"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday, 7 September 2012

አወዛጋቢዋ ድንግል ማርያም ነኝ ባይዋ ሴት በድጋሚ ወደ ዜና ብቅ አለች


  • በአዲስ አበባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግድያ ወንጀል እና በተለያዩ ክሶች አቃቤ ሕግ ከሷታል፡፡
  • በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ውጪ በፊቼ ክስ ተመስርቶባታል፡:
  • ተከታዮቿ በአዳዲስ ምልምሎችም ከበፊቱ በዝተዋል፡፡
  • ተከታዮቿ ከደብረ ሊባኖስ  መስቀል ቤተ  በመግባት እና ደብሩ ቅዳሴ ላይ እያለ ቅዱሳኑን እና መስቀሉን በመሳደባቸው ግጭት  እና ብጥብጥ ፈጥረዋ፡፡ 
ከሰማናቸው በጣም አስገራሚ እና አሳዛኙ ከስተቶች መካከል የዚህች ድንግል ማርያም ነኝ ባይ  ሴት ጉዳይ ከሁሉም አስገራሚ እና አሳዛኝ እንዲሁ በደፈናው ተከታይ ማፍራት እንደሚቻልና የዋሐንን በቀላሉ በመያዝ እንደሚጠቀሙባቸው ያሳየል፡፡ ለካ በቀላሉ የሚታለል ሰው በዝቷልና ያሰኛል፡፡
ከዚህ በፊት በዚህችው ሴት ጉዳይ ካስነበብናችሁ ዋና ጉዳይ መካከል፡-
  •   እናቷ ከሞተች በኋላ ከእግዚአብሔር መልክት ልትነግራት እንደተነሳች ከዚህ ግዚ ጀምሮ ተከታዮች ይዞ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመሄድ የማወዛገብ ስራዎች እንደሰራች
  •      በፆም ወቅት ሥጋ እንዲበሉ ማስገደዱን በሌሎች ጊዜዬም አብዝተው እንዲፆሙ ማስገደድ
  •   ተከታዮቿ ሰማያዊያን ነን የሚሉ እንደሆነ
  •      3ቱ ልጆቼንም የወለድኩት በመንፈስ ቅዱስ ነው ጠባቂዬ ተርፌሳ ዮሴፍ ማርያምን እንደሚጠብቃት የእኔ ጠባቂ ነው፡፡
  •      እየሱስ ክርስቶስ ከእኔ ይወለዳል…….

ዘማሪት ዘርፌ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልጠበቀ ጋብቻ


ሁሌም ቢሆን ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ እያየን ዝም የሚል ልብ የለንም፡፡ በተለይ በመድረክ አገልግሎት ላይ በመናያቸው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲጣስ ማየተ ደግሞ በጣሙን የቆስላል፡፡ መቼም ሳይገባው የቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ለመውጣት የሚደፍር አለ ብለን አናስብም ትንሽም ቢሆን ምስጢራትን የተማረ እና የስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያወቀ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓትማ ካየንው አንድ ሰው ወደ አገልግሎት ከመግባቱ በፊት በፈሪሐ እግዚአብሔር ሊቀርብ ይገባዋል::“በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።” ዘዳ.12:28፤ እንደተባልንው ስንመላለስ እግዚአብሔርን በመፍራት የሚያዘንን በመፈጸም መሆን ይኖርብናል:: 
እግዚአብሔርን የሚፈራ ትውልድ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል ይገዛል በእግዚአብሔርም የባረካል፡፡ በንስሃ ህይወቱም ሁል ጊዜ ተጠብቆ መኖርም ይገባል “እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ” ራእ.3:3 ንስሃ የሚገባ ሰው ደግሞ ህይወቱ በጸሎት የመሰረታል ሁል ጊዜም ይሰግዳል ይጾማልም ለአገልግሎቱም መቃናተ ፈቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ ይኖራልም፡፡ እነኝህ ያነሳናቸው በጣም ጥቂቱን ግዴታዎች ነው ይህቺን ትንሻን ህይወት የሌለው ክርስቲያን አገልጋይ አይደለም ክርስቲያን ለመሆኑም ጥርጣሬ ውስጥ ይገባል፡፡ 


ይሁንና ይህቺን በጥቂቱ ያልነው የዘማሪት ዘርፌ አይን ያወጣ ጋብቻ ነው፡፡ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ማናት? በዘፋኝነት ህይወት እያለች ምን አይነት ህይወት ነበራት? የሚሉትን ሁሉ እንተወውና በቤተ ክርስቲያናችን ወደ አገልግሎት ከመጣች ብኋላ በኢትዮጵያ እያለች ከፕሮትስታንት ተሃድሶ አራማጆች ጎን ብዙ ጊዜ ስሟ ሲነሳ የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካም ከሄደች ወዲህ ከአባ 

ወልደ ትንሳኤ ጋር በአንድ ጉባኤ ለአገልግሎት እንደምትሳተፍ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

Thursday, 6 September 2012

ሐዘን የሸሸገው ፈገግታ


ሐዘን አጥንት ሲደርስ ደግ አይደለም:: ሰውም እግዜሩም አይወዱትም:: ለአገርም አይጠቅምም ለጠላትም ደስ አይበለው:: እንዲህ አገር ነቅሎ ሙሾውን ሲያስነካው ተዉ እሚል ይጥፋ? ያ ምስኪን ትዝ አለኝ... ጃንሜዳ ጋር ሞቶ እሚቀብረው ሲያጣ አዝኖ ወደቤቱ የተመለሰው ሃሃሃሃ…:: ለማንኛውም ሕገ መንግስቱ እንደሚለው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲያርፍ ወይም በሞት ሲለይ አንድ ቀን ብሔራዊ ሃዘን ይታወጃል:: እንደ በረከት ስምኦን ቢሮ አሥራ አራት ቀን መሆኑ ነው:: [በየቀኑ የሚጣስን ሕገመንግስት አንስቶ መከራከሩ ፅንፈኛ ያስብለኛል ስለዚህ ይለፈኝ] በዛ ላይ ዋሽንት አለ [ለአንዳንዶች vuvusela ሆኖባቸዋል]:: ስለዚህም እንደ አንድ ሐዘናችንን ለማስረሳት እንደሚጥር ልማታዊ አፅናኝ በለቅሶው አካባቢ ከተሰሙት ንግግሮች ጀምሮ ወሬው እንዳመራን ውል አልባ ጨዋታ ብንጨዋወትስ...

ሰሞኑን እንደ ጆሮ ስቃዩን ያየ (ሰደቃውን የበላ) የለም... ጆሮ ሆይ አድናቂህ ነኝ!

የልማታዊው በረንዳ አዳሪ አስተያየት፣ "አባታችንን ተማምነን ነው በረንዳ የምናድረው" የሚለው አስገራሚ ለቅሶ የልማታዊውን እስረኛ ሰሜ ባላገሩን ቃለ ምልልስ ያስታውሰናል፤ "በመታሰሬ በጣም ደስተኛ ነኝ መንግስቴንም አመሰግነዋለው" ነበር ያለው ሰሜ ከእስር ቤት እንደወጣ [ሰሜ ሮሚዎን ሆኖ ትያትር እንደተጫወተ ላስታውስ]፡፡ ሰሜን ተንጠላጥለን ወደ ሁዋላ ስንሄድ "ታንክ ተደግፎ መጽሐፍ ያነብ ነበር" ያለው የኢትዮፈርስት ዌብሳይት  አዘጋጅ ቤን፣ "HR 2003ን ከማፅደቃቸው በፊት የአሜሪካን ሴናተሮች ጉዳዩን መላልሰው እንዲያዩት የመከሩት የብቸና ገበሬዎች፣ የአሜሪካንን ኢምፔርያሊዝም ከተሳሳተ ርዕዮተ-ዓለሙ እንዲታረም ያስጠነቀቁት የቦረና አርብቶ አደሮች"

የመለስ ዜናዊ ፲ ታላላቅ የአፍ ወለምታዎች


 የጠቅላያችንን አስር ታላላቅ የአፍ ወለምታዎች ፣ በዚህ ንግግራቸው የተገረመው አብዛኛው ሰው ወደሚሰማው ቋንቋ እንደወረደ ተርጉመን ለአደባባይ አውለነዋል፡፡


፲. በ1983  ዓ.ም. በለንደኑ ጉባዔ  በኢህአዴግ ታርጋ የተሰባሰቡት ቡድኖች የፓርቲያቸው ህወሓት ተቀጥላ እንደሚሆኑ ለአሜሪካና ብሪታኒያ ባለስልጣናት አረዷቸው፡፡ብሪታኒያውያኑ ይህንን በተቃወሙ ጊዜ ቁጣቸው በግልጽ የሚታየው አቶ መለስ እንዲህ አሉ፡፡

     “አንድ ነገር ግልጽ ላድርግ  ፤ ከጉባዔው በኋላ  ኢህአዴግ የሚባል መንግስት አይኖረንም፡፡”

         
፱.  በ1985/6  ዓ.ም. ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸውን እይታ በአንድ ቃለ መጠይቅ ማብቂያ ላይ እንዲያካፍሉ ከአንድ ዘጋቢ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ መለስ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡፡

     “የኢትዮጵያ ዕድሜ መቶ አመት ብቻ ነው ፤ከዚህ በቀር ሌላ  የሚያወሩት ራሳቸውን በተረት ተረት እያሞኙ ነው፡፡"

፰. በ1986/7 ዓ.ም. አስመራ ከተማ ውስጥ  ለአንድ የውጭ ሀገር ጋዜጠኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ስለ ኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

    “ከኢሳይያስ ጋር አንድ ሰዓት ማሳለፍ፣ 10 መጽሐፍ ከማንበብ በላይ ልበብሩህ፣ አዋቂ እና ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡”

፯. ለአምስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን ታሪክ ካጠኑት ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ጋር በ1989 ዓ.ም.  በነበራቸው ወይይት ከምንሊክ ወረራ በፊት ኢትዮጵያ የምትባል አንዲት  አገር እንዳልነበረች ተናገሩ፡፡ይህ የበለጠ አጽንኦት ለመስጠት ሲሞክሩ እንዲህ አሉ፡፡

      “ትግሬዎች የአክሱም  አላቸው ፤ ይህ ለጉራጌ ምኑ ነው? አገዎች ላሊበላ  አላቸው ፤ ይህ ለኦሮሞ ምኑ ነው? ጎንደሬዎች ቤተ መንግስት አላቸው፤ ይህ ለወላይታ ምኑ ነው?”

፮. ለመንግስት ሚዲያዎች በሰጡት አንድ ቃለ መጠይቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከጨርቅነት የዘለለ ምንም እንዳልሆነ ተናገረዋል፡፡

      “ባንዲራ የጨርቅ ቁራጭ ነው”

፭. በ1990 ዓ.ም. ሰማኒያ ሺ የሚደርሱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ኤርትራውያንን ሀብት ንብረታቸውን ቀምተው  ኢ-ሰብዐዊ በሆነ መልኩ ከሀገር ካስወጡ በኃላ ለፓርላማው እንዲህ አሉ፡፡

      “የአይናቸው ቀለም ካላማረን ፣ ከሀገራችን የማባረር መብት አለን፡፡”

፬. በ1993 ዓ.ም. ልጇ ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዘምቶ አለመመለሱ ያሳሰባት  እናት ልጇ ወዴት እንዳለ መለስ ዜናዊን  አጥብቃ ጠየቀች፡፡በጥያቄዋ ድምጸት የተበሳጩት አቶ መለስ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡፡

      “ሴትዮ፣ ልጅሽ በስድስት ወራት  ወደቤቱ ካልተመለሰ ፣ መልሱን ታውቂዋለሽ፡፡”

፫. በ1997 ዓ.ም. ምርጫን ተከትሎ በተካሄደው  ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ  በጠቅላያችን ትዕዛዝ 193 ያልታጠቁ ንጹሐን ዜጎች በአዲስ አበባ እንዲገደሉ ትዕዛዝ  ሲሠጡ የትግራዋይ ተወላጅ ለሆነው ለታማኛቸው ጄኔራል ሳሞራ አማራዎችን ለማለት አህዮች የሚለውን ቃል ተጠቅሟል፡፡

      “እነዚህ አህያ አማራዎች  ትምህርት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሰላማዊና  ሃይማኖተኛ  የሚሆኑት ክላሽንኮቭ ስትደግንባቸው ብቻ ነው፡፡”

፪. ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የከሸፈ ፣ ተከተታይ ወረራ   በ1998 ዓ.ም.  በሱማሊያ መሬት ላይ መሬት ያዛ በነበረበት ሰዓት ለ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አላማቸው የኢስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን ለማንበርከክ ሳይሆን በዚያ የሌሉትን በሱማሊያ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች ለማሰደድ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

     “እያጠቃን ያለነው   በሱማሌ ወይዛዝርት ቀሚስ ስር  የተሸሸጉ የኤርትራ ኃይሎችን ብቻ ነው፡፡”


፩. በ2002 ዓ.ም. ከሊቢያው አምባገነን ሙዐመር ጋዳፊ ጋር ስለ ሁለትዮሽ ግንኙነት በሚወያዩበት ጊዜ አቶ መለስ እንዲህ አሉ፡፡

       “እኔ የመናዊ ነኝ ፤ የመናዊ እንደሆንኩኝ አውቃለው ፤ ሁላችንም የመናውያን ነን፡፡ ከነገሥታቱ  ቤተሰብ በቀር ሁላችንም አረብ ነን፡፡”

የተማርንበትም የተማረርንበትም ሰሞን


ዳንኤል ክብረት)
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ከተረዳበት ሰዓት ጀምሮ ሀገራችን አዲስ መልክ ይዛለች፡፡ ያለፉት ቀናት ስለራሳችን የተማርንባቸው፤ በራሳችንም የተማረርንባቸው ቀናት ነበሩ፡፡ እስኪ ከተማርንባቸው ልጀምር፡፡
ትዝ ይለኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከውጭ ሀገር ወደ አዲስ አበባ የሚገቡበት ጊዜ ነበር፡፡ በቦሌ ጎዳና ፖሊሶች አዚህም እዚያም በዛ ብለዋል፡፡ እኔ ደግሞ አልሰማሁም ነበርና እዚያ አካባቢ ለሥራ መሄድ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መንገዱ ጭር አለ፡፡ ፖሊሶችም መጡና ከአካባቢው ዘወር እንድንል ነገሩን፡፡ የሚገርመው ነገር ግን አካባቢው በአፓርታማዎች የተጠቀጠቀ ነበርና ዘወር የምንልበት ቦታ ጠፋን፡፡ ፖሊሱ ግን አሁንም አሁንም ከአካባቢው ዘወር እንል ዘንድ ያዝዛል፡፡ ግን የት ዘወር እንበል? በመጨረሻ መጣና በአፓርታማው የታችኛው ክፍል ካሉት ቤቶች አንዱን አንኳኳ፡፡ አንዲት በእድሜ ጠና ያሉ ሴት ከፈቱ፡፡ ‹‹ግቡ›› አለን ፖሊሱ፡፡ አንድ ሰባት እንሆናለን፡፡ ግራ ገብቶን ተያየን፡፡ ከጀርባችን ገፋ ገፋ እያደረገ ሰው ቤት ውስጥ አስገባን፡፡ ስለ ቻይና ባቡርና ፖሊስ ያየሁት ፊልም ነው ትዝ ያለኝ፡፡ ሴትዮዋ በሩን እንዲዘጉ ተነገራቸው፡፡ ተዘጋ፡፡
አሁንም ሰው ቤት ገብተን ተያየን፡፡ ደግነቱ ሴትዮዋ ተግባቢ ናቸውና ‹‹በሉ እንግዲህ መንግሥት ካዛመደን ዐረፍ በሉና ሻሂ ጠጡ›› አሉን፡፡ እኛም ሳቅ እያልን ባገኘነው ወንበር ተቀመጥን፡፡ እዚያ ተቀምጠንም በባለ ሥልጣኖቻችንና በሕዝባቸው መካከል ስላለው ግንኙነት ተቸን፤ አማን፤ ሃሳብም ሰነዘርን፡፡ ከዚህ በፊት ያጋጠመንንም ተጨዋወትን፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን በመጣበት ማታ ይህንን አጋጣሚ ነበር የማስበው፡፡ ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ መንገድ ላይ ወጥቶ ነበር፡፡ በአንዳንድ አደረጃጀቶች በኩል ከመጡ ጥቂት ሰዎች በቀር አብዛኛው ሰው በራሱ ፈቃድ ኀዘኑን ለመግለጥ ታሪክም ለማየት ነበር የወጣው፡፡ ጧፍ እንኳን ያበራው ዕለቱ የፍልሰታ ጾም ማብቂያ የኪዳነ ምሕረት ዋዜማ በመሆኑ በቦሌ መድኃኔዓለም፤ በኡራኤል፣ በእስጢፋኖስና በግቢ ገብርኤል አካባቢ ለበዓሉ ጧፍ ለመሸጥ ከተቀመጡት እናቶች እየገዛ ነበር፡፡ ጧፍ ማብራትን ሕዝቡ ራሱ ያመጣው የአቀባበል ሥርዓት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በየ ቀበሌው ተዳረሰ፡፡

THE 5th GENERAL CONGRESS OF THE EPRP CONCLUDED


 
                                          የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
                                        Ethiopian  People's  Revolutionary Party (EPRP)                                                                                                                                                                                                                                                                                                                   .
The 5th general congress of the EPRP was held from August 29 to September 1 and has been
concluded with full success. Delegates from various sections of the party attended the congress,
heard the full report of the Leadership Committee and passed resolutions to strengthen the party,
to mobilize the people for the all out struggle and intensify the struggle against the tyrannical
regime                                                                                                                                                                                .The significance  of the 5th Congress has been appreciated due to the fact that  it has taken place at
a time when the people’s struggle for democracy has been intensified and the party has defeated
most of the conspiracies and plots hatched against it by the enemies of the Ethiopian people. The
Congress noted that the regime of Meles Zenawi is on its death bed (with the dictator himself dead)
and a transition to democracy possible if people reject the foreign inspired maneuver to  assure
the continuation of the regime or to make cosmetic changes to continue with a similar puppet
regime. The Congress has also made a full analysis of the local and international situation and set
its tasks and priorities based on its conclusion of what ought to be done to end with the divisive
and dictatorial regime and bring about real and democratic change in Ethiopia. As opposed to the
affirmation made by the apologists of the regime the Congress has firmly concluded that the
regime has brought political and economic disaster to Ethiopia and all talk of economic progress is
but a lie and a sham.
The 5
th
Congress has critically  reexamined its own experience vis-a-vis the united front and
assessed the ongoing front formation taken by various groups. It has reaffirmed the EPRP’s call
for an actual and active united action within Ethiopia itself by all viable forces committed to
democracy and Ethiopian unity. The Congress has also commended the various civic
organizations involved in human rights and the plight of women. The EPRP political program andinternal rules and regulations were also amended. In the end, the congress has elected a new
higher leadership committee, approved the resolutions on various issues and expressed the
determination of the party to continue and intensify the struggle against the dictatorship in
Ethiopia.
The struggle continues!!

Wednesday, 5 September 2012

የኢህአዴግ ስብሰባ ሊቀ መንበሩን ሳይመርጥ ተበተነ


   (ኢ.ኤም.ኤፍ ልዩ ዘገ) የመለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የተጠራው የኢህ አዴግ ስራ አስፈጻሚ አካላት ስብሰባ በዋና ዋና የስልጣን ሽግሽግ ጉዳይ ሳይስማማ መበተኑን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ የደረሰው ዝርዝር ዘገባ ያስረዳል። በዘገባው መሰረት በኢህ አዴግ የጉባዔ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ስብሰባው ለመለስ ዜናዊ  የህሊና ጸሎት በማድረግ ነበር የተጀመረው። ከዚያም የአዲስ አበባ ህዝብ እና የሌላ አገር መሪዎች ያደረጉት የሃዘን መግለጫ ጉዳይ የመጀመሪያው መነጋገሪያ አጀንዳ ነበር።
ይህ የህዝቡ ሃዘንም ህዝቡ ምን ያህል ኢህአዴግን እንደሚወደው አመላክች ጉዳይ መሆኑን፤ እራስን በማሞገስና በኩራት በመጀቦን ነበር ስብሰባው የቀጠለው። በስብሰባው ላይ ከጠቅላላው 36 ተሰብሳቢዎች መካከል ሲከራከሩና ብዙ ሲናገሩ የነበሩት የሚከተሉት የድርጅት አባላት ነበሩ። ከህወሃት በኩል አባይ ወልዱ፣ ድ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ጸሃየ በርኼ፣ በየነ ምትኩ፣ አዜብ መስፍን፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ አባዲ ዘሙ እና ደብረጽዮን ገ/መስቀል ሲሆኑ፤ በኢህዴን / ብአዴን በኩል ደግሞ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አዲሱ ለገሰ፣ አያሌው ጎበዜ፣ ብርሃን ኃይሉ፣ በረከት ስምኦን እና ተፈራ ደርበው ተገኝተው በህወሃት ሰዎች ላይ ጫና የሚያሳድር ንግግር ሲያደርጉ ነበር የቆዩት። የኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ተወካዮች በትግራይ እና በአማራ ድርጅቶች መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት ሲያደርጉ ነበር የተስተዋለው። ኦህዴድ በአቶ አለማየሁ አቶምሳ እየተመራ እነ ግርማ ብሩ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና 4 ሌሎችንም ይዞ ሲቀርብ፤ የደቡብ ህዝቦች ደግሞ በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መሪነት እነ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያምና 5 ሌሎችን በስብሰባው ላይ አሳትፏል። እስከ ምሽት ድረስ በዘለቀው በዚህ ስብሰባ ላይ በተለይ በአቶ በረከት ስም ኦን በኩል የሚቀርቡ ሃሳቦች ሆን ተብለው በህወሃት ሰዎች ውድቅ ሲሆኑ ነበር የተስተዋለው። በተለይም የኢህ አዴግን መሪ ወይም ሊቀ መንበር ማስመረጥን አስመልክቶ የተነሳው ሃሳብ በወ/ሮ አዜብ መስፍን እና በሌሎች የህወሃት አባላት የመረረ ተቃውሞ ቀርቦበታል። በተለይም ህወሃት አንድ አባሉ (መለስ ዜናዊ) በመሞቱ ምክንያት የሰው እጥረት እንዳለበት ገልጿል። በዚህም መሰረት ህወሃት በሚቀጥሉት 15 ቀናት የራሱን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መቐለ ላይ እንዲጠራ፤ ከዚያም በመለስ ዜናዊም ሆነ አሁን ብቃት የላቸውም በሚላቸው አመራር አባላት ምትክ ሰው እንዲያሟላ ተብሏል።

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግሽበት አይሎአል ፣ነጋዴው በእለታዊ የምግብ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቶአል።



በከፍተኛ ደረጃ የኑሮ ውድነት እያጠቃው የመጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ከቀድሞው በበለጠ ሁኔታ በዚህ ሁለት ሳምንታት ውስጥ በከፍተኛ የዋጋ መጠን የኑሮ ውድነቱ መጨመሩን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ያደረሰን ሪፖርት አመላክቶአል ። በዛሬው እለት በተለያዩ የንግድ ተቋማት ተንቀሳቅሶ የንግዱን ሁኔታ የተመለከተው ዘጋቢያችን በሽንኩርት እና በቲማቲም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዳለ የገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡ የመኖር አቅሞ እጅጉን እንደከፋበት አስታውቆአል ። ምንም ገቢ የሌላቸው የዜጎች ወደ ጎዳና ከመውጣት በስተቀር ምንም እድል የላቸውም ፣መንግስት የስራ ፈጠራን አድጌአለሁ እድገት ከ11 በመቶ በላይ እያሳየሁ ነው ሲል የውጭ መገናኛ ብዙሃኖች እና አይኤምኤፍ ደግሞ 7ከመቶ የኢትዮጵያ እድገት እንደተመዘገበ ይጠቁማሉ ። ይህም ሆኖ የተቸገረው ህዝብ ብዛት ከ30፣ኢሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ ይህም ማለት የአንድ አፍሪካ ሙሉ የሃገሩን ህዝብ እንደማለት ሲሆን የኢትዮጵያ የሃገሪቱን ከ1/4 በላይ የሚሆነው ህዝብ በረሃብ እንደተጠቃ  የሚያሳይ ነው ሲሉ ተንታኞችም አክለዋል ። በተለይም ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሞት በሁዋላ እየታየ ያለው የሃገሪቱ የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ግሽበት የተከሰተው ከ2 ሳምንታት በላይ ያለምንም ስራ የሃዘን ቀን ተብሎ ህዝቡ ስራ መፍታቱ እና የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን ማቆማቸው እንደሆነ ይናገራሉ በሌላም በኩል አንዳንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የምሽት ክለብ ባለቤቶች እንደሚናገሩት ከሆነ ያሳለፍነው የመከራ ሳምንታት ነበር ከስራችን ተስተጓጉለን ቆይተናል ብዙም ኪሳራ ደርሶብናል ፣አሁንም ምንም ገበያ የለንም ፣ እንደዚያም ሆነን ላልሰራንባቸው ቀናቶችም ገና ታክስ ጭነው ያመጡብናል የቤት ኪራይ እና የኑሮው ውድነት እኛ ከምንጠብቀው በላይ ስለሆነ አንደበታችንን  እንደ ዘጋን በግፍ ዘመን መኖርን መርጠናል ምንም አማራጭ የለንም ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል። በሌላም በኩል አንድ አባ ወራ እንደ ተናገሩት ከሆነ ህይወታችንን ለማሳመር ስንል ያሉንን ሁሉ እያደረግን መኖር ጀምረናል የደርግ ስርአት እራሱ ተመልሶ በጓሮ በር መጣ ሲሉ ለማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ለ ጋዜጠኛ ወንደሰን ሃሳባቸውን ማካፈላቸውን ሪፖርተራችን  በላከልን መልእክት መሰረት  ለመገንዘብ ችለናል ።ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃዘን ምክንያት በከተማይቱ ዝቅ ብሎ የነበረው የሰንደቅ አላማ ከነገው እለት ጀምሮ ከፍ ብሎ እንደሚውለበለብ የተገለጸ ሲሆን ወደ ቀድሞው የኑሮ ይዘት ለመመለስ ግን ከፍተኛ የሆነ የልፋት ቀናቶች ይጠብቁናል ሲል አክሎ ገልጾአል።

በሕግ አምላክ! ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትሪያሪክ አይሾምም



መግቢያ:

አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን ፓትሪያሪክ የሆኑት አባ ጳውሎስ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨገ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ድንገተኛና አነጋጋሪ ሞት ተከትሎ መንበሩ በማን ይተካ? ለሚለው ጥያቄ ባለፈው ሳምንት “ፓትሪያሪክ መርቃሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ!” ስል ለንባብ ማብቃቴ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ስርዓትና ቀኖና በጠበቀ መልኩ በምትካቸው ከነባር ሊቃነ ጳጳሳት መካከል መርጣ መሾምና ሹመቱንም ማጽደቅ አዲስ ነገር አይደለም። ሆነም ግን የቤተ-ክርስቲያኒቱ መሪዎች የውጭ ተጽእኖዎችና እክሎች በሚገባ መቋቋም ተስኖአቸው ከከፈቱት ክፍተት የተነሳ ላለፉት ፪፰ ዓመታት ለሰሚ በሚያሳፍር መልኩ እርስ በርስ ሲተረማመሱና መሪው ወደ ወሰደው የሚሄደው ሕዝብም ሲታመስ እዚህ መድረሳቸው የሚታወስ ሆኖ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የቤተ- ክርስቲያን መሪዎች በሚወስዷቸው እርምጃዎችና በሚያስተላልፍዋቸው ውሳኔዎች ቀደም ሲሉ የተፈጠሩ ችግሮች በመቅረፍ ረገድም ሆነ በአንጻሩ ጉዳዩን በማወሳሰብ ቁልፍ ሚና መጫወታቸው የማይቀር ነው።
ይኸውም: ራሱ የቅዱሳን ማህበር በሚል የቁልምጫ አጠራር የሚጠራ ፊዘኛ ድርጅት ፈለግ በመከተል ፓትሪያሪክ በህይወት ሳለ (ፓትሪያሪክ ሳይሞት) አዲስ ፓትሪያሪክ ለመሾም የደፈሩ: የተቀመጡ ወይንም የመረጡና የሾሙ እንደሆነ ሰላም የሚባለውን ነገር ላለማየት ብቻ ሳይሆን ቋንቋው በራሱ ላለመስማት ከመቁረጣቸው በላይ ያለ ኃጢአታቸው ሲወቀሱ: ስማቸው ሲነሳና ሲረገሙ የኖሩትን አባ ጳውሎስ ከዚህ ሁሉ ተጠያቂነትም ሆነ ሃላፊነትም ከመውሰድ ነጻ መሆናቸው ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ያለፈውን ስህተት ላለመድገም ስርዓተ ቤተ- ክርስቲያን ከማፋለስ አንጸር ድርጊቱ ሕገ ወጥ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ አዲስ/ሌላ ፓትሪያሪክ መሾም በራሱ ሊያስከትለው የሚችለውን ጠንቆችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተጀመረውን እርቀ ሰላም እንዲቀጥል በማድረግ የቀድሞ ፓትሪያሪክ ወደ መንበራቸው የሚመለሱበት መንገድ የፈጠረ እንደሆነ ለዓመታት የዘለቀውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስቲያን ችግር መፈታቱ ነው።

Tuesday, 4 September 2012

ይድረስ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ስድብ አምራቾች!


ይቺ ጨዋታ ባለፈው ጥር ወር በዌብ ሳይቶች እና በፍትህ ጋዜጣ ላይ ወጥታ ነበር። ዝም ብዬ ሳስበው ዛሬ ደግመን ብንጫወታት ወቅታዊ ትመስለኛለች… ጎሽ እስቲ እናውጋ…!
በመጀመሪያም 1
ይህ ፅሁፍ ባለፈው ሳምንት ለምናፍቃት ፍትህ ጋዜጣ ልኬው የነበረ ነው። ታድያ እንደምናውቀው ለፍትህ ሲፃፍ ራስን ሳንሱር ማድረግ ግድ ይላል። እናም በተቻለኝ አቅም ቆጠብ ሰደር ብዬ ነው የፃፍኩት። እየተሳቀቅሁ። ምክንያቱ ደግሞ ለራሴ በመስጋት አይደለም።
እኔማ አንድ ጊዜ “የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” አንዲሉ ከውዲቱ ሀገሬ ከተሰደድኩ እንደዋዛ ሶስት ወራት አለፉ። እስከምመለስ ድረስ ስንት ወራት እንደሚያልፉ እንጃ! ነግቶ በመሸ ቁጥር ሁሌም ፒያሳ በአይኔ ላይ ትሄዳለች። አራት ኪሎ መቀጣጠር ያምረኛል። ሽሮሜዳ ደረስ ብሎ መመለስ ይናፍቀኛል። የአዲሳባ ስታድየም ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ለመታደም እጓጓለሁ። በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ መገኘት ያሰኘኛል። እንኳን ሌላው ቀርቶ ካገር እንድሰደድ ምክንያት የሆነኝ ኢህአዴግ፤ የሚጠራቸው ባለ አበል ሰልፎች ላይ ራሱ አባልም ባልሆን አበልም ባይሰጠኝ ለመታደም የማደርገው ጥረት ራሱ ዛሬም ይናፍቀኛል።
ትዝታ
“የባንዲራ ቀን” ክበረ በዓል በአመቱ መጀመሪያ መከበር ከጀመረ አራት አመት አልፎታል። በርግጥ ባንዲራ ከተፈጠረ የትየለሌ ዘመናትን አስቆጥሯል። ነገር ግን ኢህአዴግ በባንዲራ ጉዳይ ላይ ልብ ከገዛ አራት አመት ሞልቶታል። እንዲሁ በሰባዊ መብት ጉዳይ ላይ፣ በተንሸዋረረ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ፣ በሴራ አስተዳደር ጉዳይ ላይ፣ በሙስና ጉዳይ ላይ፣ በስንፍና ጉዳይ ላይ፣ በወዘተ ጉዳይ ላይ ልብ ይገዛል ብለን ብንጠብቀው፤ ብንጠብቀው ልብ ተወደደበት መሰለኝ ይህው ሃያ አመት ሙሉ ልብ አልገዛም። የሆነ ሆኖ በዚሁ አመት መጀመሪያ ላይ የባንዲራ ቀንን “ላከብር” አዲሳባ ስታድየም ዙሪያ ታድሜ ነበረ።

Monday, 3 September 2012

የሕዝባዊ ከያኒ ያለህ



ወልደ ገብራኤል – ስዊትዘርላንድ
የዛሬው ‘ የጽናት’ ሬድዮ ጋዜጠኛ የቀድሞው አቀንቃኝ ሰለሞን ተካልኝ ‘ቅንድባሙ መሪ’ የሚለውን ዘፈኑን ወደ ሸገር ዘልቆ ካስባረካና ከስርዐቱም ጋር እርቅ ካደረገ በሁዋላ የመጀመሪያ ልምጩን ያሳረፈው የሙያ ወዳጁ አቀንቃኝ ነዋይ ደበበ ላይ ነበር። ( አቀንቃኝ ሲያረጅ ኮሚቴ ይሆናል መሰል ነዋይ ደበበ የልቅሶ ኮሜቴ አመራር ውስጥ ይህን ጽሁፍ ሳዘጋጅ ሰማሁ ሹመት ያዳብር ብለናል ነዋይ ) የሰለሞንን እርቅና እርሱን ተከትሎ አውራ ወያኔ ለመሆን መሻቱን ካልወደዱለት መሃል ነዋይ አንዱ ሳይሆን አልቀረምና ሰለሞን እንዲህ ሲል የወረፈው ዛሬ ድረስ ፈገግ ያሰኘኛል፡
ፍየል ቅጠል እንጂ አትበላም እንጉዳይ
በጥርሷ ሰላሳ በአይኗ መቶ ገዳይ
የሚለውን የነዋይ ዘፈን አዜሞ ሲያበቃ ከመቼ ወዲህ ነው ፍየል በጥርሷ መቶ ስትገድል ነዋይ ያየው ሲል አድማጮቹን በተሳልቆ ድምጸት ጠየቀ። ሰለሞን በዚህም አላበቃም ነዋይ በሶስተኛ ወገኖች በኩል ወደ ሀገሩ ለመግባት ‘ድርድር’ ላይ እንደሆነ እንደሚያውቅ ሁሉ ለሬዲዮ አድማጮቹ ጠቅሶ አላርፍ ካልክ ‘ ብዙ እናውቃለን’ ሊለው ቃጥቶት ነበር። (ምናልባትም ሁለቱንም ልማታዊ አቀንቃኝ ይሆኑ ዘንድ ከስርዓቱ ጋር የሚያደራድሯዋቸው ሰዎች መረጃ እየሸላለሙ ያቃርኑዋቸውም ይሆናል) ዛሬ ነዋይ ደበበም ሰለሞንም የስርዓቱ ልማታዊ አቀንቃኞች ናቸው። ምን አልባትም ቀድሞ ለሰለሞን ያልታየው የፍየሊቱ አይነ ገዳይነት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጸበል ሲጠመቅ ይገባው ይሆናል። አልያም ነዋይ ሂስ ውጦ የፍየሊቱ ጉዳይ ትምክህተኛ አመለካከት እንደሆነ ያምንም ይሆናል ። ከዚህ ባለፈ ግን የእነርሱ እንካ ሰላንታ ፤ የእነርሱ ትላንት ሰበታ ነገ ወላይታ መገኘት እኪነት አካባቢ ምን እየሆነ ነው ወደሚለው ጨዋታ ይወስደናል። የአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት ተከትሎ የታዘብነው ደግሞ ምነው በዚህ ዕድሜ ፤ ምነው ምነው ፕርፌሰር እገሌ ፤ ምነው አትሌት እገሌ ፤ ምነው ዶፍተር እንቶኔ ደግሞ ደጋግሞ አሰኝቶናል። ምንም እንኳን ያለፉት ጥቂት ቀናት የአርቲስቶቻችንን ብዛት ከሺዎች ከፍ አድርጎት ፌዲራል ፓሊሱም፤ አትሌቱም፤ ዶክተሩም፤ ካድሬውም ፤ የዪኒቨርሲቲ መምህራን ሳይቀሩ ተሰጥዖዋቸውን ካሜራ ፊት ያሳዩበት ቢሆንም ማህበረሰባችን አልቦ የኪነት ሰው መሆኑን ያሳየበት ሁነት ይበልጥ ገኖ ተስተውሏል።

የወያኔው መሪ በኢትዮጵያ በሚቀበርበት ሰዓት በኖርዌ ኦስሎ ታላቅ ሰላማዊ ሰለፍ ተደረገ።



ቀኑ እሁድ  ነሀሴ 27_ 2004  ሲሆን ሰአቱ በግምት ከቀኑ 8 ፣30  ይሆናል ።  በእለቱ በኖርዌ የምንገኝ  የኢህአፓ እና  የ ዲሞክራቲሲ ለውጥ በኢትዮጵያ፡ አባላት እና  ደጋፊዎች  በጋራ   ታላቅ ሰላማዊ  አደረግን።  የሰላማዊው ሰልፍ ዋናው አላማ  የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር የሆነው ምላስ ዜናዊ በመሞቱ  ምክንያት ሲሆን፧ ለ21 ዓመታት ሲያለቅስ፦ሲያዝን፦ሲራብ፦ ሲጠማ ፦ሲሰደድ ፦ሲታሰር  ፦ሲገረፍና፡ሲገደል የነበረው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  እንኳን ደስ አለህ በማለት ደስታውን ለመግለጽ  ነው።   በፎቶው እንደሚታየው በዛ ያለ  ኢትዮጵያዊ በዝግጅቱ ላይ ተገኝቷል። በዕለቱ የተገኙት                                              ከሁለቱ  የፖለቲካ  ፓርቲ እና    ድር ጅት አባላት          
ውጭ  ደጋፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች   በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል። በመጀመሪያ  የዲሞክራሲ ለውጥ  በኢትዮጵያ ሰበሳቢ የሆኑት አቶ ዳዊት  ዕንኳን ደስ አላችሁ በማለት የመክፈቻ ነግግር ሲያደርጉ  በመቀጠለል የኢህአፓ ተወካይ የሆኑ አቶ ሞላ ንግግር አድርገዋል  ። ፕሮግራሙን በመምራት  ከኢህአፓ  አቶ አርጋው  ከዲሞክራሲ ለውጥ አቶ ማተቤ ሲሳተፉ ተስተውሏለል።በኖርዌ ከምንገኝ ኢትዮጵያውያን መካከል  በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ተሳተፎዋቸው ጎልትው ከሚታዩት  ውስጥ  ዶክተር ሙሉ አለም፧ አቶ አምሳል ካሴ፧ አቶ ግደይ፧ ሁሉም በቅደም ተከተል ንግግር  አድርገዋል።                                                                                                                                                     አቶ እንግዳሽት  መች ደረስኩባችሁ የሚለል ግጥም  ሲያቀርቡ፤ኧቶ ቴዎድሮስ ታደሰ  ደግሞ  ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዛብሄር ተዘረጋለች የሚል  ግጥም  አቀረቡ፤እንዴሁም አቶ ልዑል  በ እንግሊዘኛ  ግጥም አቅርበዋል ።  ወይዘሪት ሜርሲ ቀስቃሽ የሆነውን ኢትዮጵያ  አገራችን የሚለውን  ዜማ አዜመዋለል                                                                                                                                                          
 በዚ መሃል ጥቁር በጥቁር የለበሰ ማለትም መሪያቸው በመሞቱ በሃዘን ላይ የሚገኝ  የወያኔ ደጋፊ  የእለቱን ደስታችንን      ለማበላሽት ፕሮገራሙን ለማቋረጥ  ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።ችግር ለመፍጠር ሞክሮ  የነበረው የወያኔ  ቀንደኛ ደጋፊ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኘውን ኢትዮጵያዊ  ቪዲዎ በመቅረጽ ላይ እያለ  ነው እጅ ከፍንጅ የተገኘው። ለምን ትቀርጸለህ ተበሎ ሰለተጠየቀ   ነው  ገርግር ፈጥሮ  ተመታሁኝ በማለት ፖሊስ በማምጣት ችግር ለመፍጠር ሞከሮ የነበረው ግን ሳይሳካለት ቀርቷለ ። የእለቱ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቋል።በእውነቱ እኛ አንድ ስንሆን ህብረታችን በጠነከረ ቁጥር ጠላቶቻችንን ለማሸነፍና  ለማጥፋት በዙ ጊዜ አይወስድብንም እንበርታ  እንጠንክር።                                                                               ዜናው የራሴ  እይታ ነው ከ እንዳለ  ጌታነህ