ሰለሞን ታረቀኝ
ድሮ ነው አሉ፤ አንዲት በናዝሬት ትምህርት ቤት ትማር የነበረች ተማሪ ጥርሷን ጣፋጭ ጨርሶት ነበርና ወላጆቿ በፍጹም ቼኮላት እንዳትበላ ያስጠነቅቋታል፤ ከዚያም አንድ ቀን አንዲት ጓደኛዋ ቼኮሌት አምጥታ ኖሮ በእረፍት ሰዓታቸው ጓደኛዋ የሰጠቻትን ጥቂት ቼኮሌት ታናሽ ወንድሟ እንዳያሳብቅባት ተደብቃ ስትበላ ያ ከውካዋ ወንድሟ ድንገት ቢደርስባት እጅዋ ላይ የቀረውን በድንጋጤ ወደ አፍዋ አስግብታ ቁልቁል መስደድ፤ ወንድምየውም ቼኮሌት እንድትሰጠው ቢጠይቃት እንዳለቀባት ትነግረዋለች። እሱም ይናደድና አሳብቃለሁ ብሎ ያስፈራራታል። ከዚያም ከትምህርት ቤት ወጥተው ቤታቸው እንደደርሱ ወንድሟን ለመቅደም ብላ ማንም ሳይጠይቃት፥ እማዬ፥ እማዬ እኔ እኮ ዛሬ ቼኮሌት አልበላሁም አለች ይባላል።
የቀድሞዋ ቀዳማዊትም እንዲሁ ቀደም ቀደም ብላ ሳትጠየቅ ተክለፍልፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባሌ የ፮ ሺህ ብር የወር ደመወዝተኛ፥ ከዚህም ተቆራርጦ ፬ ሺህ ብር ያገኝ ነበር ስትል አበሰረችን። የቼኮሌቱ አይነት መሆኑ ነው።
ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ ነበር። በትክክል ካስታውስኩ አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር። ይህንን ተከትሎ የመለስ ዜናዊ መንግስት የትንሳኤ ሬድዮን አሜሪካን አገር በቨርጂኒያ ስቴት በሚገኝ ፍርድ ቤት በስም ማጥፋት ወንጀል በሚል የክስ ፋይል መስርቶ እንደነበርና በሁዋላ ግን የሚያስከትለውን መዘዝ በመፍራት ይመስላል ክሱን መሳቡ (ዊዝድሮው ማድረጉ) ተነግሮ እንደነበር ይታወሳል።
ይህ ሲገርመን ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በኢሳት ሬድዮ ቀርቦ የነበረ ጋዜጠኛ እንዳመለከተው ሴሌብርቲ ኔትወርዝ የተባለ ድረ ገጽ አቶ መለስ ዜናዊ ያላቸው ሀብት ፫ (ሶስት) ቢሊየን ዶላር እንደሆነ ያሳያል። ይህንን በርግጥም ማንም በተባለው ድረ ገጽ አድራሻ በ http://www.celebritynetworth.com/ ሊመለከተው የሚችል ዘገባ ነው። ድረ ገጹ በዓለም ላይ ያሉ ታዋቂ ሰዎችንና እንደ እነ አቶ መለስ ዜናዊ ያሉ አምባ ገነን መሪዎች ያላቸውን ሀብት የሚዘግብ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላቸው ተብሎ የተዘገበው ከፍተኛ ሀብት ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠውና ሊመረመር የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል።
እዚህ ላይ በተለይም ኢትዬጵያውያን ጋዜጠኞች፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ይህን ጉዳይ ለማጣራት አቅምና ችሎታ ያላቸው ግለሰቦች በትንሳኤ ሬድዮም ሆነ በሴሌብሪቲ ኔትወርክ የተመለከቱትን የወያኔ ባለስልጣኖች የተካባተ ሀብት መጠንና የሚገኝበትን ስፍራ መርምረውና አጣርተው ለሕዝብ ማጋለጥ ያለባቸው ይመስለኛል።
እንደሚታወቀው ባገራችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱና ያገራችን ሀብት በከፍተኛ ደረጃ በመዘረፍ ላይ እንደሚገኝ የአደባባይ ምስጢር ነው። ትናንት ምንም ያልነበራቸው የዛሬዎቹ ባለጊዜ የወያኔ ባለስልጣኖች ባገር ውስጥ የባለ ብዙ ሕንጻዎችና ሌሎችም ንብረቶች ባለሀብቶች መሆናቸው በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች መገለጹ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለያየ ጊዜ እንደዘገቡት ካገራችን ብዙ ቢሊዮን ዶላር እንዲሸሽ መደረጉን መግለጻቸው ያገር ሀብት ዘረፋው በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን በግልጽ የሚያመለክት ነው።
የቀድሞዎቹ አምባገነኖች የግብጹ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክና የሊቢያው ኮሎኔል ሙዓመር ጋዳፊ በውጭ አገሮች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት አካብተው እንደነበርና፤ የስርዓታቸውን መገርሰስ ተከትሎ የያገራቸው ሕዝቦች ይህን የተዘረፈ ሀብት ለማስመለስ እንደሚንቀሳቀሱ መገለጹ ይታወሳል።
በተመሳሳይ ሁኔታ እኛም ኢትዮጵያውያኖች እነዚህን ለ፪፩ ዓመታት እንደመዥገር ከሕዝባችን ተጣብቀው የዘረፉትን ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ሀብት በሚቻለው አቅም ተከታትለን ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ማጋለጥ እንዳለብን ይሰማኛል። ይህም ወደፊት ከአይቀሬው የስርዓቱ መገርሰስ በሁዋላ ሀብታችንን ለማስመለስ ለምናደርገው ጥረት እንደ ቅድመ ዝግጅት ሊያገለግል እንደሚችል አምናለሁ።
ኢትዮጵያ አገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር።