"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 15 February 2013

ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ ምሽት[እንዳለ ጌታነህ ከኖርዌ እንደተመለከተው]

እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ አገራችን እንገባለን

የዳመነው ችግር;ሰማዩ  እስኪጠራ፤ ካገር ተሰደድን በተራ በተራ።አንድ ቀን ይታየኛል፡ታብሶ የኛ ዕንባ ፤እጅ ለእጅ ተያይዘን አገር ቤት ስንገባ። ይህ ዜማ በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ  በአሜሪካ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባቀረበው የሙዚቃ  ዝግጅት ላይ በአገር ፍቅርና ናፍቆት ለሚሰቃየው አገር ወዳድ  እጅ ለእጅ አያይዞ  ያላቀሰበት ዘፈን ነበር።እኛም ዛሬ በፎቶው እንደሚታየው ለኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ በመሆን  የሚያገለግለውን የእሳትን መለያ ካኔተራ በመልበስ በእሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ  ምሽት ላይ በኖርዌ የምንገኝ  ስደተኞች ከአጭር ድራማ በኋላ የዘመርነው መዝሙር ነው።                                                                           ልቀጥል በዝግጅቱ ላይ የተገኘውን ህዝብ ስመለከት አንድ ነገርአሰብኩኝ፤ደግሞም ተመኘሁኝ፤ማሰብም መመኘትም መብቴ  ቢሆንም ምናልባት እኔ  እንዳሰብኩት  ይህንን ጽሁፍ የሚያንብ ሰው ሃሳቤን ይጋራል ብዬ ልገምት፤ሀሳቤ ምን መሰላችሁ፤በፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ የነበረው ዕድምተኛ በሙሉ  ለሁሉም አገራዊ ጥሪ ህብረቱ፤አንድነቱ፦ትብብሩና በጋራ መስራቱ ሁል ጊዜ እንዳሁኑ ቢሆን፤ልክ የድራማው መጨረሻ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝሙሩን በአንድነት ከልብ ከስሜት እንደዘመርን ፤በእምነታችንና በዘራችን ሊለየን ፤የንግግር፦የመጻፍና በሰላም የመኖር መብታችንን ያሳጣንን፤አገራችንን ለባዕድ እየሰጠ ገበሬውን መሬትና አገር አልባ አድርጎ በአገሩ ላይ ስደተኛ እንዲሆን የሚያደርገውን  ጨቋኝና ከፋፋይ የሆነውን የወያኔ መንግስት በጋራ ለማጥፋት፤ህብረታችን እንዲቀጥል፤የእርስ በርስ  መናቆራችንን በመተው ላገርና ለወገን የሚበጀውን ቅድሚያ  በመስጠት በህብረት ብንቀሳቀስ; ብዬ ተመኘሁ። ደግሞ ቀደም ብዬ  ተናግሬአለው  መመኘት መብቴ ነው ብዬ ።                                                                                                                                                     እስኪ ይታያችሁ እኔ  የተመኘሁት ከመጀመሪያው ቢሆን ኖሮ አይደለም 21 ዓመት አንድም ዓመት አይቆዩም ነበር።እረ  የምን አንድ ዓመት አመጣህ ያኔ ገና ሰባት እንዳሉ   በአንድ ቦምብ እምሽክ ነበር እንዳለው ይሆን ነበር።ትሉኝ ይሆናል ፤ግን ነበርን ትተን ላለፈው ክረምት  ቤት አይሰራም ለሚመጣው  ይታሰባል የሚለውን አገርኛ አባባል ተቀብልን ወደፊት በሉለት ይለይለት የሚለውን የጥላሁንን ዘፈን ለአንባቢዎቼ ስመርጥላችሁ፤ለቃሉ ታማኝ በመሆን ከእሳትና ከውሃ እሳትን በመምረጥ የእናት አገሩና የህዝቡ መጠቃት ዘወትር የሚያገበግበው እንደ  ሌሎቹ አርቲስት ነን ባዮች ምሳሌ ከርሳሙ ሰለሞን ተካልኝ እና  መሰሎቹ ለጥቅም ሳይገዛ ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠር ጀምሮ  ቃል የእምነት እዳ እንጂ የእናት አባት አይደለም በማለት ብዙ መከራና ችግር  በመቀበል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለእኛም ከኢትዮጵያ ውጭ ላለነው ምሳሌ  በመሆን እንድንሰባሰብና በደስታና በፍቅር እንድንገናኝ ላደረገው፤አንድዬና ብርቅዬ ልጃችን፤ወንድማችንና ፡አባታችን  ለሆነው የሰባዊ መብት ተሟጋች ፤አክቲቪስትና  አርቲስት ታማኝ በየን እረጅም እድሜና ጤና  ለእሱና ለመላው ቤተሰብ  እየተመኘው ጥቁር ሰው የሚለውን ዘፈን በታማኝ ስም አዳምጡልኝ በማለት ነው።                                                              በዕለቱ ስለ ነበረው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ትንሽ ነገር ልበል፤ፕሮግራሙ የሚፈለግበትን  አላማ አሟልቷል።  ማለትም የሚፈለገው ገንዘብ ማግኘት ነው አዎ  ገንዘቡ ተገኝቷል ።ቅድመ ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነበር ። አብዛኛው ሰው በተለያየ ኮሚቴ  ውስጥ በመግባት ያደረገው እርብርብ  በትንሹ የሚገመት አይደለም።በአስራ አምስት ቀን  እንዳይሞት ለምግብ ብቻ  የሚሰጠውን  900 ክሮነር በመቆጠብ ከተለያዩ ቦታ ለትራንስፖርት ወጪ በማድረግ  ለማረፊያ  እንኳን ሳይጨነቁ ባላቸው ጉልበት ለኢሳት ያላቸውን ፍቅር  በተለያዩ  ስራዎች ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ያደረጉ በካምፕ ያሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች በጣም ሊመሰገኑ ይገባል።                                                                                                                                                               የውያኔ ሰራዊት  ኢትዮጵያን  ከተቆጣጠረበት ጊዜ  አንስቶ  እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይና  እንግልት  የሚያሳይ ተመልካችን  በእንባ  ያራጨና  ወደ ኋላ  በትዝታ ወስዶ  ለካ  እንደዚህም ተደርጓል ብሎ ከልብ ያሳዘነ  በስደተኛው ተጽፎ የተዘጋጀ አጭር ተውኔት  ለዕይታ  ቀርቧል ።ተውኔቱን  የጸፉትም  ለምለም  ሀይሌ እና ያሬድ ኤሊያስ  ሲሆኑ  እንዳለ ጌታነህ ተውኔቱ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል ።በድራማው ላይ ሳላነሳ  ያማላልፋቸው እናት በመሆን  የተጫወቱት  ወይዘሮ መዓዛሽ መኮንን  እና ልጅ በመሆን የታጫወተው ያሬድ በትክክል ባህሪው  የሚፈልገውን  ካራክተር ከልብ በመጫወታቸው ሰውን በእንባ  አራጭተውታል። 
ከድራማው በኋላ ከታማኝ በየነ ጋር
                                                                                                                                                               ላልፈው  ወይም ልተወው የማልችለው ችግር ትንሽ ልበል ፤በርግጥ በትንሽ ወጪ ብዙ ብር  ማግኘት ቢሆንም አላማው ምንም አይሰራም ያልነው ሃሳብ ችግር ሲሆን አይተናል ምሳሌ  ፕሮግራምን በተመለከት፦የቅደም ተከተል ችግር ነበር።የድምጽም መሳሪያን በተመለከት፤ ዋናውና ሰው በአንክሮ ሊከታተለው የሚገባ የታማኝ ዝግጅትን በድምጽ ምክንያት ለመከታተል  ሲቸገርና ታማኝም በትክክሉባለማቅረቡ ሲበሳጭ በቅርብ ሁሉም ያየው ነው።ስራ ሲሰራ  ስተት  መፈጠሩ አይቀርም ጥሩ ትምህርት ሆኖ ያልፋል ግን ይህንን የተፈጠረውን ትንሽ ስህተት ቀድመን ስለተነጋገርን ቢያንስ ብንሰማማ ኖሮ  ችግሩ ባልመጣ ነበር ፤እንደዚ ዓይነት ብዙ ሰው የሚያሳትፍ ዝግጅት ሲኖር ቢያንስ ሙያው የሚመለከተውን ስራ ለሙያው ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ከተቻለ  ሀላፊነቱን መስጠት ካልተቻለ  ማማከር ተገቢ ነው ብዬ  አምናለው።ሃሳቡን እናንሳው እንጂ ዋናው ነገር በኖርዌ የምንገኝን ኢትዮጵያውያንን አንድ ያደረገ  ጥሩ ምሽት ሆኖ አልፏል።ላሁኑ ላብቃ  ሰላም ያገናኘን ደህና  ሰንብቱልኝ።ዝግጅቱን የኢሳት ቴሌቪዥን በቅኝት ፕሮግራሙ ላይ ያቀረበውን እየጋበዝኩኝ እሰናበታለው።ጽሁፉን በተመለከተ አስተያየት መስጠት ያለኝን ደካማ ጎን ማጎልበቻ  ስለሆነ እባካችሁ ። 

መረጃ ቁልፍ ነው። ቁልፉ ደግሞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን( ኢሳት) ነው።

 


NORWAY OSLO ESAT FUNDRAISING FEB.10 2013
የመልካም አስተዳደር እጦት፣ነፃነትና የፍትህ እጦት፣የነፃ ፕሬስ እትመት መታፈን ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች አባልና ደጋፊ በማሰር ፣ጋዜጠኞችን ማሰርና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ፣የውሸት ምርጫዎች መብዛት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የሥራ አጥነት መበራከት፣ የአግአዚ ጦር ሠራዊት እናየጆሮ ጠቢዎችበወገናችን የሚያደርሱት እልቂትና ስቃይ ሰለባ የሆናችሁና ነጻነትና ፍትህን ናፋቂ የሆንን ፣የአገራችሁ አንድነት የሚያንገበግባችሁ ዜጎች ሁሉ አሁን ወቅቱ የሚሻው የትግል ጊዜ ላይ በመሆናችን ለዚህ ሁሉ ደግሞ መረጃ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን የሕዝብ ብሶት የሚያሰማው የሕዝብ ሀብት የሆነውን ኢሳትን መርዳት ከዘመናዊ ባርነት፣ከውሸት ፕሮባጋንዳ ለመዳን፣የሕዝብ ብሶትንና በደልን ለማሳወቅ ትልቁ የመገናኛ መሣሪያ መሆኑን አያጠራጥርም! ኢሳት የማያጠያይቅ ቁልፍ መረጃ ነው።ለዚህ ደግሞ ኢሳትን መርዳትና መደገፍ የዜግነት ግዴታ ውዴታም ነው።የሕዝብን የስቃይ ግዜ ለማሳጠር ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ተደራጅተን መረጃዎችን ለኢሳት በመስጠት ሕዝባችን መታደግ አለብን።
ሀገሩንና ሕዝቡን የሚወድ ደግሞ ኢሳትን ይታደግ!

እውነት እንዲ ነው!! ”…እኔ አርቲስት ነኝ በአርቲስትነት መኖር እችል ነበር። መፅሐፉ የሚለው ከፊትህ እሳት ቀርቦልሃል እጅህን ወደወደድከው ጨምር ነው። እኔ እጄን ወደ ውሃ ከትቼ በአርቲስትነቴ እየደነስኩ መኖር አያቅተኝም ነበር። ነገር ግን የእውነት ጉዳይስ? የኢትዮጵያ ጉዳይስ? ዝም ብሎ የሚኖር ህሊና አለን?… እድሜዬ እንደምታዩኝ ላይሆን ይችላል። ፖለቲካ ያቃጥላል፣ ያናድዳል። ሆኖም ግን እስከመጨረሻ ለመፅናት ነው ቃል የገባሁት።አርቲስትና አክትቪስት ታማኝ በየነ
ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ነው !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ

Wednesday 13 February 2013



ጂሃዳዊ እርምጃን በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩት ሲጋለጡ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ሀገርኛ በሆነ መንገድ ከውስጥ በፈለቁ ጠላቶች ጉልበት የማፈራረስና ከካርታ የማጥፋት ሂደት ሴራ የተፈለገውን ያህል ውጤት ባያመጣም ሀገሪቱን ግን የሁዋልዮሽ እየጎተተ እንደሚገኝ ይታወቃል። ስለምን ብለው እኒሁ የኢትዮጵያ ልጆች እናታቸውን ለመግደል ሀገራቸውን ለማፈራረስ ተነሱ? ፍጻሜያቸውስ ምን ሊሆን ነው? የሚለው ጥያቄ ሁሉንም ሰው የሚያሳስብና የሚገርምም ነው። የፈለገውን ያህል ሚስጥራዊ ስራ ይሰራ፣ ምንም አይነት የጉልበት ጫና ይደረግ የፈለገውን ያህል የገንዘብና የመሳርያ ክምችት ይኑር ለውጥን ለቅጽበት ማገድ እንጂ ማቆም ከቶውኑም አይቻልም። አገር ለማፈራረስ ተነሱ የሚባሉትና ሀገር በማፈራረስ ከበሩ በሚባሉት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ይልቁንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቆርጦ ሊታገል የሚገባው ጎጠኛነት መሰረት ያደረገ ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ አውጆ ሀገር እያፈረሰ ያለውን የትግራይ ተገንጣይ ድርጅት ‘ጂሃዳዊ’ እርምጃን ሊሆን ይገባል።

ሰሞኑን ከተለያዩ ዜናዎች ላይ የተለቃቀሙ የፊልም ቅንጫቢዎችን አስፈሪ በሚመስል ሙዚቃ በማጀብ አንድና ሁለት አረፍተ ነገር ከታሳሪዎች ድምጽ በመቀነጫጨብ ለማጅ የሰራው ፊልም ውሸት በማይታክተው ኢቲቪ ለእይታ ቀርቦ ተመልክተናል። ይህንን "ተጨፈኑልኝ ላታላችሁ" ድርሰት ተመልክቶ የሳቀ እንጂ የተሳቀቀ ይኖራል ብሎ የሚያምን የለም። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን አሸባሪዎች በየጊዜው ቁልቁል የወረደ ነገር የሚያደርጉት መካከላቸው የነበሩ ጥቂት ሻል የሚሉ ሰዎች እንኳን አብረዋቸው ባለመኖራቸው መሆኑ በግልጽ እየታየ መጥቷል። እንደሁልጊዜውም የአምባገነን መንግስት ራሱን በልቶ የሚሞት ነውና፣ እራሳቸው አሸባሪዎቹ አሮጌ ሽፍቶች ሬሳ ሳጥን ውስጥ ሆነው የሰሩቱን ፊልም ማየት የሀገር ጉዳይ ግድ አስብሎን እንጂ የምርጫ ነገር ሆኖ አልነበረም። ጥንቆላና መተት በማሳየት ፊልም መስራት የጀመሩት የናይጄርያ ኖሊውዶች እንኳን እንዲህ ያለ ነገር አላደረጉም። ፍርድ ቤት ያለ ጉዳይ ውሀ አላነሳ ሲል በጉልበት ውሸት የሚጋተው የሀገራችን ሕዝብ ግን በጣም ያሳዝናል።

Monday 11 February 2013

አጭር ልብ ወለድ

የማይቀርበት ስራ እንዳለበት ሰው በጠዋት ተነስታ ከቤትዋ ወጣች፡፡

ፀሃይ ስትወጣ፡ ወፎች ሲዘፍኑ፡ አዲስ አበባ ከእንቅልፏ ስትነቃ ለመጨረሻ ጊዜ የምታይበት ቀን መሆኑን አስባ አልተከፋችም፡፡ ፀሃይ ምን አባትዋ! መሰረት የለችም ብላ ነገ እምቢ አሻፈረኝ አልወጣም አትል፡፡ አለመውጣት ቀርቶ አንድ ሰአት እንኳን አትዘገይም፡፡ ወፎችም እንዲህ የሚያባባ ዘፈን ሲዘፍኑ አይመስሉም እንጂ ገና በማለዳ ከዚህ አለም መሰረዝዋን ሲሰሙ በነጋታው ዘፈናቸውን በሙሾ አይተኩም፡፡ አዲስ አበባም ገደል ትግባ! “መሰረት ከሞተች አበባዬ ረግፏልና አዲስ አበባ አትበሉኝ” አትል፡፡ ሃዘን አያጠወልጋት፡፡ ለነገሩ ሕይወትዋን ሙሉ አዲስ አበባ እሾህ እንጂ አበባ ሆናላት አታውቅም፡፡

“ሕይወት አጭር ናት፡፡ ደስተኛ ሁኚ፡፡ “ይላት ነበር የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ቦይፍሬንዷ፡፡

እሱ ምናለበት! ገንዘብ አይቸግረው፡፡ ደስታ አይቸግረው፡፡ ደስታ ተርፎት “ደስተኛ ሁኑ” እያለ ለከፋው ሁሉ ያከፋፍል ነበር፡፡ እንደሱ ለተደሰተ ሕይወት አጭር ነት፡፡ እንደርሰዋ ከኑሮ ለተኳረፈ፡ አንደርስዋ ከጊዜ ረጅምና ማይበርድ ጠብ ውስጥ ለገባ፡እንደርስዋ ኑሮ የጉልበት ስራ ብቻ ለሆነበት፡ እንደርስዋ ሕይወት ረጅም ቅዠት ለሆነበት ሕይወት ረጅም ናት፡፡ ኑሮ ዘልዛላ ነው፡፡

ቦይፍሬንዷን ሰምታ ደስተኛ ሆና ሕይወት አጭር ናት ከሚሉት ለመመደብ ብዙ ወጣች፡ ብዙ ወረደች፡ ብዙ ተራመደች፡ ብዙ ሮጠች፡፡ ደስታ ስትደርስበት ከርስዋ እንደሚሸሽ ሁሉ የማትነካው፡ የማትደርስበት ህልም ሲሆንባት እንደነገሩ፡ እንደዋዛ በእርሳስ የተፃፈውን ይህን ቀለም አልባ ሕይወትዋ በሞት ላጲስ ልታጠፋው ቆረጠች፡፡

ዛሬ ሕይወቷን በጉልበት የምትቋጭበት ቀን ነው፡፡

እውነቱን ለመናገር ነገሩን ለሳምንታትና ለወራት ስትብሰለስለው አልቆየችም፡፡ እስከ ትላንት ድረስ እንደነገሩ፡ እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጌ እኖራለሁ ብላ ወደር በሌለው የግዴለሽነት መንፈስ መኖርን ተለማምዳው ነበር፡፡
ወደር በሌለው የግዴለሽነት መንፈስ ስትኖር ሲርባት ያኘችውን ከመብላት፡ ለመብላት ስትል ያገኘችውን ስራ ከመስራት፡ እንቅልፏ ሲጨቀጭቃት ከመተኛት ያለፈ ታላቅ የሕይወት ግብ አልነበራትም፡፡ መብላት፡ መስራት፡ መተኛት፡ የቀን ቀን አዙሪትዋ ይሄ ነበር፡፡

ትላንትና ግን በድንገት አዙሪቱን የረበሸ ነገር ተከሰተ፡፡

ለሳምንታት ራሷን ሲያማት ገርፏት የማይታክተው የኑሮ ጅራፍ ያመጣው ህመም ውጤት መስሏት ችላ ብላው ነበር፡፡
ለሳምንታት ወደላይ ሲላት የሚያቅራት ኑሮዋ በአፏ ለመውጣት እየተናነቃት መስሏት ከቁምነገር ሳትፅፈው ሰነበተች፡፡
ለሳምንታት በተለየ ሁኔታ አሁንም አሁንም ሲርባት “የምበላው ሳጣ…” ይሉት ተረት በዚህ እከካም እድሏ ምክንያት ልጅ እንኳን ሳይኖራት ደርሶባት መስሏት በለመደችው ግዴለሽነትና ውሃ በመጠጣት ታባርረው ነበር፡፡

ያቺ የማትወዳት የወር እንግዳዋ ለሁለት ወራት ሳትጠይቃት መክረሟ የተከሰተላት ዘግይቶ ነበር፡፡

ሲከሰትላት…
ላብ የማያውቃትን ክፉኛ አላባት፡፡
ትንፋሽ አነሳት፡፡
ለእንባ እንግዳ ያልሆኑት አይኖችዋ በታማኝነት አዳዲስ እምባ ዘረገፉ፡፡

“እኔ በግዴለሽነት መኖር እችላለሁ፡፡ ልጄ ግን አይችልም” ብላ ወሰነች፡፡

ያቺ የችግር ዘመድዋና ደባልዋ ጤና ጣቢያ ሂጂና አረጋግጪ አለቻት፡፡
ሄደች፡፡
ቀድማ ብታውቀውም ልጅ እየሰራች እንደሆነ ሃኪሙ ነገራት፡፡
እንደገና አላባት፡፡
ትንፋሽ አነሳት፡፡

ለአንባ እንግዳ ያልሆኑ አይኖችዋ የዘረገፉት ትኩስና ብዙ እምባዎች ወደ ማዲያታም ጉንጭዋ፡ አጭር አገጭዋ፡ ከዚያም ደግሞ ዘለው ወደ ጭኖችዋ ተከሰከሱ፡፡

“አትፈልጊውም?” ሃኪሙ ጠየቃት፡፡
“አትፈልጊውም?” ብሎ ጥያቄ ምንድነው…?
ልጅ እንዴት እንደሚገዛ እቃ አትፈልጊውም ይባላል…?ልጅ እንዴት አይፈለግም?
“እፈልገዋለሁ፡፡” እምባዋ አልቆመም፡፡
“ደስ ብሎሽ ነው ምታለቅሺው ታዲያ?”

በደስታ ይለቀሳል እንዴ…?ለለቅሶ የሚያደርስ ደስታ ምን አይነት ነው? አታውቀውም፡፡

“አልችልም፡፡ እኔ ልጅ ማሳደግ አልችልም፡፡ “ንፍጧን በሹረብዋ እጀታ ጫፍ እየጠረገች ተናገረች፡፡
“አሁን እፈልገዋለሁ አላልሽኝም እንዴ?”
“እፈልገዋለሁ ግን አልችልም፡፡ “
ሃኪሙ በአልገባኝም አያት፡፡

ሰው እንዴት ሃኪምን ያህል ነገር ሆኖ መፈለግን ከመቻል ያምታታል? ብላ አሰበች፡፡ ምናልባትም ሕይወት ካጠረባቸው ደስተኛ ሰዎች ይሆን ይሆናል፡፡

“አባቱ አብሮሽ ነው…?”
“አባቱ ውጪ ሃገር ነው፡፡ አይመለስም፡፡”
“ብታገኚው አይረዳሽም…?”
ሃኪሙ የሆነ ነገር እየሞነጫጨረ ጠየቃት፡፡
እንደስዋ ያለ ወደር በሌለው ግዴለሽነት የሚኖር ሰው ውጪ የሄደ የቀድሞ ቦይፍሬንድ ፍለጋ አይዞርም፡፡ ልክ አይመጣም፡፡

ብድግ አለችና
“አልችልም አልኩህ ዶክተር!”
“እሺ…እንደዛ ከሆነ እንግዲህ አማራጮች አሉ፡፡”
ብዙ ብሎ፡ ብዙ ዞሮ አንድ ቦታ ደረሰ፡፡ ልጅሽን ግደይው አላት፡፡

አሰበች፡፡

ለኑሮ ጉጉት የላትም፡፡ በራስዋ ላይ ሞት ማወጅን እስከዛሬ አስባው ባታውቅም በምክንያት የመጣ ሞት ላይ የከረረ ቅራኔ የላትም፡፡
ከጤና ጣቢያው ከወጣች በኃላ በየደቂቃው ውስጧ በማደግ ላይ ያለ ልጅዋን ከመግደል ራስዋን መግደሉ በአንፃራዊ ሁኔታ ሃጥያቱ ዝቅ ያለ መሰላት፡፡

ራስዋን ትገድላለች፡፡
እሷ ትሞታለች፡፡
እሷ በመሞትዋ ልጅዋ ይሞታል፡፡
እሷ ራሷን ገደለች እንጂ ልጅዋን አልገደለችም፡፡
የልጅዋ ሞት የእሷ ሞት አሳዛኝ ውጤት እንጂ ግድያ አይሆንም፡፡
ወሰነች፡፡


ልጅ ሆና ስትሰማ “እገሌ እኮ በአስር ሳንቲም ገመድ ተንጠልጥሎ ሞተ!” ይባል ነበር፡፡እንደሌላው ነገር ራስን ማጥፋትም ተወዷል፡፡ ከዛሬ ጋር ያለውን የጊዜ ልዩነት አስልታ “መቼም ቢጨምር ቢጨምር ከ5 ብር አይበልጥም፡፡ “አለችና ከፍራሿ ስር ያስቀመጠችውን ከታጣፊ አልጋዋ ውጪ በስሟ ያለ ብቸኛ ገንዘብዋን አወጣች፡፡ አስር ብሯን በግራ እዿ አፍናና ጨምድዳ ይዛ ወጣች፡፡
“ገመዱን ገዝቼ የሚተርፈኝን አምሰት ብር አምላክ ይቅር እንዲለኝ ለሚካኤል እሰጠዋለሁ” ብላ አሰበች፡፡ በአምስት ብር ገመድ የተሰራ ሓጢያትን የአምስት ብር ስጦታ ይፈታዋል ብላ፡፡

አብዲ ሱቅ ደርሳ ብታይ ማንም አልነበረም፡፡ በመስኮቱ አንገትዋን ገባ አድርጋ “አብዲ!” ብላ ተጣራች፡፡ አብዲ ሳይሆን አንድ አይታው የማታውቅ ትንሽ ልጅ ብቅ አለ፡፡
ቅር አላት፡፡

“አብዲ የለም እንዴ…?”
“የለም፡፡” ልጁ ፈጠን ብሎ መለሰ፡፡
ቢኖር ደስ ይላት ነበር፡፡ ከመሰናበትዋ በፊት ሁሌም እንደ ሙሉ ሰው በሙሉ አይኑ የሚያያትን፡ ሲቸግራት የሚያበድራትን፡ ሲከፋት የሚያስቃትን ፍልቅልቁን አብዲ ብታገኘው ደስ ይላት ነበር፡፡
“ገመድ አለ?” ከማቅለሽለሽ ስሜት ጋር ግብግብ ገጥማ ጠየቀችው፡፡

አውጥቶ ሰጣት፡፡
“ስንት ነው?”
“አስራ ሁለት ብር” አዲሱ ልጅ ከረሜላ ከገዛው ትንሽ ልጅ ብር እየተቀበለ መለሰ፡፡
“አስራ ሁለት…?”
ወደ ላይ አላት፡፡
ትንፋሽ አነሳት፡፡
እምባዋን ግን ገታችው፡፡

“አዎ አስራ ሁለት” ልጁ ከረሜላ ሲያወጣ መሬት የበተናቸው ማስቲካዎች ቦታቸው እየመለሰ መለሰላት፡፡
“እኔ…አስር ብር ነው የያዝኩት፡፡ አስር ብር ሽጥልኝ?” ተለማመነችው፡፡
“ዋጋው አስራ ሁለት ነው አልኩሽ እኮ!”

አስር ብር ስትለው፡ ዋጋው አስራ ሁለት ነው አልኩሽ ሲላት፡ አሰር ብር እንካ ስትለው ሁለት ብር ጨምሪ ሲላት አብዲ ብዙ እቃ ተሸክሞ ወደ ሱቁ ደረሰ፡፡
ደስ አላት፡፡

“አብዲ! “
“መሲዬ! “እቃዎቹን መሬት አስቀምጦ ጨበጣት፡፡
“ባክህ ይሄ ልጅ ይህን ገመድ አልሸጥልሽ አለኝ”
“ምነው አንተ…?!”ልጁ ላይ አፍጥጦ ጮኸ፡፡
“ለመሲ 10 ብር ነው” ብሎ ገመዱን ሰጣትና አስር ብሩን ተቀብሏት ለልጁ ሰጠ፡፡

ይህ አብዲ የሚሰራላት የመጀመሪያው ሳይሆን የመጨረሻ ውለታ ነበር፡፡ የገታችው እምባዋ ካልወጣሁ እያለ ሲታገላትና ስትመለሰው በአፍንጫዋ አድርጎ ወደ አፍዋ እየመጣ ጨው ጨው አላት፡፡
አብዲን ነገ እንደምታገኘው ሁሉ፡ ወግ በሌለው ሁኔታ ተሰናብታው ወደ ቤትዋ ተራመደች፡፡

ቤትዋ ስትገባ ደባልዋ የሰራችውን እህል ቅጠል የማይል ሽሮ እየተናነቃት በልታ ተኝታ እንደማታውቅ ተኝታ አደረች፡፡

ጠዋት…

የካ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ስትሳለም ለምትሰራው ሃጢያት ማሰረያ የምትሰጠው ገንዘብ ስላልተረፋት ግንቡን ተደግፋ ስቅስቅ ብላ አነባች፡፡
በቅቷት ሳይሆን መርፈዱ አሳስቧት ወደ ተራራው የሚወስደውን ቀጭን መንገድ ቀጠሮ እንደረፈደበት ሰው ተጣድፋ ወጣች፡፡
ዛፎች የበዙበትና ጭር ያለ ቦታ ስትደርስ ገመድዋን አውጥታ ጠንካራና በአጭር ቁመቷ የምትደርስበትን ዛፍ ፍለጋ ጀመረች፡፡
አገኘች፡፡

የምትቆምበት ትልቅ ድንጋይ ፍልጋ ሄዳ ይዛ ወደ ሞት ዛፏ ስትመለስ አብዲን አሰበችው፡፡

“በአንተ ገመድ ተሰቀለችና ሞተች!” ሲሉት ምን ይል ይሆን ብላ አሰበች፡፡
“ሁለት ብር ቀንሰህ በሸጥክላት ገመድ ተንጠልጥላ ላትመለስ ሄደች” ብለው ሲወቅሱት ታያት፡፡
ካወቀችው ጀምሮ እስከየመጨረሻው የህይወት ቀኗ ደግነት ያሳያት አብዲ ላይ የጨከነችበት መሰላት፡፡
“ምን አንቀዥቅዦ ከመርካቶ አመጣኝ…?ምናለ ትንሽ ዘግይቼ ቢሆን ኖሮ.!?.ምናለ አይቀንስም፡፡ አያዋጣም ብዬ በመለስኳት ኖሮ!” እያለ በነዛ እምባ በማያውቁ አይኖቹ ሳያቋርጥ ሲያለቅስባቸው፡ ሃዘን ሲያጎሳቁለው፡ ፀፀት ሲያንገበግበው ታሰባትና ለቅሶ ለቅሶ አላት፡፡

ለአብዲ ስትል ዛሬ ባትሞት ተመኘች፡፡
አብዲ እንዳያለቅስ፡ አብዲ እንዳያዝን: አብዲ እንዳይወቀስ ባትሰቀል ፈለገች፡፡
አቅለሸለሻት፡፡
ገመድዋን አንጠለጠለችበት ዛፍ ጋር ስትደርስ አንድ ጠመንጃ የያዘ ሰው ቆሞ አየች፡፡

ደስ ብሏት እንደማያውቅ ደስ አላት፡፡
hiwot