                                                                            ክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ                                                                                                                                     መሳቁን ይስቃል ጥርሴ  መች አረፈ፧                                                                                                                        ልቤ ነው በጣሙን  እጅግ ያኮረፈ ።                                                                                                                                               አርቲስት መልካሙ ተበጀ                                                                                                                                                                              በ ዳይ ይረሳል  ቀን ቀን ወልዶ ቀን ሲጨልም ቀን ሲተካ                                                                                                                   አይረሳም ተበዳይ ለካ ፧                                                                                                                                                         የበደልሽኝን እንዳልረሳ ሁኛለው                                                                                                                          ከልቤ እንዴት እስቃለው።                                                                                                                                                                ልል የፈለኩት የ21 ዓመት በደል ባንድ ቀን እንባ አይታጠብም።21 ዓመት ያዘነ ፦ያለቀሰ፧አንጀቱ ኩምትር ያለ ፦ ጨጓራው የተላጠ፧ ወያኔ እስካልጠፋና  ስርኧቱ እስካልተቀየረ ድረስ  ልብን ማግኘት አይቻልም።

ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በህይወት አሉ



ሰሞኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በተያያዘ መጥፋታቸው ሲነገርላቸው የነበረው እና ቀጥሎም ሞተዋል በሚል በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ሲነገር የቆየው የባለሃብቱ ሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ  በህይወት መኖራቸው ተረጋገጠ ።  የባለ ብዙ ኩባንያ ባልተቤት እና የገቢ ምንጫቸው በአረብ አገር የሚገኘው የነዳጅ ኩባንያ እንደሆነ የሚነገርላቸው እኝሁ ባለሃብት በዚህ ሳምንት ውስጥ አዲስ አበባ ገብተው መታየታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል ።በዛሬው እለትም የጠቅላይ ሚንስትሩ አስከሬን ለማየት ወደ ቤተመንግስት አምርተው የህሊና ጸሎት አድርገው መመለሳቸውን የማለዳ ታይምስ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቦአል ።ሼኩ ምክንያቱ ምንም ባልታወቀበት ምክንያት ከወዳጃቸው ጠ/ሚንስትር ሞት በሁዋላ ያለመታየታቸው ብዙ ስጋትን በህብረተሰቡ ውስጥ ፈጥሮ እንደ ነበር የገለጸው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ በአሁን ሰአት የህወሃት አባላት ክፉኛ ታመዋል እየተባለ አገር በሚታመስበት ወቅት እሳቸውም ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸውም ታምው ነበር፤ በህይወት አልፈዋል የሚለው በሃገርቤት እና  እንዲሁም ኢሮጵ እና አሜሪካ ተሰራጭቶ መወራቱ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ነበር ።ይበልጥ በሼክ መሃመድ ሁሴን አላህሙዲ ስር የሚተዳደሩት ከ20.000 በላይ የሚጠጉት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ከፍተኛ ውድቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላል በሚል ስጋት ህብረተሰቡ ስጋታቸውን በግልጽ አንጸባርቀዋል። የሼክ መሃመድ ሁሴን አል አሙዲ በምርጫ 97 አ.ም የንብ ምልክት ያለበትን ቲ-ሸርት ለብሰው መታየታቸው ህብረተሰቡን አስከፍቶ የነበረ ቢሆንም ለሃገሪቱ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ስራ  እና ደሃውን ህብረተሰብ ከስራ አጥነት ማላቀቃቸው ትልቁ ራእያቸው ነው ሲሉ አንዳን ወገኖች ገልጸዋል። ሆኖም ግን በሚድሮክ ኢትዮጵያ የወርቅ ማእድን ስራ በሚደረገው የሰራተኞች ጉልበት ብዝበዛ እና የወርቅ ማእድን ወደ ሌሎች ሃገሮች ቅድሚያ ተሰጥቶ መላኩ ደግሞ የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት ማራቆት ነው የሚሉም አልታጡም ። ይህም ሆኖ ግን በህዝብ ዘንድ መከበር እና መወደዳቸው እስካሁንም ድረስ እንደጸና ነው ።     l



Wednesday, 29 August 2012

Teddy Afro pays tribute to the late Premier at the National Palace


Teddy Afro pays tribute to the late Premier at the National Palace
Posted by admin on August 29, 20122 Comments
Awramba Times(Addis Ababa) – Teddy Afro and His wife Amleset Muche pay tribute to the late Ethiopian Prime Minister, Meles Zenawi.

Teddy Afro and his wife Amleset Muche walking to view the coffin of the Premier at his official residence of the national palace where his body was lying.
Teddy and his wife have arrived yesterday to view the coffin of the Premier at his official residence of the national palace where his body was lying.
Meanwhile Teddy Afro and Adika Communication and Events have announced that the  “Tikur Sew” concert has been rescheduled for unstipulated time following the death of Meles Zenawi. “Tikur Sew” Concert was originally scheduled for the Ethiopian New Year’s Eve, September 10, 2012 in Addis

ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ? ወይስ የለም


የ ”ኢትዮጵያን ሪቪው” ድረ-ገጽ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዳጅ (አረቡ ቱጃር) ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ ሞተዋል! ሲል የዘገበ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ “ኢ ኤም ኤፍ” ድረ-ገጽ የለምሰውየው አልሞቱም ይልቁንም ለመለስ ዜናዊ ቀብር አዲስ አበባ ገብተዋል ባይ ነው።

ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ የለም?

(ኢ.ኤም.ኤፍ.) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ሼኽ መሃመድ አል አሙዲ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል። “ሼኽ አላሙዲ ሞተዋል” የሚል ዜና በሰፊው ተሰራጭቶ የቆየ ቢሆንም፤ ከአገር ቤት የደረሰን ዜና እንዳረጋገጠው ከሆነ ሼኩ በህይወት መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል። የቅርብ ምንጮች ለኢ.ኤም.ኤፍ. እንደገለጹት ከሆነ፤ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ አዲስ አበባ የገቡት በመጪ እሁድ በሚደረገው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት፤ ሼኽ አላሙዲ ወጪውን ሸፍነው ለማሳከም ጥያቄ ቢያቀርቡም የቀድሞዋ ቀዳማዊ ሴት አዜብ መስፍን ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ፤ አስፈላጊውን ወጪ በማድረግ በሼኹ በኩል ሊደረግ የነበረ ህክምና ሳይደረግ ቀርቷል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ ወዳጅ የመሆናቸውን ያህል፤ የቀድሞዋ ቀዳሚዋ ሴትዮ ከሼኽ አላሙዲን ጋር አግባብ የላቸውም። ወደፊት በሚኖረው የስልጣን ሽግሽግ እና ሽግግር ወቅት አዜብ መስፍን ወደ ስልጣን የምትመጣ ከሆነች በሼኽ አላሙዲ የንግድ ድርጅቶች ላይ ግልጽ የሆነ ጥቃት እንደምትፈጽም ይጠበቃል። በዚህም ምክንያት በህወሃት አማካኝነት፤ አዜብ መስፍን እንደገና ወደ ስልጣን መውጣቷን እንደስጋት የሚቆጥሩ ውስጥ አዋቂዎች በርካታ ናቸው። እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች እንደገለጹልን ከሆነ፤ “ከእሁዱ ቀብር በኋላ፤ ሼኽ አላሙዲን እንደቀድሞው ወደ ኢትዮጵያ የመመላለሳቸው ጉዳይ ሊቀንስ ይችላል።” ብለዋል በሃዘን።

Tuesday, 28 August 2012

ሰበር ዜና ፡የፍትህ ጋዜጣ ዋና ኧዘጋጅ ክስ ተቌረጠ


የፌደራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተበት ሦስት ክሶች ምክንያት ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ዋስትና ተከልክሎ በማረሚያ ቤት እንዲቆይ የተደረገው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ክሱ እንዲቋረጥ ተደረገ፡፡
ክሱ እንዲቋረጥ ያዘዘው ከሳሹ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ለክሱ መቋረጥ በምክንያትነት ያቀረበው ተጨማሪ ምርመራ አደርጋለሁ በማለቱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በጻፈው ደብዳቤ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸውን ክሶች ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ተመስገን በዛሬው ዕለት ከእስር እንደሚለቀቅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ የተመሠረተበት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ራሱ በዘገባቸውና በጋዜጣው ዓምደኞች በተዘገቡ አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉ ሦስት ጽሑፎች ሳቢያ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስር መለስ ዜናዊ ሕመም ጋር በተገናኘ ዘገባው ምክንያት ከታተመ በኋላ እንዳይሠራጭ በፍትሕ ሚኒስቴር መታገዱም ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም በማለቱ ምክንያት ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡ 

BREAKING NEWS; AL Amoudi is dead


Ethio-Saudi billionaire Ato Mohamed Al Amoudi, one of the late dictator Meles Zenawi’s closest friends, has died today in Saudi Arabia after receiving medical treatment in London, Ethiopian Review Intelligence Unit sources reported this afternoon.
Ethiopian Review could not confirm this breaking news from more than one source, but the source is credible enough for us to report it.
As we prepared to report the news, the TPLF-controlled EthiopianTelevision (ETV) this evening reported that Al Amoudi has arrived in Addis Ababa today, but showed only an old photo. ETV reported Al Amoudi’s arrival in Ethiopia with an old photo to preempt any talk of Al Amoudi’s death which could turn people’s attention away from Meles Zenawi’s burial program that is scheduled for next Sunday, September 2, according to Ethiopian Review analysts.

Monday, 27 August 2012

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተከትለው ሄደዋል መሞታቸው በአዲስ አበባ በስፋት እየተነገረ ነው።



       
ዘንድሮ ወያኔን እና ወያኔን አፍቃሪያን ምን ነካቸው ያሰኛል በከፍተኛ አመራሮች ላይ ክፉኛ የሞት ጥላ ጥላውን አድርቶባቸዋል።በዚህ ወር ብቻ ሶስት ታላላቅ ወያኔ እና ወያኔ አፍቃሪያንን በሞት ጥላ ተነጥቀናል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ፣በአዲስ አበባ በአሁን ሰአት በከፍተኛ ደረጃ እየተናፈሰ ያለው ወቅታዊ ወሬ ከመለስ ዜናዊ ሞት ባሻገር  የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ መሞት እንደሆነ ተገልጾአል ። ለረጅም ዘመን በበሽታ ሲሰቃይ የከረመው አንድርያስ እሸቴ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አማካሪ በመሆን ሲያገለግል ነበር  ። በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት መሰረተ ድንጋይ ሲጣል የአፍሪካ የሰበአዊ መብቶች ጥሰትን የሚያስታውሰውን ማእከል ለመገንባት ጊዜአዊ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር ። በተለይም እንድርያስ እሸቴ በሃገር ውስጥ የሚታሙበት እና የሚጠሉበት ዋነኛ ጉዳይ ቢኖር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሪ በነበሩበት ወቅት ሃላፊነታቸውን ያለትወጡ ከመሆኑም በላይ ለብዙ ተማሪዎች ሰለባ የመሆናቸው ምክንያት በዋናነት ይጠቀሳል ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ውስጥ የሰበአዊ መብት እና የትምህርት መሟላት ጥቅማጥቅሞችን በሚጠይቁ ሰአት ፣ወታደር ፣ፖሊስ ሰራዊት እና ሌሎች ደህንነቶችን በማስገባት ተማሪዎችን በማሳፈን እና ወደ ዘብጥያ በማስጋዝ ሚና ሲጫወቱ ብዙ ተማሪዎችም የሞት ጽዋን እንዲቀምሱ ከፍተና ገቢራዊ የሆነ ሚና ተጫውተዋል ። በሌላም በኩል ሜ.ጀነራል ሃየሎም አርአያን ሞት ተከትሎ ለግድያው ዋነና አቀነባባሪ እና ተጠያቂ ናቸው ሲሉ የወያኔ አመራር አባላቶች ሲኮንኗቸው ፣ይህንን ፍራቻ ከህዝቡ እና ከሌሎች የወያኔ አባላቶች ለማራቅ ሲባል ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ መስሪያቤት በአማካሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚንስትሩን በአማካሪነት ሲመሩ የቆዩት የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጆች እነዚህ ናቸው ።‹‹‹‹…አማካሪ ፋሲል ናሆም፣ አማካሪ ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ፣ አማካሪ ሬድዋን ሁሴን፡፡››…meles and andriyas

Ethiopia PM’s death leads to uncertainty





WHAT NOW? Meles Zenawi ruled his famine-stricken country for 21 years and tried to make authoritarianism acceptable
THE death of Meles Zenawi, Ethiopia’s prime minister, on Aug 20 reveals much about the country he created. Details of his ill health remained a secret until the end. A short broadcast on state television, late by a day, informed Ethiopians that their “visionary leader” of the past 21 years was gone.

Meles Zenawi
He died of an unspecified “sudden infection” somewhere abroad. No further information was given. In the two months since the prime minister’s last public appearance, the only Ethiopian newspaper that reported his illness was pulped, its office closed and its editor arrested. Further details of Meles’ death surfaced only when an European Union official confirmed that he died in a Brussels hospital.
A towering figure on Africa’s political scene, he leaves much uncertainty in his wake. Ethiopia, where power has changed hands only three times since World War 2, always by force, now faces a tricky transition period.

ጊዜያዊ መንግስት እስከሚቋቋም ትግላችንን እናፋፍማለን[ኢወክንድ]


 የኢሕአፓ ወጣት ክንድ  በላከው መግለጫ “ዛሬ የትግላችን አቅጣጫ የስርአቱ ቁንጮዎች በጥላቻ በሽታ ስለተከረከሙ የስርአት ለውጥ ይመጣል ብለን ፍፅም ብዥታ ስለሌለን የትግላችን አልፋና ኦሜጋ ፀረ ወያኔ ሕዝባዊ ትግላችን በሜዳው ላይ አፉፍመን ወያኔን ሕገ ወያኔንም በስረ ነቀል ለውጥ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግዝያዊ ሕዝባዊ መንግስት እስከምቁቁም ኢወክንድ ተመሳሳይ አቁም ካላቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ወጣቶች ጋር በመሆን እናት ድርጅታችን ኢሕአፓ የሚከተለውን መርሆ ተከትለን 40 ዓመት በትግልና በመሰዋትነት ያቆዩልንን ትግል እንደምንቀጥል ስንገልፅ በኢትዮያዊ ቃል ኪዳን ነው::” አለ።
“ለውጥ ስንል ለውጥ ሲሉ!!” በሚል ር ዕስ ባለ 2 ገጽ መግለጫ ለዘ-ሐበሻ የላከው የኢሕአፓ ወጣት ክንድ (ኢወክንድ) “ሕዝባዊ ጸረ ወያኔው ትግላችን ይፉፉም ስንል አዲስ ስርአትን ላረገዘ አሮጌ ስርአት አዋላጁ ከተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል ውጪ ሌላ ስለሌለ ነው::” ብሏል።
“በኢሕአፓ የትግል መንፈስ ተፀንሰን የተደራጀን የኢሕአፓ ልጆች ነንና ከአላማው አላማ ሰርፀናልና ስር ነቀል ኢትዮጵያዊ ለውጥ ያሻል ሲል ኢሕአፓ ኢወክንድም ከዚህ ሌላ መፈክር አያነሳም ምክንያቱም በኢሕአፓ ውስጥ ያለን የወጣት ክንፍ ድርጅት ነንና:: ይህ መነሻችን አድርገን ወደ ላይ ካለው ርዕሳችን ስንጉዝና መግለጫችንን ስናብራራ በኢትዮጵያችን ለለውጥ የምንታገለው ቀጠን ያለ መለሰ ወፈር ባለ መለሰ ለመለዋወጥ ለመተካካት ሳይሆን ይህ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ማለትም የሚኮራበት ስም እና በምንጠየፈው የተግባሩ መጠርያ ወያኔ ከነስረዓቱ ከስሩ ካልተመነገለ በተሸራረፈ የግለሰብና የባዕድ ቡድን በሚለዋወጥ ጉልቻ ጣፋጭ የሆነ የነፃነት አየር እንደማናገኝ ግንዛቤውን ከድርጅታችን ያገኝን የድርጅታችን ወጣቶች መሆናችንን እንገልፃለን: