"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 5 January 2013

በኬንያ ስደተኞች ከተማ ልቀቁ ተባሉ ኢትዮጵያውያኑ እንታፈናለን ብለው ሰግተዋል


ወቅቱ 2003 አጋማሽ ላይ ነው። ሁለት የኢህአዴግ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ናይሮቢ ይገባሉ። በናይሮቢ አድርገው ወደ ሌላ አገር ለመኮብለል ጊዜያዊ ማረፊያ መጠነኛ ሆቴል ይከራዩና ለሁለት አንድ ላይ ያርፋሉ። አንደኛው ከሰዎች ጋር ቀጠሮ እንዳለው አስታውቆ ወደ ጉዳዩ ይሄዳል። ቀጠሮው ቦታ ቆይቶ ለጓደኛው ስልክ ሲደውል “እንዳትመጣ፣ ጓደኛህን ከተኛበት ገብተው የማይታወቁ ሰዎች ወስደውታል” የሚል መልዕክት ይደርሰዋል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለጓደኛው ሰምቶ አያውቅም። እሱም አገር ቀይሮ በስደት በመንከራተት ላይ ይገኛል።
ኬንያ ሶስት ዓይነት ስደተኞች አሉ። በኢኮኖሚ ድቀት የዕለት ጉርስ ፍለጋ የሚሰደዱ፣ በፖለቲካ ሳቢያ ኢህአዴግን ሽሽት አገር ለቀው የወጡ፣ በኢህአዴግ ልዩ ተልኮ ስደተኛ መስለው ኬንያ የሚኖሩ፤ ከናይሮቢ በስልክ ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ወገኖች እንደደሚሉት በየጊዜው እየታፈኑ ወደ አገርቤት የሚላኩ ጥቂት አይደሉም። ይህ የሚሆነው ደግሞ በኬንያ ውስጥ ኢህአዴግ እጀ ረጅም በመሆኑ ነው። በዚህም ሳቢያ ለፖለቲካ ስደተኞች እያንዳንዷ ቀን የሰቀቀን ነች። ራስን የመጠበቅ!!
የኬንያ መንግስት “ለደህንነቴ ቅድሚያ” በሚል ሰሞኑንን ያስተላለፈው መመሪያ በስደት ናይሮቢ የሚኖሩትን ወገኖች ያስደነገጣቸውም ለዚሁ ነው። በኬንያ የሚኖሩ ስደተኞች ከተማ ለቅቀው ወደ ካምፕ እንዲገቡ በተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት መመሪያው የሚመለከታቸው ኢትዮጵያዊያን የመፍትሄ ሃሳብ የላቸውም። ግን ጭንቀታቸውን ለማሰማት ያህል ይናገራሉ።
በናይሮቢ የዓለም የስደተኞች ኮሚሽንን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ካሉት ስደተኞች መካከል አንዱ ብርሃኑ በየነ ይባላል። በዝዋይ ማረሚያ ቤት ታስሮ ተገርፏል። እሱ እንደሚለው የኬንያ መንግስት ሁሉንም ስደተኞች ባንድ መነጽር ሊመለከት አይገባም። በጅምላ ከዘጠኝ አገሮች ተሰድደው ኬንያ ለገቡት ጥገኝነት ጠያቂዎች በግል የፋይል ቁጥራቸው ወደ ካምፕ እንዲገቡ መመሪያ ተላልፏል።

የባለ አእምሮ ሥራ እንሥራ




ቀሲስ ስንታየሁ አባተ
በግብፅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወኪል

ይኽን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሣኝ ነገር በቅርቡ ቤተ ክርስቲያናችንና አባቶቻችን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን አስመልክቶ በተለያዩ የጡመራ ዐውዶች የሚለቀቁ ጽሑፎች ናቸው። እነዚህን ጽሁፎች ትክክል ናቸው ወይም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን አባቶች አስመልክቶ እየተባለ ያለው ነገር ትክክል ነው ወይም ሐሰት ነው ለማለት አይደለም፡፡
በመሠረቱ ሰው የመሰለውንና ያመነበትን ሐሳብ የማቅረብ መብት አለው። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቸረው የነጻ ምርጫ ፈቃድ አለውና ነው። ይኽን መብቱን ተጠቅም ይኽን ወይም ያንን ደግፎ ወይም ነቅፎ መናገር ይችላል። በሚናገርበት ወይም በሚጽፍበት ወቅት ግን ያ ሐሳቡ በእውነተኛ መረጃ ላይ ስለ መመስረቱ እርግጠኛ መሆን አለበት። እርግጠኛ ካልሆነ ግን ራሱን አሳስቶ ሰሚውንም ሆነ አንባቢውን ሊያሳስት በዚህም ለባልንጀራው መሰናክል ስለ ፈጠረ በእግዚአብሔር ዘንድ ይጠየቃል።

ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሰዎች ስለሚናገሩት ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን የሚጠየቁ መሆናቸውን አስተምሯል። ከንቱ ነገርም ለሰሚውም ሆነ ለተናጋሪው አንዳች ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕይወት ጠቀሜታ አልባና እውነተኛነት የሌለው ነገር ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ “አትግደል” በሚለው ትእዛዘ እግዚአብሔር ላይ በሰጡት ማብራርያ አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ሐሳብን በነጻነት ሆነው በጽሑፍ የመግለጥ መብት ተጠቅመው የብዙዎችን ስም በማጉደፍና ገመና በመግለጥ ቅስምም በመስበር መግደላቸውን ገልጠዋል።
ባለፈው ሳምንት በአንዱ የጡመራ መድረክ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያናችንን ሁኔታ ማለት የሽምግልናውንና ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ እየተደረገ ያለውን አንዳንድ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ተቃውሞአቸውን የሚገልጡትን ወይም የገለጡትን ተቃውሞ መልሰው የሚቃወሙትን በቃለ እግዚአብሔር አስታኮ በማሸማቀቅ ሕዝቡ አንዳች እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ በጸሎት ብቻ ችግሩ ይፈታል ብሎ እጁንና እግሩን አጥፎ እንዲቀመጥ የሚያደርጉ ለዚህም የተደራጁ አካላት መኖራቸውን ሳነብ እጅጉን ገርሞኝ ነበር።
ይኽን ጽሑፍ የጻፈው አካል የመጻፍ መብቱ የተጠበቀ ነው። ግን ፀሐፊው እንደገለጠው ይኽን ለማድረግ የተደራጀ አካል ለመኖሩ ምን ያኽል ርግጠኛ ነው? በትክክል እንደ ተባለውም ያ ተደራጀ የተባለው አካል ካለ ቃለ እግዚአብሔርን የራስን አመለካከት ማሳኪያ አድርጎ በመውሰዱ ከፍርድ ሊድን ይችላልን? ይኽን የተሳሳተ መንገድ እንደ በጎ አካሄድ አድርገው የሚጠቀሙ አንዳንድ ግለሰቦች ቢኖሩ እንኳን ያን ያክል ቦታ ሰጥቶ እንደ አንድ የተደራጀ ቡድን ወይም አካል አግዝፎ በጡመራ መድረክ ላይ መግለጡ ራሱ ለእኔ እንዲህ ዓይነቱን አካሄድ ላላሰቡት ሳይቀር ማሳሰብ መስሎ ይታየኛል።
አሁን አንድ ነገር ብናስብ ጥሩ ይመስለኛል። ቤተ ክርስቲያናችንን አባቶቻችንን የሚያምሰው ችግር አንዳንዶች እንደሚያስቡት አባቶች መንፈሳዊነትን አጥተው ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት አይሎ አይመስለኝም። እግዚአብሔርን ያላስደሰትንበት አንዳች ጉድለት ይኖራል ብየ አምናለሁ። እግዚአብሔር ለሕጉና ለፈቃዱ ቀናተኛ አምላክ ነው። በገዛ ደሙ የዋጃቸው ምእመናን ከአሕዛባዊ የኖሮ ሥርዓት ርቀው በቀናነትና በንጽሕና እንዲያመልኩት ይፈልጋል። ይኽ አልሆን ሲል ግን ወደ በጎ ፈቃዱ እስኪመለሱ ድረስ ለማይመች አካሄድ ኣሳልፎ ይሰጣል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለክብሯ የማይገባ ነገር ሲፈጸም እኛ ካህናት በንጽሕና ማገልገል ሲሳነን፣ ሥርዓቱ ሲጓደል፣ እምነት ጠፍቶ ማስመሰል፣ መሞዳሞድና መመሰጋገን ሲበዛ እግዚአብሔር ቋንቋችንን ይደበላልቀዋል። ስለ አንድ ነገር በአንድ ቋንቋ እየተነጋገርን እንዳንግባባ ማስተዋሉን ይነሣናል። እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ፤ ከመቅደስ እስከ ዓውደ ምሕረቱ ያለው አገልግሎት በእምነትና በፍቅር ይፈጸማል? በትዳራችን፣ በማኅበራዊ ኑሮአችን፣ በሥራ ገበታችን፣ በጓደኝነታችን ታማኝነትና እውነት አሉ? መታመንን ሰብከን እምነት አጉዳይነትን ገንዘብ ካደረግን፣ ፍቅርን አስተምረን ጥላቻን በልቡናችን ካነገሥን፣ ከእግዚአብሔር፣ ከሕዝብና ከመንግሥት አደራ ተቀብለን አደራ ካጎደልን፣ ዘረኝነትን በአደባባይ ኰንነን በመካከለችን ዘረኝነትን መሸሸጊያ ካደረግን……እግዚአብሔር እንመለስ ዘንድ በትንሹ ይቆነጥጠናል።
ለእኔ አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሆነ ያለው እገሌ ብለን ጣታችንን የምንቀስርባቸው ሰዎች ያመጡት ሳይሆን የሁላችን የኀጢአት ውጤት ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ አሁን ጊዜው የመነቃቀፊያ አይደለም፤ የንስሐ እንጂ።
የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ካልዓይን መርጣ መሾሟን አብዛኛው ሕዝባችን ያውቀዋል። ብዙዎቻችንም አሁን በቤተ ክርስቲያናችን እየተከሰተ ላለው ጊዜያዊ አለመግባባት ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ እንድንወስድ ባገኘነው አጋጣሚ ሐሳብ ስንሰጥ ይስተዋላል። መልካም ነው። ጥሩ ጥሩውን ከጎረቤት መውሰዱ ተገቢ ነው። ታድያ ምሳሌነታቸውን ስንወስድ በመገናኛ ብዙኀን የተገለጠውን ብቻ መሆን የለበትም። ያ ፍጻሜው ያስደስት የነበረው የፓትርያርክ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ለዚያ የበቃው በየት በየት አልፎ ነው? ብለንም መጠየቅ ይገባናል።
ባለፈው ኮፕቶች ባደረጉት የፓትርያርክ ምርጫ ለውድድር የቀረቡት አሥራ ሰባት ሰዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን የምርጫ ሕግ አንጠርጥረው ቢያውቁም ምክንያቱን ለማወቅ በማይቻል ሁኔታ ሕጉ ባይፈቅድላቸውም፡ (ለምሳሌ ሀገረ ስብከት ያላቸው፣ ከዚህን ቀደም ፓትርያርክ ለመገልበጥ የሞከሩ) ሳይቀሩ በራሳቸው አነሣሽነት ተመዝግበው እስከ መጨረሻው ድረስ ሲወዳደሩ ነበር። ከእነዚህ ተወዳዳሪዎች መካከልም አንዳንድ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትን በመያዝ ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርኩን ማለት ብፁዕ አቡነ ጳኵሚዎስን ጫና ሊያደርጉባቸው ያስፈራሯቸው እንደ ነበሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ። ሌላ በኩል ደግሞ የወጣቶች ጉዳይ ጳጳስ የሆኑት ተወዳጁ ብፁዕ አቡነ ሙሳን የመሳሰሉት ደግሞ ከአንዴም ሁለቴ እንዲወዳደሩ ቢጠየቁ “እኔ አሁን ዕድሜየ ሰባዎቹ ውስጥ ገብቷል፤ አሁን እኔን ሾማችሁ ገና ደስታችሁን ሳትወጡ ብሞት ለሌላ ድካምና ወጪ ትዳረጋላችሁ። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ እኔ አባቴ ብፁዕ ወቅዱስ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተቀመጠበት መንበር እቀመጥ ዘንድ ብቁ አይደለሁም” ብለው ራሳቸውን ከተወዳዳሪነት ያገለሉ ጀግኖችም ነበሩ።
በአንድ ወቅት ጫናው የበዛባቸው ብፁዕነታቸውም ነገሩ እንዲካረር ለሚያራግቡ የመገናኛ ብዙኀንና ጫናውን በተለያዩ መንገዶች ለሚፈጥሩ የውስጥና የውጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ካልታቀቡ እየተደረገ ያለውን ነገር ለሕዝባቸው አስታውቀው ወደ ገዳማቸው እንደሚመለሱ በይፋ ተናገሩ።
አቡነ ጳኩሜዎስ ከዚሁ መግለጫቸው ጎንም በሦስት የተለያዩ ጊዜያት ለሦስት ሦስት ቀናት የሚቆይ የጾምና የጸሎት ጊዜ አውጀው ነበር። እዚህ ላይ ትልቁ ነገር የምሕላ ጊዜ ማወጃቸው ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የኮፕቲክ ኦርቶዶከስ አባለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ተራው ምእመን ድረስ እንዲሳተፍበት ያደረጉበት ጥበብ ነው። በእነዚያ የጾምና የጸሎት ዕለታት የጳጳሳቱ፣ የካህናቱና የምእመናኑ ውሎ በቤተ ክርስቲያን ነበር። ይኽ ማለት መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት የሱባኤው ተሳታፊዎች ነበሩ ማለት ነው። ይኽ ማለት ዕለቱን በሰዓታት ከፈለው ሰዓታት ይቆሙበት፣ ጸሎተ ምሕላ ያደርሱበት፣ ቅዳሴ ይቀድሱበት፣ ትምህርት ያስተምሩበት፣ ሕዝቡን ያወያዩበት ነበር ማለት ነው። በተለይ በካይሮ በሚገኙ ታላላቅ አድባራትና በሀገሪቱ በሚገኙ ገዳማት ጾሙ ጸሎቱ ይመራ የነበረው በሊቃነ ጳጳሳቱ ነበር። ከሥራቸው ጠባይ የተነሣ በመደበኛው የጸሎት ጊዜ መገኘት ያልቻሉ ሰዎች ወይ የዓመት ፈቃድ ወስደዋል፤ ወይ ደግሞ መላ ሌሊቱን ይደረጉ በነበሩት ጸሎቶች ላይ ተሳትፈዋል።
የሱባኤው በሦስት ጊዜያት መካፋፈል ሁሉም በጉጉት እንዲጠባበቀው ታላቅ አስተዋጽዖ አድርጓል።
እንግዲህ ያ እንደዚያ አምሮና አስለቅሶን የተፈጸመው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫ እነዚህን ሁሉ ጫናዎች ይኽን በመሰለ ጾምና ጸሎት እንባና ዋይታ መፈጸሙን ልብ በሉልኝ። የእኛስ? እግዚአብሔር ይመስገን ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶሱ የምሕላ ዐወጅ ዐውጆ ነበር። እስቲ ከላይ በገለጥኩት አፈጻጸም መዝኑት። አበውን እንድንነቅፍ አይደለም፤ ለወደፊቱ ግን አንድ ምሕላ ሲታወጅ አስፈጻሚው፣ አፈጻጸሙ፣ ሁሉን አሳታፊነቱ (ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ሳይቀር) የጊዜው ርዝማኔ…. ከግምት ሊገባ ይገባዋል። ሠራተኛውም ከአባቶቹ ጋር በቤተ ክርስቲያን አድሮ በጸሎቱ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት የእኔነቱን ያጎለብተዋል ብየ አምናለሁ።
ወደ ግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ። ጥቂት ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሕጉ በማይፈቅድ አካሄድ ለምርጫ መመዝገባቸውን ሕዝቡ ያውቅ ነበር። ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ላይ ያደረሱትን ጫና ያውቅ ነበር። ግን ላግልላችሁ አላለም። ሁሉን ወደሚያውቅ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው ፈጣሪው ግን አነባ፤ ዛሬ ከፉ ብሎ የትናንት መልካም ሥራቸውን አሽቀንጥሮ ገደል ውስጥ አልወረወረም። ዛሬም እንደ ቀድሞው ይወዳቸዋል።
እኛስ? ሰሞኑን የተወሰኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የምርጫውን መዘውር ራሳቸው በፈለጉት መንገድ እየዘወሩት ነው ተብሎ ከመስጋት ያለፈ የትችት ቃላት በአንዳንድ የጡመራ መድረኮች ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ተሰንዝሮ አየሁ። አሁንም የሌላውን መብት እንዳልጋፋ ፀሐፍያኑ ለምን እንደዚህ አሉ? ብየ አልወቅስም። በርግጥ ፀሐፍያኑ ያንን ነገር ሲጽፉ ለሚቆረቆሩላት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከማሰብ አንጻር ሊሆን ይችላል። ግን አንድ ነገርም እናስተውል። እነዚህ አበው ትናንት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አንዳች መልካም ሥራ አልሠሩምን? እኒያ ትናንት መልካም ሥራ የሠሩ አበው እንደ ሰውነታቸው ደክመው ቢስቱ (መሳሳታቸውን እግዚአብሔር ብቻ ቢያውቀውም) የእኛ መልስ መኰነን ነው ወይ? እነዚህ አበው ከባድ በሆነ ፍቅረ ሢመት ተያዙ እንበልና ልንጸልይላቸው ወይስ ልንጸልይባቸው ነው የሚገባው?
ለቤተ ክርስቲያን፣ ለሃይማኖት፣ ለወገኖች የሚኖረንን ቅናት ገንቢና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ብቻ መግለጥ ያለብን ይመስለኛል። ስሕተት ተፈጽሟል ብለን ስሕተትን በስሕተት ለማረም መነሳሣት አግባብነት የለውም። ያ ከሆነ መጽሐፍ “ኵሉ ዐረየ ወኅቡረ ዐለወ” እንዳለው ይሆንብናል።

ስለዚህ ምን እናድርግ?
1. አባቶቻችን አጠር አጠር ባሉ ጊዜያት የተከፋፈሉ የምሕላ ጊዜያት እንዲያውጁልን እንጠይቅ፤ ምሕላው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሁሉን አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ
2. ሁላችንም ምሕላውን በንስሐና በፍቅር እንጀምር
-ምናልባት ሁላችንም ሲባል እንደ ድፍረት ባይቆጠርብኝ። ምክንያቱም አበው “ከገቢር
ቢነፁ ከኀልዮ አይነፁ” ይላሉና ነው። እርስ በርሳችን እኔ የኬፋ እኔ የአጵሎስ ብለን
ብንጀምረው ፍቅር ስለሚጎድለን ልመናችን ቅድመ መንበሩ አያርግልንምና ነው።
2. አባቶቻችንን ከምንወቅሳቸው በፍቅር ቀርበን መሆን አለበት የምንለውን ምክንያታዊ
በሆነ መልኩ ብናስረዳቸው። ምናልባት እኛ አይተን እነርሱ ያላዩት፣ እነርሱ አይተው
እኛ ያላየነው ነገር ሊኖር ይችላልና።
3. ያቅማችንን ፍፁም መንፈሳዊ በሆነና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በተከተለ አካሄድ ከተወጣን የተቀረውን በሙሉ እምነትና ተስፋ ለእግዚአብሔር እንስጠው
4. ብፁዓን አባቶችም ለመጨረሻው ውሳኔ ሳትቸኩሉ ይኖራሉ ተብለው የሚታሰቡ የመፍትሔ አሳቦች እንዳሉ ከልጆቻችሁ ጋር በመነጋገር አሉ በተባሉ የመፍትሄ አሳቦች ላይ ለመነጋገር ዕድል ስጡ።
የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ምእመናን ከውስጥ ከውጪ ያሉባቸውን ጫናዎች ተቋቋመው የቀደሙት አበው የሠሩላቸውን ቀኖና አክብረው ለዓለም ኅብረተስብ ቤተ ክርስቲያኒቷ በትክክል በክርስቶስ ዓለትነት መመሥረቷን፣ እነርሱም በትክክል የቅዱሳን አባቶቻቸው ልጆች መሆናቸውን አሳይተዋል። ኢትዮጵያ ሀገራችን የሥልጣኔና የአምልኮ ጀማሪ መሆኗን፣ ሕዝቦቿም ሕግንና ሥርዓትን ጠንቅቀው የሚያውቁና የሚፈጽሙ መሆናቸውን ታላላቅ የዓለም ታሪክ ፀሐፊዎች ሳይቀሩ መስክረዋል።
እንግዲህ በእግዚአብሔርና በዓለም ሕዝብ ፊት ማንነታችንን የምናሳይበት ጊዜው አሁን ነው። ታሪክ ከመቃብር በላይ ይኖራል። ማንኛውም ዓይነት ሥራችንም በእግዚአብሔር ዘንድ ይቆየናል። ስለዚህ መለያየትን መነቃቀፍን አስወግደን በፍቅርና በእምነት ሰንሰለት ታስረን ለወገኔ ይጠቅማል ሳንል ወይም በጊዜያዊ ነገር ሳንደለል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጪው ትውልድ ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያስችለንን የምእመንና (የአማኝ) የባለ አእምሮ ሥራ እንሥራ።

ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን። አሜን።
Like ·  · Share

Thursday 3 January 2013

ትግላችን እና ፎቶዋችን


ቁ 1 የኖርዌ ፖሊስ የዋሸበት 
ቁ2 ጂ 20
ቁ1 ነገሩ እንደዚ ነው በእለቱ የኖርዌ ንጉስ በፓርላም በመገኘት ከሚኒስትሮች ጋራ የሚገናኙበት ቀን ስለሆነ  እሳቸውን ለመማጸን  እና መንግስት አልስማንም  እርስዎ ይስሙን ለማለት በጠዋት ሰብሰብ ብለናል።በፎቶው እንደሚታየው ጥቁር የሀዘን ልብስ ለብሰን አፋችንን በፕላስተር ሸፍነን የመናገር፧ የመጻፍ፧የመሰብሰብ ነጻነት በኢትዮጵያ የለም።ዲሞክራሲ፧ፍትህ፧ነጻነትና እኩልነት ሞቷል በማለት የሬሳ ሳጥን በመያዝ ዝም ብለን የሚያልፉበትን መንገድ  ዳሩን ይዘን  እንጠብቃለን ፤የኖርዌ ፖሊስ እኛ የምናደርገውን አጠገባችን በመሆን ይከታተላል፧ካሁን አሁን መጡ እያልን ስንጠብቅ ፖሊሱም ሰዓታቸው ደርሷል ብሎ ምልክት ሲያሳየን እኛም  እሱ ያለንን  አምነን  አይናችን ሲንቀዋለል ንጉሱ መንገድ ቀይረው ከጀርባችን ራቅ ብሎ ባለው ሌላ መንገድ እብስ አሉ።ሰልፉን ፖሊስ ነው የፈቀደው የቆምንበትን ቦታ  የሰጠን ፖሊስ ነው በዚህ ነው የሚያልፉት ብሎ ።ከፊታችን ስንጠብቅ ጀርባችንን አይተው ሄዱ። ያንን ሰልፍ የኖርዌ  ፖሊስ የዋሽበት ቀን በማለት አስታውሰዋለው።                                                                                     ቁ2   ጂ 26   መከራ ና ትግል አንድ ያደረገን፡የሚመጣውን ማንኛውንም ችግር  በጋራ ለመጋፈጥ ቆርጠን የተነሳን በአንድ የምንተነፍስ በአንድነት የምንራምድ።ያሰባሰበን ችግር ቢሆንም በአብሮነት ያሳለፍነው ጊዜ  ግን በፍቅር የተሞላ ነበር።ጂ20 የሚባሉት በሀብት የበለጸጉ ሲሆኑ ፤ጂ26 ደግሞ  በፍቅር የበለጸጉ ነበሩ።አንዱ የፍቅር ማሳያ  ፎቶው ላይ  እንደሚታየው  ባንዲራችን እንዲታይ ወጥረው የያዙት እናንተ  ተስተካክላችሁ ተነሱ  እኛ ባንዲራ መስቀያ እንሆናለን ብለው ቅድሚያውን ለብዙሀኑ ሲሰጡ።ትንሹዋ ምሳሌ  ነች ።በወቅቱ ትግላችን የነበረው ጨቋኝ እና ዘረኛ የሆነው የኢትዮ ጵያ  መንግስት በህዝቦቹ ላይ የሚያደርሰው ግፍና መከራ በዛ በተጨማሪ የኖርዌ መንግስት ገዳይ እና አረመኔ ለሆነው ለመለስ ዜናዊ አስተዳደር አሳልፎ  ሊሰጠን ነው አግባብ አይደለም የስደተኛ መብት አልተከበረም ለበዙ ዓመት በስራ ላይ በመቆየት  ግብር በመክፈል በህጋዊነት ስንሰራ  የቆየን  ነን  ስለዚ አስረው እንዳይመልሱን ችግራችንንም የዓለም ህዝብ ይወቅልን በማለት ወደ ስዊድን በመሄድ ድምጻችንን ያሰማን የበፊት ታጋዮች ያሁን ጓደኛሞች።                                                                                                                                                      ቁ3  የፍረሃት ቀን ያልኩት በፎቶው ላይ እንደምታዩት ፕሮግራሙ የሻማ ማብራት ስነስርአት ነው። ይህ  ፕሮግራም የኖርዌ  መንግስት ለእኛ የመኖሪያ ፍቃድ ለሌለን ኢትዮጵያውያን[ፓፒር ሎስ ወይም ኡሎቭሊ]  የመጨረዛው ቀን ነው።ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ  ፖሊስ ማጅራታችንን  እያነቀ  አንጠልጥሎ  ወደ ኢትዮጵያ  እንደሚመልስ እየፎከረ እያቅራራ  በተደጋጋሚ መግለጫ እያወጣ በኛ በምስኪን ስደተኞች ላይ ሽብር እያፈጠረ ነበር።ስለዚ አብዛኛው ስደተኛ ነገሩ እስኪጣራ በማለት በየ ዘመድ አዝማድ ለመደበቅ የሚኖርበትን መጠለያ[ካምፕ]በመተው ኦስሎ የተሰበሰበበት ቀን ነበር  ።ያም የፍርሃት ቀን አለፈ ። እኛም በፕሮግራሙ ላይ እንዲ በለን ዘምረን እንባችንን አፍሰን እግዛብሄርን ለምነን ነበር።ሀይል የእግዛብሄር ነው፤ማዳን የእግዛቤር፧አንመካም በጉልበታችን፤እግዛቤር ነው የኛ ሀይላችን።
ቁ4   አርያዎቻችን
 ቁ4 ጉዋዲት ገነት ግርማ ና ጉዋድ እያሱ አለማየሁ ሁለቱም  በትግል ለብዙ ጊዜ  እድሜያቸውን ማለት ይቻላል ብዙ መከራ ስቃይ ስደትና ችግርን ያሳለፉ፤ ለፍትህ ለዲሞክራሲ ለእኩልነትና ለህዝቦች ነጻነት ሲሉ የታገሉ አሁንም እየታገሉ ያሉ እውነተኛ ኢትዮ ጵያዊ ናቸው።አንድ ነገር ልበል በዛ የመከራ ወቅት የኖርዌ መንግስት አላስቆም አላስቀምጥ ብሎ ከዛሬ ነገ ያዘን ወደ ነብሰ በላው የወያኔ  መንግስት አሳልፎ  ሰጠን ብልን  በተጨነቅንበትጊዜ በኖርዌ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች በደል እየተፈጸመባቸው ነው።ወደ አረመኔው  የወያኔ መንግስት አስረው ሊልኳቸው ነው።በማለት ጄኔቭ በሚገኘው  የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ላይ ችግራችንን አንስተው የተከራከሩልን እውቅ  ታጋይ ናቸው።

Monday 31 December 2012

አክሱምን ወላይታ አገኘሁት!!!



(ናትናኤል ፈለቀ)
40 minch
ኅዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በሥራ ጉዳይ ወደ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ለሁለት ቀን ተኩል የሚበቃኝን  ሸክፌ ከመሥሪያ ቤቴ በተመደበልኝ መኪና ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ለሚነሳው በረራ ለመድረስ ወደቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ላይ የተደረደሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት አቀባበል ወይንም ሽኝት የሚደረግለት ባለሥልጣን/እንግዳ እንዳለ ስለጠቆመኝ መንገዱ ሳይዘጋ ቦሌ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርግ ለሹፌሩ ጠቆምኩት፡፡ ብዙም ሳንጓዝ አትላስ ሆቴል የትራፊክ መብራት ላይ ስንደርስ በስፍራው የነበሩት የትራፊክ ፖሊሶች ወደ ቺቺንያ ወይንም ወደ ቦሌ ሩዋንዳ የሚወስደውን መንገድ እንድንጠቀም አስገደዱን፡፡ ወዲያውኑ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ ለሰባት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ይላል፤ ብዙም አልተረበሽኩም፡፡ በስተቀኝ በኩል ታጥፈን በውስጥ ለውስጥ አቋራጭ መንገድ ጥቂት ከሄድን በኋላ መልሶ ዋናውን መንገድ ስላገናኘን መኪናውን አቁመን እንግዳውን እስኪያልፍ መጠባበቅ ጀመርን፡፡
በዚያው ሰሞን ወደ ሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ሄዶ የነበረ አንድ የሥራ ባልደረባችን በአምስት ቀን ቆይታው ሁለት ጊዜ በመንገድ ያለፋቸው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በከተማው መንገድ ላይ ሲጓዙ እሳቸው ከሚጓዙበት አቅጣጫ በተቃራኒው የሚወስደው የመንገዱ ጎን ክፍት እንደሚሆን የነገረኝን ለሹፌሩ እያጫወትኩት ሳይረን እያሰማ የሚከንፈውን ሞተረኛ ተከትለው ካልተሳሳትኩ አምስት መኪኖች በፍጥነት ወደ ቦሌ የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሲያልፉ አየን፡፡ ካለፉት መኪናዎች ሦስቱ ባለግርማ ሞገሶቹ ጥቋቁር ሼቭሮሌቶች ነበሩ፡፡ ያለፉት ባለሥልጣን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆን አለባቸው (በእርግጥም ነበሩ፤ ለሥራ ጉብኝት ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ እያቀኑ)፡፡ እንደ ሥራ ባልደረባችን ከሆነ ፕሬዝዳንት ካጋሜን የሚያጅቡት አንድ ሞተረኛ ፖሊስ ከፊት እና አንድ መኪና ከኋላ ሆነው ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ይህን ሁሉ ጥበቃ የሚደረግላቸው ከፕሬዝዳንት ካጋሜ ይልቅ ለደኅንነታቸው የሚሰጉ መሪ ስለሆኑ ነው? ወይስ ኢትዮጵያዊያን ከሩዋንዳዊያን ይልቅ አስፈሪ ሕዝብ ስለሆንን? ይህንን እቆቅልሽ እያሰላሰልኩ መንገዱ ተከፍቶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የአገር ውስጥ በረራ የሚደረግበት ጣቢያ ቁጥር 1 ደረስኩኝ፡፡