"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Thursday, 4 October 2012
ለኢትዮጵያ መንግስት ቢጫ ሊሰጠው ነው – ከአቤ ቶኪቻው
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሙስሊሙ ህብረተሰብ በየቀበሌው ሄዶ ምርጫ ላይ እንዲሳተፍ ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑ ታይቷል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “ምርጫችን በመስጂዳችን” የሚል እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት በዚህ ሰዓት፤ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “የታሰሩ ወንድሞቻችን ይፈቱ” ብለው እየጠየቁ ባለበት በዚህ ሰዓት፤ መንግስት ግን የመስማት ፍላጎቱ በመቀነሱ ሳብያ ሊሰማቸው አልቻለም። ሊሰማቸው ባለመቻሉም የታሰሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሳይፈቱ ምርጫውንም በቀበሌ አድርጎታል።
በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ ትልቁ ችግሯ “መናገር እንጂ መስማት አለመቻሏ ነው” ብለው ተናግረው ነበር። እኔ የምለው ይህንን ችግር የሚያክም አንድ እንኳ ባለሞያ ይጥፋ እንዴ!? ሌላው ቢቀር ባህላዊ መፍትሄ እንዴት ይጠፋል? እሺ ሌላው ይቅር በፀሎትስ ቢሆን ይህንን ህመም ለማስታገስ ጥረት መደረግ የለበትም ትላላችሁ!
ለማንኛውም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በነገው ጁምዓ ለመንግስት ቢጫ ሊያሳዩት እየተሰናዱ እንደሆነ መስማቴን አልደብቃችሁም። እንደሰማሁት ከሆነ በአርቡ የሶላት ጊዜ በተለያዩ መስጊዶች ቢጫ ቀለም ያለው ወረቀት ወይም ጨርቅ በመያዝ ማስጠንቀቂያው ለኢህአዴግ ተጫዋቾች ይሰጣቸዋል።
ይህንን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ስነ ስርዓት ክርስቲያን ወገኖችም ተሳታፊ እንደሚሆኑበት ሰምቻለሁ።
መንግስቴ ግን ይሄን ሁሉ የእልህ ጨዋታ እና ተደጋጋሚ “ፋዎል” መስራት ለምን እንደፈለገ ሊገባኝ አልቻለም። እስቲ የገባው ግራ ለገባው ያስረዳ!
የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ?
እ.አ.አ በ1997 በጨረታ ወደ ግል ንብረትነት ተዛወረ የተባለው የኢትዮጵያውያን ሀብት የተሸጠው 172 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ሽያጩ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ሽያጩን ተከትሎ በርካቶች አርረዋል፤ ተቃጥለዋል። “ዋይ ዋይ ወርቃችን” ብለው አንብተዋል። ህዝብ የፈለገውን ቢል ደንታ የሚሰጠው አካል ስለሌለ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ እጅ በአዋጅ ተነጠቀ።
ሽያጩን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን አሊ ሲሆኑ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ አሰፋ አብርሃ የኤጀንሲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ። ሁለቱም ባለስልጣናት ዛሬ ሃላፊነት ላይ የሉም። ስለ እውነትና ስለ አገር ሲሉ የሚያውቁትን ለመተንፈስ እስከዛሬ ቢጠበቁም ያሉት ነገር የለም። ሃሰን አሊ ሲኮበልሉ፣ አቶ አሰፋ አብርሃ ከወንድማቸው ጋር በሙስና ተወንጅለው የወህኒ ቤት ጊዜያቸውን አጠናቀው እየኖሩ ነው።
ምዕራብ ሃረርጌ አሰበ ተፈሪ መምህር የነበሩትና ኢህአዴግን መንገድ ላይ የተቀላቀሉት ሀሰን አሊ ካገር መኮብለላቸውን ተከትሎ የተለያዩ መረጃዎች ይወጡ ነበር፡፡ በርካቶች ጉዳዩን ከኦነግ ጋር ቢያያይዙትም “ካገር ውጡ ተብለው፣ ሀብትና ንብረት ተዘጋጅቶላቸው ኮብልለዋል” የሚል መረጃ ለባለስልጣናትና ለባለሃብቱ ቅርብ ነን ከሚሉ ወገኖች እንሰማ ነበር። በወቅቱ ኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ በነበረኝ ሃላፊነት ሳቢያ ከሰማኋቸው መረጃዎች ውስጥ ሃሰን አሊ “ውጡ” ተብለው እንደ ኮበለሉ የሰማሁት መረጃ ካለኝ ሃላፊነት ጋር ተዳምሮ እንዳጣራው ወሰንኩና ጊዜ ሰጥቼ አነፈንፍ ገባሁ።
የሌሎችን ባላውቅም እንደ ኦሮሞነቴ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ውድ ንብረት ለሼኽ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ መሸጡ ሁሌም ያንገበግበኛል። ሽያጩን አስመልክቶ የተለያዩ ጽሁፎች ቢወጡም እኔ ካሰባሰብኩት መረጃና እውነት ጋር የሚመጣጠን መስሎ ስላልታየኝ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለመተንፈስ ወሰንኩ።
ሼኽ መሐመድ አላሙዲና ሃሰን አሊ እንዴት ተዋወቁ?
ሼኽ መሀመድ አላሙዲና ሀሰን አሊን እንዳስተዋወቃቸው የነገረኝን ሰው ባንድ አጋጣሚ የማወቅ እድል አጋጥሞኝ ነበር። ተግባሩ ብዙም ደስ ስለማያሰኝ ፊት እነሳው ነበር፡፡ ባለስልጣናትን በገንዘብ እየደለለ ሲሰርቅ ብዙ ጊዜ ስለማውቅ አልወደውም ነበር። የራሱን ትልቅነት ለመግለጽ ድንገት ቢሮዬ በመጣበት ወቅት የነገረኝ ፍንጭ ትዝ ሲለኝ ላገኘው ወሰንኩ። ይህ ሰው ባለኝ ሃላፊነት እንደፈለገኝ ላገኘው ስለምችል፣ እሱም ለሚሰራው ድለላና አየር ባየር ንግድ እኔ ከፈለኩት ቅር ስለማይለው ፊት ነስቼው ያቋረጥኩትን ግንኙነት እንደገና መቀጠል ብቸኛ አማራጬ ሆነ፡፡ይህን ሰው ከተጠቀሙበት በኋላ ወርውረውት በነበረበት ወቅት ላይ ስላገኘሁት የፈለኩትን ለማግኘት አጋጣሚው ተመቻቸልኝ፡፡
ቀደም ሲል ሃሰን አሊን ያውቃቸው እንደነበር፣ አብረው ሃድራ እንደሚያሞቁ፣ የፈለገውን ነገር ማድረግ ከፈለገ ሃድራው በሚሞቅበት ወቅት እዛው በሙቀት እንደሚያከናውኑ አውግቶኛል። ለዚህ ጽሁፍ ስለማይጠቅም እንጂ በርካታ ታላላቅ ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ ሳይሆን በተፈረሸ መደብ ላይ እንደሚከናወን በስፋት ስም እየጠቀሰ ነግሮኛል። እንግዲህ ይህ ሰው የ“ባለሃብቱ” ወዳጅ ነበር። ለዚያውም የመጀመሪያ!
በዚሁ ሽርክናቸው ሰውየው ሃሰን አሊን መተዋወቅ እንደሚፈልጉ ባሳወቁት መሰረት ሃሰን አሊን በመያዝ ሳር ቤት አካባቢ አገናኛቸው። ባለሃብቱ በወቅቱ ብዙም የሚያውቃቸው ባልነበረበት ወቅት ሃሰን አሊን አስቀድመው ተወዳጁ። በመኖሪያ ቤት ሃድራ ላይ የተመሰረተው ወዳጅነት ጠበቀ። በኦሮሚያ በኩል አድርገው ዋናውን ሳሎን ወረሱ።
ሀሰን አሊ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነታቸው ለቀው ስደትን ለምን መረጡ?
Wednesday, 3 October 2012
በጠ/ሚ/ር አሰያየም ላይ የታመሰው ኦሕዴድ ባለስልጣኖቹን ሊያንጓልል ነው
በዘሪሁን ሙሉጌታየኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው።
ከቴዲ አፍሮ ሠርግ ጀርባ፣ …..እንባ እና ሳቅ
ምንም ጣጣ ሣላበዛ፣ የወጌን ርዕሠ ጉዳይ ልንገራችሁ፤ በዕለተ ሀሙስ፣ መስከረም 17 ቀን 2005 ዓ.ም ስለተከበረው የመስቀል በዓል እንዳይመስላችሁ፤ በዚሁ ዕለት በሒልተን ሆቴል ስለተካሄደ የቴዲ ሠርግ ላወጋችሁ ነው፡፡ እናሣ ታዲያ፣ “ሠርግ የዘፋኝም ሆነ የንጉሥ ያው ሠርግ ነው፤ ባታወጋን ምን ሊቀርብን…” እንዳትሉኝማ – አደራ፡፡ እኔም ብሆን የታዋቂውን ዘፋኝ ሠርግ ከመነሻ እስከ መጨረሻ የመዘከር እቅድ የለኝም፡፡ ባይሆን፣ በሠርጉ ላይ በእቅድ ከተከናወኑ ጥቂቱን፣ ያለ እቅድ በሞቅታ ከተከናወኑት ደግሞ ጥቂቱን ላጫውታችሁ ከጅዬ ነው፤ እናም አያቴ “ሲውጥ ይሥቅ” የሚል አባባል ነበራት፤ ሀበሻን ለመግለፅ ይመሥለኛል፤ ካልበላ ያኮርፋል አይነት የጀርባ ፍካሬ ቢጤም ሊወጣለት ይችላል፡፡ ለመዋጥ ወይም በመዋጥ ለከት ካልተበጀ፣ ለመሣቅም በመሣቅም ያው ነው – ለከት ይጠፋል ማለቴ ነው፤ እስኪ ይሁን … ሠርጉን እንደ ገጠር ሙጌራ (ዳቦ) እያገለባበጥን፣ አንደዜ የፊለፊቱን፣ አንደዜ የጀርባውን፣ አንደዜ ገጠመኞቹን አሊያም ግጥመኞቹን እናውጋ፡፡
ከኋላው መጀመር አሠኘኝና ጀመርኩ፡፡ “ቴዲና ኤሚ” ከደርዘን ያለፉ ሚዜዎቻቸውን አስከትለው፣ ከክብር ወንበራቸው ተነሡ፤ የመሠናበቻ ሙዚቃ አዳራሹን እየናጠው ነው፡፡ ቴዲን ለመሠናበት አንዳንድ ፊታቸው ለኢትዮጵያዊው ምታተመስኮት (ኢቴቪ) አዲሥ ያልሆኑ፣ ሞንዳላ እንስቶች፣ በሱፍ ጢቅ ያሉ ጐልማሣና አዛውንቶች ወደ መድረኩ ቀረቡ፡፡ በተለይ ሙሽሮችን በምስል ለመቅረፅ፣ ዘመነኛ ሞባይላቸውን እንደ መሥቀል ችቦ ሽቅብ የወጡ እጆች አቤት መብዛታቸው!? “ሴኪዩሪቲ” የሚል የእንግሊዘኛ ጥሁፍ ሠፋፊ ደረታቸው ላይ የለበጡ፣ በደህናው ቀን ደንዳና ሠውነት ያበጁ ጠብደሎች “ማነው ወንድ ቴዲን እስከ ልዕልቱ የሚጨብጥ!” ብለው ቀውጢ ፈጠሩ፤ ሳይሞቅ፣ ሳይቀዘቅዝ እንደው ግርግር ተፈጠረ፡፡ ከአዳራሹ ወጥቶ እያለ አንድ አስጨፋሪ አንድን ጨፋሪ ወደ ግድግዳው አስጠግቶ በጥፊ ጋጋው! ወቾ ጉድ አልኩኝ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ዩ-ቲዩብ እና ፌስ ቡክ ተዘጋ ;ኢንተርኔት መጠቀም በግቢው ውስጥ ተከልክሏል
October 2, 2012 · 0 Comments
እንደ ደረሰን መረጃ መሰረት በትምህርት ተቋም ውስጥ የተከሰተው ይኸው የኢንተርኔት መታገድ ምክንያት ባለፈው በማለዳ ታይምስ ላይ ተሰርቶ የነበረውን ዜና አስመልክቶ አስተዳደሩ ስለተናደዱ ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩ መምህራን ለማለዳ ታይምስ ጠቁመዋል ።በግቢው ውስጥ ለምተገኙ መምህራን እና ተማሪዎች የተዘጋውን ዌብሳይት ለመክፈት ይህንን ሊንክ http://pray3.com/ በመፈለጊያ ቦታው ላይ በማስቀመጥ ፈልግ ብላችሁ ፣እንዳይዘጋባችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ትብብሩን ያደርጋል ፣ለዚህም ሊንክ እንደ ገና ከተዘጋባችሁ ሌላ ተያያዥ ሊንኮችን በመቀያየር መክፈት የምትችሉ መሆኑን እንጠቁማለን ።
በተዘጋው የኢንተርኔት መጠቀምን አስመልክቶ ብዙዎችን ሰራተኞችን ተማሪዎችን እና ሌሎችንም የአስተዳደር አካላትን ያስቆጣ መሆኑን ሲጠቁሙ ፣በማደግ ላይ ያለ ተቋም ከሚባሉት ተርታ ሳይመደብ ትልቅ ተቋም ነው እየተባለ የሚወራውን ይህንን ተቋም የመረጃ ነጻነት እና የአገልግሎት እጥረት የተማሪውን የመማር አቅም የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ የወደፊት እራእያቸውን የሚያቀጭጭ ነው ሲሉ መምህራኑ አስተያየታቸውን ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል።ይህ ደግሞ የ እኛን የመምህርነት ምግባር በትክክል እንዳንሰራ የሚያግደን እና ነጻነታችንን ጭምር የሚጋፋም ነው ብለዋል ።በተለይም የተለያዩ ምርምራዊ ስራዎችን ለመስራት እና ዋቢ መጽሃፍትን ከተለያዩ ቦታዎች በአጭር ጊዜ ለመፈለግ እና እውቀትን ለተማሪዎቻችን መመገብ የሚገባንን ሁሉ ለማድረግ ያግደናል ይህ ግን የነጻነት እና የመናገር እንደዚሁም የሰውልጅ መብትን ሁሉ የሚጋፋ ነገር ነው ሲሉ ገልጸዋል።በዚሁ ሁኔታ መምህራኖች የጋራ አቋም መግለጫ ወይንም የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ በጥረት ላይ መሆናቸውን ምንጮቻችን ለማለዳ ታይምስ ዘግበዋል።
በሌላም መልኩ በገለጹት መረጃ መሰረት አስተዳደሩ በሙስና የተጨማለቀ እና እንዲሁም ከመለስ አስተዳደር ጋር አጣብቂኝ የነበራቸው ሰዎች ዛሬም ከአማራ ክልል መንግስት ጋር እና እንዲሁም የወያኔ ኢሃዴግ አስተዳደርን የሙጥኝ ብለው የጥቅማቸው መሳሪያ ያደርጉት መምህራን እና አስተዳደሮች የጎንደር ዩኒቨርሲትይን የልዩ ጥቅም ቤታቸው አድርገው ከመሰረቱት ቆይተዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአጠቃላይ ለተለያዩ ሃገራዊ ክብረ በአሎች መሰጠት የሚገባው ክብር ቀርቶ ለግንቦት ሃያ የሚሰጡት ክብር እና ዝና ከምንም በላይ ነው በ እለቱ የሚሰጣቱት መዋእለ ነዋይ እጅግ ውድ ከመሆኑም የተነሳ የዩኒቨርስቲውን በጀት የሚያራቁት እንደሆነም አክለው መምህራኑ ገልጸዋል
Tuesday, 2 October 2012
መሀሙድ አህመድ በብሔራዊ ቲያትር ተረሳሾ ወይ የተባለውን ተወዳጅ ዜማ ለህዝብ ሲያቀርብ በ1992 ዓ ም
Sunday, 30 September 2012
ከሰሞኑን ካራቆሬ አካባቢ የተከሰተው ዘግናኝና አሳዛኝ ክስተት
ከአካባቢው የተገኘ ዜና ነው። ባለ ታሪኩ ሙስሊም ሲሆን ካራ አካባቢ የሚኖር የመንግስት ካድሬ ነው። እከሌ ቀረ በማያስብል ደረጃ ባካባቢው ሚኖሩ ንፁሀን ሙስሊም ወንድሞቹን ለቀበሌ ስልጣንና ለብር ሲል አስለቅሞ ጨርሷቸዋል። ነገሩ በጣም ያሳሰባቸው ያካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ሰውየውን በፀባይ ከመምከር አልቦዘኑም። እሱም በተቃራኒው ሙስሊም ወንሞቹን የፖሊስ እራት ማድረጉን ተያያዘው በስተመጨረሻም የሰውየውን ግፍ መሸከም ያቃታቸው ሙስሊሞች በለሊት በሩ ላይ የመጨረሻ ማጠንቀቂያ ለጠፉለት። ከዚህ ድርጊቱ ማይቆጠብ ከሆነ ዱአ እንሚያረጉበት የሚያስጠነቅቅ አጭር መልክት ጻፉለት።
ሰውየው ግን ማጠንቀቂያውን ከቁብም አልቆጠረው አሁንም ቀጠለ…..ቀጠለ……ቀጠለ። ታዲያ ይሄኔ ነው እጅግ አሳዛኙና ዘግናኙ ክስተት የተከሰተው። የባለታሪኩ የ 12 አመት ታዳጊ ሴት ልጁ ከቤት ከተሰወረች ቀናቶች ያልፋሉ። በክስተቱ በጣም ያዘኑት እኚው ምስኪን ሙስሊም ነዋሪዎች ልጅቱን ደከመኝ፤ ሰለቸኝ ሳይሉ ያፈላልጓት ጀመር። በመጨረሻም ልጅቷ ተገኘች። ይህች ያባቷ ሰለባ የሆነችው ምስኪን ልጅ ግን እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ ላይ ነበር የተገኘችው። ሁለቱም አይኖቿ ተጎልጉለው ወጥተው፤ ግማሽ የፊት አካሏ ወድቆ ልቦቿ ተሰንጥቀው፤ ኩላሊቶቿ …እረ ምን ቀረ እንዲህ በሚያዝን ሁኔታ ላይ ነበር ወንዝ ውስጥ ወድቃ የተገኘችው። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን እስኪ ላፍታ እንኳን ራሳችሁን የዚች አሳዛኝ ልጅ ወላጆች አርጋችው አስቡት ምን ያህል የዘላለም ፀፀት እንደተሸከሙ?
አሁን ቢሆን እናንተ … ይሄን አረመኔ መንግስት ተማምናችው ታላቁን ፈጣሪያችንን አላህ (ሱ.ወ) ክዳችውና ዲናችውን በገንዘብ ሽጣችው ያላችው በተለይ በተለይ ሙስሊም ካድሬዎች በአላህ (ሱ.ወ) የበላ ጎር ውስጥ ከመጥለቅለቃችው በፊት ወደአላህና ወደ ዲናችው ተመለሱ ሚለው ደሞ የኛ የመጨረሻ ማጠንቀቂያ ነው፡፡
የተበዳይን ዱአ ተጠንቀቁ የተበዳይ ዱአ ከልካይ ሂጃብ የለውምና. ረሱል (ሰ.ዓ.ወ)
የተበዳይን ዱአ ተጠንቀቁ የተበዳይ ዱአ ከልካይ ሂጃብ የለውምና. ረሱል (ሰ.ዓ.ወ)
Ethiopia’s Genocide of the Ogadeni Continues
Posted by quatero | September 28, 2012 |
The genocide in the controversial Ogaden region, a territory comprising the southeastern portion of the Somali Regional State in Ethiopia, has continued with a massacre of 17 and missing of 14 Ogadenis.
Hassen Abdulahi, the representative of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), the rebel group fighting with the Ethiopian government seeking for more autonomy for the underdeveloped Somalia region, said: “On September 3, 2012 Ethiopia’s government troops collected 31 people in Korelie Kebele, Deniese Woreda, Wardier Zone and killed 17 of them and took the rest 14 to an unknown place accusing of supporting the ONLF”
He said no one knew where 14 of the people were. Here, many are arguing that the missing people would be killed somewhere else.
“It is a usual phenomena that the Ethiopia’s troops commit a massacre on innocent people, Hassen Abdulahi said, “but what makes the current one so special is that its victims are prisoners, women and old enough people as well as a child aged seven.”
የሳውዲ አረብያ መንግስት ኢትዮጵያን ከሀጂና ኡምራ ጉዞ አገደ
ኢሳት ዜና:-የሳዑዲዓረቢያ መንግስት ኢትዮጵያን ከሐጂና ዑምራ ጉዞ በድንገት ማገዱ ሙስሊሙን ኀብረተሰብ ማስደንገጡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋገጡ፡፡
በየዓመቱ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለሐጂ ጸሎት ወደ ሳዑዲዓረቢያ የሚያደርጉት ሃይማኖታዊ ጉዞ የአረፋ በዓል ሊደርስ አንድ ወር ሲቀረው ጀምሮ የሚከናወን መሆኑን አስታውሰው ዘንድሮም በሙስሊሙ ኀብረተሰብ አመኔታ ያጣው የኢትዮጵያ እስልምና ም/ቤት(መጅሊስ) ጉዞውን እንደሚያስተባብር ማስታወቂያ በይፋ አስነግሮ የነበረ ቢሆንም የሳዑዲ መንግስት ግን በተለየ ሁኔታ ኢትዮጵያን ከጉዞው ማገዱን አስታውቋል፡፡
የሳዑዲ መንግስት ለምን ይህን እርምጃ እንደወሰደ በይፋ የገለጸው ነገር ስለመኖሩ እንደማያውቅ የጠቀሰው ምንጫችን እየተነገረ ያለው ምክንያት ግን ከሙስሊሙ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ በመጅሊሱ ወይም በእስልምና ምክር ቤቱ ላይ እምነት በማጣቱ ሳይሆን እንደማይቀር ጠቅሰዋል፡፡
ጉዞውን አስተባብራለሁ በሚል ከሙስሊሙ ኀብረተሰብ ገንዘብ እየሰበሰበ የነበረው መጅሊስ የጉዞው እገዳ ከተሰማ በኃላ ገንዘባችንን መልስ በሚል ጥያቄዎች መወጠሩ ታውቋል፡፡
እንደምንጫችን ዘገባ በሐጂና ዑምራ ጉዞ በየዓመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በነፍስወከፍ እስከ40ሺ ብር በመክፈል እንደሚጓዙ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ አረብያ መንግስት ኢምባሲ ተወካይ ጋር በጋራ ይሰራሉ ያላቸውን የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩን የአቶ ጁነዲን ሳዶን ባለቤት ማሰሩን በይፋ አስታውቆ ነበር። ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶም ለመገናኛ ብዙሀን በበተኑት ወረቀት ባለቤታቸው ከሳውዲ አረብያ ኢምባሲ ጋር ያላቸው ግንኙነት እናታቸውን ከመሞታቸው በፊት በአርሲ የሚገኝን መስጊድ እንዲያሰሩ አደራ ብለዋቸው ስለነበር፣ በዚያ መሰረት ከሳውዲ ኢምባሲ ያገኙትን እርዳታ ለመቀበል ባለቤታቸው ወደ ኢምባሲ እንደተመላለሱ እንጅ የሙስሊሞችን ተቃውሞ በመደገፍ አለመሆኑን ገልጠዋል።
መንግስት የሙስሊሞችን ተቃውሞ ለማቀጣጠል ገብተዋል ያላቸውን ሶስት የሳውዲ አረብያ ዜጎችን ከአገር ማባረሩም ይታወሳል።
የመንግስትን እርምጃ ተከትሎ ይመስላል ሳውዲ አረብያ ፣ የመንግስት ደጋፊ በሆነው መጅሊስ አስተባባሪነት የሚካሄደውን የሀጂና ኡመር ጉዞ ለመሰረዝ የወሰነው።
የሳውዲ አረብያ መንግስት የወሰደው እርምጃ ምናልባትም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱን የሚያመላክት ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች። ሳውዲ አረብያ በቱጃሩ በሼክ ሙሀመድ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ አፍስሳለች።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሪዎቻቸው ታስረውም እንኳ ተቃውሞአቸውን አላቆሙም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ህዝብ በሚውልባቸው ቦታዎች የሀይማኖት መዝሙሮች እንዳይሰሙ እንዲሁም የሀይማኖት ጥቅሶች እንዳይለጠፉ የሚከለከል አዋጅ ሊያወጣ ነው።
በታክሲዎች፣ ሆቴሎችና መናፈሻ ቦታዎች የሀይማኖት መዝሙሮች አይደመጡም። እንዲሁም በመንገዶች ላይ የሚደረጉ ሀይማኖታዊ ስብከቶች ይታገዳሉ።
መንግስት ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳው በአገሪቱ ውስጥ እየታየ የመጣው የሀይማኖት አክራሪነት ስጋት ላይ ስለጣለው መሆኑ ታውቋል።
ንግድ ባንክ ለሼክ አል አሙዲ ፈቅዶት የነበረው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር ታገደ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በቅርቡ ለሼክ መሐመድ አል አሙዲ የፈቀደው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲታገድ መወሰኑን የንግድ ባንክ ምንጮች ገለጹ፡፡ ንግድ ባንክ ይህን ብድር ለመስጠት ሲስማማ የማበደር አቅሙን አልፈተሸም፣ ዘንድሮ ከባንኩ ብድር የሚፈልጉ እንደ ስኳር ፕሮጀክቶች የመሳሰሉ የመንግሥት የልማት ዕቅዶች የብድር ፍላጎት በአግባቡ አልተጤነም፣ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ለአንድ ተበዳሪ ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑ ስለታመነበት፣ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መንግሥት መወሰኑን እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ተበዳሪው ሼክ አል አሙዲ ብድሩን ለመውሰድ ጥያቄ ያቀረቡት ለአፍሪካ ኅብረት ለሚያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃ ሊፍት መግዣና መግጠሚያ ነው፡፡ ብድሩም በቀጥታ ሊሰጥ የታቀደው ሊፍቱን ለሚያስመጣው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ለተባለው ሌላኛው የሼክ አል አሙዲ ኩባንያ ሲሆን፣ ንግድ ባንክ ለሊፍቱ ማስመጫ ራሱ ኤልሲ ከፍቶ ኮሚሽን ከማግኘት ይልቅ፣ በኤልሲ ኮሚሽን የሚያገኘውን ገቢ ትቶ በቀጥታ ለኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ብድሩን ለማስተላለፍ መምረጡ፣ የብድር ክፍል ሠራተኞችን ያስገረመ ጉዳይ እንደሆነ የባንኩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለሼክ አል አሙዲ ኩባንያዎች 942 ሚሊዮን ብር ብድር መፍቀዱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ብድሩ የፀደቀው ሚድሮክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለሚገነባው የአፍሪካ ኅብረት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃና ለማያ ፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ግንባታ ነው፡፡ ለአፍሪካ ኅብረት ሆቴል ሕንፃ ማጠናቀቂያ 850 ሚሊዮን ብር ተፈቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ለከረጢት ፋብሪካው ግንባታ ደግሞ 92 ሚሊዮን ብር ነበር ቦርዱ ያፀደቀው፡፡ ለብድር ማስመለሻ የተያዙት ዋስትናዎች (ኮላተራልስ) እየተገነቡ ያሉት የሆቴል ሕንፃና የከረጢት ፋብሪካዎች ነበሩ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)