"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 6 August 2013

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ[ ስሙ ለጊዜው ካልታወቀ ገጣሚ)

ማታ ልተኛ ስል አንድ ጓደኛየ ይሄን ግጥም ላከልኝ ባጭሩ መተኛቴን ተውኩት!!!! ከፍ ካለ ይቅርታ ጋር የገጣሚውን ስም ማግኘት አልቻልኩም (የምታውቁት ካላችሁ እባካችሁ ስሙን አካፍሉን ....... እንደተላከችልኝ ይሄው .....ገጣሚውን እጁ ይባረክ እያልኩ ....ኡፉፉፉፉ እንዴት ደስ ይላል!!

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
(ስሙ ለጊዜው ካልታወቀ ገጣሚ)

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው ........?

... እኛማ.....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ ...........

አይንህን ካየነው
ሁለት ሽ ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ....

እንደውም እንደውም.....
‹‹በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሽ ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው ›› እያሉ ያሙሃል

እኔ ምን አውቃለሁ ....
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ .....ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚ...ኦ በሉ ሲባል ....እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ .....በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ......