"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Saturday, 12 January 2013
Friday, 11 January 2013
“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ መንግሥት ተመቻችታ አልቆመችም። የፋይናንስ ስርዓቱም የተረጋጋ አይደለም። የገቢና ወጪ ቁጥጥሩ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ለሙስና የተጋለጠ ነው። የጁባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የአገሪቱ ሃብት በግለሰቦች እጅ ነው። በተለያዩ መስኮችም የባለሙያና የአቅም ችግር አገሪቱ ምስጢርና የኔ የምትለው አስተዳደር እንዳይኖራት አድርጓታል የሚሉ በርከቶች ናቸው።
ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በሚል ኢህአዴግ ደቡብ ሱዳንን ከተወዳጀ ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የመከላከያ መኮንኖችን አሰልጥኗል፤ የፖሊስ ኃይሉን አደራጅቷል። በአማካሪነት በተለያዩ ዘርፎች የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆ አሁንም ይህንኑ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል። የተመሰረተው ግንኙነት ወደፊትም እንዲሁ በቀላሉ ንፋስ የሚገባው አይመስልም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ በህወሃት አማካይነት ደቡብ ሱዳንን ጠፍንጎ የያዘበት ሰንሰለት በቀላሉ ሊበጠስና ሊሸረሸር የሚችል እንዳልሆነ ይናገራሉ።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እነዚሁ በጁባ የሚኖሩ ክፍሎች በፋይናንስ፣ በፖሊስ፣ በመከላከያ፣ በደህንነት፣ በተለያዩ ከፍተኛ ግዢዎችና በገንዘብ ዝውውር በኩል የደቡብ ሱዳን ማናቸውም እንቅስቃሴ ከኢህአዴግ እይታና ክትትል ውጪ አይደለም። እንደ አገር ኢትዮጵያ በቀጠናው ኃያል መሆኗ ቢያስደስትም አሰራሩ “ህወሃት በኢትዮጵያ ስም፣ የህወሃት ልጆች በኢህአዴግ ስም” መከናወኑ ቅሬታ ፈጥሯል።
“ብሔራዊ ጥቅምን በብሔራዊ አጀንዳ ማስጠበቅና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማስኬድ ኩራቱ የሁሉም ዜጎች እንዲሆን ያደርገዋል” የሚሉት ክፍሎች በተግባር የሚታየውና በብሔራዊ ስም የሚከናወነው ስራ “ህወሃትና የህወሃት ሰዎች በብቸኛነት እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ነው፤ ሕዝብ የወከለውና የራሱን አገር ጥቅም የሚያስከብር አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ እስከለሌለ ድረስ አካሄዱን ብሔራዊ ወይም የአገር ኩራት ለማለት አይቻልም” ብለዋል። አያይዘውም ኃያልነታችን በብሔራዊ ደረጃ እንጂ በድርጅትና በጎሣ ደረጃ መሆን የለበትም በማለት ይከራከራሉ፡፡ ሲያስረዱም በብሔራዊ ሽፋን ለመበልጸግ የሚደረግ ሩጫ ዓቅምን ካላገናዘበው የኤርትራ ፍላጎትና በውጤቱም ከጎረቤት ሁሉ ጋር ከጠብ እስከ ዓይነቁራኛ መተያየት ከመድረስ ጋር ልዩነት አይኖረውም ይላሉ፡፡
በአቅም ማጎልበት፣ በማማከርና በባለሙያ ድጋፍ ስም የሚካሄደው ምልመላና ምደባ በቀጥታ ተቀማጭነቱ ጁባ ከሆነው የመረጃና የደህንነት ቡድን ጋር የሚቆራኝ ነው። በምልመላው የሚካተቱት አብዛኞቹም ከህወሃት የሚወከሉ ናቸው። ከዚሁ የመረጃ ቡድን ጋር በመተሳሰር የሚሰሩ ነጋዴዎችና በግል ስራ የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ተወላጆችም አሉበት።
በብሄራዊ ደረጃ በጥንቃቄ መያዝ ያለበት የጥቅም፣ የኢኮኖሚ ስትራቴጂና የደህንነት ጉዳይ በፓርላማውም ሆነ በአባል የኢህአዴግ ድርጅቶች በወጉ የማይታወቅ፣ በዚሁ ሰንሰለት ስር የሚገኘው ያገሪቱ ገቢ ቁጥጥር የማይደረግበት እንደሆነ የመረጃው ምንጮች ይናገራሉ። አያይዘውም ይህንኑ ብሔራዊ ሽፋን ያለውን ግንኙነት በመንተራስ የህወሃት ሰዎች አለአግባብ እየበለጸጉበት መሆኑን አመልክተዋል።
የሚሰሩበትን አገርና ስማቸውን እንዳይገለጽ የጠየቁ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የተማሩ የደቡብ ሱዳን መንግስት የመዋቅር ሰው “ህወሃት ወርሮናል” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፤ “ከተራ የችርቻሮ ንግድ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የወጪና የገቢ ንግድ የህወሃት ሰዎች እየተቀራመቱን ነው” የሚሉት እኚሁ ሰው በከፍተኛ ደረጃ ባሉ አመራሮች ዘንድ የሚሰማው ቅሬታ እየጨመረ መሆኑንን ያስረዳሉ።
“አገራችን” አሉ “አገራችን ካንዱ ነጻ ከወጣች በኋላ ሌላ እጅ ላይ የወደቀች ያህል የሚሰማን ብዙዎች ነን” በማለት ቅሬታቸው የጨመረ ክፍሎች መበራከታቸውን የሚናገሩት የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ሰው፣ በትግሉ ዘመን ኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ የሚረሳ ባይሆንም አሁን እየተደረገ ያለው ድርጊት ከብሔራዊ ደረጃ የወረደ ስግብግብነት፣ ለመዝረፍ የመራወጥ፣ በከፍተኛ ደረጃ ደግሞ ሙሉ የአገሪቱን ንግድ እንቅስቃሴ የመቆጣጠር እንደሚመስላቸው አመልክተዋል።
“በበርካታ ባልደረቦቼ ዘንድ ያለው እምነት እንደገና የመወረር ዓይነት ነው” በማለት አስተያየታቸውን የሚያጠናክሩት ባለስልጣን፣ ውስጥ ውስጡን ያለው ቅሬታ ሳይባባስ ኢህአዴግ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት “ክብር የተላበሰ፣ በአገርና በመሪዎች ደረጃ ስትራቴጂና የጋራ ጥቅም ላይ ብቻ ባተኮረ መንገድ ለማድረግ አካሄዱን መመርመር አለበት” ባይ ናቸው።
“ካለብን ተጽዕኖ የተነሳ ለባለውለታችን ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም ያሰራነውን ቪላ ለመሸለም እንኳን አልቻልንም” ሲሉ የተጠፈሩበትን የቁጥጥር ገመድ ጥብቅነት ባለስልጣኑ አመልክተዋል። አያይዘውም ይህ ስሜት እያደገ ሲመጣ ህወሓት አገር ውስጥ ከሚታማበት የንግድ የበላይነት ጋር ተዳምሮ አላስፈላጊ መተራመስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል። ደቡብ ሱዳን ነጻ አገር መሆኗን ስታውጅ ባለስልጣናቱ በዕለቱ ለኮሎኔል መንግስቱ ቪላ ቤት ለመሸለም እቅድ መያዛቸውን ይፋ ማድረጋቸው፣ እቅዱ በተለያዩ ሚዲያዎች ይፋ እንደሆነ የኢህአዴግ የስለላ ሰዎች ባደረጉት ተጽዕኖ እቅዱ መሰረዙንና ቀደም ሲልም የተነገረው ስህተት መሆኑ ተጠቅሶ ማስተባቢያ መበተኑ የሚታወስ ነው።
ጄኔራል ጻድቃን በበላይነት የደቡብ ሱዳን የመከላከያና የደኅንነት አማካሪ እንደሆኑ በማስታወስ አስተያየት የሚሰጡት ክፍሎች፣ ህወሓት በኢትዮጵያ እንዳደረገው በደቡብ ሱዳንም ለወደፊቱ ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ለመክፈት ዝግጅት እንዳለ ገልጸዋል። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ኢህአዴግ ብሔራዊ ክብሩን ጠብቆና ብሔራዊ ኃላፊነቱን በማስቀደም ካልተንቀሳቀሰ በውስጥም በውጪም ችግር ይገጥመዋል።
በደቡብ ሱዳን የሚፈጸሙ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ሙሉ በሙሉ ዝርዝሩን ለጊዜው ከመናገር መቆጠባቸውን የሚናገሩት ወገኖች “ኬንያን ጨምሮ በቀጣናው ኃያል አገር መሆናችን ያስደስተናል። ይህ የኃያልነት ሚናችን እንዲቀጥል በብሔራዊነት ስር ሃብት እያግበሰበሱ ያሉትን ወገኖች መለየትና፣ መንግሥትም እንደ መንግሥት ክብሩን ሊጠብቅ ይገባል” በማለት ማሳሰቢያቸውን ያስተላልፋሉ። ከሌሎቹ ከባድ ንግዶች ውጪ ህዝብ እየተራበ በኮንትሮባንድ እህል ወደ ሱዳንና ወደ ሌላም አገር የሚያጓጉዙት ክፍሎች፣ በሱዳን በባለሃብት ስም የሚንቀሳቀሱትንና በተራ የሱቅ በደረቴ ስራ ተሰማርተው ዶላር የሚሰበስቡት ክፍሎች ጉዳይ ሊታሰብበት እንደሚገባም አሳስበዋል።
Thursday, 10 January 2013
ታላቅ የኢሳት ምሽት በኦስሎ
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ150 ያላነሱ ሱሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ
ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሱሪ አካባቢ ተገኝቶ ያየውን ሁኔታ በብዕሩ ያሰፈረ በአንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ የውጭ አገር ዜጋ የሚከተለውን ሪፖርት ልኳል።
...
ዲሰምበር 20፣ 2012 የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በባሌሳ ሱሪ መንደር፣ ቢያሆላ ወይም በአገሬው ቋንቋ ነጭ ድንጋይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መጡና ነዋሪዎችን ከበቡዋቸው። ወታደሮቹ ወንዶችን መንግስት ይህ እልቂት ፣ ሴቶችንና ህጻናትን እርስ በርስ ካሰሩ በሁዋላ ወደ ዲዲቢ ጫካ ወሰዱዋቸው። 7 ወጣቶች
ብቻ ሲያመልጡ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ረሸኑዋቸው። በመንደሩዋ 154 ሱሪዎች ይኖሩ ነበር።እንዳይነገርበት የሚችለውን ሁሉ እየጣረ ነው። እግዚአብሄር ይመስገን ዜናው ይፋ ወጣ። ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄ ያለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት ለምን ይሆን የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉት? አሸባሪነትን መደገፍ ሳይሆን መዋጋት አልነበረባቸውም?የሟቾቹ አስከሬን በዲቢዲብ ጫካ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ እንዲቀበር ተደርጓል። አንዳንድ አስከሬኖች በጥንብ አንሳ አሞሮች እና በአውሬዎች ተበልተዋል። አብዛኞቹ ህጻናት በአቆቦ ወንዝ ላይ ተጥለዋል። ከጭፍጨፋው በሁዋላ ወታደሮች ይህን ድርጊት ሪፖርት ባደረገው ላይ ሁሉ ከዚህ የበለጠ አስከፊ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
በሱሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንደቀጠለ ነው። በየወሩም እየከፋ በመሄድ ላይ ነው። ማንም ግን ስለችግሩ የተናገረ አካል የለም። በምእራብ አገሮች በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ የምእራብ ሚዲያዎች ሰፊ የዜና ሽፋን እንደማይሰጡት ሁሉ ፣ በደቡብ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ መጠን ሲገደሉ ግን የዜና ሽፋን ሊያገኙ አልቻሉም።
ባለፉት ሳምንታት ብቻ 147፣ ከሶስት ወራት በፊት 30፣ ከአራት ወራት በፊት ደግሞ 70 ሰዎች ተገድለዋል።
የሱሪ ህዝብ በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን ይገኛል። ሱሪዎች ቻይ፣ ቲርማጋ እና ባሌሳ እየተባሉ በሶስት ይከፈላሉ። ሱሪዎች ከኦሞ ወንዝ በስተምስራቅ በኩለ ከሚኖሩት ሙርሲዎች
ይመሳሰላሉ። አንድ አይነት ባህልና አንድ ቋንቋ ይናገራሉ። ዛሬ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች መሬቶቻቸውን ለመውሰድ እያፈናቀሉዋቸው ነው። ዲፊድ፣ ዩኤስ አይዲ፣ ቻኢና፣ ህንድ፣ የአውሮፓ ህብረትና ሳውዲ አረቢያ እነዚህን ባለሀብቶች እየደገፉ ጥፋቶች እንዲሰሩ እያደረጉ ነው።
አሁን የተፈጸመው ጭፍጨፋ ምክንያቱ ሰፈራ ነው። ሱሪዎች መሬታቸውን ለቀው መንግስት ባዘጋጀላቸው የሰፈራ ጣቢያ እንዲሄዱ ተነግሮአቸዋል ምክንያቱ ደግሞ ሬታቸው ለአንድ የወርቅ ማእድን ፈላጊ ኩባንያ በመሰጠቱ ነው። ሱሪዎች መሬታችንን ለቀን አንሄድም ይላሉ፤ የኩባንያው ሰራተኞች ደግሞ ስራችንን ማከናወን አልቻልንም በማለት ክስ ያሰማሉ።
ጀግናን መግደል ይቁም
ጀግናን መግደል ይቁም
ከሳሙኤል ሽፈራው፣ ከዳላስ
CNN HEROES, በ2007 እ ኤ አ ጀምሮ በአለማችን ለሰውልጆች መልካም አሳቢና አድራጊ ናቸው የሚባሉ ግለሰቦችን በመፈለግ ለመልካም ተግባራቸው አለማቀፍ እውቅና እንዲያገኙና ለመልካም ተግባራቸው ምስጋና ይሆን ዘንድ በአንደርሰን ኩፐር በአመት አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ የምርጫ ቀን ነው። መልካም ስራ ያከናወኑ በዚህ ቀን የሰሩት ተግባራት ለአለም በCNN ኔትወርክ ቀርቦ ከመሃላቸው በላጭ ተግባር ላደረገ ተገቢ ሽልማት ይሰጠዋል። ጀግናን ማወደስ ለአሜሪካኖች አዲስ ነገር አይደለም። ለእኛ ትንሽ ብለን ለምናስበው ተግባር የፈጸመን ሰው የጀግና ስም ይሰጠዋል። ለስራውም ሙሉ ምስጋና ያገኛል። አንዳንዴ ግለሰቦች እረ የሰራሁት ጀግና አያሰኘኝም እስኪሉ ተገቢውን ከበሬታ በህብረተሰቡ ይለገሳቸዋል። እናም ይህን ያየ ሁሉ በክፉ አጋጣሚና ጊዜ ዜጋን ለመርዳት ወደኋላ አይልም። አንዳንዴ እውነትም አስገራሚ የሆኑ ተግባራትን የሚያከናውኑ ብዙ ናቸው። ይህ ደግ ባህል ነው። ጀግናን ማሞገስ ተገቢ ነው። ክፉ ቀን ሲመጣ አለሁ የሚል ይገኛል። ለወገን ለአገር ለመቆም፤ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል አቅም ያለው ሁሉ ዝግጁ ይሆናል።
ጀግንነትና መስዋእትነት በዛሬይቱ ኢትዮጵያ
እንዴው ከመቶ አመታት በፊትና የአገራችን የተፈጥሮ አቀማመጥና የከባቢ ፖለቲካ ያስከተለውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ነቅተን እንድንጠብቅ ያደረገንን ትተን፤ ላለፉት 60 እና 70 አመታት የተከሰተውን የባህልና የአስተሳሰብ ለውጥን መመልከቱ በቂ ግንዛቤ የሚሰጠን ይመስለኛል። ከታየው ባህላዊና ስነልቦናዊ ለውጦች አንዱ፤ ለሕዝባችን አዲስና ባእድ የሆነ፤ ጀግናን የመግደልና ፈሪን የማንገስ የማወደስ ባህል የመጣው በነዚሁ አመታት፤ በተለየም ከጠላት ወረራ ወዲህ በመሆኑ። ለዚህ ስነልቦናዊ ለውጥ ምክንያቶችን መመልከቱ በቂ ግንዛቤ ይሰጠናል። ይህን የኔን ሀሳብ የማይቀበል ሰው የራሱን ቢያቀርብ ከውይይት መልካም ግንዛቤ ሊገኝ ይችላል።
ጀግና የመግደል፤ የማዋረድና፤ ፈሪን፤ ፈርጣጭን የማወደስ ታሪካችንም የጀመረው ከሁለተኛው የጠላት ወረራ በኋላ ይማስለኛል። ስለአገራችን ጀግኖች፤ ለትውልድ ይደርስ ዘንድ ብዙ ያለፉም አሁንም በሕይወት ያሉ ታላላቆቻችን በመጽሀፍ አቅርበውልናል። በቅርቡም በአቶ ዘውዴ እረታ የቀረበው የቀዳማዊ ሐይለስላሴ ንግሰ ታሪክ አንዱና ሊነበብ የሚገባው ነው። ከመሐላችን ያሉትን ዘውዴ እረታን እድሜ ከጤና ጨምሮ ይስጥልንና መጭ ትውልዶች እንዲደርሳቸው ብዙ ታላላቅ ታሪካዊ ስራወቻቸውን አካፍለውናል።
እናም ከታሪክ እንደምንረዳው አገራችን ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው አያሌ ሰማእታት ነበሯት፣ አሁንም አሏት። ሆኖም ካለፉት ታሪክ ለመማር ቀርቶ ዛሬ ዛሬ እንድናወድስ በሰፊው እየተገደድን ያለው ፈሪንና ክፉ አድራጊን ሆኗል። የጀግና ስምን ማንሳት የፋሮች፣ ነውና ውግዝ ከማሪወስ ይባላል። በቅርብ ታሪካችን እንኳን ብንነሳ እንደ ዶክተር ታየ ወልደሰማያት አይነት አንበሳ የዚህች አገር ልጆች ዛሬ የት ደረሱ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ጠላት ያልሰበረውን ስነልቦናቸውን፤ ጠላትን እቃወማለሁ የሚል ዛርጢ አንገብግቦ እንዲሰወሩ አደረጋቸው ብል ስህተት አይመስለኝም።፡አንድ ሰው ለሰራው ስራ። ለከፈለው መስዋእትነት ምላሹ የስም ማጉደፍ ዘመቻ ከሆነ፤ ሌላው እንዴት የዚያን እግር ተከትሎ እንቢ ለሀገሬ እንቢ ለሕዝቤ ነጻነት ብሎ በልበ ሙሉነት ሊነሳሳ ይችላል? ለዚህም መልሱ ያው አንገት መድፋት የሚያስከትልን ነገር መራቅና አርፎ መቀመጥን መምረጥ፡ዛሬ የብዙ አያሌ ጀግኖቻችን እጣ ፈንታ ሆኗል።
ድሮ የዚያ የአብዮታዊ የንቢ ባይ ትውልድ ሲነሳሳ ፋና አድርጎ የተነሳው አገራችን በጠላት ስትወረር በዱር በገደሉ ተሰደው መላ አለም በተለየም የሰለጠነው አለም አለቀላቸው ብሎ በአንድ አብሮና ተባብሮ በነሱ አንጻር ሲቆም፣ መሳፍንትና መኳንንት አለቀልን ብለው አገር ለቀው ሲሰደዱ፤ ስም ያልነበራቸውና የማይታወቁ ገበሬወች ናቸው
ዛሬ ላይ ሆነን ያንን ስንመለከት (ስንዘክር) ጀግንነት የፋራነው በሚያሰኝ የአፍ ጀግኖችንና ጀግና ገዳዮችን አንግሰን እንገኛለን።
በቅርቡ የወያኔው ቁንጮ አንገት ያስደፋውን የአበበ ገላውን ቪዲዮ አይቸ መጥገብ አልቻልሁም። ቁጭ ብየ ስተክዝ ሁል ጊዜ የሚታወሰኝ የዘርአይ ደረስ በጣሊያን ዋና ከተማ የአከናወነው የጀግንነት ታሪክ ነው። እናም አበበ እንደዚያ ይመሰልብኛል። በአንጻሩ በእርግጠኝነት ይህን ጀግና እንደ ታየ ወልደሰማያት ለማብጠልጠል የሚሸርቡ ጀግና ገዳዮች እንዳሉ ሲታሰበኝ፡ይዘገንነኛል። ምክንያቱም ላለፉት አራት አስርት አመታት ያለፉ ጀግኖችን ስም ሲወደሱ ሳይሆን፣ ዘርና አጥንታቸው እየተቆጠረ ልክ እንደወያኔው ዘረኛ ቡድን ሲብጠለጠሉ ተመልክቻለሁና ነው። ገርማሜንና መንግስቱ ነዋይን፤ ወይንም ወርቅነክ ገበየሁንና ጽጌ ዲቡን ዛሬ የሚያነሳ የሚያወድስ የለም። ተስፋየ ደበሳይን፣ ግርማቸው ለማን ወይንም ውብሸት ፍስሀና ጽገየ ገ/መድሕን (ደብተራው) እና በአዲስ አበባ ዘመን ከሰጠው ጠባብ ቡድን ጋር 1994 ዓም በቀን ተታኩሶ የወደቀውን ጋይምን የሚያነሳ የሚያወድስ ወይንም ፈለጋቸውን ለመከተል የሚፎክር ባለማየቴ ነው።
በዚህ በተነሳሁበት እርእስ ብዙ ማለት ይቻላል። ከጠላት ወረራ ጊዜ ጀምሮ ያገራቸው አፈር በልቷቸው የቀሩ ለዝክረ ሰማእትነት እድሉ የተነፈጋቸው ብዙ ናቸው። ከላይ እንዴው ለላሙና ያክል ምሳሌ እንዲሆነን እንጅ ሁሉን መጥቀስ ቢቻል እንዴት መልካም ነበር። ለዚህ መጥፎ ልማድ ያበቃን ሁለት ኩነቶች ባገራችን ተከናውነዋል። አንደኛውና ዋነኛው፤ ጣሊያን በጀግኖቻችን መስዋእትነትና ተጋድሎ አገር ለቆ ከወጣ በኋላ ሲሆን፤ ይኸውም አርበኛን ወደጎን አድርጎ ባንዳንና ስደተኛን መሾም መሸለም፤ አርበኛን ማግለልና ማናናቅ፤ ብሎም ለግዞትና እስራት መዳረግ ሲሆን። ለዚህ ቅድሚያውን የበላይ ዘለቀ ከሁለት ወንድሞቹ ጋር የደረሰባቸው የሞት እጣ ሲሆን፣ በቀጣዩ አመታት ገረሱ ዱኪ፤ ነጋሽ በዛብህ፣ መንገሻ ጀንበሬ፣ ኋላም ታከለ ወልደ ሐዋርያት በተዋደቁላት አገር በክብር አላለፉባትም።
ሁለተኛው ባህላዊ ለውጥ በወታደራዊ ደርግ የተከናወነ ሲሆን። ሕዝብን ስነልቦናውን ሰብሮ በአደባባይ ልጅን ገድሎ እሬሳን መሸጥ ብሎም ወላጅ አባትና እናት ልጆቻቸውን አልቅሰው በክብር እንዳይቀብሩ የተከለከለበት አዲስ ሁኔታ ነው። ያን አይነት በወገን በአገር ላይ የደረሰ የመንፈስ ጉዳት ለዛሬው አገርን ለአናሳ ጠባብ ብሄርተኛ አስረክቦ መቀመጥ ምክንያት ሆነ የሚል የግል እምነት አለኝ። ሁሉ ነገር ፖለቲካ ነው ብሎ መፈጸምና ክብርን አሳልፎ መስጠት ብልጠት እንጅ ጅልነት ያልሆነበት ጊዜ ላይ ነን። ለአገር ብለው የሚታገሉትን ማብጠልጠል፤ ማዋረድ እና ክብራቸውን መዳፈር አዋቂነት ነው። ይህ አድራጎት ይበልጥ እንዲስተጋባና ስር እንዲሰድ ዘመናዊው የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው አስተዋጽኦው የሚናቅ አይደለም። ፓልቶኮችና ድህረ ገጾች ሕዝብ አሰባሳቢና ቀስቃሽ የሆኑትን ያክል፤ከምኝታ ቤታቸው ጎድበው ስም ለሚያራክሱ ፈሪወችም አስተዋጸኦ አላቸው። ፓልቶክን ካነሳን ላይቀር በቅርቡ በቃሌ አስተዳዳሪወች የተጀመረው ለአገር አስተዋጸኦ ላደረጉት የምስጋና ፕሮግራም መጀመር እሰየው የሚያሰኝ ነዉና እንዲበረታቱና ቀጣይነት እንዲኖረው አበጃችሁ እላለሁ።
ሰሞነኛው የፈሪወች ዘመቻ
ለዚህ አጭር መጣጥፍ ያበቃኝ በዚህ ባሳለፍናቸው ሳምንታት በታሕሳስ ወር የመጨረሻ ያየኋቸው ናቸው። መጀመሪያ አቶ እያሱ አለማየሁ ለአንድ የራዲዮ ቃለ ምልልስ ቀርበው ግለሰቡን አስታከው የቀረቡ አስተያየቶችና ጥያቄወች ከፊሉ አንድን ትውልድ አውጋዥና የተከፈለን መስዋእትነት አራካሽ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። በእርግጥ ተገቢም የሆኑና መልስ የሚፈልጉ ጥያቄወች እንደነበሩበት ልክድ አልችልም። ሌላው በለንደን የሸንጎ ስብሰባ ተንተርሶ በትቂት ግለሰቦች በአቶ መርሻ ላይ የቀረቡ ዘለፋወች ናቸው። እናም የዚያ ትውልድ አካል እንደመሆኔ፤ አፍላ እድሜየን ለዴሞክራሲ ጥያቄን አንግበው ከተነሱት ጋር በኢሕአፓ ስር ሆኘ የታገልሁ የታሰርሁ የተንገላታሁን ከትውልዱ ተረፉ ከሚባሉት ትቂቶቹ አንዱ ነኝና ከላይ በጠቀስኳቸው ሁለቱ ግለሰቦች ላይ የተሰነዘረው መረን የለሽ ዝልፊያን መቀበል፤ የተከፈለን መስዋእትነት እንደመካድ ቆጥሬዋለሁ። ግለሰቦቹ በየቅል ሰው እንደሞሆናቸው ሊኖራቸው የሚችሉ ድክመቶች ቢኖሩ አስገራሚ ባይሆንም፤ የከፈሉት እና እየከፈሉት ያለን መስዋእትነት መካድ ብሎም ማብጠልጠሉ አግብነት የለውም። ከላይ እዳሳየሁት አዲሱ ባህል ፈሪን አንግሶና አወድሶ ጀግናን ማራከስ የሚጠቅም ሳይሆን ለትውልድ የሚተላለፍ ክፉ ደዌ ነውና መቆም አለበት። እናም በየትኛውም ሚዛን ከላይ የጠቀስኳቸው ግለሰቦች የጀግንነት መስፈሪያውን ያሟላሉና ነው።
እንዴው ለማለት ያክል ለመሆኑ ሙሉ እድሜን ለዚህ ትግል ብሎ ያሳለፈ ሰው ወይንም እያሳለፈ ያለ አለወይ? ዛሬ ይህን ከፋፋይ ጠባብ ቡድን ለመለወጥ በሚካሄደው ትግል አንደኛውና ዋነኛው ችግር እኮ የትርፍ ጊዜ (part-time) ታጋዮች መበራከት ነው። ታዲይስ አቶ መርሻን አይነት እና የዚያን ትውልድ መሪወች ማብጠልጠል ምኑ ነው የሚጠቅም? እስኪ አሁንም በኢሕአፓ ስር ካሉት አንድ ሁለት ተብለው ከሚቆጠሩት ውጭ ኑሮ ትግሌ ብሎ የሚኖር አመላክቱኝ። አወ የነሱን ፈለግ ተከትለው በየትም ይሁን በየት የሚንቀሳቀሱ ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ቁጥራቸው 10 እና 20 ከደረስ እሰየው ያሰኛል። ይህ ማለት ለእውነት እንነጋገር ከተባለ ሁላችንም በተቃዋሚነት ቆመን ይህን ዘረኛና አሸባሪ አንባገንነን እንጥላለን ስንል የኑሮ ነገር ስላጋደለብን ሙሉ ጊዜንና ሕይወትን ለትግሉ የሚሰጥ ስለጠፋ ነው ድል እየራቀን፤ በወገን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል እየበዛብን የቀጠለው። እናም እነዚህን መሰሎች ለማውጣት ያሉንን መንከባከብ ሲገባ፤ ስድብና ዘለፋ ከጠላት የሚወረወረው ይበቃል።

ኢትዮጵያ ሐገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።
አገራችን እጹብ ድንቅ ያሰኙ ጀግኖች የተፈጠሩባት አገር ናት። እንዴው የረጅሙን ዘመን ታሪክና የአገር አውራ ጠባቂወችን ትተን፤ ከቅርቡ የሁለተኛው አለም ጦርነት ብለው አውሮፓውያን ከሚጠሩት መባቻ ጀምረን ይህችን አገር አሳልፎ ላለመስጠት ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ቆጥረን የምንዘልቀው አይሆንም። እናም በዚያ አርበኛ ትውልድ የተካውም ቢሆን እንደነሱ ለአገሩ ከልክ ያለፈ ፍቅር የነበረውና የነዚያ ያርበኛ ትውልድ ልጆች ነበሩ የየካቲቱን የለውጥ ትግል ያቀጣጠሉት። ለውጡን ከነጣቂ ለማስቀረት ሲሉም በየጎዳናው በጥይት የተረፈረፉት። ታዲያ እንደዚያ ያሉ ጀግና ትውልዶች ያለፉባት አገራችን ለምንና እንዴት ተቃራኒ ባህልን ማስተናገድ ተቻላት? ይህ አዲስ ጀግና አራካሽና ፈሪ አወዳሽ ባህልን ከመስፋፋቱ በፊት በነበረው ጊዜ ለግምት በሚያስቸግር አያት ቅድም አያቶቻችን ነጻነታችንን በተጋድሎና በመስዋእትነት ጠብቀው አቆዩን።በቀደመውም ጊዜ ላገር መሰዋት ክብር ነበርና፤ ዜጎች የአርበኛን ገድል በዘፈንና አፍ ለአፍ በሚተላለፍ ታሪክ አቆዩን።የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።
በሻህ ቢሰዋ ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብሻ ለብቻ፡
ይህ ከላይ ያስቀመጥሁት በአደዋ ጦርነት ከዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ጋር የዘመቱት በሻህ አቡዬ በጀግንነት ሲሰው፤ ባልቻ አባነፍሶ ተክተው ጀግንነቱን ሸፈኑ ለማለት የተቀኘ የፉከራ ስንኝ ነበር።መድፍ አገላባጭ ብሻ ለብቻ፡
ተሰቀለ ቢሉኝ፤ ጀበርናው ነው ብየ
ተሰቀለ ቢሉን ዝናሩ ነው ብየ
ለካስ በላይ ኖሯል ትልቁ ሰውየ
ይህ ደግሞ በበገናና በክራር አንጎራጓሪ የደረደረው የሐዘን እንጉር ጉሮ ነው። ይህን ከላይኛው የሚለየው አንዱ በጀግንነት በጦር ሜዳ የተሰዋ ሲሆን። ሌላው ጠላትን ያርበተበተና እግዞ ያሰኘ ጀግና በራሱ ወገን በፈሪ ስብስብ የተፈረደበት ጀግና ነው።ተሰቀለ ቢሉን ዝናሩ ነው ብየ
ለካስ በላይ ኖሯል ትልቁ ሰውየ
ጀግና የመግደል፤ የማዋረድና፤ ፈሪን፤ ፈርጣጭን የማወደስ ታሪካችንም የጀመረው ከሁለተኛው የጠላት ወረራ በኋላ ይማስለኛል። ስለአገራችን ጀግኖች፤ ለትውልድ ይደርስ ዘንድ ብዙ ያለፉም አሁንም በሕይወት ያሉ ታላላቆቻችን በመጽሀፍ አቅርበውልናል። በቅርቡም በአቶ ዘውዴ እረታ የቀረበው የቀዳማዊ ሐይለስላሴ ንግሰ ታሪክ አንዱና ሊነበብ የሚገባው ነው። ከመሐላችን ያሉትን ዘውዴ እረታን እድሜ ከጤና ጨምሮ ይስጥልንና መጭ ትውልዶች እንዲደርሳቸው ብዙ ታላላቅ ታሪካዊ ስራወቻቸውን አካፍለውናል።
እናም ከታሪክ እንደምንረዳው አገራችን ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው አያሌ ሰማእታት ነበሯት፣ አሁንም አሏት። ሆኖም ካለፉት ታሪክ ለመማር ቀርቶ ዛሬ ዛሬ እንድናወድስ በሰፊው እየተገደድን ያለው ፈሪንና ክፉ አድራጊን ሆኗል። የጀግና ስምን ማንሳት የፋሮች፣ ነውና ውግዝ ከማሪወስ ይባላል። በቅርብ ታሪካችን እንኳን ብንነሳ እንደ ዶክተር ታየ ወልደሰማያት አይነት አንበሳ የዚህች አገር ልጆች ዛሬ የት ደረሱ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ጠላት ያልሰበረውን ስነልቦናቸውን፤ ጠላትን እቃወማለሁ የሚል ዛርጢ አንገብግቦ እንዲሰወሩ አደረጋቸው ብል ስህተት አይመስለኝም።፡አንድ ሰው ለሰራው ስራ። ለከፈለው መስዋእትነት ምላሹ የስም ማጉደፍ ዘመቻ ከሆነ፤ ሌላው እንዴት የዚያን እግር ተከትሎ እንቢ ለሀገሬ እንቢ ለሕዝቤ ነጻነት ብሎ በልበ ሙሉነት ሊነሳሳ ይችላል? ለዚህም መልሱ ያው አንገት መድፋት የሚያስከትልን ነገር መራቅና አርፎ መቀመጥን መምረጥ፡ዛሬ የብዙ አያሌ ጀግኖቻችን እጣ ፈንታ ሆኗል።
ድሮ የዚያ የአብዮታዊ የንቢ ባይ ትውልድ ሲነሳሳ ፋና አድርጎ የተነሳው አገራችን በጠላት ስትወረር በዱር በገደሉ ተሰደው መላ አለም በተለየም የሰለጠነው አለም አለቀላቸው ብሎ በአንድ አብሮና ተባብሮ በነሱ አንጻር ሲቆም፣ መሳፍንትና መኳንንት አለቀልን ብለው አገር ለቀው ሲሰደዱ፤ ስም ያልነበራቸውና የማይታወቁ ገበሬወች ናቸው
ሞፈሬን ቀንበሬን ሰጠሁት ለሌላ
አገሩ ለሚኖር ሰርቶ ለሚበላ።
እልም ነው፤ ጭልጥ ነው እውሀ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም።
በማለት ዱር ቤቴ ብለው የነበራቸውን ጋሻና ጦር ከፍ ሲል ደግሚ አንድ ጎራሽ መውዜር አንጠልጥለው ጫካ የገቡት። እነዚያ ጀግኖች በሽሬ በራስ እምሩ በሚመሩት ሰራዊት። በማይጮ በራስ ሙሉጌታ ይገዙና በሰራዊቶቻቸው። በደቡብ በራስ ደስታ ዳምጠው የተከፈለውን መስዋእትነት ፋና ወጊ አድረገው እንጅ፡ ቦዶሊዮ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት የምን አገር ማዳን ብለው የተሰደዱትን ተመልክተው አልነበረም።አገሩ ለሚኖር ሰርቶ ለሚበላ።
እልም ነው፤ ጭልጥ ነው እውሀ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም።
ዛሬ ላይ ሆነን ያንን ስንመለከት (ስንዘክር) ጀግንነት የፋራነው በሚያሰኝ የአፍ ጀግኖችንና ጀግና ገዳዮችን አንግሰን እንገኛለን።
በቅርቡ የወያኔው ቁንጮ አንገት ያስደፋውን የአበበ ገላውን ቪዲዮ አይቸ መጥገብ አልቻልሁም። ቁጭ ብየ ስተክዝ ሁል ጊዜ የሚታወሰኝ የዘርአይ ደረስ በጣሊያን ዋና ከተማ የአከናወነው የጀግንነት ታሪክ ነው። እናም አበበ እንደዚያ ይመሰልብኛል። በአንጻሩ በእርግጠኝነት ይህን ጀግና እንደ ታየ ወልደሰማያት ለማብጠልጠል የሚሸርቡ ጀግና ገዳዮች እንዳሉ ሲታሰበኝ፡ይዘገንነኛል። ምክንያቱም ላለፉት አራት አስርት አመታት ያለፉ ጀግኖችን ስም ሲወደሱ ሳይሆን፣ ዘርና አጥንታቸው እየተቆጠረ ልክ እንደወያኔው ዘረኛ ቡድን ሲብጠለጠሉ ተመልክቻለሁና ነው። ገርማሜንና መንግስቱ ነዋይን፤ ወይንም ወርቅነክ ገበየሁንና ጽጌ ዲቡን ዛሬ የሚያነሳ የሚያወድስ የለም። ተስፋየ ደበሳይን፣ ግርማቸው ለማን ወይንም ውብሸት ፍስሀና ጽገየ ገ/መድሕን (ደብተራው) እና በአዲስ አበባ ዘመን ከሰጠው ጠባብ ቡድን ጋር 1994 ዓም በቀን ተታኩሶ የወደቀውን ጋይምን የሚያነሳ የሚያወድስ ወይንም ፈለጋቸውን ለመከተል የሚፎክር ባለማየቴ ነው።
በዚህ በተነሳሁበት እርእስ ብዙ ማለት ይቻላል። ከጠላት ወረራ ጊዜ ጀምሮ ያገራቸው አፈር በልቷቸው የቀሩ ለዝክረ ሰማእትነት እድሉ የተነፈጋቸው ብዙ ናቸው። ከላይ እንዴው ለላሙና ያክል ምሳሌ እንዲሆነን እንጅ ሁሉን መጥቀስ ቢቻል እንዴት መልካም ነበር። ለዚህ መጥፎ ልማድ ያበቃን ሁለት ኩነቶች ባገራችን ተከናውነዋል። አንደኛውና ዋነኛው፤ ጣሊያን በጀግኖቻችን መስዋእትነትና ተጋድሎ አገር ለቆ ከወጣ በኋላ ሲሆን፤ ይኸውም አርበኛን ወደጎን አድርጎ ባንዳንና ስደተኛን መሾም መሸለም፤ አርበኛን ማግለልና ማናናቅ፤ ብሎም ለግዞትና እስራት መዳረግ ሲሆን። ለዚህ ቅድሚያውን የበላይ ዘለቀ ከሁለት ወንድሞቹ ጋር የደረሰባቸው የሞት እጣ ሲሆን፣ በቀጣዩ አመታት ገረሱ ዱኪ፤ ነጋሽ በዛብህ፣ መንገሻ ጀንበሬ፣ ኋላም ታከለ ወልደ ሐዋርያት በተዋደቁላት አገር በክብር አላለፉባትም።
ሁለተኛው ባህላዊ ለውጥ በወታደራዊ ደርግ የተከናወነ ሲሆን። ሕዝብን ስነልቦናውን ሰብሮ በአደባባይ ልጅን ገድሎ እሬሳን መሸጥ ብሎም ወላጅ አባትና እናት ልጆቻቸውን አልቅሰው በክብር እንዳይቀብሩ የተከለከለበት አዲስ ሁኔታ ነው። ያን አይነት በወገን በአገር ላይ የደረሰ የመንፈስ ጉዳት ለዛሬው አገርን ለአናሳ ጠባብ ብሄርተኛ አስረክቦ መቀመጥ ምክንያት ሆነ የሚል የግል እምነት አለኝ። ሁሉ ነገር ፖለቲካ ነው ብሎ መፈጸምና ክብርን አሳልፎ መስጠት ብልጠት እንጅ ጅልነት ያልሆነበት ጊዜ ላይ ነን። ለአገር ብለው የሚታገሉትን ማብጠልጠል፤ ማዋረድ እና ክብራቸውን መዳፈር አዋቂነት ነው። ይህ አድራጎት ይበልጥ እንዲስተጋባና ስር እንዲሰድ ዘመናዊው የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው አስተዋጽኦው የሚናቅ አይደለም። ፓልቶኮችና ድህረ ገጾች ሕዝብ አሰባሳቢና ቀስቃሽ የሆኑትን ያክል፤ከምኝታ ቤታቸው ጎድበው ስም ለሚያራክሱ ፈሪወችም አስተዋጸኦ አላቸው። ፓልቶክን ካነሳን ላይቀር በቅርቡ በቃሌ አስተዳዳሪወች የተጀመረው ለአገር አስተዋጸኦ ላደረጉት የምስጋና ፕሮግራም መጀመር እሰየው የሚያሰኝ ነዉና እንዲበረታቱና ቀጣይነት እንዲኖረው አበጃችሁ እላለሁ።
ሰሞነኛው የፈሪወች ዘመቻ
ለዚህ አጭር መጣጥፍ ያበቃኝ በዚህ ባሳለፍናቸው ሳምንታት በታሕሳስ ወር የመጨረሻ ያየኋቸው ናቸው። መጀመሪያ አቶ እያሱ አለማየሁ ለአንድ የራዲዮ ቃለ ምልልስ ቀርበው ግለሰቡን አስታከው የቀረቡ አስተያየቶችና ጥያቄወች ከፊሉ አንድን ትውልድ አውጋዥና የተከፈለን መስዋእትነት አራካሽ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። በእርግጥ ተገቢም የሆኑና መልስ የሚፈልጉ ጥያቄወች እንደነበሩበት ልክድ አልችልም። ሌላው በለንደን የሸንጎ ስብሰባ ተንተርሶ በትቂት ግለሰቦች በአቶ መርሻ ላይ የቀረቡ ዘለፋወች ናቸው። እናም የዚያ ትውልድ አካል እንደመሆኔ፤ አፍላ እድሜየን ለዴሞክራሲ ጥያቄን አንግበው ከተነሱት ጋር በኢሕአፓ ስር ሆኘ የታገልሁ የታሰርሁ የተንገላታሁን ከትውልዱ ተረፉ ከሚባሉት ትቂቶቹ አንዱ ነኝና ከላይ በጠቀስኳቸው ሁለቱ ግለሰቦች ላይ የተሰነዘረው መረን የለሽ ዝልፊያን መቀበል፤ የተከፈለን መስዋእትነት እንደመካድ ቆጥሬዋለሁ። ግለሰቦቹ በየቅል ሰው እንደሞሆናቸው ሊኖራቸው የሚችሉ ድክመቶች ቢኖሩ አስገራሚ ባይሆንም፤ የከፈሉት እና እየከፈሉት ያለን መስዋእትነት መካድ ብሎም ማብጠልጠሉ አግብነት የለውም። ከላይ እዳሳየሁት አዲሱ ባህል ፈሪን አንግሶና አወድሶ ጀግናን ማራከስ የሚጠቅም ሳይሆን ለትውልድ የሚተላለፍ ክፉ ደዌ ነውና መቆም አለበት። እናም በየትኛውም ሚዛን ከላይ የጠቀስኳቸው ግለሰቦች የጀግንነት መስፈሪያውን ያሟላሉና ነው።
እንዴው ለማለት ያክል ለመሆኑ ሙሉ እድሜን ለዚህ ትግል ብሎ ያሳለፈ ሰው ወይንም እያሳለፈ ያለ አለወይ? ዛሬ ይህን ከፋፋይ ጠባብ ቡድን ለመለወጥ በሚካሄደው ትግል አንደኛውና ዋነኛው ችግር እኮ የትርፍ ጊዜ (part-time) ታጋዮች መበራከት ነው። ታዲይስ አቶ መርሻን አይነት እና የዚያን ትውልድ መሪወች ማብጠልጠል ምኑ ነው የሚጠቅም? እስኪ አሁንም በኢሕአፓ ስር ካሉት አንድ ሁለት ተብለው ከሚቆጠሩት ውጭ ኑሮ ትግሌ ብሎ የሚኖር አመላክቱኝ። አወ የነሱን ፈለግ ተከትለው በየትም ይሁን በየት የሚንቀሳቀሱ ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ቁጥራቸው 10 እና 20 ከደረስ እሰየው ያሰኛል። ይህ ማለት ለእውነት እንነጋገር ከተባለ ሁላችንም በተቃዋሚነት ቆመን ይህን ዘረኛና አሸባሪ አንባገንነን እንጥላለን ስንል የኑሮ ነገር ስላጋደለብን ሙሉ ጊዜንና ሕይወትን ለትግሉ የሚሰጥ ስለጠፋ ነው ድል እየራቀን፤ በወገን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል እየበዛብን የቀጠለው። እናም እነዚህን መሰሎች ለማውጣት ያሉንን መንከባከብ ሲገባ፤ ስድብና ዘለፋ ከጠላት የሚወረወረው ይበቃል።
Tuesday, 8 January 2013
ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል ከኢየሩሳሌም አርአያ
ቅሌታም ባልና ሚስት |
ጉዳዩን የተመለከተው ከፍተኛው አመራር (የፖሊት ቢሮ) ሁለቱንም አስቀምጦ ለማስታረቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ጭራሽ ባልና ሚስቱ አስገራሚ የዘለፋ ቃላት ተወራወሩ፤ ሽማግሌው ስብሃት በሰጡት የአፀፋ መልስ « ..እርሷ የምትሰራውን ነው የሰራሁት..» ሲሉ አፈንድተውት አረፉት።..(ሌሎቹ የቃላት ልውውጦች አፀያፊ በመሆናቸው ዘልያቸዋለሁ)… በዚሁ መሰረት ስብሃት የልጆች ማሳዳጊያ ተቆራጭ እንዲያደርጉ በመወሰን የፍቺ ጥያቄው እንዲፀድቅ ተደረገ። መኖሪያ ቤቱ ለሁለት ተከፍሎ እንዲኖሩበት ተወሰነ። ሽማግሌው በአብዛኛው ቀናት ወደ መኖሪያቸው ሲያቀኑ ወጣት ኮረዶችን ሻጥ ማድረጉን በግልፅ ተያያዙት። እንዳውም ሁለት ወጣት ኮረዶችን ይዘው ይገቡ እንደነበር፥ በሕይወት የሌለው የስብሃት የረጅም አመት ሹፌር ተክላይ (ወዳጄ) በየጊዜው ይነግረኝ ነበር። ( በነገራችን ላይ ሹፌር ተክላይ በአንድ የውጭ ድርጅት በተሻለ ደመወዝ ለመቀጠር ፈልጎ ለስብሃት የመልቀቂያ ጥያቄ ሲያቀርብ « ብዙ ሚስጥር ስለምታውቅ ከዚህ መልቀቅ አትችልም» ተባለ። ከዚያም በተመረዘ ምግብ ሕይወቱ አለፈ። መስከረም 2000ዓ.ም ነበር ያለፈው)
Monday, 7 January 2013
አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ
ከኢየሩሳሌም አርአያ
የህወሃት አባል ነው ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ስልጣን እስከተቆናጠጠበት ጊዜ ድረስ ያለው ታሪክ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ ግለሰብ ተስፋዬ መረሳ ይባላል። ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ተራው ታጋይ ከሴት ጋር የፍቅርም ሆነ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ እንደማይፈቀድለት አስገራሚው የፓርቲው ህግ ይደነግጋል። ይህ ህግ እስከ 1981 አ.ም የቆየ ሲሆን የበላይ አመራሩ ግን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው። ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ የተገኙ ተራ ታጋዮች ይፈፀምባቸው የነበረው ቅጣት በጥይት ተደብድቦ መገደል ነበር። በሺህ የሚቆጠሩ የፓርቲው ተራ አባላት የዚህ ቅጣት ሰለባ ሆነዋል።እነዚህ ታጋዮች እንዲረሸኑ ሲወሰን ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት እና በርካታው የፓርቲ አባላት ከሚያስታዉሷቸው ገዳዮች አንዱ እና ቀንደኛው ተስፋዬ መረሳ ሲሆን ፣ ከእርሱ በተጨማሪ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ወ/ስላሴ ፣ሃይሉ (ሳንቲም) … በጭካኔ የግድያ ተግባራ ይጠቀሳሉ። ፊደል ያልቆጠሩት እነዚህ ወንጀለኞች የገዛ የትግል ጓዶቻቸውን ለመረሸን እጅ በማውጣት “እኔ… እኔ” እየተባባሉ ያሳዩ የነበረው ሰይጣናዊ ፉክክር እና ጥድፊያ ብዙ የፓርቲው አባላት አሁን ድረስ ያስታውሱታል አቶ መለስ እነዚህን ግለሰቦች በደህንነትና ፖሊስ ቁልፍ ቦታ ያስቀመጡአቸው የታዘዙትን እንደሚፈጽሙላቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር ። እነ ተስፋዬ “ግደሉ “ሲባሉ “ስንት?” ነበር የሚሉት ።በገሃድም የታየው ይሄው ነበር ።
የክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በህግ ዲግሪ የነበራቸው ሻለቃ በፍቃዱ ቶሌራ በ1996 አ.ም ያለ አንዳች ጥፋት እንዲነሱ ተደርጎ በምትካቸው ወደ ስልጣን እንዲመጣ የተደረገው ተስፋዬ መረሳ በምርጫ 97 የአቶ መለስን ትእዛዝን በመቀበል የበርካታ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም እንዲፈስ አድርጓል ።በመቶዎች የሚቆጠሩ አካላቸው እንዲጎድል ፣በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት እንዲጋዙ በርካቶች ከስራቸው እንዲባረሩ አድርጓል።ከአዲስ አበባ ፖሊስ 400 የሚጠጉ አባላትን በቅንጅት ደጋፊነት እና አባልነት በመፈረጅ እንዲባረሩ ወስኖአል።
በወቅቱ ለዚህ የወንጀል ተግባሩ ከአቶ መለስ ሙገሳ እና ውዳሴ ለማግኘት በቅቶአል። አስገራሚው ነገር ይህ ወንጀለኛ በዚህ የጭካኔ ተግባሩ የልብ ልብ ተሰምቶት ሸራተን ጎራ ማለት ይጀምራል። የተስፋዬ ሸራተን መጥቶ መለኪያ ማንሳት ያላስደሰታቸው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ «አቅሙን፣ደረጃውን፣ልኩን አይቶ አይጠጣም?እዚህ መጥቶ ከእኛ እኩል መጠጣት እና መዝናናት ይፈልጋል ?የምን መዳፈርነው ?» ሲሉ ንዴት የተሞላበት ተግሳፅ እንዲደርሰው ያደርጋሉ ።የስብሃት አደገኛነት የት እንደሚደርስ እና ምን አይነት የበቀል መዘዝ እንደሚያስከትል ጠንቅቆ የሚያውቀው ተስፋዬ አሳቻ ጊዜ ሲጠብቅ ይቆያል።
በ2000 አ.ም ከቢጤዎቹ ጋር አንድ ፕላን ይነድፋል። ከደህንነት ሹሞች ከነኢሳያስ ጋር የመከረው ጉዳይ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ተፈጻሚ ለማድረግ ተንቀሳቀሱ ።የምክክሩ ምስጢር ይህ ነበር ። በአዲስ አበባ በተለይ ፒያሳ፣አራት ኪሎ ፣ከጊዮን_- ፍልዉሃ እስከ ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ፣አሜሪካ ግቢ፣ መርካቶ ፣ቦሌ፣22 ማዞሪያ፣መገናኛ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ከፍተኛ የዶላር ጥቁር ገበያ ይካሄዳል። ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ሲቪል የለበሡ በሺህ የሚቆጠሩ የደህንነት አባሎች በሁሉም መደብሮች በር ላይ በተመሳሳይ ሰአት እንዲገኙ ከተደረገ በኋላ በዚያው ቅጽበት ከተስፋዬ “ጀምሩ”የሚል ትእዛዝ ሲተላለፍ… መሳሪያ እየደቀኑ ዶላሩን ጠራርገው ከየመደብሩ በሃይል ወሰዱ ። ከአሜሪካ ግቢ ብቻ ከስምንት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ሲገኝ በአጠቃላይ 4.5ሚልዮን ዶላር ገደማ በጉልበት ተወረሰ ።ከዶላር በተጨማሪ ከመርካቶ እና ፒያሳ ከ2 ሚሊዮን የበለጠ ጥሬ ገንዘብ(የኢትዮጵያ ብር) ተወስዶአል። በ1984-85 አ.ም በወቅቱየሃገሪቱ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ የዶላር ጥቁር ገበያን አስመልክተው ሲናገሩ “ምንዛሬውን ከወቅቱ ገበያ ጋር እኩል እናካሂደዋለን እንጂ የጥቁር ገበያውን ቁጥጥር አናደርግበትም ፣አንነካውም “በማለት ተናግረው እንደነበር ብዙዎች ያስታውሱታል።ሆኖም ግን በቃሉ የማይገኘው የኢህአዴግ መንግስት በጠራራ ፀሃይ የለየለት የአደባባይ ዝርፊያ ሲያከናውን በርካቶች ኑሮአቸው ተናግቶአል፤ አንዳንዶችም ህይወታቸውን እስከማጥፋት ደርሰዋል።
ይህ ገንዘብ በቀጥታ ገቢ የተደረገው ወይም የተረከበው ተስፋዬ መረሳ ነበር ።በወቅቱ በመንግስት ሚዲያ ህገወጥ የዶላር አዘዋዋሪዎች እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ እና ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ መደረጉን የገለጸው ተስፋዬ፣ይህንን በተናገረ በሳምንት ልዩነት የተዘረፈውን ገንዘብ በሳምሶናይት ይዞ በቦሌ ወደ ኬንያ አመራ ።ከዚያም ወደ አሜሪካን አቀና ።ይህ በንጹሃን ደም የታጠበ ወንጀለኛ እና ዘራፊ አሜሪካን እንደመሸገ የተረጋገጠ ቢሆንም፣የት ከተማ እንዳለ እና እንደሚኖር ማወቅ አልተቻለም።
Subscribe to:
Posts (Atom)