"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 22 April 2012

     ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲያዜም ኢትዮጵያ ትከበራለች 

  አበሻ አንገቱን በሀዘን በሚደፋበት ወቅት ብቅ የሚሉ ፈርጦች አሉ፣ እንባችንን አብሰን ሀዘናችንን ተወት አድርገን ቀና እንድል

የሚያደርጉን ። ከትንሳዔው በዐል ጋር የሞራል ትንሳዔ የሚሰጥ ውብ ዘፈን ከጥግ አስከ ጥግ ድረስ ተሰማ። ብላቴናው ጥበብ ከላይ

ይፈስለታል። አመስግኖ ይቀበልና ቤት እያስመታ ይገጥማል፤ የገጠመውን ደግሞ ወደ ዜማ ይቀይርና ሰው መሆኑን እስክንረሳ ድረስ

በደስታ ያስጨፍረናል። ለዚህ ነበር ከዚህ ቀደም የቴዲ ዜማዎች ጥላቻን የሚያከስሙ የፍቅር ቅመሞች ናቸው ብዬ የመሰከርኩለት

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/1627 በዚያን ጊዜ ከትንሿ እስር ቤት ውስጥ ነበር።
የሰሞኑ ነፋስ ደግ አልነበረም የሀዘን ድባብ አጥልቶብን ነበር። ቅስም ለመስበር የተባበሩ የሚመስሉ የክፋት ሀይሎች ሸቃባነታቸው
ከፍቶብን ነበር። መስጊዱ በጸጉረ ልውጥና ተንኮል ተንኮል በሚሸት የቀኖና መስመር አንሄድም በሚሉ የእስልምና ሀይማኖትተከታዮችጩኸት ተሸብሯል። አላሁ አክበር ሲሉ ደመና እየሰነጠቀ ጩሀታቸውን አሞራም የተቀበለው ይመስላል። አሸባሪ ነህ ካልከኝ አዎን
አሸብረሃለሁ ላንተ መሰሪነት ስል ከኢትዮጵያዊነት ግን አላንስም የሚለው መሀላ በአላሁ አክበር ሲታጀብ ክርሰትያኖችም የወገኖቻቸው
ጩኸት ተሰምቷቸው በልባቸው ከነርሱ ጋር መሆናቸው እውነት ነው። ይሁን እንጂ እነርሱም ፋታ አላገኙም። ደብር አፍርሰው ለነዳጅ
የሚሆኑ እጽዋትን በስኳር ስም ሊያመርቱ ትራክተሩን እያስጓሩባቸው በጭንቀት ላይ ናቸው