"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday, 28 February 2013





ትናንት እና ዛሬ




ወጨጫ ማርያም ሲነግስ በየዓመቱ ከጎረቤቶቼ ጋር እንሄዳለን፡፡ ቤተሰቦቼም የሚኖሩት እዚያው አካባቢ ስለሆነ ወጨጫ ማርያምን ካነገስን በኋላ እነሱ ዘንድ እንገባና በሚገባ ተጋብዘን እንወጣለን፡፡በየዓመቱ ስለማንቀር በደንብ ተዘጋጅተው ይጠብቁናል፡፡
ምንሄደው አምስት ሆነን ነው፡፡ የዚያ ዕለት ታዲያ ባሎቻችንን በጠዋት ወደየሥራቸው ሸኝተን መንገዱን በእግራችን እንያያዘዋለን፡፡ በጉዟችን ላይ ስለኑሯችን፣ ስለገጠመኞቻችን፣ መንገድ ላይ ስለምናየው ነገር ሁሉ እናወራለን፡፡ከንግስ መልስ ቤተሰቦቼ ቤት ስንደርስ የሚያደርጉልን አቀባበል መቼም ልዩ ነው፡፡ ሁላችንንም አገላብጠው ስመውን ሲያበቁ እንጀራው፣ ዳቦው፣ ቆሎው፣ እርጎው፣ጠላው፣ አረቄው ቀርቦ ስንበላና ስንጠጣ ውለን አመሻሽ ላይ ከዳቦውና ከቆሎው ትንሽ ትንሽ ቋጥረን መንገዱን እንያያዘዋለን፡፡ ከሞቅታው ጋር ጨዋታውን በሳቅ እያጀብን ድንግዝግዝ ሲል ወደ ቤት እንገባለን፡፡
    የአንዷ ጎረቤቴ ቤተሰቦች የሚኖሩት መናገሻ ነው፡፡ እዚያም በየዓመቱ የንግስ በዓል ሲኖር አምስታችንም ጎረቤታሞች ተያይዘን እንሄዳለን፡፡ በእኔ ቤተሰቦች ከተስተናገድነው ባላነሰ ተስተናግደን እንመለሳለን፡፡ ይሄ በየዓመቱ የሚፈፀም ክስተት ነው፡፡ከዚህ በተረፈ በየቀኑ አንዷ ጎረቤት አንዷን ሳታይ ውላ አታድርም፡፡ አንድ ቀን ካልተያየን ምን ነክቶሽ ነው ብለን እንጠያየቃለን፡፡      የታመመችም እንደሆነ ጥፍጥ ተደርጋ የተሰራች ምግብ ነገር ከቤታችን ይዘን በመሄድ፣ “እግዚሃርይማርሽ ቀላሉንያድርግልሽ” ብለን አጫውተናት ወደጎጇችን እንመለሳለን፡፡በርበሬ ወይሽሮ ያስፈጨን እንደሆነ፣“ቅመሺ ቅመሱ” ብለን ሰፍረን እንልካለን፡፡አንዷ፡ገበያ ደርሳ ስትመለ ስረከስ ያለነገር ካገኘች በርከት አድርጋ ገዝታ ትመጣና፣“ይህን ነገር ገዝቼልሻለሁ፤ ስሙኒ ወይም ሃምሣ ሣንቲም ላኪ!” ተብሎ ይላክባታል፡፡የቸገረ ዕለት፣ከመሶቡ ቁራሽ እህል የጠፋ ጊዜ፣“አንድ እንጀራ ላኪልኝ” መባባል የተለመደነው፡፡አንዷ ቤት እንግዳ የመጣም እንደሆነ፣“ከጋገርሽው ትኩስ እንጀራ ቶሎ ስደጂልኝ” እየተባባልን መረዳዳት ይዘነው የቆየነው ባህል ነው፡፡ዓመት በዓል እንዳለፈም፣“ነይ ቅራሪ  ጠጪ የሚል መልዕክት  እርስበርሳችን መቀባበል ወይም ልጅን አንድ ጠርሙስ ቅራሪ አስይዞ መላክምእንዲሁ፡፡በባሎቻችን ዘንድ የነበረው ግንኙነትም የሚያስቀና ነበር ከሥራ መልስ፣“ተማሪ ቤት እንሂድ”እየተባባሉ እየተቀላለዱ ተያይዘው ጠጅ ቤት ይሄዳሉ፡፡የአንዳችን አጥር ሲፈርስ በጋራ ሆነው ያጥራሉ፡፡ለለቅሶ ወደ ገጠር የሚሄድ ካለ ብቻውን እንዴት ተደርጎ ይባልና የአንዷ ባል አብሮት ይሄዳል፡፡ለበዓል በሬ አርደው ሲቃረጡ፣የተወሰኑት ገንዘ ብሰብሳቢ፣ግማሾቹ ገዢ፣ሌሎቹ አራጆች ሆነው ይሠራሉ፡፡ተከፋፍለው ሲለያዩ፣ ለቀጣዩ ዓመት በሰላም እንዲያደርሳቸው ተመራርቀው ይሰነባበታሉ፡፡
ዛሬ ያንን  ጊዜ አጥብቄ እንዳስታውሰው ያደረገኝ አንድ ነገር ተፈጥሯል።

፡፡ያለሁት አራስ የሆነችው ልጄ ዘንድ ነው፡፡እዚህ የመገኘቴም ሚስጥር ላርሳት ነው፡፡    ድሮ እኛን የሚያርሰን እናት ወይም እህት ሳይሆን ጎረቤት እንደ ነበር ለልጄ አወራኋት፡፡እሷን ስወልድ ያረሱኝ ሃዳስና ሙሽሪት እንደነበሩ ገለፅኩላት፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ቡላ የሚሉትን የጉራጌ ባህላዊ ምግብ የቀመስኩት ያን ጊዜ
እንደሆነና  እንዴት  እንደሚጣፍጥ  ብቻ ሳይሆን ለሰውነት ያለውን ጠቀሜታ ጭምር ተረኩላት፡፡
ሳይቸግረኝም  ስለጎረቤቶቿ  አነሳሁባት፡፡
“አይብዙምአንግባባም እሷየዚህብሄረሰብተወላጅናት፡፡” አለችኝ፡፡“ታዲያ ትሁና ምን አለበት”
“አይ አመለካከቷ ጥሩ አይደለም

እሺ ከበታችሽ ያለችውስ”
“እሷደግሞየዚያኛውብሄርተወላጅናት፡፡”
“ታዲያ ምን  ያገናኛዋል ኢትዮጵያዊ አ;ይደለች

!?”ንዴት ጉሮሮዬን እያነቀኝ ጠየኳት፡፡አይ እማዬ በአሁኑ ጊዜ አንቺ እንደምታስቢው አይደለም፡፡ሁሉም በየብሄሩ ተከፋፍሏል፡፡መታወቂያችንን እንኳን አታይም?” አለችኝ፡፡ከልቤ አዘንኩ፡፡ልጆቼ ምን ዓይነት ጊዜ ላይ እንዳሉ እያሰብኩ ክፉኛአዘንኩኝ፡፡መቼም ልጆቼን በዚህ መልኩ በፍፁም እንዳላሳደኳቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ከጓደኞቼ መካከል ጥቂቶቹ በህይወት የሉም፡፡ቢኖሩና ይሀንን ጉድ ሲሰሙ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ማወቅ ይከብደኛል፡፡ በእኛ ጊዜ በሃዘኑም በደስታውም  አንድ ላይ ነበርን፡፡“በእኛ በትግሬዎቹ አገር እንዲህ ነው የምናደርገው፤በጉራጌ ግን እንዲህ ነው፡፡በኦሮሞ እንደዚያ ፡፡በ… እያልን እናወራለን፡፡እዚህ ላይ የእናንተ ባህል ጥሩ ነው፤እዚህ ላይ ጎጂ ነው”እየተባባልንእንነቅሳለን፡፡እንማማራለን፡፡እግዚኦ! ያዘመን ምንኛ የሚያሳሳ ዘመን ኖሯል?የሙሽሪት ክትፎ እጄን ያስቆረጥመኛል፡፡የበቀለችን ጨጨብሳ ሁሌም እናፍቀዋለሁ፡፡የሃዳስ አምባሻ፣የስፍራሽ ዶሮ ተበልተው አይጠገቡም፡፡አንዱ ካንዱ የሚማረው ሙያም ለጉድ ነበር፡፡አሁን እኔ ሁሉንም ዓይነት ምግብ ልክ እንደነሱ ልቅም አድርጌ ማዘጋጀት እችልበታለሁ፡፡ባህላቸውን ያስተማሩኝ እነሱው ናቸዋ ;በሠርግ ከጓደኞቼ ጋር እኩል ጨፍሬ፣በሃዘኑ አብሬ ተኮማትሬ ነው የኖርኩት፡፡አልቅሽ አልቅሽ አለኝ፡፡በእርግጥ ከጎረቤቶቻችን መካከል የማንግባባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ግን በዘራቸው ሳይሆን በስነምግባራቸው አሊያም በፀባያቸው ምክንያት ነው፡፡መፈቃቀር ተፈቃቀሩ ስለተባለ አይመጣም፡፡መለያየትም እንዲሁ፡፡ሰው በሚኖርበት አካባቢ እንደ አግባቡ በሰላም በፍቅር ተዋዶይ ኖራል፡፡እውነቴን ነው የምለው እስከ ዛሬ ድረስየ ሃዳስ ትግሬነት፣የስፍራሽ አማራነት፣የበቀለች ኦሮሞ መሆን፣የሙሽሪት ጉራጌነት ታውሶኝ አያውቅም፡፡ማንም እከሌ እንዲህ ነው ሳይለ ንከዘራችን በፊት ሰው መሆናችን፣ብሎም ኢትዮጵያዊነታችን አስተሳስሮን ተዋደን፣ተፋቅረን ነው ያሳለፍነው፡፡ይህንን የዛሬውን ጉድ ሳያዩ ባለፉት ጓደኞቼ ቀናሁ፡፡ብቸኝነት ተሰማኝ፡፡ልጄ በሰዎች ተከባ ባይተዋር ሆና እየኖረች ነው፡፡የህፃኑ እጣስ ምን ሊሆን ነው ሰጋሁ፡፡አባቱ ዘሩ ምን እንደሆነ ጠይቄ አላውቅም፡፡ልጄን ልጠይቃት አፌላይ አደረስኩትና፣“መልካም ሰው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ያ ከሁሉም በላይ ነው፡፡ሌላው ትርፍ ነገር ነው፡፡” ስል አስቤ ተውኩት፡፡ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ፡፡የበቀለችን ፈገግታ፣የሃዳስን ሹሩባ፣የሥፍራሽን ንቅሳት፣የሙሽሪትን ሻሽ አስተሳሰር እንባ በጋረደው ዐይኔ ተመለከትኩ፡፡* *
ከቅዱስ መጽሐፉ ውስጥ የወጣውና በሚያምር የእጅ ጽሑፍ የተጻፈው ጥቅስ የሰዎች ዐይን

በቀላሉ የሚያርፍበት ቦታ ተሰቅሏል፡፡ “እንደ እግዚያብሔር ያለ ማንም የለም” ይላል፡፡አንድ ጎልማሳ መሳይ መጣ፡፡ወደ ጥቅሱም ሄደ፡፡ከደረት ኪሱ ቀይ ብዕር አወጣና ከጥቅሱ መሃል“ግ” የተሰኘችውን ሆሄ በቀይ አቀለማት፡፡እንዲህም ሆነ፤“እንደ እግዚያብሔር ያለ ማንም የለም” “እንደ እዚ ያብሔር  ያለ ማንም የለም” አይተንኮል  አይክፋት


 *








Wednesday, 27 February 2013

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ለምን  100 ጊዜ  አተከፋፈሉም ተዉኝ ሞቴን ልሙትበት



ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።