"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 22 September 2012

Ethiopia blocked Swedish state television website


The website of Swedish state broadcaster Sveriges Television (SVT) has been blocked in Ethiopia amid claims that the reason is their reporting of the case of journalists Johan Persson and Martin Schibbye.
According to sources contacted by SVT, the svt.se website has been down in the country since early on Saturday morning.
Persson and Schibbye were recently released from Ethiopian prison and SVT is among the news media which have reported on claims that evidence was falsified to secure their convictions on terror charges.
“Ethiopia is very uncomfortable with the information that we have broadcast. They know that we are going to produce more,” said reporter Johan Ripås to svt.se.
According to Mikael Hvinlund at SVT the cause of the interruption is under investigation.
“It is very regrettable if it is that they have shut down our site, that a country imposes such restrictions. We have had a comprehensive coverage and have strong sources, and they are obviously irritated by the publicity,” he told the TT news agency.
“If they have done so deliberately then it is a very serious and powerful signal.”
He confirmed that SVT were given no notice, and that it had come as a surprise.
“We are going to contact Ethiopia’s embassy in Sweden to seek an explanation for why they have done this.”
SVT are also busy investigating whether other Swedish news sites have also suffered the same fate.
“There are others also reporting so if there should be any point with it then they should close more Swedish sites,” he said.

Thursday 20 September 2012

ሰይጣንን መልዓክ፣ ገዳይንና ጨካኝን የሰላም መልእክተኛ ለማድረግ ይህን ያህል መራወጥ ለምን አስፈለገ?




ከበቃና ኦብሴ
“… ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር፡፡ ይህ ከአደጉ በኋላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም፡፡ የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር፡፡ የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት “ባዶ ሹዱሽተ” እስር ቤት ይወሰዳል፤ … ለጥቂት ቀን ደህና ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣ ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩን ጭሮ እንዳበቃ ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ ይመልሱታል፡፡ ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም ያረካቸዋል፡፡ ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድ(በመገለል) ያቀብሉታል፡፡ ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ ነው፡፡ አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በኋላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም:: እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት አይችልም:: ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር፣ ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ድቁቋ)፤ ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም:: ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቋዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል:: … (ሙሉውን አስነብበኝ)

የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች



(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።

እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።
ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋ የሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለ ልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤት እየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽ ልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶች መስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነው – የሚጠጣ  ያቀርባሉ፤ ፍም እሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓት በየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻ ይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡና ማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋር በሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋና ስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።

የቴዲ አፍሮ የሰርግ ቀን ደረሰ






ጥቁር ሰው አልበምን በሽያጭ ላይ ከዋለ በኋላ የትዳር አጋሩን በሪሊዝ ፓርቲ አመክኝቶ ለህዝብ ይፋ ያወጣውን ድብቅ ሚስጥር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ጋብቻ እንዲቀየር በማድረግ ለሚቀጥለው ሳምንት ሃሙስ  ሴብቴምበር እ ኤ አ 9/ 27/2012 በሂልተን ሆቴል የሰርጉን ስነ ስርአት እንደሚፈጽም ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ዘገባ ያመለክታል ።ከአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ስርአት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለሰርጉ ስነ ስርአት የሚያስፈልገውን እቃዎች ሁሉ በሰሜን አሜሪካ ግዢውን አጠናቆ የሄደው ቴዲ አፍሮ ባለፈው ሳምንት ቢሆንም   በዚያው ሳምንት በሂልተን ሆቴል የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ለረጂም ጊዜ የተያዘ ፕሮግራም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በመንግስት ሃይሎች የመለስን መሞት በሃዘን ማሳለፍ አለባችሁ ብለው አገሪቱን አፍነው በመያዛቸው ፕሮግራሙ ሊተላለፍ እንደቻለ ተገልጾአል በዚህም ሳቢያ ለሚቀጥለው ሳምንት ሃሙስ በሚደረገው የሰርግ ስነ ስአርት ላይ አሁንም ችግር እንዳይፈጥሩ ህዝቡ ስጋቱን አሁንም ገልጾአል ።በዚህ የሰርግ ስነ ስርአት ላይ ታላላቅ አርቲስቶች ፣ታላላቅ ሰዎች ባለሃብቶች እና እንዲሁም የቅርብ ወዳጆቹ እና አብሮ አደጎቹ እንደሚገኙ ተጠቁሞአል ።ከሰርጉ ስነ ስርአት በኋላ የተለያዩ ኮንሰርቶችን ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም ከአቡጊዳ ባንድ ጋር የሚያደርገው የሙዚቃ ስራ ግን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ነው ።በአቡጊዳ ባንድ እና በቴዲ አፍሮ በኩል መካከል በተነሳ የውስጥ ችግር ወይንም አለመስማማት ጉዳዩ ታፍኖ ቢቀርም አሁንም እልባት ያገኛል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር ።ለዚህም እንደምሳሌ በስዊድን እና ሆላንድ የተሰረዘው ኮንሰርት እማኝነቱን ያሳያል ይላሉ  ።ሆኖም የአቡጊዳ ባንድ ለቴዲ አፍሮ የጻፉትን የአቋም መግለጫቸውን ሊቀበለው ስላልቻለ ከአስር አመታት በላይ ያለ ውል ሲሰሩ የነበሩት ባንዶቹ አሁን ግን የቆረጠላቸው ይመስላል ። የቀጣዩን የሙዚቃ ጉዞ አስመልክቶ ሰፋ ያለ ዘገባ ከሰርጉ በኋላ በሚኖረን መረጃ ይዘን እንቀርባለን የባንዶቹንም አጠቃላይ የአቋም መግለጫ  ከሚቀጥለው ሳምንት በኋላ ይዘን እንቀርባለን። ማለዳ ታይምስ

በነ እስክንድር ላይ አስገራሚ ውሳኔ ተላለፈ።በውርስ ያገኘው ቤት እንዲነጠቅ ተብሏል ዘገባው የደረጀ ሃብተወልድ ነው !



በነ እስክንድር ላይ አስገራሚ ውሳኔ ተላለፈ።
1-እስክንድር ነጋ ፦በስሙ ተመዘገበ ባለ አንድ ፎቅ ቤት እና <<በውርስ ከቤተሰቡ ያገኘው ‘ግራውንድ ፕላስ ቱ’ ቤት
2-አንዷለም አራጌ በስሙ የተመዘገበ አንድ መኪና እና
3-አበበ በለው በሚስቱ ስም የተመዘገበ <<ግራውንድ ፕላስ ዋን>> ቤት እንዲታገድ ተብሎ ነው ውሳኔ የተላለፈው።
ስለማውቀው ልናገር፦

በጣም የሚገርመው ነገር፤ እስክንድር ነጋ እናቱ ከማረፋቸው በፊት ቤታቸውን ሲያወርሱት፦” አልፈልግም !”በማለት ውርሱን ያልተቀበለ ሲሆን፤ አሁን እንዲታገድ የተባለው በውርስ የተገኘ ቤት የእርሱ ንብረት አለመሆኑ ነው።
በአጭሩ ላብራራ፦ውርሱ የሚገባው ለእሱ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ እናቱ በጣም የሚወዱትና የሚሣሱለት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆነ ጭምር ሽማግሌዎችን ሰብስበው የቤቱን ኑዛዜ እንዲቀበል ይጠይቁታል። እስክንድር ግን ገንዘብና ንብረትን አስቀድሞ የናቀ ልጅ በመሆኑ ፤ ከአቋሙ ሊነቃነቅ አልቻለም። በመጨረሻም ቤቱ የአባቱ ልጅ ለሆነች እህቱ ተሰጠ። ውርሱ ለእሷ ጸና።
ዛሬ ይህ የእህቱ ቤት ነው እንዲታገድ የተወሰነው። የእስክንድር እህት፤እህት በመሆኗ ብቻ ንብረቷ ታገደባት። ከእስክንድር ቤተሰብ መወለዷ፤ እንደ ወንጀል ተቆጠረባት።ቤቷን አጣች።

Wednesday 19 September 2012

ህወሃት አባይ ወልዱን ሊቀመንበር፤ ደብረጽዮንን ምክትል አድርጎ መረጠ



ምንጭ (ኢ.ኤም.ኤፍ) የህወሃት ሊቀመንበር የነበረው አቶ መለስ ዜናዊ ካረፈ በኋላ፤ ህወሃት እና ኢህአዴግ ሊቀመንበር ሳይኖረው መቆየቱ ይታወሳል። ኢህአዴግ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሊቀ መንበር አድርጎ ሲመርጥ፤ ህወሃት (ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ) ግን ያለ ሊቀመንበር ነበር የሰነበተው። ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የህወሃት ስብሰባ፤ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር፤ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ደግሞ የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ ተመርጧል።



New TPLF leaders: Abay Woldu and Debretsion



አባይ ወልዱ፡ ከቀድሞ ታጋዮች መካከል አንደኛው ነው። በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት እና የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር ነበር። መለስ ዜናዊ መታመሙ እንደታወቀም ሆነ፤ ከሞተ በኋላ ሊቀመንበሩን በቀጥታ ተክቶ የህወሃት አባላትን ስብሰባ ጠርቶ ሊቀመንበሩን መተካት ይኖርበት ነበር። ይህንን ባለማድረጉ ባለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ላይ ህወሃት ከሌሎች የዘር ድርጅቶች ይልቅ አንሶ እና ኮስሶ ነበር የታየው። በዚህም ምክንያት ህወሃት በኢህ አዴግ አመራር ውስጥ የነበረውን ይዞታ ማጣቱን የህወሃት አባላት በቁጭት እየተናገሩ ነው። የህወሃት ከፍተኛ ሰዎች ከነበሩት መካከልም፤ አቶ ስብሃት ነጋ… “መለስ ዜናዊ ህወሃትን ገድሎ ነው የሞተው” ሲሉ የሚናገሩትን የሚጋሩ ሰዎች አሉ። እንደ አቶ ስብሃት አነጋገር ከሆነ፤ “ሌሎቹ የኢህአዴግ ድርጅቶች በሰው ሃይል ተጠናክረው ሳለ፤ እኛ ግን ለጠቅላይ ሚንስትርነት የሚበቃ ሰው አላዘጋጀንም። መለስ ዜናዊም በህይወት በነበረበት ወቅት አዋቂ እና የተሻሉ የነበሩትን ሰዎች በሰበብ አስባቡ ሲያባርራቸው ነበር” በማለት እነ ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እና ሌሎችንም ይጠቅሳሉ።
አሁን ዛሬ የተደረገው የህወሃት ስብሰባ ደብረ ጽዮንን ምክትል አድርጎ ከመምረጡ በስተቀር፤ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር ሆኖ ሊመረጥ እንደሚችል ቀደም ተብሎም የተጠበቀ ነበር።

What Ethiopia Is Up Against


What Ethiopia Is Up Against

A friend recently sent me a video presenting Sebhat Nega’s defense of the TPLF constitution. My friend was rightly


Sebhat Nega
amazed at the dismissive and arrogant nature of the defense.  My reaction wandered a bit in the direction of assessing the origin of the defense: I could not help but ask what torturous path led a Tigrean to a defense erasing the shared legacy of a very long history.  Let me first briefly summarize the content of Sebhat’s discourse.

Sebhat refers to a hypothetical situation where opponents intent on dismissing the TPLF constitution succeed in seizing power. Sebhat emphatically predicts the inevitable disintegration of Ethiopia and the outbreak of war. According to him, the TPLF constitution is the foundation of Ethiopian unity. It originated from a consensus of all the peoples of Ethiopia and remains the sole guarantee of equality. Since equality is the basis of unity, any change altering its main principles inexorably entails the collapse of unity. In his assumption, this almost happened in 2005 when forces inimical to the constitution scored important electoral gains. If the movement had not been violently crushed, it would have certainly resulting in war and disintegration.

Tuesday 18 September 2012

ከመለስ የተላከ ደብዳቤ



     
ከመለስ  የተላከ  ደብዳቤ
ለውድ ተጋዳላይ ጎደኞቼና ዘመዶቼ እንደምን አላችሁ፤ አኔ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነኝ;; ያእግዚአብሄርን ስም ጠራህ ትሉኝ
ይሆናል ግምገማ ስላለ ነው;; መቼም ድንገት በመሄዴ እንደ ደነገጣችሁና እንደ ተረበሻችሁ አባ ጻውሎስ ነገሩኝ፤ በመንፈስ ከኔጋር
ልትተባበሩ በስጋ አጥምቄአችሗለሁና ሁሌም መንፈሴ ከናንተ ጋር ነው;;የኔን ቦታ የሚተካ ሰው ውስጣችሁ እንደሌለ አውቃለሁ;;
በዚህም ምክንያት ሀያ አንድ አመት ለናንተ መኖሬን ታውቃላችሁ አሁንም ማድረግ ያለባችሁ መከላከያውን አጠናክሩ ጠቅላላ
መከላከያውን ከተቐጣጠራችሁ ማንም ምንም ሊያመጣባችሁ አይችልም;; የብሄር ተዋጽዎ የለውም ብለው ቢያወሩባችሁ
አትስሞቸው እስከመቸም መንግስቱን እደፈለጋችሁ የምታዙበት ቁልፉ ነገር እሱ ነው;; ቃሌን አድምጡ ፖሊሲየን ጠብቁ ራዕየንም
አትዘንጉ;;ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን ሌላም እምቢ ያሏችሁን ልታስሩና ልትፈርዱባቸው አትፍሩ አንዳንድ ትችቶች ሊሰነዘርባችሁ
ይችላል ቦታ አትስጡት;; ምእራብያኖችን ስሟቸው እድሜአችሁ ይረዝማል አድርጉ ያሉአችሁን አታቅማሙ ይጠብቛችሗል
ስትከፉም መሸሸጊአችሁ ናቸው;; ከቻይና ጋር ስራችሁን አብዙ ለመስረቅና ለመከፋፈል ይመቻሉ;; በተረፈ ላለቀሱልኝ ደጉሟቸው
ለአናተም ይጠቅሟችሗል፤ ውሻ የሚበላው አይጎዳም ስራው ግን ትልቅ ነው;; ሌላ ካአባ ጳውሎስ ጋር አንድ ለይ ነን ያለንበት ቦታ
ብዙም አይመችም እነ ጋዳፊም እዚሁ ናቸው እኔም አባጻውሎስም ፍርድ ቤት ቀርበን ነበር፤ የአባታችን ጉዳይ በልዩ ፍርድ ቤት
እንዲታይ ትዛዝ ተሰጥቶበታል፤ የኔ ግን በጣም ይገርማችሗል የክስ መዝገቡ ተነቦ እስከሚያልቅ ብቻ ሀያ አንድ ዓመት ያስፈልጋል
ስለተባለ፤ የዋስ መብት አንዲከበርልኝ ጠይቄ ነበር? አቃቢ ህጉ የተከሰሱበት ክስ ፈፅሞ ዋስትና ሊያሰጣቸው አይችልም በሁለተኛ
ደረጃ ደግሞ ሰውየው ጫካ የነበሩ ስለሆነ አሁንም ጠፍተው ጫካ ይገባሉ ብሎ ስላቀረበ በዚሁ ሆኛ እድከታተል ፍርድ ቤቱ
ወስኗል;; ዳኛው ገርሞአቸው ሀያኛው ከፍለዘመን ከገባ እንደዚህ ክሱ እንዳተ የበዛ አላየሁም ብለው ባግራሞት ነው ያዩኘ
ለማንኛውም ሁላችሁም መምጣታችሁ አይቀርም፤በምድር የሰራንውን ወንጀል አንድ ላይ ስለሆነ እዚህም አንድ ለይ ነን;;
ይቀጥላል………//

Sunday 16 September 2012

New fighting force in Ethiopia’s Ogade


New fighting force in Ethiopia’s Ogade

(Aljazeera) – The conflict In Ethiopia’s Somali, or Ogaden, region has killed thousands of people over the last 15 years. But the crisis is little known because of media restrictions by the government.
It borders Djibouti, Kenya, and Somalia. The people there are predominantly ethnic Somali and Muslim.
It is also home to a separatist campaign led by the Ogaden National Liberation Front, or ONLF, which has fought for independence since 1984.
Ethiopian forces waged an offensive against the rebels in late 2007 after an attack on a Chinese-run oil facility.
Last week Ethiopia’s government held peace talks with the ONLF in Kenya.
In the second part of Al Jazeera’s series on Ogaden, Mohammed Adow meets the region’s new fighting force.
Source: Aljazeera


ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!!



ህወሓትና ስዩም መስፍን በኢህአዴግ ምክር ቤት ድምጽ ተነፈጉ!
September 16, 2012 (ጎልጉል)

የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም።

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ መለስን የሚተካ መሪ መሰየም አለመቻሉን አቶ በረከት ስምኦን ያሳበቁበት ህወሓት በቀጣዩ ምርጫም ወንበሩን እንደማያገኘው አቶ በረከት በግልጽ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ ሁለቱ አዲስ ተሿሚዎች በስልጣናቸው እንደሚቀጥሉ በይፋ ተናግረዋል።

የኢህአዴግን የአመራር ወንበር ላለማጣት ያደረገው ሙከራ በየድርጅቶቹ በተካሄደ የተናጠል ስብሰባ ተሞክሮ ሊሳካ እንዳልቻለ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። በስም ተጠቅሰው ኢህአዴግን እንዲመሩ የቀረቡትን የህወሃት ሰዎች አንቀበልም ያሉት አባል ድርጅቶች በተቃራኒ በቀጣዩ የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ መተካካቱ በተዋጽዖ የተመጣጠነ እንዲሆን የሚያሳስብ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል።ከአቻ ድርጅቶቹ በተጨማሪ አሜሪካ ያስተላለፈችው መመሪያም ተጽዕኖ መፍጠሩ ተገምቷል።

ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያዋ በሆነው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈች



የመጀመሪያዋ በሆነው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ ታላቋ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ከወጡት ኬኒያዊቷ ኪፕላጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና ጋር
በለንደን ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ፣ በ5 ሺህ ሜትር ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያ ያገኘችው ኢትዮጵያዊቷ ታላቅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለመጀመሪያ ጊዜ የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ተሳትፋ ርቀቱን በአንድ ሰአት ከ07 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አሸንፋለች። ኬኒያዊቷ የአለም የማራቶን ሻምፒዮን ኤድና ኪፕላጋት ጥሩነሽን ተከትላ ሁለተኛ ስትወጣ፣ በለንደን ኦሎምፒክ የማራቶን ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ኢትዮጵያዊቷ ቲኪ ገላና ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች።

ኒውካስል ውስጥ በተካሄደው በዚህ የታላቁ ሰሜን ሩጫ ግማሽ ማራቶን ውድድር ጥሩነሽ ልክ ለረጅም ጊዜ በበላይነት በተቆጣጠረችው የትራክ ውድድር ላይ እንደምታደርገው ሁሉ ከመሪዎቹ ጋር በመቀላቀል እና ብዙም ሳትርቅ ከኋላ እየተከተለች በመሮጥ ነበር ውድድሩን የጀመረችው። ርቀቱ ሊጠናቀቅ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው ከኪፕላጋት እና ቲኪ አፈትልካ በመውጣት በጎዳና ውድድሮች ላይ ከእርሷ የተሻለ ልምድ ያላቸው ሁለቱ አትሌቶች እንዳይደርሱባት ሩጫውን  ካፈጠነች በኋላ 400 ሜትር ሲቀረው የበለጠ ፍጥነቷን የቀየረችው ጥሩነሽ በታሪክ የመጀመሪያዋ በሆነው ውድድር የመጀመሪያ ጣፋጭ ድሏን ልታገኝ ችላለች።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ በኦሎምፒክ በርካታ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ቁጥር አንድ የሆነችው ጥሩነሽ ዲባባ ቀጣይ አላማዋ ማራቶንን ጨምሮ በጎዳና ውድድሮች ላይ ድርብ ድሎችን ማግኘት ሲሆን፣ በቀጣዩ የአትሌቲክስ ውድድር አመት ማራቶንን ለመሮጥ እቅድ እንዳላት ከግማሽ ማራቶኑ ድሏ በኋላ በሰጠችው አስተያየት ይፋ አድርጋለች።

“የዛሬው ውድድር በጣም ፈጣን ነበር። ነገር ግን ወደውድድሩ ማብቂያ አካባቢ የጣለው ዝናብ አየሩ በመጠኑም ቢሆን ቀዝቃዛ እንዲሆን በማድረጉ በውድድሩ ላይ መጠነኛ አሉታዊ ተጽእኖ እንዲኖረው አድርጓል” ያለችው ጥሩነሽ፣ “በቀጣዪ አመት ትንሽ ሞቅ ይላል በሚል ተስፋ ከዚህ በተሻለ ሰአት ውድድሩን ለማሸነፍ እሞክራለሁ” ብላለች።

በወንዶቹ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው የማነ መርጋ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቶ ሲያጠናቅቅ፣ በለንደኑ ኦሎምፒክ በማራቶን የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት ኬኒያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ ርቀቱ ሊጠናቀቅ 10 ሜትር ያህል ብቻ ሲቀረው የሀገሩ ልጅ ሚካ ኮጎን በፍጥነት በመቅደም በ59 ደቂቃ ከስድስት ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቆ አሸንፏል።