"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Friday, 23 November 2012
በምስራቅ ኢትዮጵያ ከባድ ዉጊያ እየተካሄደ ነው!
አምባገነኑ የወያኔ መደብ ለአመታት በኬንያ መሽጎ ድርድር ሲያደርግበት የነበረው ውይይት ከተኮላሸ በኋላ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከባድ ዉጊያ እየተደረገ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ምንጮች ጠቆሙ::
በኦጋዴን ቀላፎ እና ጎዴ በሚባሉ ቦታዎች የታጠቁ ሃይሎች በወያኔ ወታደሮች ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት ከባድ ጥፋት አድርሰው መሰወራቸዉን የገለጡት እነዚህ ምንጮች ወያኔ በምክር ቤቱ አሸባሪ እያላቸው የሚከሳቸዉን የኦብነግ አባላት ከህዝብ ተደብቆ ሲደራደር ከቆየ በሁዋላ ድርድሩ መክሸፉን ተከትሎ የተነሳው ዉጊያ ማብረጃ አላገኘም ሲሉ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::
ለቀጠና ጥበቃ በተሰማሩ የወያኔ ወታደሮች ላይ የተደረገውን ጥቃት የቀሰቀሰው ውጊያ በጦሩ ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ ናችሁ ተብሎ መስመራዊ የጦር መኮንኖች ወደ እስር ቤት ተልከዋል;
በጦሩ ላይ ለደረሰው ጥቃት ራሳቸዉን ነጻ ማድረግ የፈለጉት የምስራቅ እዝ የጦር ኣዛዥ አብርሃ ወ/ማርያም እና ተከታዮቹ ግንባር ላይ ተሰልፈው የነበሩትን መስመራዊ የጦር መኮንኖች ጥፋተኛ በማድረግ ከያሉበት ተለቅመው ሐረር ከተማ በሚገኘው የምስራቅ እዝ ዋና ማዘዣ በሆነው እስር ቤት ዉስጥ መታሰራቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል::
በምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ የሚመራ አንድ ግብረ ሃይል/ቡድን/ ተቋቁሞ እነዚህን የመስመር መኮንኖች ለመዳኘት እና የጥፋተኝነት ዉሳኔ ለመስጠት በስራ ላይ መሆኑን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ አመልክተዋል::
Thursday, 22 November 2012
ሰማቱ የኔሰው ገብሬ ለፍትህ እና ለነፃነት ሲል እራሱን አቃጥሎ የሞተበትን አንድኛ ዓመት በኦስሎ ታሰቦ ዋለ። በእንዳለ ጌታነህ ኖርዌ
መጣሁ እያለ ያስፈራራል።ቀኑ ደግሞ በጣም አጭር በመሆኑ ጭለማው ረጅሙን ጊዜ እየወሰደ የድብርቱን ሰዓት አራዝሞታል።[በተለይ ስራ ለሌለን ሳንወድ በግድ በካምፕ ውስጥ ለተጎለትን] ግማሹ ከራሱ ጋር ያወራል ሌላው አጠገብ ከሚገኝ ጉዋደኛው ጋር በረባ ባረባው ይጨቃጨቃል ፤ይጣላል፤ ደግም ምን አዲስ ነገር አለ በሚለው ዘመን አመጣሽ ጥያቄ ሃሳብ ይሰበስባል ደግም ላልሰሙት ያሰራጫል። ግማሹ ኮምፒውተር ላይ ተቀምጦ የሆነ ያልሆነውን ይከፍታል ይዘጋል ።ገሚሱ ደግም ሰብሰብ ብሎ ቡናውን እያፈላ እናንተ ሰማችሁ የተባለውን ዛሬ እኮ ፓርላም የሚያወሩት ስለ ስደታኛ ነው እኮ አሉ፤ሌላዋ ትቀጥላለች የሆነ ካፕ ውስጥ ፖሊሶች ገብተው ፈተሸው ሰው ይዘው ሄዱ፤እረረረረ እንዳው ምን ተሻለን ?ደግም ይቀጥላል........ ። እንግዲህ የየዕለቱ ውሎዋችን ይህንን ሲመስል አልፎ አልፎ ግን ከሰው ጋር የሚቀላቅለን አንዳንድ አገራዊ ጉዳዮች ሲኖሩ ያቅማችንን ለመሳተፍ ወደ ከተማ ብቅ እንላለን።ስለዚ በዛሬው ዕለት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አዘጋጅነት በኦስሎ ለወጣቱ ስለፍትህ ስለ ነፃነት ስለ ሰብአዊ መበት መከበር ሲል ውድ ህይወቱን ቤዛ ላደረገልን መምህር የኔሰው ገብሬ እና በግፍ የታሰሩና የተገደሉ የነፃነት ታጋዮችን ለማሰብ እና ለማስታወስ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ይደረጋል ። በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት እና ያቅሜን አስተዋፅኦለማድረግ ከተባለው ሰዓት ቀደም ብዬ ነው በቦታው ላይ የታደምኩት።
መፈረካከሱ ቀጥሏል፤ ፍርሃት፣ ጭንቀትና መደነባበሩም በወያኔ መንደር ተባብሷል
ከይኸነው አንተሁነኝ
በቆፈሩት ጉድጓድ ይገቧታል |
የእያንዳንዱ አርሶ አደር ጎጆ በአንጻራዊ ሲሳይና ደስታ በሚጎበኝበት በዚህ ጊዜ፤ ምድሪቱ ያላትን በረከት ያለስስት እየጋበዘች ባለችበት በዚህ ወራት፤ የምግብ እጦት ፍርሃት ለጊዜውም ቢሆን በተረሳበት፣ የርሃብና የስደት ፍርሃት ላፍታ እንኳ በማይታሰብበት የጥጋብ ወራት፣ ምርት እንዴት እንደሚሰበሰብ እንጅ የጥላቻ፣ የመራራቅና የጦርነት ስጋት እንደደራሽ እንግዳ እንኳ ቢሆን ትዝ በማይልበት በዚህ የኢትዮጵያ የደስታና የሃሴት ወራት ምነው ወያኔ ፍርሃት ፍርሃት አለውሳ። በ99.6 የኢትዮጵያ ህዝብ ተመረጥኩ እያለ ያወራበት አፉ ሳይደርቅ እንዴት ወያኔ በህዝባችን የልበ ሙሉነት ወራት ስለፍርሃት ያወራል? ምነው ወያኔዎች ተራሮችን ያንቀጠቀጡ ጀግኖች አልነበሩም እንዴ? ታዲያ ሰሞኑን ምን ተገኝቶ ነው ተንዘፈዘፉሳ።
አርበኞች ግንባር በየቀኑ ፋታ አሳጥቶ እየኮረኮመኝ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ደግሞ ያለ እረፍት እየቆነጠጠኝ ነው፤ ፌደራል ፖሊስም በተከታታይ የእከዳና ወደ ጠላት እየተቀላቀለ ነው፤ በጠላት ተከበናል፤ ስለ ኢትዮጵያ እንደሚያስብ ጥሩ መንግስትና ለሕዝብ እንደሚጨነቅ አመራርም ሀገራችንን ለማፍረስ ተነስተውብናል ዘምተን ልንከላከላቸው ይገባል ወዘተ ወዘተ እና ሌሎችም። የወያኔ የትንፋሽ እርግብግቢት ፍርሃቱን እያሳበቀበት ነው፤ በእርግጥም ወያኔ መፈረካከስ ጀምሯል። ሰራዊቱን ይቅርታ ፌደራል ፖሊስን ወደ ግዳጅ ለመላክ የተጠቀሙበት የማሳመኛ ዘዴ እንኳ እርስ በርሱ የሚጋጭና የራስ መተማመን የጎደለው ደካማ ነበር። እንድ ጊዜ ”ኢትዮጵያ ሀገሬ ማለትና ስለ አድዋ ማውራት ዋጋ የለውም ታሪከ ስለሆነ” ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ ”ሰራዊታችን ግዳጅን በመፈጸም ያታወቃል ጀግና ነው ለዚህም ታሪክ ምስክር ነው” ይሉናል። ባንድ ራስ ሁለት ምላስ ይላል ይህን ነው።
ያርበኞች ግንባር፣ ትህዴን እና ሌሎችም የዴሞክራሲ ሃይሎች ለሀገራችን ሉአላዊነትና ለሕዝባችን አርነት ከወያኔ ጋር ወያኔ በመረጠው ቋንቋ ግንባር ለግንባር ሲፋለሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም የመጨረሻቸውም አይሆንም። ወያኔ ተጨነቀም አለቀሰ፣ ፈራም ተርበደበደ፣ አቅራራም አስጠነቀቀ ሀገራችን ከወያኔ ነጻ አስክትሆንና ሕዝባችንም በነፃነት መንቀሳቀስ እስከሚችል ድረስ ከዲሞክራሲያዊ ሃያሎች የሚደርስበት ጥቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ስለዚህም የነዚህ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጥቃት ላሁኑ የወያኔ ባለስልጣናት ለቅሶና ሙሾ ሰበብ ይሆን እንደሁ እንጅ እንደዋና ምክንያት ሊጠቀስ አይችልም።ስለሆነም የወያኔ ባለስልጣናት ፍርሃትና ጭንቀት ዋናው መነሻ የሰራዊቱና ፌደራል ፖሊስ በገፍ መኮብለልና ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር መቀለቀል ነው እንጅ ሌሎች ምክንያቶች ሁሉ አጃቢዎች ናቸው።
ወያኔ በጣም ከመረበሹና ግራ ከመጋባቱ የተነሳ ፌደራል ፖሊስን እንደ ሀገሪቱ ጦር ሰራዊት በየጦር ግንባሩ በግልጽ ወታደራዊ ትእዛዝ እያዘመተ ይገኛል። ይህም ፌደራል ፖሊስ ከተመሰረተበትና ከሰለጠነበት ዓላማ ውጭ እንዲያገለግል እየተገደደ መሆኑን ያሳያል። ይህን በማድረግም ወያኔ ከስልጠናው ዓላማ ውጭ በማንአለብኝነት ፖሊስን ወደ ግንባር በማዝመት የራሱ የወያኔ ህገመንግስት ያጸደቀውን የጋራ ስምምነት እንኳ በመጣስ አምባገነንነቱን መግልጽ አሳይቷል። በግልባጩ የወያኔ ድንጉጥ ባለስልጣናት ግን በቅድሚያ እራሳቸው የደፈጠጡትን ተራራ የሚያክል የህግ ሽረት ትተው ከድተው ከዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር ስለተቀላቀሉት ፌደራል ፖሊሶች ውል ማፍረስ እየተርበተበቱና እየተንተባተቡም ቢሆን ያለ ሃፍረት ሊገልጹ ሲሞክሩ ያታያሉ።
የወያኔ ፌደራል ፖሊስ ድረ ገጽ በግልጽ እንደሚያሳው የፌደራል ፖሊስ ራዕይ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ፤ የህዝቦችን እርካታና አመኔታ ያረጋገጠ የፖሊስ አገልግሎት ተፈጥሮ ማየት የሚል ሲሆን፡፡ ዓላማውም የሀገሪቱን ሕገ-መንግስትና ሌሎች ህጐችን በማክበርና በማስከበር ሕብረተሰቡን በወንጀል መከላከልና ምርመራ በማሳተፍ የመንግስትና የሕዝብን ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ነው ይላል፡፡ ስለሆነም ከላይ እንዳየነው ወያኔ ራሱ ካስቀመጠው ብንነሳ እንኳ ፌደራል ፖሊስ ከሕዝብ ጋር ሆኖ ሕዝብን ያገለግላል እንጅ እንዲህ ሰሞኑን እንደሰማነውና እንዳየነው የወያኔ ባለስልጣናት ወዬው እናቴ አይነት ልቅሶ እና ራስ መተማመን የጎደለው ልፍስፍስ ትእዛዝ እንደ ሀገር ጥበቃ ሰራዊት ታጥቆና ወታደራዊ ትእዛዝ እየተቀበለ ድንበር ለማስከበር እንዲዘምት የሚገደድ አልነበረም። አይደለምም።
ስለዚህ የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችና አባላት እንዲሁም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ጀምበር እየተለቀች መሆኑን ከዚህ ማሳያ በላይ ሌሎች ማረጋገጫዎች አያሹንም። ወያኔ ከመዳከምም አልፎ በያቅጣጫው እየተፈረካከሰና እየተለያዬ በራሱ ለመጥፋት ተቃርቧል። ስለሆነም ከወያኔ በሗላ ስለሚመጣው መንግስት መነጋገርና መወያየት ከማስፈለጉም በላይ ይህን ጉዳይ ለማስፈጸም እንድ ሆኖ መቆምና እየሞተ ያለውን ወያኔ ግብአተ መሬት ማፋተን ይጠበቅብናል።
“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ነውና ብሂሉ ይነስም ይብዛ የሚናቅ እገዛ የለም። ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችን የሚያጠናክር፣ የሕዝበችንን ሞራል የሚገነባና ወደ አንድ አቅጣጫ የሚያመጣ፣ ጠላት ወያኔን የሚያጋልጥ ማንኛውም አይነት መረጃ በማቅረብ፣ ተስማሚውን ወቅት፣ ሁኔታና ጊዜ በመምረጥ ወያኔን በመክዳት ከዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ጋር በመቀላቀል ወያኔን በማደከም ትግላችንን ማስፋትና ማጠናከር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ ቀጠሮ አያስፈልገንም ዛሬውኑ ወስነን ስራችንን እንጀምር
የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው
የእምዬ ሚኒሊክ ሐውልትም ሊፈርስ ይችላል
(አንድ አድርገን ህዳር 13 2005 ዓ.ም)፡- የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው ተሾሙ። በ1928 ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ አገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ውቅያኖስ አቋርጦ በመምጣት ኢትዮጵያን ሲወርና ሕዝቧን፣ ሊቃውንቷን፣ ገዳማቷንና አድባራቷን በግፍ ሲጨፈጭፍ ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ቆረጡ። የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከአረመኔው ፋሺስት ጦር ጋር በመፋለም ላይ የነበረውን አርበኛ ለማበረታታት ወደ ማይጨው በሔዱ ጊዜ ብፁዕነታቸው ተከትለው ሔዱ። ከዚያ እንደ ተመለሱም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ተሰባስበው የቤተ ክርስቲያን አምላክ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጣውን ችግር እንዲያስታግሥ በጸሎት እየተጉ ወደነበሩት አባቶችና አርበኞች በመሔድ ለአገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ሁሉም እንዲጋደሉ ማሳሰብ እና ማትጋት ጀመሩ። ኋላም የገዳሙ መነኮሳትና የሰላሌ አርበኞች ይባሉ የነበሩት አርበኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሳታፊ ሆኑ። ከዚያም አርበኞቹ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ወደ ሰላሌ ሲመለሱ ብፁዕነታቸው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ በጠላት እጅ ተያዙ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስምንት ጥይት አሁን ሃውልታቸው ከሚገኝበት ቦታ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡
Tuesday, 20 November 2012
Monday, 19 November 2012
የታክሲ ውስጥ ጥቅሶች
‹‹ ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል ››
· የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ· ሠውን ማመን ተፈራርሞ ነው· ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
· በቴሌቶን ሂሳብ መክፈል ክልክል ነው
· ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
· ለፀባይኛ ተሳፋሪ የፀባይ ዋንጫ እንሸላማለን
· ለስራ ነው የወጣነው
· በመጀመሪያ የጋለ ደምህን ተቆጣጠርና ሀሳብህን ግለፅ
· ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
· ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
· ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር
· ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል
· ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን
· ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር
· ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ
· ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ
· ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::
· ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን
· ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ
· መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!
· ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል
· በጭነት መኪና መታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ
· የክፍለ ከተማ ሠዎች ካላችሁ ሒሳብ በቅድሚያ
· ኑሮአችሁ ሳይሞላ "ታክሲው አልሞላም?! " ትላላችሁ!· ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን
መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡
· ለዓለም ሙቀት መጨመር መንስዔው ጭቅጭቅ ነው
· ይህ ታፔላ የሚሉት ከመጣ ፤ ምሳችን በቆሎ ራታችን ቂጣ
· ታክሲው ሳይቆም መውረድ ይቻላል፡፡
· እንዴት ጭት አትቃሙ ይባላል፣ ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነው
· የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ
· ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
· የቤትህን አመል እዛው!!!
· የሠው ትርፍ የለውም . . . ተጠጋጉ!
· በታክሲ. . . . . ህግ አላውቅም
· ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም
· ለታላቅ መልስ አይሰጥም
· ነገን ለመኖር መጀመሪያ ዛሬን ኑር..በመቃም
· ‹‹ደሀ›› ከፍ ብሎ የሚታየው ባስ ላይ እና እራሱን ሲሰቅል ብቻ ነው፡፡
· እባክዎን የአባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ ይበሉልን
· ለካፌና ለላዳ ብዙ ይከፍላሉ፤ እኛ ጋ ሲሳፈሩ ለምን ይጨቃጨቃሉ
በመጨረሻ
ተሳፋሪ፡- የሰጠከኝ ልክ አይደለም፤ሒሳብ አትችልም" ? አልተማርክም? ደደብ . . . .
ወያላ፡- ጋሼ ድንጋይ ለመጫን እስከ ሁለተኛ ክፍል መማር በቂ ነው
አበቃሁ፡፡
· የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ· ሠውን ማመን ተፈራርሞ ነው· ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
· በቴሌቶን ሂሳብ መክፈል ክልክል ነው
· ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
· ለፀባይኛ ተሳፋሪ የፀባይ ዋንጫ እንሸላማለን
· ለስራ ነው የወጣነው
· በመጀመሪያ የጋለ ደምህን ተቆጣጠርና ሀሳብህን ግለፅ
· ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
· ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
· ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር
· ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል
· ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን
· ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር
· ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ
· ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ
· ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አስተያየት፣ቅሬታ፣ትዝብት ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት ነገር ካለ አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::
· ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን
· ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ
· መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!
· ጤነኛ ካልሆኑ መውረጃዎ ደርሷል
· በጭነት መኪና መታችሁ እዚህ ትቀናጣላችሁ
· የክፍለ ከተማ ሠዎች ካላችሁ ሒሳብ በቅድሚያ
· ኑሮአችሁ ሳይሞላ "ታክሲው አልሞላም?! " ትላላችሁ!· ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን
መጀመር አትችሉም! የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡
· ለዓለም ሙቀት መጨመር መንስዔው ጭቅጭቅ ነው
· ይህ ታፔላ የሚሉት ከመጣ ፤ ምሳችን በቆሎ ራታችን ቂጣ
· ታክሲው ሳይቆም መውረድ ይቻላል፡፡
· እንዴት ጭት አትቃሙ ይባላል፣ ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነው
· የበታችነት ከተሰማህ ዛፍ ላይ ውጣ
· ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
· የቤትህን አመል እዛው!!!
· የሠው ትርፍ የለውም . . . ተጠጋጉ!
· በታክሲ. . . . . ህግ አላውቅም
· ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም
· ለታላቅ መልስ አይሰጥም
· ነገን ለመኖር መጀመሪያ ዛሬን ኑር..በመቃም
· ‹‹ደሀ›› ከፍ ብሎ የሚታየው ባስ ላይ እና እራሱን ሲሰቅል ብቻ ነው፡፡
· እባክዎን የአባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ ይበሉልን
· ለካፌና ለላዳ ብዙ ይከፍላሉ፤ እኛ ጋ ሲሳፈሩ ለምን ይጨቃጨቃሉ
በመጨረሻ
ተሳፋሪ፡- የሰጠከኝ ልክ አይደለም፤ሒሳብ አትችልም" ? አልተማርክም? ደደብ . . . .
ወያላ፡- ጋሼ ድንጋይ ለመጫን እስከ ሁለተኛ ክፍል መማር በቂ ነው
አበቃሁ፡፡
ፓርኪንግ .............. ዳንኤል ክብረት
አሜሪካን ሀገር ወደሚኖሩ ወዳጆቼ ቤት ሄጄ ነበር፡፡ ከተጋቡ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ቤታቸው ስገባ የቤቱም ዕቃ የቤቱም ሰዎች ዝምታ ውጧቸዋል፡፡ አባ አጋቶን ቤት የገባሁ ነው የመሰለኝ፡፡ እርሱ ክፉ ላለመናገር ሰባት ዓመት ድንጋይ በአፉ ጎርሶ በአርምሞ ተቀምጧል፡፡ ነገር ዓለሙ አላምር ሲለኝ ‹ምነው ያለ ወትሯችሁ ዝምታ ዋጣችሁ› ብዬ ተነፈስኩ፡፡ እዚህ ቤት የነበረውን ሳቅና ጨዋታ ስለማውቀው፡፡ ‹ሳቅና ጨዋታ ዝና ካማራችሁ› ሲባል አልሰማችሁም፡፡
የመለሰልኝም የለ፡፡
በኋላ ነገሩን ሳጠናው ሁለቱም ተኳርፈዋል ለካ፡፡ ‹‹ለመሆኑ እንዲህ ሳትነጋገሩ ስንት ጊዜ ተቀመጣችሁ› ብዬ ስጠይቅ ስድስት ወር ሆኗቸዋል፡፡ ሁሉም በየሥራው ይውላል፤ ማታ ይመጣል፤ ኪችን ገብቶ ያበስላል፤ በልቶ ቴሌ ቭዥን ያያል፤ ከዚያም ይተኛል፡፡ ቢል ሲመጣ ይህንን እኔ ከፍያለሁ ብሎ አንዱ ወረቀት ጽፎ ይሄዳል፤ ሌላው በተራው ይከፍላል፡፡ ይቺ ናት ትዳር፡፡
ድሮ የሰማሁትን ቀልድ ነበር ትዝ ያሰኙኝ፤ ባልና ሚስቱ ተኳርፋው አይነጋገሩም አሉ፡፡ ቤቱ እንደ መቃብር በጸጥታ ተውጦ ከርሟል፡፡ አንድ ቀን ባል ሌሊት አሥር ሰዓት የሚነሣበት ጉዳይ ገጠመው፡፡ ከተኛ መነሣት የሚከብደው ቢጤ ነበርና የመቀስቀሻውን ሰዓት ሊሞላ ሲስበው ተበላሽቷል፡፡ አዘነም፤ ተናደደም፡፡ ምን ያድርግ፡፡ ባለቤቱ ገና ከሥራ አልገባችም፡፡ ‹የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይመርጡ› ነውና፡፡ በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ላይ ቀስቅሽኝ› ብሎ ጽፎ በራስጌው ባለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠና ተኛ፡፡
ሚስቱ ስትመጣ አየችውና ስቃ ተኛች፡፡ ልክ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ነቃችና በዚያው በቁራጭ ወረቀት ላይ ‹አሥር ሰዓት ሆኗልና ተነሣ› ብላ ጽፋለት ተኛች፡፡ እርሱ ዕንቅልፉን ለጥጦ ለጥጦ ሲነሣ ነግቷል፡፡ ተናደደ፤ ግን እንዳይናገራት ለካስ ተኳርፈዋል፡፡ እዚያው ወረቀት ላይ ‹በጣም ታሳዥኛለሽ› ብሎ ጻፈላት፡፡
እነዚህ ወዳጆቼ ይህን ነበር ያስታወሱኝ፡፡ አሁን እንዲህ ያለው ኑሮ ምን ዓይነት ኑሮ ይባላል? ብዬ ስም ፍለጋ ብዙ ጊዜ አሰብኩይህን እያሰብኩ እያለ አንድ ዕቃ ለመግዛት‹ካስኮ› ወደሚባለው አሜሪካ ውስጥ ካሉት ታላላቅ መደብሮች ወደ አንዱ ከእነዚሁ ወዳጆቼ ጋር ተጓዝን፡፡ እዚያ መኪናችን ለማቆም አራት የፓርኪንግ ፎቆችን መውጣትና እንደ አዲስ አበባ ስታዲዮም የተለጠጠውን ሰፊ የማቆሚያ ሜዳ ማካለል ነበረብን፡፡ ለዓይን እስኪያታክት ድረስ መኪኖቻ ተኮልኩለውበታል፡፡ በዓይነት ባይነታቸው፡፡ ረዥም፣ አጭር፣ ሽንጣም፣ ቁመታም፤ ያበጠ፣ የከሳ፣ ግልጽ፣ ድፍን፣ ነጭ፣ ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ወይን ጠጅ፣ ምኑ ቅጡ፤ ተደርድረዋል፡፡ ጎን ለጎን፣ ፊትና ኋላ፤ በኋላ መመልከቻቸው ሊነካኩ እስኪደርሱ ድረስ ተደርድረዋል፡፡
የሚገርመው ግን አንዱ ከሌላው ጋር አያወሩም፣ አይጫወቱም፣ ኧረ እንዲያውም አይተዋወቁም፤ አንድ ያደረጋቸው በአንድ የፓርኪንግ ሜዳ መቆማቸው፣ ጎን ለጎን መሆናቸው፣ በአንድ ጣራ ሥር ውሎ ማደራቸው ብቻ ነው፡፡ የዚያኛውን ጠባይ፣ ሥሪት፣ ዓላማና፣ የኑሮ ጓዳ ይህኛው አያውቅም፤ እንዴው በአንድ ፓርኪንግ ቦታ ብቻ አብሮ ቆሞ ማደር፡፡ እነርሱምኮ ‹ቢል› አለባቸው፡፡ የፓርኪንግ ቢል፡፡
ያኔ ስም አገኘሁለትና እነዚህን ወዳጆቼን‹የእናንተ ኑሮኮ ፓርኪንግ ነው› አልኳቸው፡፡ ሁለቱም ወደ እኔ ዞሩ፡፡ ‹እስኪ እነዚህን መኪኖች እዩዋቸው፤ አይፋቀሩ፣ አይጣሉ፣ አያወሩ፣ አይጫወቱ፣ አይወያዩ፣ አብረው አይሠሩ፣ አብረው መከራ አይካፈሉ፣ አብረው አይደሰቱ፤ ግን በአንድ የፓርኪንግ ቦታ ቆመዋል፡፡ ሁሉም በየራሱ መጥቶ ቆመ፡፡ ሁሉም በየራሱ ተነሥቶ ይሄዳል፡፡ የእናንተስ ከዚህ በምን ተለየ፡፡ ሁለታችሁም በየራሳችሁ ትውላላችሁ፤ ማታ ስትመጡ ቤታችሁ ውስጥ ፓርክ ታደርጋላችሁ፤ በቃ›
ከልባቸው ነበር የሳቁት፡፡ ፍርስ እስኪሉ፡፡
የኖርዌዩ ወጣት የጥላቻ ማኅደር
መስፍን ወልደ-ማርያም
ይህ መልካም የሰው ቅርጽ የያዘ ወጣት ተግባሩ የአውሬ ነበር፤ በኦስሎ በኖርዌይ ዋና ከተማ በመኪና ውስጥ ቦምብ ጠምዶ በፍንዳታው ስምንት መንገደኞችን ገደለ፤ አልበቃ ብሎት በጣም ዘመናዊ መሳሪያ ይዞ ወጣቶች ወደተሰበሰቡበት ደሴት ሄዶ እያነጣጠረ ስድሳ ዘጠኝ ያህል ወጣቶችን ገደለ፤ አልሸሸም፤ ሆን ብሎ በእሱ ግምት በአገሩ ላይ የአንዣበበውን አደጋ ለማየት ህዝቡ ጥሩ እንዲነቃ ለማድረግ ነበር፤ አውሮፓ በእስላሞች እየተወረረ በመሆኑ የአውሮፓ ህዝብ ይህንን አደጋ እንዲገነዘብ ለማድረግ የፈጸመው አስፈላጊ ተግባር ነው ብሎ በአደባባይ ተናገረ፤ እስልምናንና እስላሞችን ይጥላ እንጂ ቆም ብሎ ማሰብ ቢችል እንደሱ በጥላቻ የታጨቀ እስላም ብቻውን ሆኖ ኖርዌያዊው ራሱ ከአደረሰው ጥፋት የበለጠ ምን መስራት ይችል ነበር?
በሕግ አምላክ! ከፕሮፌሰር መስፍን
በሕግ አምላክ!
በቢሾፍቱ መንገድ አራተኛ ክፍለ ጦርን አልፌ እየነዳሁ ወደመሀል ከተማ እመጣለሁ፤ ትራፊክ መብራቱ ዘንድ በግራ በኩል ዳር ይዤ ቆምሁና አረንጓዴ ሲበራ መንገዴን ቀጠልሁ። በድንገት ከኋላዬ የነበረ ሚኒባስ በቀኝ በኩል በጣም ተጠግቶ ወደግራ ለመታጠፍ ተጠመዘዘ፣ ፍጥነቴን ቀንሼ ላሳልፈው ስል ድንገት ቆመ። አንድ የካድሬ አንደበት ያለው ጎረምሳ ወረደና ወደኔ መጥቶ “መታጠፍ መብቴ ነውኮ!” አለኝ እየተቆጣ፤ በቀኝ በኩል ተጠምዝዞ መቅደም እንዴት መብቱ ሊሆን እንደሚችል በጥሞና ጠየቅሁት። ወደግራ መዞር መብቱ እንደሆነ ደጋግሞ ይነግረኛል። እኔም እንግዲህ የትራፊክ ፖሊስ መጥቶ ይገላግለናል ብዬ አርፌ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ ቲያትር የማይ መሰለኝ።
አንድ ከሚኒባሱ ጋር ይሁን ከሌላ ግንኙነቱ ያልገባኝ ሰው፣ ከሚኒባሱ ወጥቶ ሞባይሉን ጆሮው ላይ ደቅኖታል፤ ግን ምንም ንግግር አይሰማኝም። ከእኔም ጋር ይሁን ከሹፌሩ ጋር ምንም አልተነጋገረም፤ ሞባይሉን ይዞ ይንጎራደዳል፤ እኔ ተመልካች ነኝ። አንዲት ወጣት ሴት ነገሩ አላማራትም መሰለኝ ከሚኒባሱ ወጥታ ወደ ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት አጥር አቅጣጫ ኼደች። ሹፌሩ እንደተሰበረ ሸክላ ያንኑ በቀኝ በኩል የመታጠፍ መብቱን እጆቹን እያወራጨ ይነግረኛል፤ ወጣቱን ካድሬ ሹፌሩ ትኩር ብዬ ሳየው ተወው! ቀልድ ነው! የሚለኝ ይመስላል። ባለሞባይሉም መኳንንት የማስመሰል ትርዕይቱን ቀጥሏል። ከእኔም ጋር ሆነ ከሹፌሩ ጋር ንግግር የለውም። አለኝ የሚለውን ክብሩን በዝምታ ሸፍኖታል፤ የወጣቱን ሹፌር አንደበት የሚያንቀሳቅስበት የራሱ ዘዴ ያለው ይመስላል። ወጣቱ ሹፌርም መሣሪያነቱ ገብቶት የሚቀልድ ይመስላል፤ እኔም ከተቀመጥኩሁበት አልተንቀሳቀስሁም፤ መናገርም ትቻለሁ። የትራፊክ ፖሊስ መጥቶ ይገላግለናል እያልሁ አስባለሁ። በድንገት ባለሞባይሉን መኳንንት ሹፌሩን በዓይኑ ጠቅሶት ወደ መኪናው ውስጥ ገባ። መኼድ ሲጀምሩ እኔ አሁንም እንደተደናገርሁ ነኝ፤ ምናልባት ትራፊክ ፖሊስ ሊያመጡ እንደሆነ በማለት ሳልንቀሳቀስ ትንሽ ቆየሁ፤ ሲርቁ ጊዜ እኔም መንገዴን እየተገረምሁ ቀጠልሁ።
የተፈለገው ምን እንደሆነ አሁንም አልገባኝም። በሆነው ባልሆነው ምክንያት እየተፈጠረ ሰውን ማጉላላት የሚቻል መሆኑን ለማሳየት ነው? ጉራ መንፋት የሚባለው ነው? ለማስደንገጥ ነው? ለማስፈራራት ነው? አደጋ ፈጥሮ በዚያ ሳቢያ ትንሽ ጥቅም ለማግኘት ነው?
ነገሩ ሁሉ ፍፁም ፉርሽ ሲሆንብኝ ያደረብኝ ጥርጣሬ ጥሩ አይደለም። በወንበዴነትና በሕጋዊ ሥራ መሀከል ያለውን የሠፋ ልዩነት በጣም ያጠብበዋል። ስለዚህም ወንበዴውን ከሕጋዊው ሠራተኛ ለመለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ሕጋዊ ሥራውን ያረክሰዋል። በአሁኑ ጊዜ በፈረንሣይ ውስጥ አንድ ፖለቲከኛን ሲከታተሉ የነበሩ አሥር ሰዎች ታስረው በምርመራ ላይ መሆናቸውን ከዚያው የተሠራጨው ዜና ይናገራል። እኛ ዘንድ እንዲህ ያለውን አቤቱታ ማን ይሰማው ይሆን?
በአፄ ምኒልክ ዘመን አንድ ዘፈን ነበር ይባላል። ንጉሥ ምኒልክ ከወይዘሮ ባፈና የወለዱአቸው ልጃቸው ወይዘሮ ማናለብሽ ይባላሉ። ታዲያ ወይዘሮ ማናለብሽ አንዱን ሰው በድለዋል መሰለኝ፤ መነሻውን ረሳሁት፤ ማስታወሻዬም ጠፋብኝ፤ አንድ የሚያስታውስ ሽማግሌ ባገኝ ደስ ይለኛል፤ ለማናቸውም ዘፈኑ የሚቀጥለው ነው፦
“እናትሽ ባፈና፣ ምኒልክ አባትሽ፣
ባልሽ ማመድ አሊ አንቺ ማናለብሽ፣
ከየትኛው ዳኛ አቤት ልበልብሽ?
ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ በኋላ በያለበት በመንገድ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሬስቶራንት ውስጥም እየገቡ የቅንጅት ሰዎችን ማዋከብ፣ ማስፈራራትና አንዳንድ ጸያፍ ነገሮችን ማደረግ የተለመደ ሆኖ ነበር፤ በእውነት ያሳፍር ነበር። ጨዋነት የት ገባ? ጥልቁ ሀብታችን እሱ ነበር፤ ዛሬ የተናካሽ ውሻ ባሕሪ ከየት አመጣን? ያውም በባቡር መንገድ ላይ!
Sunday, 18 November 2012
“. . . .ከምሊሴ ፀጉር” ጀማሌ አባቢያ(ababiyjemal@gmail.com) እውነት እውነት እሊችኋሇሁ ይህ ሣይፈፀም መስከረም አይጠባም፡፡
እንዱህ ይሆናሌ፡፡ ይህን ሇመናገርም ነብይ መሆን አይጠበቅም፡፡ ቴዱ አፎሮ “ብወዴሽ ብወዴሽ አlሇወጣሌህ አሇኝ” እንዲሇው፤
ኢህአዳግ ነፍሴ ቢያስበው ቢያስበው አሌወጣሌህ ይሇውና፡፡ የነፍስኄር መሇስ ዜናዊ ፎቶ በየግዴግዲው ሊይ እንዱህ እንዯዋዛ
ተንጠሌጥል መቅረቱ ቅጥሌ ያዯርግውና፤ “ባሇራዕዩ”ን መሪ ከሰው ሌብ ጽሊት ሇማተም አማራጭ ያሠሊስሌና፤ ግዴቡም
እንዱፋጠን፣ ሐዱደም እንዯ ጉንዲን መንገዴ እንዱዘረጋ፣ ኤላክትሪኩም እንዱሸጥ፣ ይሌና በመሊ በሰበብ በዘዳ አመኸኝቶ አንዴ
ዴንቅ ሐሣብ ያቀርባሌ፡፡
የራዱዮ ፋናው ገጣሚ በረከት “መቶ ብር ሲነበብ” ብል በገጠመው ግጥም፤ “ያሇ ትክሇ ሰውነት አንገቱ ብቻ የሚታይ የአንበሣ
ቁጣ ስሇማያምር፤ በበሬ እያረስን 8ዏ ሚሉዮን መመገብ ስሊሌቻሌንና ስሇማንችሌ፣ ጀርምን ይሁን ጀርመንን ማየቱ ያሌሇየሇት
ተመራማሪ ሇትምህርት አስር ሆነው ሔዯው አዚያው የቀሩትን ዘጠኙን ያስታውሰናሌ” በማሇት በአስዯናቂ ሁኔታ እንዯገሇፀው፤
አገሪቱ በእዴገትና ትራንስፎርሜሽን እቅደ መሠሊሌ ከዴህነት ተስፈንጥራ ሇመውጣትና በአጭር ጊዜ ውስጥ በተፋጠነ ሌማት
መካከሇኛ ገቢ ካሊቸው አገሮች ተርታ ሇመሠሇፍ አቅሟን ሁለ አሟጣ እየተጠቀመች ባሇችበት በአሁኑ ወቅት፤ ነባራዊውን ሃቅ
የማይወክሌ የመገበያያ የገንዘብ ኖት መጠቀም ሕዝቡ ሊይ በስውር ከሚካሔደ የማሣነፍ እና የዴንዛዜ ዘመቻ አንደ አካሌ
እንዯሆነ በመገንዘብ፤ ከዚህም በተጨማሪ የወዲጅ አገራትን ተሞከሮ ግምት ውስጥ በማስገባት፤ አሁን በጥቅም ሊይ ባለት
የወረቀት ኖቶች አንዴ ገጽ ሊይ የአገሪቱ የእዴገትና ትራንስፎርሜሸን እቅዴ ወጣኒና መሐንዱስ የሆኑት የታሊቁ መሪያችን ምስሌ
እንዱታተም ይሇናሌ፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሇተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ይህንን ጉዲይ እንዯ ዓመቱ ቀሪ እቅዴ ያስተዋውቃለ፡፡
በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የስሌክ ጥሪ እንዯጉዴ ይጎርፋሌ፡፡ ኢቴቪ ዯግሞ የብሔራዊ ባንክ የሥራ ኃሊፊዎችን ሇውይይት ይጋብዛሌ፡፡
የሥራ ኃሊፊዎቹም ይሊለ፤ “እንዱያውም አሁን ያሇው የብር ኖት በተሇይ መቶ ብር በቀሊለ ፎርጅ ሉዯረግ እንዯሚችሌ፣
በብሔራዊ ባንክ በኩሌ ግንዛቤ የተጨበጠበት በመሆኑ የገንዘቡን የምስጢር መሇያዎች የበሇጠ ሇማጠናከር ጥናት አዴርጎ
በክሇሣ ሊይ እንዯነበርና የብር ኖቶቹ መቀየር ሇጥናቱ ተፈፃሚነት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዲሇው፣ ስሇ ብር ኖት ሇውጥ ትግበራ
ሕዝቡ ማወቅ ያሇበት ጉዲይ” ሊይ ከቀረበሊቸው የብርጭቆ ውሃ ፉት እያለ እስኪታክተን ይነግሩናሌ፡፡
ነገሩ እየበረዯ ሲሔዴ ዯግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ በተሟገት አምደ የብር ኖቶች ቅያሪ ከአገሪቱ የባንክ ሕግ አንፃር ሲፈተሽ፤ የብር
ኖቶች ሇውጥና የሀገሮች ሌምዴ የሚሌ ረዥም ጽሑፍ ያስነብበናሌ፡፡ እኒህ ሰውዬ በየአዯባባዩ ፎቶአቸው ተሠቅል እስከመቼ ነው እያሌሽ ስትማረሪ በኪስሽ ሸጉጠሻቸው ኑሮን
ትገፊያታሇሽ፡፡፡
እውነት እውነት እሊችኋሇሁ፤ ይህ ሣይፈፀም መስከረም አይጠባም፡፡
ናፍቆት ግጥም በሄኖክ የሺጥላ
ግጥም በሄኖክ የሺጥላ
መታሰቢያነቱ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ለልጁ ናፍቆት
"ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ:: አይዞህ ስራ ተቀያያሪ ነው:: ንጉሱ የወረሱት በደርግ ተመልሷል : ደርግ የወረሰው በኢህአዴግ ተመልሷል : ኢህአዴግ የወረሰው ደግሞ ኢህአዴግ ሲወድቅ መመለሱ አይቀርም::" ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ
በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች በብዛት እየለቀቁ ነው
ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በውጭ አገር አሰሪዎችና ተባባሪ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ተቆጣጣሪዎች በሚፈጸም በደል ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ገልጸዋል።
በመጀመሪያዎቹ የግንባታ ወራት አገራዊ ስሜቱ ፈንቅሎት ወደ አካባቢው በመሄድ ከአንድ አመት ከስድስት ወራት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ወጣት ፣ ሰራተኛው በየጊዜው በሚደርስበት በደል በቀን ውስጥ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ሰራተኞች ይለቃሉ ብሎአል። እርሱም ስራውን ለመልቀቅ መገደዱን ገልጿል።
ሰራተኛው ከሚዘረዝራቸው በደሎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቅሰው በሰራተኛውና በማኔጂመንቱ መካከል ያለውን የተበላሸ ግንኙነት ነው። ከውጭ ተቀጥረው የሚመጡት የጣሊያን ሰራተኞች ሳይቀር የኢትዮጵያ ሰራተኞች የሚሰሩትን ስራና አያያያዛቸውን እየተመለከቱ ነቀፌታዊ አስተያየቶችን ይሰጣሉ ብሎአል
ለሰራተኛው የተዘጋጀው ቤት የአካባቢውን ሙቀት ለመከላከል እንደማያስችል፣ የሚቀርበውም ምግብ በአካባቢው የሚታየውን በሽታ ለመከላከል የማያስችል መሆኑን ፣ የመብት ጥያቄዎችን መጠየቅ የሚያሳስር ጉዳይ መሆኑንም ሰራተኛው ገልጿል
በቅርብ ጊዜ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች መሰራታቸውን የገለጸው ሰራተኛው፣ ይሁን እንጅ ሙቀቱን ለመቋቋም የሚያስችል ኤሲ ያልተገጠመላቸው በመሆኑ ችግሩ አሁንም እንዳለ ነው ብሎአል።
ሰራተኛው ልምድ ያላቸው ሰራተኞች በብዛት እየለቀቁ፣ አዳዲሶቹ ሰራተኞችም ሶስት ወር ሳይቆዩ ሁኔታውን ተረድተው እንደሚመለሱ ትዝብቱን አስፍሯል።
ሰራተኞች ከሁለት ሳምንት በፊት ያደረጉትን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ቢሄዱም ከማስፈራራት በስተቀር በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ተመልሰዋል።
እስካሁን ድረስ ሰራተኛው በአገራዊ ፍቅር ሲሰራ እንደነበር ያስታወሰው ሰራተኛው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰራተኛው በበሽታ ሲጠቃ፣ መሰላቸት ሲመጣ ስራውም በዚያው መጠን እየተጓተተ መምጣቱን አልሸሸገም።
መንግስት ሰሞኑን ለሪዩተርስ በሰጠው መግለጫ ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል ብሎአል። ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የተባለው የጊዜ ገድብ በግልጽ ባይቀመጠም ከ4 እስከ 7 አመታት ሊፈጅ እንደሚችል ነው የመንግስት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ከሚሰጡት መግለጫ ለመረዳት ይቻላል።
ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአባይ ግድብ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በውጭ አገር አሰሪዎችና ተባባሪ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ተቆጣጣሪዎች በሚፈጸም በደል ስራቸውን እየለቀቁ መሆኑን በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ገልጸዋል።
በመጀመሪያዎቹ የግንባታ ወራት አገራዊ ስሜቱ ፈንቅሎት ወደ አካባቢው በመሄድ ከአንድ አመት ከስድስት ወራት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ወጣት ፣ ሰራተኛው በየጊዜው በሚደርስበት በደል በቀን ውስጥ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ሰራተኞች ይለቃሉ ብሎአል። እርሱም ስራውን ለመልቀቅ መገደዱን ገልጿል።
ሰራተኛው ከሚዘረዝራቸው በደሎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቅሰው በሰራተኛውና በማኔጂመንቱ መካከል ያለውን የተበላሸ ግንኙነት ነው። ከውጭ ተቀጥረው የሚመጡት የጣሊያን ሰራተኞች ሳይቀር የኢትዮጵያ ሰራተኞች የሚሰሩትን ስራና አያያያዛቸውን እየተመለከቱ ነቀፌታዊ አስተያየቶችን ይሰጣሉ ብሎአል
ለሰራተኛው የተዘጋጀው ቤት የአካባቢውን ሙቀት ለመከላከል እንደማያስችል፣ የሚቀርበውም ምግብ በአካባቢው የሚታየውን በሽታ ለመከላከል የማያስችል መሆኑን ፣ የመብት ጥያቄዎችን መጠየቅ የሚያሳስር ጉዳይ መሆኑንም ሰራተኛው ገልጿል
በቅርብ ጊዜ ውስጥ መኖሪያ ቤቶች መሰራታቸውን የገለጸው ሰራተኛው፣ ይሁን እንጅ ሙቀቱን ለመቋቋም የሚያስችል ኤሲ ያልተገጠመላቸው በመሆኑ ችግሩ አሁንም እንዳለ ነው ብሎአል።
ሰራተኛው ልምድ ያላቸው ሰራተኞች በብዛት እየለቀቁ፣ አዳዲሶቹ ሰራተኞችም ሶስት ወር ሳይቆዩ ሁኔታውን ተረድተው እንደሚመለሱ ትዝብቱን አስፍሯል።
ሰራተኞች ከሁለት ሳምንት በፊት ያደረጉትን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ቢሄዱም ከማስፈራራት በስተቀር በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ተመልሰዋል።
እስካሁን ድረስ ሰራተኛው በአገራዊ ፍቅር ሲሰራ እንደነበር ያስታወሰው ሰራተኛው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰራተኛው በበሽታ ሲጠቃ፣ መሰላቸት ሲመጣ ስራውም በዚያው መጠን እየተጓተተ መምጣቱን አልሸሸገም።
መንግስት ሰሞኑን ለሪዩተርስ በሰጠው መግለጫ ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል ብሎአል። ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የተባለው የጊዜ ገድብ በግልጽ ባይቀመጠም ከ4 እስከ 7 አመታት ሊፈጅ እንደሚችል ነው የመንግስት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ከሚሰጡት መግለጫ ለመረዳት ይቻላል።
Subscribe to:
Posts (Atom)