"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday 27 August 2012

ጊዜያዊ መንግስት እስከሚቋቋም ትግላችንን እናፋፍማለን[ኢወክንድ]


 የኢሕአፓ ወጣት ክንድ  በላከው መግለጫ “ዛሬ የትግላችን አቅጣጫ የስርአቱ ቁንጮዎች በጥላቻ በሽታ ስለተከረከሙ የስርአት ለውጥ ይመጣል ብለን ፍፅም ብዥታ ስለሌለን የትግላችን አልፋና ኦሜጋ ፀረ ወያኔ ሕዝባዊ ትግላችን በሜዳው ላይ አፉፍመን ወያኔን ሕገ ወያኔንም በስረ ነቀል ለውጥ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግዝያዊ ሕዝባዊ መንግስት እስከምቁቁም ኢወክንድ ተመሳሳይ አቁም ካላቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ወጣቶች ጋር በመሆን እናት ድርጅታችን ኢሕአፓ የሚከተለውን መርሆ ተከትለን 40 ዓመት በትግልና በመሰዋትነት ያቆዩልንን ትግል እንደምንቀጥል ስንገልፅ በኢትዮያዊ ቃል ኪዳን ነው::” አለ።
“ለውጥ ስንል ለውጥ ሲሉ!!” በሚል ር ዕስ ባለ 2 ገጽ መግለጫ ለዘ-ሐበሻ የላከው የኢሕአፓ ወጣት ክንድ (ኢወክንድ) “ሕዝባዊ ጸረ ወያኔው ትግላችን ይፉፉም ስንል አዲስ ስርአትን ላረገዘ አሮጌ ስርአት አዋላጁ ከተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል ውጪ ሌላ ስለሌለ ነው::” ብሏል።
“በኢሕአፓ የትግል መንፈስ ተፀንሰን የተደራጀን የኢሕአፓ ልጆች ነንና ከአላማው አላማ ሰርፀናልና ስር ነቀል ኢትዮጵያዊ ለውጥ ያሻል ሲል ኢሕአፓ ኢወክንድም ከዚህ ሌላ መፈክር አያነሳም ምክንያቱም በኢሕአፓ ውስጥ ያለን የወጣት ክንፍ ድርጅት ነንና:: ይህ መነሻችን አድርገን ወደ ላይ ካለው ርዕሳችን ስንጉዝና መግለጫችንን ስናብራራ በኢትዮጵያችን ለለውጥ የምንታገለው ቀጠን ያለ መለሰ ወፈር ባለ መለሰ ለመለዋወጥ ለመተካካት ሳይሆን ይህ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ማለትም የሚኮራበት ስም እና በምንጠየፈው የተግባሩ መጠርያ ወያኔ ከነስረዓቱ ከስሩ ካልተመነገለ በተሸራረፈ የግለሰብና የባዕድ ቡድን በሚለዋወጥ ጉልቻ ጣፋጭ የሆነ የነፃነት አየር እንደማናገኝ ግንዛቤውን ከድርጅታችን ያገኝን የድርጅታችን ወጣቶች መሆናችንን እንገልፃለን:
:” በማለት መግለጫውን የቀጠለው ኢወክንድ “በየጎጣችን ተከፋፍለን ኢትዮጵያዊ ራእይ እንዳይኖረን ካደረገን ስርአት ፈልቅቆ በኢትዮጵያ የአንድነት ጎዳና እንድንጏዝ በጨለመው ተስፋችን ብርሃን ላፈነጠቀልን ኢሕአፓ ምስጋና ይሰጠውና ይህንን በሕዝብ ያልተወከለና ሕጋዊ መሰረት የሌለውን ቡድን እንደ መንግስት አልተቀበልነውምና የሌለውንም ህገ መንግስት እንደህግ ተቀብለን ህገ መንግስት ብለን አንጠራውም::
ኢትዮጵያን የበተነና ጨርሶም ከምድረ ካርታ ለማስፋቅ ያመቻቸን ቡድን ለራሱ ተፍጥፎ የሰራውን ሕገ መንግስት ሕገ ወያኔ ነውና መሻሻል ሳይሆን ከስሩ መቀደድ ያለበት መሆኑን አበክረን እንገልፃለን::
ሕጉ ይሻሻል ሳይሆን ስሥርዓቱ ይለወጥ የምንለው ለዚህ ነው::” ሲል አብራርቷል።
መግለጫው ቀጥሎም “ወያኔ ሕገ መንግስቱን ለመጣስ በሚል ዜጋውን የሚያምሰው የአንድን አናሲ የጥቂት ዘረኞችን አገዛዝ ዘላለማዊ ለማድረግ የሚያደርገው መባከን መሆኑን ግንዛቤው ስላለን የሌለ ሕገ መንግስት ምኑ እንደሚጣስ ለራሱ ለጥቂት ደጋፊ ገፋ ሲልም ለባእድ ሞግዚቶች ይገባ ይሁን እንጂ እኛ ግን ድሮም ዛሬም እንደማንቀበለው አስረግጠን ለማለፍ እንሞክራለን::” ሲል ቃል ኪዳኑን አድሷል። ኢወክንድ በመግለጫው ማጠናቀቂያ ላይ “ፀረ ወያኔ ሕዝባዊ ትግላችን ይፉፉም፤ የኢትዮጵያ ትንሳዬ እውን ይሆናል” ካለ በኋላ “ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዓብዮታዊ ፓርቲ ኢሕአፓ 40 ኛው ዓመት እንኩን አደረሳችሁ!” የሚል የመልካም ምኞቱን አስተላልፎ መግለጫውን ቋጭቷል።





No comments:

Post a Comment