"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 28 November 2012

የሙዚቀኛው ማስታወሻ

  1. ሆ...ብዬ.እመጣለው...ሆ.ብዬ.በድል.ሆ...ብዬ.እመጣለው......ሆ..ብዬ.በድል ...                                                                            .ጥንትምያባቴነው.....ጠላትንመግደልን።                                                                                                        በማለት ሆሆሆ  ብሎ ተነስቶ  ቤቴ ንብረቴ ቤትሰቤ ሳይል  ይህ ሁሉ ወታደር ላቡን ደሙንና  ህይወቱን የሰጠላት፤ ሀገሩ ፦ ዳር ድንበሯ ተከበሮ ፤ ሰላምና ዲሞክራሲ በማሰብ፤ እድገትና ብልጽግናን ለህዝቦቿ በመመኘት   ነበር።ነገር ግን ያሰቡትና  የተመኙት ሳይሆን ቀርቶ  የጥቂቶች መፈንጫ ፤ የጥቂቶች ሀብት ማካበቻ  ሆኗል። ፊልሙ ላይ እንደምትመለከቱት ምን ያህሉ ተረፎ  ተመልሷል? ምን ያህሉ......  ? ቃሉን መጥራት ከበደኝ ብቻ ቤቱ ይቁጠረው፤  ብዬ እንዳልተወው ለኔ ነጻነት ሲሉ አይደል እንዴ  ልዋጭና ምትክ የሌላትን  ህይወታችውን የከፈሉት? ምን ነበር  ያለችው አርቲስቷ?   አዎ   አስታወስኩት                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                          (የሰው.ልጅ.ክቡር...ሰው.መሆን.ክቡር...ሰው.ሞቷል.ሰው.ሊያድን.ሰውን.ሲያከብር።                                        የተሰጠኝ.ህይወት.ዛሬ.በነጻነት....ሰው.ተከፍሎበታል.ከደምና.ካጥንት                                                             ስንት.ወገን.ወደቀ.በነጾነት.ምድር....ትናገር.ዓድዋ.ትናገር.ትመስክር።                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                              ብላ  በጣፋጭ አንደበቷ ዘፍና  ነበር ታዋቂዋ አርቲስት እጅጋየው ሽባባው[ጂጂ] ። አዎ ለአሁኗ ኢትዮጵያ መፈጥር  ስንት ህይወት ተከፍሎ   ነበር ። ግና ወያኔ  አላማው  ኢትዮጵያ  የምትባል  አገር  ማፈራረስ   ስለሆነ  ደማቸውንና ህይወታቸውን  በከንቱ  ሜዳ ላይ ፈሶ  ቀረ ።  ግን አይቀርም  ጌዜው ሲደርስ  ታሪክና  ትውልድ  አይረሳቸውም  ።  ለሁሉም ጊዜውን  ይጠብቅለታል ፤ በማለት ሰለሞን  ቀድሞ ተናግሮታል ።ተብሎም ተዘፍኗል፤በአሁኑ ጊዜም መሰረታቸው ተነቃንቆ    መፈረካከሳቸው ተጀምሯል፤ ስለዚ እኛም ብረትን መቀጥቀጥ እንደጋለ ነው። ትግላችንን አጠናክረን  በህብርትና ባነድነት ተነስተን የአንድ ጎሳ  አገዛዝን ገርስሰን የምንናፍቀውን ዲሞክራሲ  ባገራችን  በኢትዮጵያ ለማየት የዛ  ሰው  ያድርገን።                 ይህ ፊልም  በ1991   ዓ  ም  እንደ ኢትዮጵያውያን  አቆጣጠር  በሁመራ  ግንባር ለቅስቀሳ  በሄድኩበት ጊዜ  የተቀረጸ ነው። የሙዚቀኛው ማስተወሻ በሚል  ያዙልኝ።ይቀጥላል                                                                                                                                                                                                           

40ኛውን ዓመት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር በዓል በትንሹ ለመዘከር ቪዲዮውን ይመልከቱ

በእለቱ በዓሉን ለማክበር የተሰባሰቡት በጡረታ ላይ የሚገኙ አርቲስቶች በቃችሁ ተበለው ከመስራቤቱ የተገለሉ ሲሆኑ እድሜያቸው ቢገ ፋም ተወዛዋዦቹ  እንደ እንዝርት ሲሽከርከሩ መመልከት እጅግ በጣም መንፈስን የሚያስደሰትና የሚያዝናና  ነበር።  ያኔ ወጣት በነበሩበት ሰዓት ምን ያህል ያምሩ  ምን ያህል መድረኩን ያደምቁ  እንደነበር በጊዜው ለነበረው ተመልካች  ፍርዱን እተዋለው።ሙዚቀኞቹ በእውነት ነው የምለው እስካሁን ምትክ የሌላችው አንቱ የተባሉ ብዙ መስራት ማስተማር ሲችሉ እንደቀላል መሰናበታቸው በጊዜው በጣም ነበር የሚያገበግበው[ በጊዜው ስል ይህ ዝግጅት የቆየ  ስለሆነ ነው]ይህንን በዓል ካከበሩት ውስጥ  በአሁን ጊዜ  በህይወት የሌሉ ግን ይህ ስራቸው ታሪክ ሆኖ  ሁል ጊዜ ያስታውሳቸዋል።ለምሳሌ ያህል ከሌሉት ውስጥ 1ኛ ወዳጄነህ ፍልፍሉ ክላርኔትና አልቶ ሳክስ ተጨዋች 2ኛ አሰፋ ባይሳ  ትራምፔት ተጨዋች 3ኛ ጴጥሮስ መኮንን  ባሪቶን ሳክስና  አልቶ ሳክስ4ኛ  ዘነበች[ ጭራ  ቀረሽ]ድምጻዊ ተወዛዋዥና ተዋንያን 5ኛ ደስታ ገበሬ ተወዛዋዥ 6ኛ ብስራት አሰፋ  7ኛ ከተማ  መኮንን 8ኛ ገበያው ገሰሰ 9ኛ ጌታነህ  ሀይሌ  10ኛ ሽታዋ አዳሙ 11ኛ ወረስ ገብረ እግዜሀር .....ወዘተ  ብዬ ልለፈው ። ሌላው የባህል መሳሪያ ተጨዋቾች ፤ የባህል  ክፍል ተወዛዋዦች፤ የዘመናዊ የሙዚቃ   መሳሪያ ተጫዋቾች  ባጠቃላይ  በፊልሙ ላይ  ከምታዩዋቸው  ባለሙያዎች  አሁን ላለነው በበዙ መልኩ መስዋት በመሆን ያቆዩልን ሙያ ነው።በዛ ዘመን ለገንዘብ፤ ለነዋይ፤ለጥቅምና  አጎብድዶ ለመኖር ሳይሆን የሚሰሩት ለሙያቸው  ሲሉ ነው ።የቀጥላል

Tuesday, 27 November 2012

‹‹መለሲዝም›› እየመጣ ነው! (ከተመስገን ደሳለኝ)

 

(ከተመስገን ደሳለኝ)

22 አካባቢ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከተሰቀለው ግዙፉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ምስል ስር ‹‹መለስ ኩለ መንኡ ንህዝቢ ዘወፈየ ጂግና ወዲ ህዝብ ኢዩ›› (መለስ ሁለመናውን ለህዝብ የሰጠ ጀግና የህዝብ ልጅ ነው) የሚል የትግርኛ መፈክር ይታያል፡፡ በመላ ሀገሪቱ ከተሞችና ገጠሮች የመለስ ፎቶ ያልተሰቀለበት ጉራንጉር ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ የምንዱባኖች ጠላና ጠጅ ቤቶች እንኳ ሳይቀሩ ‹‹የመለስ ራዕይን እናሳካለን›› የሚል መፈክር ሊወድቅ ባንጋደደ በራቸው ላይ እንዲለጥፉ ተገደዋል፡፡ የሰውየው ሞት በይፋ ከተነገረ ወዲህ የኢህአዴግ አመራርና ካድሬዎች ከፖለቲከኛነት ወደ ‹‹ሀዋርያነት›› ተቀይረዋል፡፡ በየደረሱበት ስለ‹‹መለስ ራዕይ›› ሲቃ እየተናነቃቸው ይሰብካሉ፡፡ ያነበሩት መንግስት የመቀጠሉን አስፈላጊነት በእርሳቸው ስም ለማሳመን ቀን ከሌት እየባተቱ ነው፡፡

አዳዲስ ምእመናኖችንም እያጠመቁ ደቀ-መዛሙርታትን በማብዛቱ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ሰው ዝር በማይልበት ጭው ባለ ምድረ በዳ ሳይቀር ይጮኻሉ ‹‹የመለስን ራዕይ እናሳካለን!››… ከብሔራዊ ቲያትር እስከ ታላቁ ሩጫ ድረስ ያሉ ህዝባዊ መድረኮች የታላቁ መሪ ራዕይ ይዘከርባቸዋል፡፡ በዚሁ መድረክ ስለራዕዩ ቀጣይነት ተተኪዎቻቸው ቃል ይገቡበታል፡፡ ከወረዳ ካድሬ አንስቶ በተለያዩ ሀገራት አምባሳደርነት እስከ ተሾሙ ዲፕሎማቶች ድረስ ‹‹መለስ በስጋ እንጂ በመንፈስ የማይሞቱ›› ዘላለማዊ ህያው ስለመሆናቸው ይሰብኩ ዘንድ ድርጅታቸው ተልዕኮ ሰጥቷቸዋል፡፡ መለስን በማምለክ አቅላቸውን የሳቱት በተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት የአሜሪካ ‹‹ቋሚ መልዕክተኛ›› ሱዛን ራይስ በስርአተ ቀብራቸው ላይ ‹‹ …it’s deeply unfair to lose such a talented and vital leader so soon, when he still had so much more to give. He was an uncommon leader, a rare visionary… world-class mind›› (ብዙ ነገር ሊሰጠን በሚችልበት ወቅት እንዲህ አይነቱ አስፈላጊ መሪ በአጭር መቀጨቱ እጅግ ያስቆጫል፡፡

በራስ አሉላ አባነጋ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ዜናዊ ተቀየረ

 

(ከእየሩሳሌም አርአያ)

በትግራይ ተምቤን - አቢይ አዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ከ2002 .ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።

ከምረቃው ጋር በተያያዘ የራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰርዞ "መለስ ዜናዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት" ተብሎ መሰየሙን ባለስልጣናቱ በይፋ እንደገለጹ ምንጮች አረጋግጠዋል። በት/ቤቱ በይፋ የመለስ ስም ተፅፎ መለጠፉ ተጠቁሞዋል። በህዝብ ገንዘብ መዋጮ የተገነባን ት/ቤት በጡንቻና በማን አለብኝነት ህዝብን በመናቅ የተፈጸመ ተግባር ነው ሲሉ የአካባቢው ተወላጆች ማውገዛቸው ታውቁዋል።

በተለይ በአውስትራሊያ፡ ጀርመን፡ ኖርዌይ፡ አሜሪካ፡ ካናዳናሌሎች አገራት የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ባካሄዱት ቴሌ ኮንፈረንስ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት « የአፄ ምንሊክን፡ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ለማፍረስ የተጀመረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ወደ ራስ አሉላ ተሻግሮዋል። ይህ የሚያመለክተው የቆየውን የኢትዮጲያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን ነው። ይህ ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የማቆየትና የተጀመረው አደገኛ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከማውገዝ ባለፈ ለትግል መነሳሳት አለበት።ኢትዮጲያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፤» ብለዋል። አክለውም « የኢትዮጲያዊነት ጉልህ መታወቂያና መገለጫ የሆኑ አኩሪ ታሪኰችንና ታሪክ ሰሪ ጀግኖችን ለማጥፋት ኤርትራዊው ቴውድሮስ ሃጎስ፡ በረከት ስሞንና ስብሃት ነጋ የሚመሩት አካል በአገራችን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል» ሲሉ አንድ ተሳታፊ ተናግረዋል። « የዶጋሊ ዘመቻ » በሚል በየአመቱ ራስ አሉላ የሚዘከሩበት ታሪካዊ ቀን እንደነበረና ሕወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በሑዋላ ግን ይህ እንዲቀር መደረጉን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።

በሌላም በኩል በመቀሌ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የአፄ ዮሃንስን መታሰቢያ ሃውልት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው እንቀስቃሴ እንዲቆም መደረጉን የቅርብ ምንጮች አጋልጠዋል። ባለፈው አመት ከህዝብ በተዋጣ ገንዘብ ሓውልቱን ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ እንደነበር ጠቁመው፤ በኋላ ግን "የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ስለተቃወሙ ሃውልቱን መስራት አይቻልም» በማለት እነ ቴውድሮስ ሃጎስ መወሰናቸውን ምንጮቹ ገልፀው፦ "አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ተራ ምክንያት» ሲሉ ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አጣጥለውታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአድዋ ከተማ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ የነበረ የመለስ ፖስተር ተቀዳዶ መጣሉን ምንጮች ጠቆሙ። የክልሉ ካድሬዎች «የመድረክ ተለጣፊ የሆነው አረና ፓርቲ ነው ይህን የፈፀመው » በማለት ያልተጨበጠ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩና እየዛቱ ነው ያሉት ምንጮች አክለውም ድርጊቱን የፈፀመው የአካባቢው ህዝብ እንጂ የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አይደለም ብለዋል።

Monday, 26 November 2012

ከእሁድ እስከ እሁድ(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች ] የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ቀረበ። ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ገቢ አሽቆለቆለ ።የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሊፈርስ ነው ።አቶ ሳምሶን በመመሪያ መፈታታቸውን አመኑ።

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
freedom now
 
የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ቀረበ
የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል መቅረቡን ለህሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው “Freedom Now” ስራ አስፈጻሚ ዋና ዳይሬክተር ማርዳ ተርነር ለአሜሪካ ሬዲዮ አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሯ እንዳሉት ድርጅታቸው የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የጋዜጠኛነት ስራውን ብቻ ሲያከናውን እንደነበር ሙሉ አረጋግጠዋል። የታሰረውም ያለ አግባብ እንደሆነ ታምኖበታል። በእስር ቤት ከአያያዝ ጀምሮ በርካታ ጥሰቶች እንደተፈጸሙበት አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለዓለም አቀፍ ህግጋት የገባውን ኪዳንና ግዴታ በመጣሱ የእስክንድር ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ያለ አግባብ የታሰሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚመረምረው አካል ባለፈው ሚያዚያ ቀርቧል። የእስክንድር ጉዳይን የያዘው አካል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውን የሰብአዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህጎች ስለመጣሷ መርምሮ ውሳኔውን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ለእስክንድር ነጋ ጉዳይ አዲስ አበባ መሄዳቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ በውሳኔው መጨረሻ እስክንድር ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ቀደም ሲል በፓኪስታንና በበርማ ከተሰሩት ስራዎች ጋር በማነጻጸር አስረድተዋል “እንደ መንግስታቱ ድርጅት ያሉ አካሎች የሚወሰኑት ውሳኔ ቀላል አይደለም” በማለት ተናግረዋል፡፡
እስክንድር ነጋ በአሸባሪነትና በአገር መክዳት ወንጀሎች ተከሶ 18 ዓመት እንደተፈረደበት ይታወሳል።

በሽብርተኝነት የተከሰሱ 29 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተጠየቀ

 
lideta

የሽብር ድርጊቶችን በመፈጸም፣ ሕገ መንግሥቱንና መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፈራረስ ሙከራ ወንጀልና ለሽብርተኝነት ድጋፍ በመስጠት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የተመሠረተባቸው 29 ግለሰቦችና ሁለት ድርጅቶች፣ የተከሰሱት ሕገ መንግሥቱን ጥሶ በወጣ ወይም በሚቃረን ሕግ በመሆኑ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠበቆቻቸው ጠየቁ፡፡ ከሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ተጠርጣሪ ወይዘሮ ሐቢባ መሐመድ መሐሙድ በስተቀር፣ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በጋራ አሥር ጠበቆችን ያቆሙ ሲሆን፣ ክሱን እየመረመረው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት የክስ መቃወሚያ ሐሳባቸውን ኅዳር 13 ቀን 2005 ዓ.ም. አቅርበዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከፋፍለው የቀረቡትን አራት ክሶች በንባብ አሰምቶ እንደጨረሰ፣ የተጠርጣሪዎቹ ተከሳሾች የመጀመሪያ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል፡፡ በወንጀል ሕጉ 130 እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 መሠረት በቀረበው መቃወሚያ ላይ ጠበቆቹ እንዳብራሩት ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እኩል ደረጃ ኖሯቸው አንድ አካል ተደርገው በሥራ ላይ ይውላሉ የተባሉት ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ሰነዶች ናቸው፡፡ እነዚህም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ውስጥ ቁጥር 217ኤ (11) ላይ የፀደቀው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ፣ እ.ኤ.አ ዲሴምበር 16 ቀን 1966 ፀድቆ እ.ኤ.አ ማርች 23 ቀን 1976 በሥራ ላይ የዋለው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንና ጭካኔ የተሞላባቸው ኢ-ሰብዓዊና አዋራጅ አያያዞችንና ቅጣቶችን ለማስቀረት የተደረጉ ስምምነቶች እንደሚገኙ በተቃውሟቸው ጠቁመዋል፡፡ እንደጠበቆቹ ገለጻ፣ አዋጅ ቁጥር 652/2001 ከሕገ መንግሥቱና ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ይቃረናል፡፡
ጠበቆቹ አዋጅ 652/2001 እንዴት ሕገ መንግሥቱ እንደሚቃረን ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዱ፣ በሕገ መንግሥቱ የአንድ ሰው የመኖሪያ ቤትና የግል ሕይወቱ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደማይደፈር መደንገጉን ገልጸዋል፡፡ ያለ ሕግ አግባብና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አንድ በርባሪ ፖሊስ የግለሰብ ቤት መሄድ የማይችል መሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ የተጠርጣሪው ግለሰብ ቤተሰቦች ወይም አባላት ከሌሉ፣ በሕጋዊ መንገድ ለብርበራ የተሰጠውን ትዕዛዝ ትቶ እንደሚመለስ በሕገ መንግሥቱ መደንገጉን አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤትም ቢሆን የብርበራ ፈቃድ ሲሰጥ የግለሰቡን የግል ሕይወት ለመድፈር የሚያስችል መብት እንደማይሰጥም ጠቁመዋል፡፡ በተቃራኒ በድብቅ መረጃ መሰብሰብን የሚፈቅደው አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 18 ሕገ መንግሥቱንና የሰውን ክብር እንደሚቃረንም አስረድተዋል፡፡
ጠበቆቹ በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስና የተጠቀሰባቸውን የፀረ ሽብር ሕግን፣ ከሕግ አውጭው ፓርላማ ጀምረው ይቃረናል እስካሉት ሕገ መንግሥት ድረስ እንዴት እንደሚቃረን ሲያስረዱ ከዓቃቤ ሕግና ከፍርድ ቤቱ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ በክሱ ላይ ብቻ አተኩረው መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ በተደደጋሚ ከመናገሩም በተጨማሪ፣ ዓቃቤያነ ሕጉም ከመቀመጫቸው በተደጋጋሚ በመነሳት ጠበቆቹ የሚያቀርቡት መቃወሚያ ከሕጉ ውጭ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንዲያስቆምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ጠበቆቹ በበኩላቸው፣ ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ሲያቀርቡ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ ለማቅረብ የሚያስችለው የሕግ ሥነ ሥርዓት ስለሌለ፣ በተደጋጋሚ እየተነሳ ተቃውሟቸውን ማስተጓጐል እንዲያቆም እንዲታዘዝላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡